ከኦሮሞ ፖለቲካ ወደ ጃዋር ፖለቲካ? (ከመስፍን ነጋሽ )

ወንድሜ ጃዋር (Jawar Mohamed) ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሞ ፖለቲካ እና አሁን ደግሞ ስለኦሮሞ-ኢስላም ያቀረባቸው ንግግሮች ኮርኳሪ ሆነዋል። ኮርኳሪነታቸው የሚመነጨው ግን ሐሳቦች አዲስ ስለሆኑ አይደለም፤ በአቀራረባቸውም ቢሆን ያልተለመዱ አይደሉም። “የአግራሞቱ” ወይም የንዴቱ ምንጭ ጃዋር የገነባው ወይም እየገነባው የመሰለን የፖለቲካ ማንነት እና በቅርብ ያንጸባረቃቸው አቋሞቹ እጅግ የሚቃረኑ ስለሚመስሉ ነው።

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ውስብስብ ከሚያደርጉት ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ የኦሮሞ ፖለቲካ ነው። ኢትዮጵያ ዜጎች ቢያንስ በመጠኑ ሐሳባቸውን በነጻነት የሚለዋወጡባት አገር ብትሆን ኖሮ ጉዳዩን ነጋ ጠባ በተነጋገርንበት፣ በተከራከርንበት ነበር። ይህ ባለመሆኑ ግን ከትልቁ የኦሮሞ ጉዳይ ይልቅ ጃዋር የተነፈሳት አንድ አረፍተ ነገር የበለጠ ቁም ነገር ያላት ሆና ተቆጠረች። መፍትሔው ጃዋርን ማውገዝ አይመስለኝም፤ ስለኦሮሞ ፖለቲካ መነጋገርና መደማመጥ ያስፈልጋል።

ጃዋር በአልጀዚራ ላይ ባቀረበው ሐሳብና በወሰደው አቋም ዙሪያ ሌላ ውይይት/ጽሑፍ የሚያስፈልገው ሆኖ ቢያንስ በክርክሩ ሐልዮታዊ መነሻዎች ላይ ግን ቢይንስ በግማሹ ከጃዋር ጋራ እስማማለሁ። መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ ወይስ ኦሮሞ የሚለው ጥያቄም በግለሰቦች ታሪክ፣ ከባህላቸው ጋራ ባለቸው ትስስር እና በፖለቲካዊ ርእዮታቸው የሚወሰን በመሆኑ ውይይትና ዴሞክራሲያዊ የአገር ግንባታ የሚፈታው አድርጌ እወስደዋለሁ። እኔ ያደኩበት ከባቢ ጃዋር ከኖረበት ፈጽሞ የተለየ ነው። ይህ በፖለቲካዊ ማንነታችን ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ በኑሮና በእውቀት ሊለወጥ የሚችል ቢሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም። እኔ ባደኩበት ከባቢ ኖረው የጃዋርን ስሜት የሚጋሩ፣ እንዲሁም በተቃራኒው የሚሆኑ ሰዎች አሉ። አንዱ ከሌላው የበለጠ ትክክል አይመስለኝም።

ከብዙ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን ጋራ ያለኝ ልዩነት፣ በዋናነት ያለፈውን ታሪክ በምገመግምበት መንገድ ሳይሆን መጪውን ዘመን በማልምበት ስልት ላይ የተመሰረተ ነው። ዴሞክራሲያዊት እና ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ የችግሩ መውጫ ናት እላለሁ፤ ሌላ ምርጫ የለም። የኦሮሞ ሕዝብ በመገንጠል (የራስን እድል በራስ መወሰን) የራሱን መፍትሔ ሊያገኝና ብቻውን በሰላም ደሴት ላይ ሊኖር እንደሚችል የሚያስቡ ይኖራሉ። ቁም ነገሩ መገንጠል በራሱ ከሆነ ቢሞክሩት የሚከፋ አይደለም፤ ሆኖም መገንጠል የታሪኩ መጨረሻ አይሆንም። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ እውነታ የኦሮሞንም ሆነ የሌሎቹን ሕዝቦች ችግሮች በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የታመቀ አቅም እንዳለው አምናለሁ። እንደ ማኅበረሰብ ይህን አቅም ለመጠቀምና የጋራ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችለን የፖለቲካ ብስለት ላይ ግን ገና አልደረስንም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአደባባይ በዓሎቻችንና እኛ 

ሁለተኛው የጃዋር ንግግር የኦሮሞና የእስልምናን ግንኙነት፣ ከዚህ ግንኙነት የሚፈልቀው ፖለቲካዊ አንደምታ፣ እንዲሁም ሙስሊም ኦሮሞ ሙስሊም ከሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊና ሙስሊም ካልሆነ ኢትዮጵያዊ ጋራ የሚኖረውን ግንኙነት የሚያጣቅስ ነው። ይህ ንግግር በአቀራረቡ በሚገባ የታሰበበትና የተደራጀ አይመስልም። በይዘቱም ስሜታዊነት አብዝቶ የተጫነው ነው። ጃዋር የሰነዘራቸው ሐሳቦችና “መረጃዎች” አሁንም ቢሆን አዲስ አይደሉም፤ የኖሩ ናቸው። አቀራረባቸው ግን አስፈሪ ነው። አስፈሪነቱ ከጃዋር በማልጠብቀው መንገድ የቀረበ ነው። የአፍ ወለምታ ነው ብዬ እንዳላልፈው ደግሞ ስብራት ሆነብኝ።

ኢሉ አባቦራም ላይ ይሁን ቶራቦራ ላይ፣ በቁጥር አብላጫ መሆን ሜንጫ የመምዘዝ ነጻ ፈቃድ እንደሚያቀዳጅ እንደዋዛ ሲነገር እደነግጣለሁ። ሰብአዊ ድንጋጤ። እኔም ሆንኩ ማንም ሰው ሜንጫ መዛዡም የሜንጫ ሰለባውም እንዲሆን ስላማልፈልግ። ጃዋር ያለው ነገር የትኛውንም የኢትዮጵያ ክፍል፣ ኦሮሞውን ሙስሊም ጨምሮ እንደማይወክል እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን ጃዋር እንዲህ ያለው ሜንጫ መዘዛ ተራ ክስተት የሆነበት አካባቢ ኖሮ ቢሆን እንኳን ነገሩ ሳያስደነግጠው ቀርቶ፣ ጭራሹን በአደባባይ ለሌሎች የሚሰብከው አኩሪ ስልት ሲሆን ያስደነግጣል። ነገሩ ኦሮሚያ ውስጥ በእውነት የሚፈጸም ቢሆን እንኳን ጃዋር ድርጊቱን ማውገዝ በተገባው ነበር። በጣም ሐላፊነት የጎደለው፣ አስተውሎት የተለየው እምነትና አነጋገር ነው። ሜንጫ መዘዛ ዛሬ “በሌሎች” ላይ ስለሚፈጸም ፈቃድ ከተሰጠው ነገ ለራሱ ለሙስሊም ኦሮሞ መጥፊያ መሆኑ አይቀርም።

ሌላው እጅግ በጣም አስደንጋጩ ነገር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ብሶት” ያቀረበበትና የለካበት መንገድ ነው። ስለሙስሊሞች መገፋት በመርህና ላይ ተመስርተው የተናገሩና የታገሉ ክርስቲያኖች በሚሊዮን በሚቆጠሩባት ኢትዮጵያ በማንኛውም መንገድ የሙስሊሞች ትግል ከክርስቲያኖች ጋራ የሚደረግ አስመስሎ ማቅረብ ስሕተት ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተፈጸመባቸውን ታሪካዊ በደል ማቅረብ፣ በደሉ እንዳይደገም፣ ሙስሊሞች ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው እኩል ተከብረው የሚኖሩባት አገር እንድትፈጠር መቀስቀስ የተገባ ነው። አሁን የሚፈጸመውንም በደል ማቅረብ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄዎችንም መደገፍ ያባት ነው። በዚህ ሁሉ ከጃዋርና ከሌሎቹም ሙስሊም ወገኖቼ ጋራ እቆማለሁ። ይህን ሲያስረዱ የሚያቀርቡትን ምሳሌ መምረጥ ግን የተናጋሪ ሸክም መሆኑን ጃዋር ዘንግቶታል፤ ወይም የታናገረው የሚያምነውን ነው። እውነት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቁልፍ ጥያቄና ህልም አክሱም ላይ መስጊድ መገንባት ነው? ለሌሎች ታሪክና ባህል ክብር ካለን፣ ዜጎች በተቻለ መጠን ተከባብረውና ተቻችለው እንዲኖሩ ማድረግ ቀዳሚ ፍላጎታችንስ ከሆነ በዚህ ጥያቄ ወደ ግጭት መግባት ይኖርብናል? የጃዋር ኢትዮጵያ ብትፈጠርና የፖለቲካ ስልጣን ሁሉ እርሱ በሚላቸው አይነት ሙስሊሞች ቢያዝ፣ አንዱ አጃንዳቸው አክሱም ላይ መስጊድ መስራት ነው ማለት ነው? አክሱም ላይ መስጊድ ቢገነባ ለአንድ በአካባቢው ለማይኖር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የሚሰጠው የድል ስሜት ከምን የሚመነጭ ነው? መካ ላይ ቤተ ክርስቲያን ወይም ምኩራብ፣ ቫቲካን ውስጥ መስጊድ ወዘተ እንዲሰራ መታገልና ማለም እውነት ሊታገሉለት የሚገባ ምድራዊ ዓላማ ነው? (ሰማያዊ ዓላማ ከሆነ ሌላ ጥያቄ ነው።) በድጋሚ እጅግ ሐላፊነት የጎደለው የተሳሳተ አስተሳሰብና አነጋገር ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቃ!ማኅበራዊ እሴትህን ጠብቅ፤ “ፖለቲከኛን ያመነ ጉም የዘገነ!” - በገ/ክርስቶስ ዓባይ       

የጃዋርን ንግግሮች ስሰማ በተደጋጋሚ የሚታወሰኝ በቀለ ገርባ ነበር፤ በግልጽ ምክንያት። (ስለበቀለ የፍርድ ቤት ንግግር የጻፍኩትን ማስታወስ።)

ለማጠቃለል፣ ውይይቱ ስለጃዋር ከመሆን አላመለጠም። (ፖለቲካዊ) ማንነት የእቅድና የአጋጣሚዎች ድምር ውጤት ነው። ጃዋርም ማንነቱን በዚሁ መንገድ እየቀረጸ ይታያል። ጥያቄው ጃዋር አንዳንዶቻችን ያሰብነው አይነት፣ በዴሞክራሲያዊ መርሆች የምሩን የሚያምን፣ ስለኦሮሞ ሕዝብ መብትና ነፃነት ሲታገልና ተረዱኝ ሲል በተራው ለሌሎች ማንነትና ፍላጎት ክብር የሚሰጥ፣ በመስጠትና በመቀበል የፖለቲካ መርህ የሚገዛ፣ ከቅርብ ነጠላ ድሎች ይልቅ ለረጅም ጊዜ ሰላምና ነጻነት የበለጠ ክብደት የሚሰጥ፣ ወይም ይህን ሁሉ የሚሞክርና የሚመኝ ይሆናል ወይስ ተቃራኒውን የሚል ነው። ጃዋርን በፊትም አሁንም ከእነዚህ አንዱንም አይደለም የሚሉ ወዳጆች አሉኝ። በፊት የነበረውም ሆነ አሁን ያለው ጃዋር ምንም ይሁን፣ የወደፊቱን ተክለ ቁመናውን መወሰን ለእርሱ ብቻ የተከለለ መብቱ ነው። እርግጥ ጃዋር እዚህ እኔ ከተመኘሁት የተለየ ሰው እንዲሆን የሚመኙና የሚጋብዙት ሌሎች ወገኖቼም እንዳሉ አውቃለሁ። ምርጫው የባለቤቱ ነው። ምርጫው የትኛውም ቢሆን ግን ስለሜንጫ መዘዛው ይቅርታ ቢጠይቅ ጃዋር ይከበርበታል እንጂ ይዋረድበታል ብዬ አላምንም። ጥያቄው መሆን አለመሆን ነው፤ አንዱን ወይም ሌላውን።

ከዚህ ቀደም እንደሆነው ሁሉ ከነልዩነቶቻችን ከጃዋር ጋራ ውይይታችንና ግንኙነታችን ይቀጥላል።

15 Comments

  1. Ato Messfin
    I agree with most of what you said but lets be honest who build Jawar Mohammed a monster he is now? Isn’t that the diaspora calling him ” the young political analyst, ESAT & VOA making him expert witness for every Ethiopian political issues. My question is what does I take for the so called Ethiopain intellectual “Social Mrorons” to learn from the past . Jawar Mohammed fanatic Narrow minded Anti Ethiopian is a regular guest on ESAT. But Mr Obang Metho was is real Ethiopian & Humanitarian is barley invited to appear n ESAT. The political direction of G7 & it’s confused leaders have created the best opportunity for people like Jawar Mohammed & Tesfay Gebreab (the double agent) who divided Oromo and Amhara people but that was not a problem for ESAT because G7 leaders don’t care about Amhara people and they are too busy creating alliance with OLF , OLFd, OLFe just anyone who can help them get to 4-Killo by any means.

    Just as I oppose Woyane i also hate OLF, or any Gugmangug Derejet alliance

    • Thank you Mahider, all I have been thinking even before this speech that is causing uproar now. I always chuckle when I hear the media call him, “young political analyst”, I am laughing as I write this.

      He reminds me of that kid, I forgot his name, 16 yrs old kid then who was primed to be the PM of Ethiopia adn the EPRDF camp was putting hallo on him. After a few crazy public writtings and speeches, he has disapeared.

      This Jawar kid is no different. He has already gotten over his head.

  2. We are not expecting any kind of apologies from this guy. Tell him not to waste his time for that matter. He should rather get ready himself to face justice. It will be a matter of time.

    • I think he is by far better than any political analist we have seen in ethiopian issue. he is so young and can improve a lot! let us not be too fast. I think he can really make a difference very soon!

  3. Betam asafari sew honoal belibu siaysbewu yenebre neger newu yetenagerwu tikklegna YEthiopia ALQAIDA newu 1nd fidel kotrealehu kemil sewu yihn mesemat yemejemeria Ethiopiawi sayhon aykerm. chencah le christianoch yazegajewu endale negronla. Ethiopiawi yehone hulu behig mefared alben. kezih belay ashebari yet ale? no.1extrimist. no body did not say as like him it is very stupid even in Afganistan did not say like this.

  4. to b honest, who made him popular for JUWAR? ESAT and ye TAMAGE BEYENE group. when Juwar was with them they said hero.when JUARE is talking his polotical thinking they start blaming. juwar is extrmist and Tamage toxicboth are the same to me .Tamage doing his job for ESAT fund rising in the name of Ethiopia,he has 30%shere from fund money.JUWAR most of the time seting next of Tamage beyene.both are historical enemy of Ethiopia.both are Boko Harame..was founded as an indigenous group turning itself jihadist .
    ke JUWAR ena Tamage gorade….TPLF asero befetan yeshalal

  5. መስፍን ነጋሽ … የምን መርመጥመጥ ነው እሱ? ይሄ ሰው ለማንም የማይበጅ አተላ ነው:: በራሱ ጊዜ ፖለቲካዊ suicide ፈጽሞ ከእስስትነቱ ገላግሎናል:: የምን ጥንብ አንሳ መሆን ነው እሱ:: ሰልፍ ሴንተርድ ደደብ ሰው ስለሆነ እኮ ነው ፖለቲካውን በራሱ ሃይማኖቱና በብሄሩ ብቻ የተማከለ እንዲሆን በጽንፈኝነት እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ሌላው ቀርቶ በቃልቻ ስለሚያምነው የጥንቱ ኦሮሞ ደንታ የሌለው ሰው እኮ ነው:: እርሱ በሚለው መልኩ ምንም አይነት ፖለቲካ አንዲት ስንዝር መራመድ አይቻልም:: ከእስላሙ ጋር ጽንፈኛ እስላም ለመሆን ሲሞክር ይኸው ኦሮሞ ብሄርተኞችን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያውያኖችን ያስቆጣል:: ከኦሮሞ ብሄርተኞች ጋር ጽንፈኛ ብሄርተኛ ለመሆን ሲሞክር ደግሞ እስላሞችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣል:: ከራሱ ውጪ ማንንም የማይመለከትበት የተጣረሰ ፖለቲካውን እዛው የራሱን ማንነት ይቅረጽበት እንጂ ዳግም ወደ መድረክ የሚመጣበት ቅንጣት ታክል ዕድል ሊሰጠው አይገባም:: ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንዳልኩት (በቅርብም ስለማውቀው) ጀዋር ለኦሮሞ ብሄርተኞችም የማይበጅ መሰሪ ሰው ነው::

    ይልቅ ሌሎችን ለመምራትና ለመስበክ የሚሞክርበትን ፖለቲካውን ያቆየውና፤ ማንነቱን በደንብ እንዲያውቅ ምክሩት:: እውነተኛ ኦሮሞ ከሆነ፡ የገዳ ስርዓትንና እስልምናን ምን እንደሚያገናኛቸው ጠይቁት:: በግድ የተጫነበት ማንነት ኢትዮጵያዊነት ወይስ የእስልምና እምነት? ጠይቁልኝ::

    • Gama, I think you have to be peciant and improve your thinking caliber, I feel like you never had education and you attitiude is realy very local to dembecha!

  6. @mahoder and the writer of the article wedi Negash,you are praising each other for your evil deeds. Mesfin is supporting the idea of insane JEWAR who is blaming Ethiopians for subscribing ethiopian nationality to oromos and your buddy probably your homeboy mahider was also furious about ESAT and G7 achievements as they are real threats for the survival of your TPLF government. Mesfine would like to advice Ethiopians to acknowledge JEWAR’s independent oromia and facilitate a discussion forum for his damn fabricated history to get internalized by Ethiopians. Even Mesfin didn’t hesitate to confirm the data provided by the confused OLF cadre JEWAR is flawless. That is what time has told us. It is not too long for us to figure out the identity of Individuals like Dawit of Awramba and Mesfin Negas. Do you think we will welcome JEWAR on our ESAT to announce his hatred against Christian and fantasy of free oromia? Never again. If you are sympathetic with his ideology you can put him in touch with any of the medias run by your TPLF government proposing article 39 on the constitution. JEWAR’s 50years OLF propaganda and TPLF ethinic politics will no longer be tolerated. So there is no room in ESAT to intertain anti-Ethiopia subjects and thoughts. In principle you and your government TPLF are identical with JEWAR in all aspects so stay intertwined but leave us alone we have nothing in common. Your master deceased Zenawi philosophy of ‘give and take’ has no place in ESAT because we can prove it wrong with Assab and Bademe. That is the legacy of your visionary leader who had struck by brain cancer. The snake is bitten on his head. The same fate will happen to all evil people who conspires against Ethiopia and Ethiopians.

  7. አቶ መስፍን ከፈለግህ አንተ በሜጫ አንገትህን ልትስቆርጥ ትችላለህ። ሌላውን ግን ዝም ብሎ አንገቱ ሲቆረጥ የሚያይ አይኖረም።

    አቶ መስፍን ያልተገነወበው ዋናው ጉዳይ ጃዋር ብቻውን አለመሆኑን ነው። ብቻውን ቢሆንማ ያ ሁሉ ተሰብሳቢም እና ሀጅ ናጂብ የጃዋርን የክርስቲያኖችን አንገት በሜጫ ለመቁረጥ መዛት በተቃወሙት ነበር። ከተሰብሳቢወች ውስጥ አንድም ሰው ይንን የጃዋርን አንገት መቁረጥ የተቃወመ አላየነም። እንዲያውም እኛ ከቪዲዮው ያየነው አብዛኞች ተሰብሳቢወች በጃዋር የአንገት በሜጫ እቆርጣለሁ ድንፋታ በጭብጨባ ነው ሲቀበሉት ያየነው።

    እናም አቶ መስፍን ጃዋር አንድ ብቻ ሰው ሳይኖን በርካቶችን ሰብስቦ የጃዋር እምነት ማለትም አንገት የመቁረጥ ስምጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ነው የተረዳነው።

    ከላይ እንዳልኩት አቶ መስፍን ከፈለግህ አንት በጃዋር አንግትን በሜጫ ማስቆረጥ ትችላለህ። ሎችን ግን ዝም ብላችሁ አንገታችሁ እስኪቆረጥ ተቀምጣችሁ የምትለው ነገር ተቀባይነት የለውም።

  8. Jawat Mohammed is a muslim extremist who believe that Oromia is a muslim state, shame on Jewar.

  9. >>አድማሱ>ጋማ>አምባሰል ያቀረቡት ሐሳብ ይመቻል። አቶ መስፍን ነጋሽ ምን ማለት እንደፈለገ ግልጽ አደለም አገም ጠቀም ይበዛዋል በለው! ይህ ነው ሀገርና ሕዝብ የጎዳ።ለማናቸውም ዋናው ለጃዋር ኦሮሞን ለእሰላማዊነት እንዲጀውር መድረክ የከፈተለት እንዲያውም ከሕንድ ባህል ለመወዳዳር “ሜንጫ ‘ታጥቆ ሚኒያፖሊስ ሜዳ ሲፈነጭ የሚቀርጸውና የሚያባዛለት?የሚያደምቅለት? የሚያሽቋልጥለት? የሚያንቆለጳጵሰው? ባንዲራ እየወጠረ ውሃ እያቀረበ የሚያስቦጠልቀው? ማነው?…አደለምን። ግን ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም!ይኸው ያችኑ ከነጭ የዋጣትን ፖለቲካ ተፍቶ ጨረሳት ጭራሽ ጉራጌው፣ኦሮሞ፣ወሎ፣አፋር ኦጋዴን የሚባል ለም ሁሉም እስላማዊ ኦሮሞ ብቻ ነው ብሎ መሪያቸውን ሼህ ናጂብን አሳመነው። ታዲያ ይቺ የምትሰማ ድምፅ የማነች? የመገንጠል የእስላማዊ መንግስት? ወይንስ መልካም አስተዳደርና ፍትህ ድምፅ? እንግዲህ ይህ የሚጮህ ሁሉ ኦሮሞ ሲገነጠል አክሱምና ፋሲል ግንብ ላይ መስጂድ ለመገንባት ከጮኽ ችግር አለ። አይ የፍየል ወጠጤ…
    የአቶ መስፍን ነጋሽ ማለባበስና ፕሮፌሰር ኤፍሬምን መተካት አይጠቅምም። ለሀገር ፀር፣ ከፋፋይ፣ ገዳይ፣ አረመኔ፣ ጨካኝ፣የሰው ልጅ ከእነነፍሱ ገደል የሚጨምረው የጃዋር ደጋፊ ሁሉ የወንጀል ተባባሪ (አሸባሪ) ብቻ ሳይሆን የሰው ፀር(አውሬ) ነው። ለፍርድ ይቀርባል።ወያኔ ያሰለጠናቸውን ሆድ አደር፣ አድርባይ፣ የቅርብ ባለሥልጣናትም ሊከታተልና ቶሎ ቶሎ ሊፈትሽ ይገባዋል ሀገርና ህዝብ ለእርስ በበእርስ የሜንጫ ጭፍጨፋ ጥሎ መጥፋት የወንጀለኛ ፈጣሪም ፣አሰተማሪም፣የብጥብጥ ንድፍ ያወጣና ያስተገበረ ተደርጎ ያስጠይቀዋል።(ኢንተራምወይ) ያላትን ያስታውሷል ስለዚህ እራሱን ከውስጥም ከውጭም እንዲፈትሽ አካባቢውን በአስቸኳይ እንዲያጠራ እንጣራለን እስከዚያ አንዳንድ ልፍስፍሶች እራሳቸውን ከድብቅ ሴራና የውሸት ፍቅርና አንድነትን መስበክ ይቆጠቡ በለው!።

  10. I didn’t know him before but after I watched his interview on different television and media outlet I realised this young man has a good understanding and knowledge.he is too young because of that he made a mistake. I advise Jawar not to do this type of mistake for the future and learn from your mistake.all of us we made a mistake when we were young.I think good to forgive him.

Comments are closed.

Share