“የመንግሥቱ ኃ/ማርያም የትምህርትና ዕውቀት ውስንነት እንዳለ ሆኖ፤ የተፈጥሮ ብሩህ አዕምሮውን ግን ለመካድ አይቻልም።” – ፕ/ር ገብሩ ታረቀ

“የመንግሥቱ ኃ/ማርያም የትምህርትና ዕውቀት ውስንነት እንዳለ ሆኖ፤ የተፈጥሮ ብሩህ አዕምሮውን ግን ለመካድ አይቻልም።” – ፕ/ር ገብሩ ታረቀ

ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ፤ ስለ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም የአገዛዝ ዘመን ጅምርና ፍጻሜ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ “The Ethiopian Revolution: War in the Horn of Africa” እና “Ethiopia: Power and Protest: Peasant Revolts in the Twentieth Century” መጻሕፍት ደራሲ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድመት የደረሰባቸውን ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ!

7 Comments

  1. Yemigerimew yeahunuwa Ethiopia YE MOT FIRID FERDABET hagerun yiwedatal…ENEHO kesashochu end ferajochu yet new yalut ???????

  2. ፕሮፊሰሩና ገነት የሚያወሩት ስለ መንግስቱ ታሪክና ፖለቲካ ነው:: አሁን የሚያስፈልገው ግን ወንጀለኛውን መንግስቱን ለፍርድ ማቅረብ ነው:: 500000 ሰዎችን ገድሏል::

  3. ታሪክ የማያቋርጥ ሂደት ነው፣ታሪክ ሰሪው ሰፊ ህዝብ ነው አዎ ይሄንን ታሪክ በአግባቡ እና በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ሳይዛባ እና አድልዋ(bias) ሳይኖረው ያለፉ ድርጊቶችን ጥሩም ሆነ መጥፎዎችን አውቆና ተረድቶ አሁ ን ላለውና ወደፊት ለሚመጣው ትውልድ የተሻለ ሁኔታዎች እንዲፈጠር ታሪክን ማወቅ ይገባናል፣፥
    አዎ ይሄንን የማያቋርጥ የታሪክ ሂደት መዝግቦ ለትውልድ ለማስተላለፍ ደግሞ በታሪክ እውቀትና ሞያ ያላቸው ምሁራን የግድ አስፈላጊ ነው፣የኢትዮጵያ ታሪክ በውጭ ጸሃፍት ተጽፈዋል፣በኢትዮጵያውያን ጸሃፍትም ተጽፈዋል አሁንም እየተጻፉ ነው፣
    በተለይ የአዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንት ምሁራን እድሜና ጊዜአቸውንየኢትዮጵያን ታሪክ በማጥናት በመጽሃፍ መልክ በማሳተም ጉልህ ድርሻ ነበራቸው ብዬ አምናለሁ በተለይ እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት፥ፕሮፌሰር መርእድ ወልደ አረጋይ ሁለቱም በህይወት የሌሉ እንዲሁም አንጋፋው ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን ታሪክ ሲነሳ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፥፥የኢትዮጵያ ወዳጅ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያለቸው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፥ ባለቤታቸው ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያን ታሪክ በአለም አቀፍ ደረጃ በማሳወቅ በግንባር ቀደም የሚጠቀሱ ናቸው፣
    የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ ከዳማት የጥንታዊ ኢትዮጵያ ታሪክ እስከ አጼ ሃይለስላሴ ዘመናዊ ታሪክ ያለመታከት ለትውልድ ጸፈው ያቆዩልን እውቁ የታሪክ ጸሃፊ ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ መቼም የሚረሱ አይደሉም፣
    በነገራችን ላይ በዚሁ በስድስት ኪሎ የኒቨርስቲ ውስጥ በጋደኛዬ መረጃ መሰረት በታሪክ መምህርነት ከአርባ አመት በላይ world history ከመጀመሪያ አመት እስከ አራተኛ አመት የታሪክ ትምህርትን በማስተርስ ዲግሪ በመስጠት የሚታወቅ የውጭ ዜጋ የእንግሊዝ ይሁን የአይሪሽ ዜግነት ያለው ከጋደኛዬ በጨዋታ መልክ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያዊት ያገባና ልጆች የወለደ በሚሰጣቸው ኮርሶች ለማስተማሪያ መርጃ የሚሆኑ በጣም ዳጎስ ያሉ የተለየዩ መጽሃፍቶችን ጽፎ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኬኔዲ ላይብረሪ የተቀመጠለት አንጋፋ ረጅም ቀጠን ደከመኝ ሰለቸን የማያውቅ ደቂቃ በስራው ላይ አለአግባብ የማያባክን ያለ ምንአልባትም አሁን በህይወት ይኑር አይኑር አላውቅም መምህር ነበረ ስሙም ዴቪድ ቻፕል ይባላል፣በእኔ እምነት ይሄም መምህር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መጠቀስ የሚገባው ይመስለኛል ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም ስለሱ ምንም ነገር አናውቅም እስቲ እባካችሁ ተማሪዎቹ ወይም አሁን በህይወት ያሉት ተማሪዎቹ ወይም ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ቢያሳውቁን ስለስራው ስለታሪኩ በጣም ደስ ይለኛል፣
    በተረፈ ግን ፕሮፌሰር ገብሩ አሁን በዚህ ፕሮግራም ላይ እንደሰማሁዎት አቀራረብዎ በጣም ደስ የሚል እና በቀላሉ ልንረዳ የሚያስችል ነው በእኔ በኩል።በንጽጽር መልክ ካቀረቡት ውስጥ የታሪክ ባለሙያ ባልሆንም አንዳንድ ነገሮችን ብል በጣም ደስ ይለኛል
    በአንደኛነት የደርግ መንግስት የሶማሊያን ጦርነት ማሸነፉ ተጠቅሶአል ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ደርግ ስልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምድርጦሩን አየር ሀይሉን ባህር ሃይሉን የፖሊስ ሰራዊትን ጨምሮ ከአርባ ሺህ በላይ አይበልጥም ነበር እናም ወረራውን ለመቀልበስ እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸውን የተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች በመሳሪያና በሰው ሃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ በማደራጀት በተለይም የሚሊሺያ ሰራዊቱን በታጠቅ ጦር ሰፈር ከሶስት መቶ ሺህ ሰራዊት በላይ በሶስት ወራት ውስጥ በማደራጀት የሶማሊያን ወረራ ለመቀልበስ ችሎአል፣ህዝቡን ሞቢላይዝ የማድረግ ችሎታው በወያኔም ሆነ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግስታቶች ለየት ያደርገዋል፣ልብ በሉ ሶማሊያ ከሰባት መቶ ሃምሳ ኪሎ ሜትር በላይ ዘልቃ ገብታ ነበር፣
    ወያኔስ በቅርቡ እንኩዋን በባድሜ ጦርነት የባድሜ ጾረናን ግናባር ለሁለት አመታት በሻእቢያ ቁጥጥር ስር ነበር በእርግጥ ጦርነቱ ሲጀመር በሶስት ቀናት ውስጥ ሻእቢያ ሊደመሰስ ችሎአል
    ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ሰራዊቱን በትኖአል አሁን የባህር ሃይል የለንም አየር ሃይልም የለንም ማለት ይቻላል።የሀገሪቱን መሬት ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በገዛ ፈቃዱ ለሱዳን እየሰጠ ነው
    በሁለተኛ ደረጃ የውጭ ፖሊስን በተመለከተ ደርግ የሶሻሊዝም ስርአት ተከታይ መሆኑ እና ፖሊሲውም በሰላም አብሮ የመኖር ፖሊሲ peaceful co_existance ነበረ በማናቸውም ሀገሮች የውስጥ ጉዳይ በግልጽ ጣልቃ ገብ አልነበረም እንዲያውም በሱማሊያ ጦርነት ወቅት የሩሲያ ወታደራዊ አማካሪዎች የኩባ እና የየመን ወታደሮች በውጊያ ውስጥ በግንባር በመሳተፍ የመታሰር የመሞት የመቁሰል አደጋ አጋጥሞአቸዋል
    በወያኔ ጊዜስ እንኩዋንስ ከጎናችን ሊቆሙ ቀርቶ የኢትዮጵያ ወታደሮች በማያገባቸው በማይመለከታቸው የውክልና ጦርነት proxy war እየተሳተፉ አካላቸውን ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል፥አሜሪካኖች በኢራቅ በውጊያ ተሳትፈው የሞቱባቸው ወታደሮች በክብር አምጥታ ስትቀብር ወያኔ ግን በሶማሊያ የተሰዉ ወታደሮችን ሬሳቸው እንዲጎተት ያደርገ መንግስት ነው፣
    በሶስተኛ ደረጃ በእምነት በኩል የተናገሩትን እስማማበታለሁ በፊውዳል ዘመን መንግስትና ቤተ ክህነት የማይነጣጠሉ እንዲያውም የቤተ ክህነት መሪዎች የሚፈልጉት መሪ ከስልጣን ላይ እንዲወታ ታላቅ ቅስቀሳ ያደርጉ እንደነበር ለምሳሌ ይኩኖ አምላክን ወደስልጣን ለማምጣት የተደረገውን መጥቀስ በቂ ነው ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የነገስታቱን ስራና ድርጊት ለመቃወም አፈንግጠው የወጡ ለምሳሌ በጸሎተ ሚካኤል እምነታዊ የጥገና ለውጥ ለማምጣት ሲጥር ስደትና መከራ የተቀበለ መሆኑን እናያለን፣
    በሌላ በኩል በተጨማሪ በቀዳማዊ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት ወቅት የንጉሱን ስራና ድርጊት በመቃወማቸው በእስራትና በግዞት የተቀጡ ቀሳውስቶች ነበሩ። አምደ ዮን ከእናቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት አድርጋል በሚል እርሱም የተኛሁአት የእንጀራ እናቴን እንጂ ወላጅ እናቴን አይደለም የሚል ክርክር ነበር፥እዚህ ላይ መጽሃፍ ቅዱስም ቃል ኦሪት ዘሌዋውያን ምእራፍ 18 ቁጥር 6 እስከ 23 ማንበቡ ይጠቅማል
    ደርግ የሃይማኖት እኩልነት ቢደነግግም መሪዎቹ ሃይማኖት የለሾች ነበሩ ስርአታቸውን የተቃወመውንም በማሰር እና በመግደልም የታወቁ ነበሩ ነገር ግን ደርግ በአመራር ደረጃ ህብረ ብሄራዊ የነበረ በተለያዩ የእምነት ተቃማት የነበሩትም ከሞላ ጎደል ህብረ ብሄራዊ ነበሩ፣
    በወያኔ ጊዜስ የነበረውን ሲኖዶስ አፍርሶ ከአንድ ብሄር ብቻ የወጡ ጳጳሳትን በማስቀመጥ የእምነት ስራ እንዲስተጋጎል ቤተክህነት ሀብትና ንብረት እንዲሁም ቅርሶች እንዲዘረፉ እንዲጠፉ ያደረገ በአደባባይ ላይም የተቃወሙትን በጥይት የረሸነ ያሰረ መምግስት ነው በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያ ቅጥር የደፈረ እና መሬትዋን አሳልፎ የሰጠ ዘረኛ እምነት የለሽ መንግስት ነው ከዚህ በተጨማሪ በርግጥ በግራኝ ወረራ ወቅት እና በዮዲት ጉዲት ዘመን ቤተክርስቲያኖች የተቃጠሉና የተዘረፉ እንዲሁም forced conversion የተካሄዱ ሲሆን ይሄ ማለት በፊውዳል ነገስታቶች ዘመንም እስላሙ ወደ ክርስቲያንነት በግድ እንዲለወጡ ተደርገዋል። በወያኔ ግን የእምነት ተቃማትን በማፈራረስ መሪዎችን በማሰር ከፍተኛ ደባ የፈጸመ መንግስት ነው ይሄም ነታወቅ አለበት፥

  4. ሀገርን ለመምራት በቂ ትምህርት ነው የነበራቸው ፕሬዚዳንት መንግሥቱ።
    አሜሪካን ሀገር Auto Mechanics በሚሊታሪ አካዳሚ የተማሩት እና በርሳቸው ዘመን 12ኛ ክፍል ድረስ የወሰዱት እውቀት ከማንም ምሁር አያንስም።
    ሀገርን ለመምራት PHD ወይም ከዚያ በላይ አያስፈልግም።
    በአደጉ ሀገራት ምሳሌ ብንወስድ የአሜሪካን መሪዎች ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ኒክሰን የባሕር ኃይል ኮማንደር ነበሩ።
    ሌሎችም በቅርቡ ሪፓብሊካንን ወክለው ከኦባማ ጋር ተወዳድረው የነበሩትም የአየር ኃይል አብራሪ ነበሩ።

  5. የቀሩኝን ሃሳቦች ልጨምር በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጣሊያን ወረራ ወቅት ህዝቡ ለጣሊያን ወረራ ፈጽሞ እንዳይገዛ የነፋነት ትግሉን አጠናክሮ ወራሪውን ሃይል እንዲያስወጣ ታላቁ የእምነት አባታችንና ሰማእቱ አቡነ ጴጥሮስ የህይወት መስዋእት ከፍለዋል.፣፥በወያኔ ጊዜ ያሉትን የሞተውንና አሁን ያሉትን ጳጳስ እና በሲኖዶሱ ውስጥ ያሉትን አባቶች ስራና ድርጊት ደግሞ ስናይ ፈጽሞ ከእምነት አባቶች የማይጠበቅ ህዝብ ላይ ሰቆቃ ሲደርስ መሬት በግፍ ተነጥቀው ሲፈናቀሉ ከእምነት አባቶች የሚጠበቀውን ያላደረጉ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ናቸው
    ሌላው ስለ መንግስቱ አወጣጥ ነው፣ፈረጠጠ ወይስ ተገዶ ወጣ ለሚለው ተገቢ ምላሽ መገኘት አለበት አሁን በህይወት አለ ነገር ግን እንደተጨማሪ መረጃ ሊጠቅም ይችላል፣ከጋደኛዬ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ነው ብላቴ ማሰልጥና ውስጥ ነበር፣ያው እንደምታውቁት ደርግ መውደቂያ ሰአት ላይ በሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወንድና ሴት ተማሪዎች በብላቴ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ እኔ በግዳጅ ነው የምለው ለወታደራዊ ስልጠና ገብተው ነበር ይሄን ያነሳሁበት ዋነኛ ምክንያት ፕሬዚዳንት መንግስቱ ተማሪዎችን ለመጎብኘት ሆዶ በዚያው ተገዶ ወጣ ነበር የሚባለው ይሄንን እንደማጠናከሪያ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁኔታዎች በማሰልጠኛው በወቅት የታዩ ምልክቶች ነበሩ ይሄውም የአየር ወለድ የክብር ዘብ መንግስቱን ለመቀብል በአየር ማረፊያው ላይ ተሰልፎ ይታይ ነበር በተጨማሪም መንግስቱን ይዛ የነበረችው አውሮፕላንም በብላቴ ማሰልጠኛ በአየር ላይ በግልጽ ትታይ ነበር ይሄ ሲታይ ምን አልባት ተገዶ ሳይወጣ አልቀረም ያስብላል፣ከእዛ በተረፈ ግን ወታደራዊው ማሰልጠኛው ዋና አዛዥ የነበረው ዶክተር ኮሎኔል ጥላሁን ሀይለማርያም ነበር የፕሬዚዳንቱ ወንድም ነበር፥ምን አልባት በህይወት ካለ ስለሁኔታው ጠቃሚ መረጃ ሊሰጥ ይችላል፣ስል ብላቴ ትንሽ ብል ደስ ይለኝ ነበር፣
    በመጭረሻ ግን ስለ መጽህፋቸው ግን አንድ ነገር ልበል አንድ አባባል አለ ከሀገሩ የወጣ ደራሲ እና ከባህር የወጣ አሳ አንድ ናቸው ምን አልባት ይሄ አባባል ለልብ ወለድ መጻህፍት ደራሲያን ሊሆን ይችላል እንደዚህ የታሪክ መጽሃፍት አዘጋጆች ልይ አባባሉ ላይሰራ ይችላል.የፍቅረስላሴን አንብቤዋለሁ የፍስሃ ደስታን ግን አላነበኩትም እኔ የሁለቱን ሳነጻጽር ግን የፍቅረ ስላሴ ጋር በምንም አይገናኝም በአጻጻፉ ይበልጣልብዙ ምክንያት ልንሰጥ እንችላለን ፍቅረ ስላሴ ከመጽሃፍት አጻጻፍ ጋር በቂ እውቀትና ችሎታ ያላቸው ሰዎችን ኢትዮጵያ ውስጥም ስለነበረ በቂ የታሪክ መረጃዎችን እንዳገኘ በመፍሃፍ ላፅ ጠቅሶአል ።መንግስቱ ግን ያ ሁኔታዎች አልተሳኩለትም በነዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል ጽሁፉ በካድሬ ቃላቶች የተሞሉ አንዳንድ ቦታዎች በውሸት የተሞሉ ናቸው፣ስለ መጽሃፍ ከተነሳ ለመሆኑ ርእሳቸው ከጣሪያ በላይ የጮሁ መጻህፍትን ታውቃላችሁን አንደኛው ተራራውን ያንቀጠቀጠ ትውልድ የሚለው የተስፋዬ ገብረ አብ መጽሃፍ ነው በርግጥ አላነበብኩትም ሁለተኛው ደግሞ ያነበብኩት የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች የሚለው ነው ደራሲውን አላስታውሰውም ምንም ፍሬ ነገር የሌለው መጽሃፍ ነበር
    በተረፈ ግን አንድ ታልቅ ማስጠንቀቂያ አለኝ ከተስፋዬ ገብረአብ ከልደቱ አያሌው እና ከጁዋር መሃመድ እርሾ ኢትዮጵያውያን ተጠበቁ አደራ

  6. ዶር ገብሩ ስለ መንግስቱ ኃይለ ማርያም የጻፉት በታሪክ ምሑር እይታ ነው።የመንግስቱ ጉዳይ ግን መታየት ያለበት በፍትሕ መነጽር መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም መንግስቱ በቀጥታ በራሱም ሆነ በሱ አገዛዝ ከ500000 ሰው ያላነሰ ተጨፍጭፏል። ስለዚህ ለሐገራቸው ክብርና ፍትሕ የሚቆጩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለዓለም መንግስታት ድርጅት ያላሰለሰ አቤቱታ በማቅረብ መንግስቱ ለፍትሕ ቀርቦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ግፍ የፈጸመ አምባ ገነን መሪ ከፍርድ እንደማያመልጥ ታሪካዊ ተግባር ማከናወን ግዴታችን ነው።

Comments are closed.

Share