እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ንብረት የሆነው መሬት በተጭበረበረ ካርታ ለባለሃብቶች መሸጡ ተነገረ

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለየ ስሙና ቦታው እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አዲስ የተመረጠው ሰበካ ጉባኤ ለባለሃብቶች በተጭበረበረ ሰነድ እየሸጠ ነው ሲሉ ምእመናን ብሶታቸውን አሰሙ::

“ለማን አቤት ይባላል? ለፈጣሪ እንጂ” የሚሉት እነዚሁ ተቆርቋሪ ምእመናን “በቅርቡ የተመረጡት የሰበካ ጉባዔ አባላት በቤተክርስትያን ስም ሁለት ማህተም በማሰራት የቤተክርስትያኑ ንብረት የሆነውን ቦታ በማጭበርበር እየሸጡት ነው፡፡” ነው ይላሉ:: ምዕመናኑ አክለውም “የቤተክርስትያኑ ሰንበቴ ቤት የነበረውን ክፍት ቦታ ለቤተክርስትያኑ ገቢ ማስገኛ በማለት ለግለሰብ ቢያከራዩትም ሰነዱን በማጥፋት ካርታ አስወጥተው እንደሸጡት ታውቋል:: አሁን ደግሞ የማቴዎስ ግቢ የሚባለውን የቤተክርስቲያኑን ቦታ አገልጋይ ካህናትን በማስወጣት ለግለሰብ ለ20 ዓመት ሊሸጡት እየተደራደሩ ነው:: ይህንንም ለማሳመን ሁለት ዓይነት የተጭበረበረ ሰነድ አቅርበዋል:: ስለዚህ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን የቤተክርስትያን ቦታ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር በህግ አምላክ ብለን እናስቁማቸው::” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርቧል::

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአዲስ አበባ መሬቶች ለሕወሓት ሰዎች እና ለውጭ ባለሃብቶች በልማት ስም ተቸብችበው ያለቁ በመሆኑና የመሬትም እጥረት ስላለ የቤተክርስቲያን መሬቶችን ወድ መቀራመቱ ተደርሷል:: በቅርቡ አዲስ አበባን በማስፋፋት በሚል ሰበብ በወጣው አዲስ ማስተር ፕላን የኦሮሚያ ገበሬዎች መሬት ተቀምቶ ለባለሃብት ሊሰጥ ነው በሚል በተነሳ የሕዝብ ጥያቄ በርካቶች የጥይት ራት መሆናቸው ይታወቃል::

እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አለአግባብ ለባለሃብት ቸብችበዋል የተባሉትን የሰበካ ጉባኤ አባላት ዘ-ሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም:: እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ግን የቤተክርስቲያናችን ንብረት ሊሸጥ አይገባም የሚሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን አደባባይ ይዘው ለመውጣት እየተዘጋጁ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  (በጣም አስቂኝ) - የቦሌ ክፍለከተማው ፖሊስ አዛዥ "አይደለም ዲሲ መንግስተሰማያት ብትሆን አመጣሃለሁ"

1 Comment

  1. “እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ

    መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውንለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለውተብሎበካሜራተቀርፆመነገሩየሚያሳዝንመሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል።

    ‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

    ሪፖርተር እንደዘገበው አቶ ገብረውሃድ መሬት መቀበላቸውንነገር ግንቤትለመሥራትአቅምስለሌላቸውምእንዳልሠሩበትዘግቧል።

    ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ” ልንመሰገንበት በሚገባ ስራ ወንጀለኞች መባላችን ያሳዝናል ” ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።

    “አቶመላኩከገቢያቸውጋርየማይመጣጠንከ3.2 ሚሊዮንብርበላይየሆነንብረትናገንዘብአፍርተዋል”በሚልለቀረበባቸውክስ፣እንደማንኛውምሰው 175 ካሬሜትርቦታላይቤትመሥራታቸውን፣ይህደግሞለእሳቸውብቻተነጥሎወንጀልሊሆንእንደማይችልገልጸው፣ ዓቃቤሕግየቤቱንግምትአሳስቶማቅረቡንምተናግረዋል።

    ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮቹን ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።

Comments are closed.

Share