March 21, 2016
4 mins read

ወደ ኤርትራ ለመዝለቅ የሞከሩ የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ሰላዮች ተረሸኑ

በልኡል አለም

በኤርትራ እና በዙሪያዋ ለስለላ ስራ እንዲሁም ለቅኝት የዉጊያ ስምሪት እንዲጠቅሙ ተብለዉ የተሰማሩ የህወሃት ወታደራዊ መረጃ አባላቶች እየታደኑ መታፈናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አፈትልከዉ ወጥተዋል።

በተልይም ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ህዉሃት ከፈረጠጠ ወዲህ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ነጻነት ሐይሎች የደህንነት ክትትል ምክንያት በህወሃት መረጃ ሰንሰለት ስር የነበሩ ሰላዮች በሙሉ መረሸናቸዉን የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ለመከላከያ ሚኒስቴሩ እና ለሚመለከታቸዉ የደህንነት ክንፎች አሳዉቋል።
ወታደራዊ ደህንነቱ ሌሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ኤርትራ ሰርገዉ እንዲገቡ የተደረጉ የስለላ ሰዎች በተለይም የአርበኞች ግንቦት ሰባትን አጠቃላይ ፖለቲካዊና መሰረታዊ የአደረጃጀት እርከን፣ እንዲሁም ወታደራዊ ኮርሶችና ዲስፕሊኖችን፣ ስልታዊ መዋቅርንና አቀማመጥን ለመሰለል እንዲረዱ ከተሰማሩ ግለሰቦች ዉስጥ አንዳቸዉም የት እንደገቡ ለማወቅ ያለመቻሉን ምንጮቻችን ጠቅስዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ዉጊያዉ አምድ ከተቀላቀሉ ወዲህ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት እየአሰገሰ በመምጣት ላይ የሚገኘዉን የለወጥ ነዉጥ መቛቋም የተሳነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት የአርበኞች ግንቦት7ን እና የጥምር ሐይሎችን እንቅስቃሴ ማወቅ እንኳ እንደተሳነዉ በወታደራዊ የደህንነት ስልትም መበለጡን በተለይም የተሳሳቱ መረጃዎች እየደረሱት ላም ባልዋለበት… ሲቅበዘበዝ የነጻነት ሐይሎቹ ሽምቅ ዉጊያ ሰለባ እየሆነ መምጣቱን ለተደራቢ አዛዡ ሌተናንት ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ውይይት እንዲደረግበት ከቀረበው አጀንዳ ለመረዳት ተችሏል።

ስርአቱ አሁን ባጋጠመዉ የመረጃ መዳፈን ምክንያት ስጋት ላይ ስለወደቀ ድንገተኛና የተጠናከረ ተመላላሽ ጥቃት እንዲሰነዘር እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት በእጅጉ እንዲጠናከር ለማድረግ ከሸዋሮቢት የመጡ አዲስ ወታደሮች ወደ ክፍለ ጦሮቹ እንዲካተቱ እና አጥቂዉ የግንባር ሐይል ለመመሪያ ዝግጁ እንዲሆን በአመራሮች ቢወሰንም ከተራ ወታደር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሮች መመሪያ ለመቀበል ስጋት ላይ ናቸዉ።

ይህን መረጃ አያይዘዉ የላኩልን ምንጮች በኤርትራ የሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ከምንዜዉም በበለጠ በንቃትና በመጠናከር እየወደቀ የሚገኘዉን ባለ ሁለት እግር ዝሆን ለመጣል እንዲዘጋጁ መዘናጋትን ፈጽመዉ እንዳያስቡት አስጠንቅቀዋል።

ከአራት እግሮቹ ሁለት የፊት እግሮቹን የቆሰለ ዝሆን ለመጣል ዝሆን መሆን አያስፈልግም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

1 Comment

  1. 20 ሠዐት አፈርድሜ በልቶ የሚሠራውን የለፍቶ አደር ገንዘብ እንዲህ እያጃጃልክ ልቀምበት።በእድሜ ጣራ ባስቀምጥልህ በዉጭዉ ዓለም ከሚኖረው ሕዝብ ከ18_30 እድሜ 95/100 ስባሪ ሣንቲም አታገኝም ከ31_45እድሜ 75/100አያቀምስህም ከ45_50 እድሜ 55/100እንደታናናሾቹ ነቄ ነው ከ 56 እድሜ በላይ የአንተናቸዉ።እባክህን ሰው ሁሉ ለምን እንደ እራስህ ትገምተዋለሕ?ፖለቲካ ስታወራ እነማናቸው ታዳሚዎቼ ብለህ እራስህን ጠይቅ አለበለዚያ ከፖለቲካው እራስህን አግልል።ከፖለቲካ ወሬዎች 85/100 ዉሸት ነው የቀረቺዉን 15/100 አጨናንቀህ እዉነት አክልበት በዉሸት ዜና ዉስጥ ዝራው ያኔ አድማጮች ታገኛለህ አሊያ ይህ ከላይ ቃላቶችን አጭቀሕ ያመጣኸልን እንቶፈንቶ አሁን ላለዉ ትዉልድ አይመጥንም ካልሆነ ደግሞ ከ40 ዐመት በታች አታንብቡት ይባልልን።ስለቸከቸከዉ የወሬ ደርዘን ብዙ ጥያቄ ማንሳት ይቻል ነበር ለአሁኑ ትቼዋለሁ በሚቀጥለው የተሻለ ይዘህ ለመምጣት ሞክር።ቸር ሠንብት

Comments are closed.

Previous Story

Hiber Radio: ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም አንድ የተቃዋሚ መሪ ከሃገር ቤት ጠየቁ፣ ሁለት የጅቡቲ የጦር ምርኮኞች ከኤርትራ እስር ቤት አምልጠዋል፣ በእስራኤል የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን በቴላቪቭ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ…

Next Story

ፍቅራችን የት ገባ? – ከተማ ዋቅጅራ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop