March 21, 2016
13 mins read

ፍቅራችን የት ገባ? – ከተማ ዋቅጅራ

በአሜሪካ አገር በተደረገው የአለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና ኢትዮጵያ አመርቂ ድልን በልጆቿ ተቀናጅታለች።ጥቂት ተወዳዳሪ በማሰለፍ ብዙ መዳሊያን ከሚያገኙት አገራት ውስጥ ግንባር ቀደሙ እኛ ነን ብል የተሳሳትኩአይመስለኝም። ከብዙ የውድድር ዘርፎች ውስጥ በጥቂቱ ብቻ በመሰለፍ ከአለም ተወዳዳሪ አገራት መካከልበመዳሊያ ብዛት ውስጥ በመግባት ኦሎምፒክም ሆነ የአለም ሻንፒዮናም ሆነ ክሮስ ካንትሪም ሆነበአትሌቶቻችን ጥንካሬ እና በህዝባችን ጸሎት የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ በመግባት ኢትዮጵያን ከ 1-10 ውስጥትጨርሳለች።ከአበበ ቢቂላ ብጀምርW- አበበ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የማራቶች አሸናፊ፣ የመጀሪያው አፍሪካዊ የኦሎምፒክአሸናፊ እና የሪከርድ ባለቤት፣ የመጀመሪያው ብቻ ሳይሆን የመጨረሻም በሚያስብል መልኩ ሊደፈርየማይችል የማራቶንን ውድድር በባዶ እግሩ የሮጠ፣ የሮጠ ብቻም ሳይሆን ውድድሩን ያሸነፈ የአለማችንብርቅዬ እና ብቸኛ አትሌት አበበ ቢቂላ ነው። አበበ ሁለት የኦሎምፒክን ማራቶን ውድድርን ካሸነፈ በኋላሶስተኛው ላይ በሆዱ በደረሰበት ህመም ምክንያት ውድድሩን ሲመራ ቆይቶ መያል ለይ ህመሙ እያየለበትሲመጣ ያቅተዋል የዚህን ግዜ ውስጡ በሃዘን ተዋጠ የሱ አሸንፎ የመዳሊያ ባለቤት መሆኑ ሳይሆን የኢትዮጵያንስም ዳግም ማስጠራቱ ባለመቻሉ ነበረ። ወደ ማሞ ወልዴ ተጠግቶ በል እንግዲህ እኔ በጣም አሞኛልውድድሩን መጨረስ አልችልም የኢትዮጵያ ህዝብ አደራው አንተ ለይ ነው ያለው አሸንፈህ ባንድራችንን ከፍአድርገህ ማውለብለብ አለብህ አለውና ወደኋላ ቀረ። ማሞ ወልዴም የአበበን አደራ ተቀብሎ በድል ማጠናቀቅችሏል።
ሲቀጥል በነ ዋሚ ቢራቱ፣ በነ ምሩጽ ይፍጠር፣ በነ ቶሎሳ ቆቱ፣ በነ መሐመድ ከድር፣ በነ ፍስሐ አበበ፣ በነ ፊጣባይሳ፤ በተወዳደሩበት ውድድሮች ላይ ተከታትለው በመግባት አረንጓደው ጎርፍ የሚል ስያሜ እስከማስገኘትብርቅዬ አትሌቶችን ኢትዮጵያ አፍርታለች። በነዚህ አትሌቶች ዘመን 7 አትሌቶች የጎዳና ውድድር ላይለመወዳደር ወደ ውጪ ይሄዳሉ በዚህ ውድድር ፍስሐ አበበ ያሸንፍና 15 ሺ ዶላር ይሸለማል ሌሎቹ ግንምንም ሽልማት ሳያገኙ ይቀራሉ አትሌት ፍስሐ የተሸለመውን 15 ሺ ዶላር ለሰባቱም እኩል ያካፍላል።ውጠቱ የኔ ብቻ አይደለም የናተም ጭምር ነው በማለት ብሩን ያካፍላቸዋል። በፍቅር ለሃገር ፍቅር የሚሮጡሲያሸንፉም በፍቅር የሚተቃቀፉ የተሸለሙትንም ሽልማት በፍቅር የሚካፈሉ አገራቸውንም ህዝባቸውንምየሚወዱ አትሌቶች ነበሩን።በነ ደራርቱ ቱሉ፣ በነ ጌጤ ዋሚ፣ በነ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ዘመን በኦሎምፒክ እና በአለም ሻንፒዮን ውድድር ላይኢትዮጵያኖቹ ኮኮቦች ደምቀው መታየት ብቻ ሳይሆን ከድል በኋላ በፍቅር ተቃቅፈው ባንድራ ለብሰውእየተሳሳሙ የሚላቀሱ ነበሩ።በነ አሰፋ መዝገቡ፣ በነ ሐይሌ ገብረስላሴ፣ በነ ሐብቴ ጁፋር፣ ዘመን የኢትዮጵያ ኮኮቦች በአለም ሲደምቁ ከድልበኋላ ከአሸናፊው ጋር አብረው በመሆን የአንዱ ድል የሌላው ድል የአንዱ ማሸነፍ አገር እንዳሸነፈች በመቁጠርደስታቸውን አብረው ባንድራ ለብሰው ይገልጹ ነበረ። ሲዲኒ ኦሎምፒክ ላይ ሃይሌ እና ፖል ቴርጋት ያደረጉትእልህ አስጨራሽ ውድድር አሰፋ መዝገቡ ሶስተኛ በመሆን ነበረ ያጠናቀቀው። አሰፋ ከራሱ እሩጫ ይልቅየሃይሌን ማሸነፍ እየሮጠ ይጨነቅ ነበረ። ሃይሌም በድል ሲያጠናቅቅ የራሱን ትልቅ ድል እረስቶት ውድድርውስጥ ሆኖ ሜዳ ላይ ደስታውን ይገልጽ ነበረ ፍቅር ማለት እንደዚ ነው። በወንድም ድል እንደራስ መደሰትየወንድም ድል የአገር ድል መሆኑን አውቆ የኢትዮጵያ አትሌት በድል ሲያጠናቅቅ በእውነተኛ ፍቅር ደስታንአብሮ መግለጽ ነው።
በነ ቀነኒሳ በቀለ፣ በነ ስለሺ ስህን፣ በነ ሃይሌ ገብረስላሴ በነ ኢማና መርጋ፣ በኦሎምፒክ እና በአለም ሻንፒዮናስለሺ እና ቀነኒሳ ሃይሌ ወደኋላ በቀረ ግዜ አንገታቸውን እያዞሩ ይፈልጉ ነበረ ሌላው ቀርቶ ቀነኒሳየውድድሩን ፍጥነቱን በመቀነስ ሃይሌ እንዲጠጋ ሙከራም አድርጎ ነበረ። በዚህ ውድድር ላይ ቀነኒሳ የወርቅስለሺ የብር ሃይሌ ደግሞ የአምስተኛን ደረጃ አግኝቶው አጠናቀዋል። በድሉም ሶስቱም ተቃቅፈውደስታቸውን ሲገልጹ ነበረ ድል ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም ያሳዩን ነበረ። ኢማና መርጋ በጣም ጠንካራ እና ጀግናአትሌት ብቻ ሳይሆን የፍቅር ሰውም ጭምር ነው። በየውድድሩ እዩት ለአገሩ ልጆች የሚያሳየው ከበሬታናፍቅር ትልቅ ነው። ውጤቱን እሱም ያምጣው ማንም ኢትዮጵያዊ ካሸነፈ ከልብ የሚደሰት ልጅ ነው። ኢማናፍቅርን እና የአገር የማሸነፍ ክብርን ካንተ ተምረናል።ታዲያ ያሁኖቹ ምን ነካቸው? 90 ሚሊዮን ህዝብን ወክለው መሮጣቸውን ለምን እረሱት? ጡርነሽ እናመሰረት በሚሮጡበት ግዜ ከራሳሸው ክብር ይልቅ ኢትዮጵያ አገራቸው ወክለው መሄዳቸውን እና 90 ሚሊዮንህዝብን የማሸነፋቸውን ውጠት በጉጉት እንደሚጠብቅ አያውቁ ይሆንን? የአንዱ ማሸነፍ ሌላኛውን ለምንአያስደስታቸውም። ለኢትዮጵያ ህዝብ አገርን ወክለው እስከሄዱ ድረስ ሁሉም ለኛ አንድ ናቸው። ደስታችንሙሉ እንዲሆን ለምድነው ፍቅርን ያላሳያችሁን? ውድድሩ እኮ የሁለት ወይንም የሶስት ሰዎች አይደለምየአገር ውድድር ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ እናተን ልካለች። ታዲያ የአለማችን አገራት ሁሉ በመቅደምየኢትዮጵያን ባንድራ ከፍ የሚያደርጉ አትሌቶች ሁሉ ከራሳቸው ክብር የሃገር እና የህዝብ ክብር እንዴትማስበለጥ አቃታቸው? ይሄንን ጽሁፍ ልጽፍ የቻልኩበት ምክንያት ዛሬ በገንዘቤ እና በመሰረት ውጤት ደስብንሰኝም ፍቅራችሁን ማየት ባለመቻላችን ግን ቅር መሰኘታችንን ሳልገልጽ አላልፍም ብዬ ነው።በ 3 ሺ ሜትር ውድድር ላይ መሰረት እና ገንዘቤ የአመቱን ጠንካራ ውድድር እንደሚያደርጉ ሚዲያዎችዘግበው ነበረ። መሰረት ከብዙ እረፍት በኋላ ወደ ውድድር መምጣቷ እንደሚከብዳት ቢታወቅም ባላት ልምድተጠቅማ ውጤታማ ትሆናለች የሚል ግምት የብዙሃሉ ግምት ነበረ። ገንዜቤ ደግሞ ከባለፈው አመት ጀምሮብቃቷን ለአለም ህብረተሰብ እያሳየች ያለች የባለ ብዙ ሪከርድ ባሌቤቶች ብቻ ሳትሆን ለ 25 ዓመት ማንምሊሰብረው ያልቻለውን ሪከርድ ጭምር በመስበር ብቃቷን ያሳየች በመሆኗ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት ነበረ።በውድድሩም እንደተመለከትነው ገንዘቤ ከጥሩ ብቃት ጋር የአንደኝነትን ደረጃ ስትይዝ መሰረት የሁለተኝነትንደረጃ ይዛ ውድድራቸውን በድል ጨርሰዋል። ሁለቱም የኢትዮጵያ ኩራት ልጆች ናቸው። ሁለቱምለአገራቸው መዳሊያ በማስገኘት ባንድራችንን ከፍ አድርገው አውለብልበዋል። ታዲያ ገንዘቤ እና መሰረትፍቅራችሁን ግን አላየንም። ፍቅራችሁን የት ወሰዳችሁት? መዋደዳችሁን የት ጣላችሁት? የኢትዮጵያ ህዝብእኮ ከውጤታችሁ እኩል በድላችሁ ተቃቅፋችሁ ስትደሰቱ ማየት ይፈልጋል። ኽረ ፍቅር ወዴት እየሄደ ነው?በዚሁ የአለም ሻንፒዮና ላይ የሁሉም ሃገሮች ሲያሸንፉ ተቃቅፈው ደስታቸውን አብረው ይገልጻሉ 800 ሜትርየአሜሪካ የወንድ ሯጮች አንደኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል። አንደኛ የወጣው ጥቁር ነው ሶስተኛ የወጣው ነጭነው ውድድሩን ሲጨርሱ ግን ሁለቱም ተቃቅፈው ደስታቸውን አሳይተውናል ምክንያቱም ሁለቱም ሃገርንወክለው ስለመጡ የአንዱ ማሸነፍ ለሌላው ደስታ ነውና። ታዲያ የኛዎቹ ምን ነካችሁ? ኸረ እየተስተዋለ።ወደፊትስ ምን አይነት ነገር ሊታይ ይችል ይሆን? የአትሌቶች አሰልጣኝ ለአትሌቶቹ ፍቅርንና መዋደድንአስተምሯቸው። አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቹ በሚያሳዩት ጥሩ ያልሆነ ነገር ገስጿቸው እንዲዋደዱእንዲከባበሩ አድርጓቸው ማንም ያሸንፍ የሃገር እና የህዝብ ሃላፊነት ስላለባቹሁ የአንዱ ማሸነፍ የነሱም ድልእንደሆነ ንገሯቸው። እኔ ግን ባሳዩት ፍቅር አልባ ድርጊት አዝኛለው። በእግዚአብሔር ቃል ጽሁፌን ላብቃእምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ጸንተው ይኖራሉ ፍቅር ግን ይበልጣል ከሁሉ። ወደ ቀድሞ ፍቅራችንእንመለስ።

ከተማ ዋቅጅራ

21.03.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

2 Comments

  1. አቶ ከተማ ጥሩ ታዝበሃል ከዚህ በፊት ገንዘቤ ዲባባ ባ5ሽ መሰለኝ በሊላ ኢትዮጵያዊት ስትሽነፍ ያየሁት ደስታ ሳይሆን ሃዘን ነው በጊዜው ብስጭቶዋ ፊቶዋ ላይ ሲንቀለቀል በግልጽ ይታይ ነበር:: የውጢቱ ባለቤት የነበረችውን ስም በትክክል ባላስታውስም ይህን ክስተት ግን ከዚህ በፊት አስተውያለሁ:: እንዳልከው ከመቸ መቸ ነው ወደ መሰረት ሂዳ ተቃቅፈው የሚሳሳሙት ብየ ስጠብቅ ጭራሽ ሳይሆን ቀረ:: መርሳት ያለለብህ ግን በየትኛውም መድረክ ላይ የኢትዮጵያውያኖች ልዩነት እንዲሰፋ ያለ እንቅልፍ የሚሰሩ ሃይሎች መኖራቸውን ነው:: ፊደረሽኑም ለጋራ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅም እንዲያተኩሩ እንደሚመክራቸው አትጠራጠር:: አይሆንላቸውም እንጂ በንደዚህ አይነት ውድድሮች የሚውለበለው ባንዴራ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሳይሆን የወያኔ ቢሆን ደስታውን ባልቻሉት ነበር:: ፖለቲካዊ መመሪያቸው የግለሰብን ጥቅም ማስከበር እንጂ የሕብረተሰብን ጥቅም አንዳልሆነ ማኒፊስቶቸው ላይ በግልጽ አስቀመጠውታል:: ወንድሜ እግዚአብሔር እራሱ የነበረን ፍቅር ይመልስልን እንጂ ግዥዎቻችን ገፍተው ገስተው ግደል ጫፍ አድርሰውን ሽል ሊሉ ምንም አልቀራቸውም::

  2. ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ዋነኛ ጥያቄ በተጨማሪ መመለስ ያለበት ይመስለኛል.፣አንደኛው እስከ አሁን በአየነው የአትሌቲክስ ሩጫ ውድድር ላይ ከሁለቱ በተሻለ ውጤት አስመዝግባ የነበረችው አልማዝ አያና ለምን እንድትሳተፍ አልተደረገችም በርግጥ በዚህ ውድድር ላይ ሁለቱም ገንዘቤም ሆነች መሰረት አኩሪ ውጤት አስመዝግበዋል ልምን አልማዝ አልተሳተፈችም ወይስ እንደተለመደው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጉቦ የተጨማለቀ መስሪያ ቤት በመሆኑ ነው።ከውድድር እንድትቀር የተደረገችው፣
    በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ተከለከለ አሸንፈው የመጡ አትሌቶቻችንን በነቂስ ወጥቶ ፍቅሩን ለአትሌቶቻችን ያለውን ክብር እንዳይገልጽ እንደከዚህ ቀደሙ ለምን መንግስት ይከለክላል
    አ.ትሌቶቻችን በሚያደርጉት የአካል ብቃት ስፖርት ብቻ አይደለም አሸናፊ የሚሆኑት ህዝቡ በሚያደርግላቸው የሞራል ድጋፍ ጭምር ነው ብዬ ስለማምን ነው•።

Comments are closed.

Previous Story

ወደ ኤርትራ ለመዝለቅ የሞከሩ የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ሰላዮች ተረሸኑ

mengistu hailemariam
Next Story

“የመንግሥቱ ኃ/ማርያም የትምህርትና ዕውቀት ውስንነት እንዳለ ሆኖ፤ የተፈጥሮ ብሩህ አዕምሮውን ግን ለመካድ አይቻልም።” – ፕ/ር ገብሩ ታረቀ

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop