ነብር ዠጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር አይችልም ይላል በታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ። ይህ ቃል የኔ ወይም የናንተ አልያም የወያኔዎች ቃል አይደለም ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ሁሉን ማድረግ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኢትዮጵያዊ መልኩን ኢትዮጵያዊነትም ሊቀየር አይችልም ይላል እግዚአብሔር። ታዲያ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳው ከምን ተነስቶ ነው? የሰው ልጅ መጋፋት የሚቻለው ከሰው ጋር ሊሆን ይችላል ወያኔ ግን ከፈጣሪ ዘንድ ነውና ኢትዮጵያን ማጥፋት ከቶውኑ አይችልም። ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም።
አዎ ኢትዮጵያዊ ማለት
እግዚአብሔር የመረጣት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ህዝብ የሚኖርባት መሬት.. በህገ ልቦና ገና ህግ ሳይሰራ ሊቀ ነብያት ሙሴም ህግን ከእግዚአብሔር ሳይቀበል በፊት እግዚአብሔርን በማምለክ የኖረች አገር ነች።
ኢትዮጵያ ማለት በህገ ኦሪት ሙሴ ህግን ከእግዚአብሔ ከተቀበለ በኋላ ኢትዮጵያ በሙሴ አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ህግ ተቀብላ በህገ ኦሪት ስትመራ የቆየች አገር ነች።
ኢትዮጵያዊ ማለት በህገ ወንጌልም ግዜ ወንጌልን ተቀብላ የእግዚአብሔርን ቃል በአገሪቷ እያስነገረች ለአለም ምሳሌ የሆነች አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች አላወቁ ይሆን።
ክርስትናን ከእስራኤል በመቀጠል የተቀበለች አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች አልተረዱ ይሆን።
እስልምናን ከሳውዲ አረብ በመቀጠል የተቀበለች አገር እና አዛንን ለመጀመሪያ በአደባባይ ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አላወቁ ይሆን።
ኢትዮጵያ ማለት በውስጧዋ የሚኖሩት የተለያየ ባህል ያላቸው እና ድንቅ መልከአ ምድር የያዘች አገር መሆኗን ዘንግተውት ይሆን።
ኢትዮጵያዊ ማለት ስም ብቻ ሳይሆን ስሜት የተቀላቀለበት እውነት የሚነገርባት ፈጣሪ የመረጣት ቅዱሳን የሚኖሩባት በደምስራችን የታተመች ለውጥ የማያሻት የታሪክ ማህደር የውበት መንደር እንደሆነች አላወቁ ይሆን።
ኢትዮጵያዊ ማለት አፍራሾች ቢከቧት የማትፈርስ ጠላቶች የማይተኟላት ግን የማይችሏት ታግለው የማይጥሏት የፈጣሪ ጥበቃ የማይለያት አገር መሆኗን ዘንግተውት ይሆን።
እናም ኢ..ት..ዮ..ጵ..ያ ማለት ዘር ቀለም ሳንል በሃይማኖት ሳንለያይ የምንኖርባት አገር እንደሆነች ማወቅ አለባቸው።
ገበሬው እያረስ ህዝብን የሚመግበውን ያለ ምክንያት በግፍ በወያኔ ሆዳም አደሮች ከመሬቱ ሲፈናቀል ኢትዮጵያዊ ማለት ገበሬው ነው ገበሬው ሲነካ ያመኛል።
ተማሪው ነገ አገር ለመረከብ ወደ ትምህርት ገበታው እውቀት ለማወቅ በሚሄድበት ግዜ ወያኔ የኔን ፖሊሲ ተማር የኔን ፖለቲካ አራምድ ብለው በግድ ተማሪውን እያስገደዱ እውቀቱን የሚያጨናግፉ ኢትዮጵያዊ ማለት ተማሪው ነው ተማሪው ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት ፖለቲከኛው ነው። ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የፖለቲካ አመራር ለመወሰድ ፖለቲከኞች ለአገራቸው ሲሰሩ የግድ እንደ ቦይ ውሃ በአንድ መስመር መፍሰስ አለባችሁ ተብለው የገንጣይ አስገጣይ ፖለቲካ አራምዱ ሲባሉ እንቢ ኢትዮጵያዊ ማለት ኢትዮጵያዊ መሆን ነው እንጂ ዘረኛ መሆን አልያም መከፋፈል አይደለም ብለው ለእውነት የቆሙትን ሲታሰሩ እና ሲገደሉ ኢትዮጵያዊ ማለት ፖለቲከኛው ነው ፖለቲከኛው ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት ጋዘጠኛው ነው። ጋዜጠኞችም እኛ የጻፍንላችሁን አንብቡ የጻፋችሁትንም እኛ ኤዲት አድርገን ካለፈ ብቻ ነው ማቅረብ የምትችሉት ብለው የጋዜጠኝነትን ሙያ አቃለው ስህተት ብቻ እንዲዘግቡ ሲያስገድዷቸው የለም ጋዜጠኛ ማለት ትክክለኛውንና የተሰማውን የሚሰራና የሚያቀርብ ለህሊናው የሚኖር ለእውነት የሚገዛ እውነትን ወደ ህዝብ አቅራቢ እውነትን ዘጋቢ ነው የሚሉት ኢትዮጵያዊ ማለት ጋዜጠኛው ነው። ጋዜጠኛው ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት ሰራተኛው ነው። አገር ለማሳደግ ጠዋት ወጥቶ ማታ የሚመለሰው ሳይሰለቹ ለለውጥ አገር ለማሳደግ የሚሰሩት ሰራተኛው ነው ኢትዮጵያዊ። ሰራተኛው ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት መምህሩ ነው። የነገን አገር ተረካቢ ለማፍራት እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ትውልድን ለመቅረጽ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ሲደክሙ እውቀታቸውን ጨምቀው የሚያስተምሩ ኢትዮጵያዊ ማለት መምህሩ ነው። መምህሩ ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት አርቲስቶች ናቸው። በዜማ በስነ-ጹሑፍ በስነ-ስዕል ስለ አገራቸው ክብርና ዝና ሲያቀርቡ የውስጥ ተሰጦአቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ እውነትን በጥበባቸው ሲገልጹ ህዝብን ሲያዝናኑ እና ሲያስተምሩ ኢትዮጵያዊ ማለት አርቲስቶች ናቸው። አርቲስቶች ሲነኩ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት ስፖርተኖች ናቸው። በዓለም መድረክ ድንቅ ችሎታቸውን በመጠቀም ከኢትዮጵያ የበቀሉ አይበገሬ መሆናቸው ሲያሳዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ኢትዮጵያዊ ማለት ስፖርተኛው ነው። ስፖርተኛው ሲነካ ያመኛል።
ኢትዮጵያዊ ማለት ኢትዮጵያዊ ነው ከአምላክ የተሰጠን ድንቅ ስጦታ በምንም በማንም የማትለወጥ በልቦናችን ውስጥ የታተመች አገር ኢትዮጵያ።
ታዲያ ይህቺን አገር ነው ወያኔ ሊያፈርሰው ሌት ተቀን የሚማስነው። ይህቺን ከፈጣሪ የተሰጠች አገር ሊያጠፋ ነው ሽር ጉድ እያለ የሚገኘው። መስመር አበጅቶ ለመገነጣጠል እንዲያመቸው አንዱ ከሌላው ጋር የማያባራ ጠላትነት እንዲመሰርት እና አንዱ ከሌላው ጋር እርስ በራስ እንዲጠፋፋ የማይሆን ታሪክ እየተናገረ ያለው። አልቻለም እንጂ እንደ ውያኔ ሃሳብ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንድትኖር አይፈልግም አገር ብቻ ሳይሆን በውስጧ የሚኖሩትንም ህዝብ እርስ በእርስ በማናከስ እና በማጥላላት ወደ ግጭት አምርተው እንዲጠፉ ነው የሚፈልገው ነገር ግን በእግዚአብሔር ጠባቆትነት ስር ስላለች መቼም ማፍረስ አይችልም።
እናም በአገራችን በሰላም ለመኖር እና የፈለግነውን እየሰራን፣ እየተናገርን በፍቅር ለመኖር ወያኔ የሚባለውን ጭራቅ በእግዚአብሔር ስም በአላህ ስም ተቀናጅተን እናጥፋው ያኔ ኢትዮጵያ እንኳን ለኛ ለዓለም ሁሉ የምትተርፍ አገር ትሆናለች።
አርበኞች ግንቦት 7 መቼም ቢሆን በሰላማዊ ትግል ሊወርድ እንደማይችል ተገንዝበን ወደ ትጥቅ ትግሉ ገብቷል። ኢትዮጵያን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ የሁላችንም ግዴታ ነው። የምንወዳትን አገር የማንም ሽፍታ መጥቶ ማፍረስ ሲፈልግ ማንም እንደማይፈቅድለት ማሳወቅ ያለብን ሁላችንም ወደ አርበኞች ግንቦት 7 በመቀላቀል በአጭር ግዜ ውስጥ ወያኔን ደምስሰን ማጥፋት አለብን። ኢትዮጵያን የመጠበቅ ስራን ሁላችንም መወጣት እንዳለብን ማወቅ አለብን። በአገር ቀልድ የለም!! ወያኔ ከአሁን በኋላ በምንም መልኩ እያጭበረበረ የኢትዮጵያን ህዝብ እያሰረ እና እየገደለ የሚኖርበት ዘመን ሳይሆን… ኢትዮጵያኖች ወያኔን ከነ መርዙ ነቅለው ለማጥፋት ሁሉም ኢትዮጵያ ለትግል በአንድነት ይነሳ።
በኢትዮጵያ ቀልድ የለም። አገር ወዳድ ሁሉ በቆራጥነት በልበ ሙሉነት ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ከ-ሳሙኤል አሊ