ከነመላኩ ፈንታ በኋላ የቆመ መርከብ የሆነው ፀረ – ሙስና ኮሚሽን

ከሰናይ ቃል
መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ እየሆኑ ከመጡት ነገሮች መካከል የሙስና ተግባር በጣም በጣም አሣሣቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ሰዎች በአንድ ጀምበር የሚመነጠቁበት ይህ የሙስና ተግባር ታዲያ በአግባቡ ቁጥጥር ተደርጐበታል ወይም ክትትሉ የሁሉንም አካል ጥያቄ ያማከለ ነው ለሚለው ብዙ አሻሚ የሆኑ ነገሮች አሉበት፡፡ ለዋቢነት መጥቀስ የሚቻለው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዜና በረጅም አመት ሙሰኛ ተገኘ ብሎ አንድ ትልቅ ባለስልጣንን የማያዝ እንጂ በትክክለኛው መንገድ መስመር ተከትሎ የሚሰራ ባለመሆኑ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን እንደሚታወቀው ከሆነ ትልቅ ዜና ሆኖ የሰነበተው የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን በአቶ መላኩ ፈንታ የሚመራው ቡድንና ሌሎች ነጋዴዎች ከሙስና ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ምናልባትም ሲደረግ ወይም ሲተገበር ያስደነገጠው የሕብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ እንዴት ይህ ሊደፈር ቻለ ይህ እርምጃስ አሁን በምን ታወሰ የሚል አልጠፋም፡፡
ኢህአዴግ አንድ የሚገርም ባህሪ አለው ነገሮችን የማስቀየሻ ተግባራትና ለመስዋእትነት የሚያቀርባቸው ባለስልጣናት፡፡ በወቅቱ አንድ በመንግስት ላይ ፍጥጫ የሚፈጥር ወይም የሕዝብ ትኩረትን የሚስብ ነገር ካለ ያንን ነገር ለማስለወጥ ወይም ለጋሽ ሀገራትን ሀሣብ ለማስቀየስ ይህንን ተግባር ይፈፀማል፡፡ በወቅቱ ታዲያ ትልቅ ዜና የነበረው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ያቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ በሕዝቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ሲጠበቅ የነበረ ጉዳይ ነበር፡፡ እናም ግን ታዲያ ይህ የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ ሆነ፡፡ በተለይ የእስክንድር ነጋ ንብረት ምንም በማይገናኝ መልኩ እንዲወርስ መደረግ ደግሞ ይበልጥ የሕዝብን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ለማጨለምና ለማጥፋት ታዲያ ኢህአዴግ አጋጣሚው ከተጠቀመባቸው መንገዶች መካከል አንዱና ዋንኛው ነገር ምንም ሣይሆን ይህ እነመላኩ ፈንቴ በሙስና የተያዙበት ጉዳይ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ እንደነ “UNDP” ያሉ ተቋማት በሀገሪቱ ለሚደረገው የፀረ ሙስና ዘመቻ የገንዘብ ድጐማ ያደርጋሉ፡፡ ይሁንና ግን እነሱ በኢትዮጵያ ያለውን የሙስና ጉዳይ በሚመረምሩበት ወቅት በ15 ወይም በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ መውጣቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም የዚህ ገንዘብ መውጫና የወጣበት አካልም ማንም ሣይሆን የመንግስት አካል መሆኑ በቀጥታ ጣቱን ቀስሮ የመጣው ወደ መንግስት ሆነ፡፡ እናም ይህን ጉዳይ ማስተባበል የሚቻለው ለመላምትነት በሚቀርቡ ባለስልጣናት ዙሪያ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ መላኩ ፈንቴ የሚመራ ቡድን በሙስና ተጠርጥሮ ወህኒ ወረደ፡፡ ሙስና በዚህች ሀገር ላይ አይፈፀምም ሣይሆን ሙስና ሌላው የመተዳደሪያ ደንብ ተደርጐ ሁሉ እስከመቆጠር ተደርሷል፡፡ ታዲያ አቶ መላኩ ላይ ይህ በትር ሲያርፍ እሣቸው በበርካታዎች ዘንድ በዚህ ነገር ስለማይጠረጠሩ ጉዳዩን ግራ የሚያጋባ እንዲሆን አድርጐታል፡፡ እንደውም አሁን በአንዳንድ ወገኖች በኩል እሣቸው እንዲፈቱ ፒቲሽን ሁሉ ሣይቀር የሚያስፈርሙ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አዜብን የሚጠረጥር ደፋር ጠፋ?እንደሚታወቀው ታዲያ የነአቶ መላኩ ፈንቴ የሙስና ጉዳይ ከተፈጠረ በኋላ “ትላልቆቹን አሳዎች” አጠምዳለሁ ሲሉ የተነሣው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጉዳይ ውስጥ ያለውን የሙስና ተግባር ለማጣራት ተደስቻለሁ ሲል ገልጿል፡፡ እንደሚታወቀው ከሆነ በርካታ በሙስና የሚገቡ ባለስልጣናት የተካሰሱበት ነገር በሙስና ሣይሆን ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በርግጥም የዚህ አይነት ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ለምሣሌ በ1993 ዓ.ም. አቶ ስዬ አብርሃ ሲታሰሩ የሙስና ጉዳይ ተባለ፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን እየመራሁ ነው ቢልም ከነመላኩ ፈንቴ በኋላ የተቋረጠ የሚመስለው ሙሰኞችን የማፈላለጉና የመያዙ ሁኔታ ብዙም አርኪ የሚባል አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፖለቲካው አሠራር ነፃ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሕዝብ እንኳን የትኛው ባለስልጣን ምን አይነት ሀብት እንዳለው፤ የማን ባለስልጣን ህንፃ እንደሆነ በደንብ ያውቃል፡፡ ይህን ጉዳይ ደግሞ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጠፍቶት ነው ብሎ በድፍረት ለመናገር የሚከብድ ነው የሚሆነው ምክንያቱም እያንዳንዱን ነገር ውስጥ ድረስ በመግባት የመመርመር ስልጣን አለውና፡፡ ፀረ – ሙስና ግን ይህን ነገር አይቶ በማለፍ የማይረቡና የዚህን ያህል አንጀት የሚያረሱ ጉዳዮች ላይ ጊዜውን ሲያባክን ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚህች ሀገር ሁሉም ነገር የተሳሰረ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ፈፅሞ ነፃ ሆነው እንዲሰሩ የሚፈቅድላቸው ተቋማት የሉም፡፡ እነ አምነስቲና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጉዳዮች የሚቆጣጠሩ ተቁማት ላይ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ግለሰቦችን ቢያስገባ ሁሉ ደስታው ነው፡፡ የማይሆን ነገር ሆኖበት ነው እንጂ ታዲያ አሁን ያለው የሙስና ሁኔታ ምን ያህል የሚያስኬድ ነው; ምን አይነት ለውጥስ ያመጣል; የሚለውን ከታዘብን፡፡
በፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚገኝ ሙስናን የማፈላለግና ለውጥ የሚመጡት ነገር ምናልባትም በኢህአዴግ ችሮታና፣ እሱ ይህንን አድርጉ ሲል የሚፈጠር ነው የሚመስለው፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ቀደም ብሎ አፈትልኮ በወጣ ምስጢር አማካይነት የተሰማ ነው፡፡ በጥቅምቱ የባህርዳር ጉባኤ ወቅት “አቶ መላኩ ፈንቴ ምን ብለው ተናግረው ነበር; እነማንንስ አጋልጠው ነበር; ማን ነው ይህንን እንዲናገሩ ሁኔታዎችን ያመቻቸላቸው; ከዛስ በማን ተጠልፋው ለዚህ ነገር በቁ;” እነዚህ እነዚህ ጉዳዩች በሙሉ ተጋልጠው ሲታዩ በውስጣቸው የፖለቲካ መንፈስ እንዳለበት በግልፅ የሚያሣይ ነው፡፡ ዛሬ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና ተነክረዋል፡፡ አንዳንደች የግምገማ በትሩ ሲበረታባቸው ካላቸው ወይም በሙስና ከገነቡት ቤት አንዱን ለፓርቲዬ ብለው ያስረክባሉ፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን የዚህ አይነት ነገሮችን ለምንና እንዴት በማለት መጠየቅ ቢገባውም ይህንን አልደፈረም፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባይነግረንም ከዚህ በኋላም ምናልባት ከአንድ አመት በኋላ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጠን ይወርዳል፡፡ ከኢህአዴግ ጋር አብሮ ከመኖር የገባን ነገር ነው፡፡ ከአንድ አመት ተኩል በኋላ ፓርቲው የአምስት አመት የስራ ጊዜውን ይጨርሳል፡፡ እናም ኢህአዴግ የሚፈልገውን ከማይፈልገው ሲለያይና ሲመዳደብ ለፀረ ሙስና ኮሚሽንም የሚሰጠው ቦታ ይኖረዋል፡፡ በቃ እንዲህ እንዲህ እየተባለ ነው ታዲያ ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ስራ ወይም እንቅስቃሴ አደረገ የሚባለው፡፡ እናም ከነመላኩ ፈንቴ በኋላ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የቆመ መርከብ ሆኗል፡፡ ሌሎች ሙሰኞች መረጃቸውን እንዲያሸሹ ከነመላኩ ጓደኞች ስህተት ተምረው እንዲዘጋጁ ያደረገ ነው የሚመስለው፡፡ ብዙ መሄድ ሲገባው በትንሹ ተጉዞ ለጊዜው በቃኝ ሲል የወሰነ ተቋም ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወልቃይት ፣ ጠለምት እና ራያ ህወሃት በከለለው ግዛት ስር ይሁን ፣ (Status- Quo -Ante) ይከበር የሚለው ቅዥት እና ተረት ተረት።

1 Comment

  1. “ሚስትህ ወንድ ልጅ ተገላገለች ብሉት ማንን ወንድ አርጋ አለ”አሉ ባል::

Comments are closed.

Share