May 28, 2013
6 mins read

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” – ከአቤ ቶኪቻው

አቶ በረከት
“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” - ከአቤ ቶኪቻው 1

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…

“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ

ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡

አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡

መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡

ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴት ነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!

አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግ ይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግ እስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡

በዚህ በ”በቃ” ጦስ እነ ርዮት አለሙ እነ ውብሸት ታዬ እነ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር እነ ሂሩት ክፍሌ ወድያው ለእስር ሲዳረጉ ቀስ በቀስ ደግሞ ሌሎችም ለቃሊቲ እና ለቂሊጦ ተዳርገዋል፡፡ (በተለይ የነዚህ ወዳጆቼን ፍርድ ሂደት ስከታተል ነበር እና አጋነንክ ቢሉኝም ባይሉኝም የአቃቤ ህግ ማስረጃ “በቃ የሚለውን የፌስ ቡክ እና የአደባባይ እንቅስቃሴ ትኩር ብላችሁ አይታችኋል” የሚል ነበር)

እንቅስቃሴው በፌስ ቡክ ተጀምሮ በየአደባባዩም “በቃ” የሚል ሃይለቃል በመፃፍ ተሟሙቆ የቀጠለ ነበር፡፡ በርካቶችም ግንቦት ሃያ መስቀል አደባባይ የሚፈጠረውን ተዓምር እያሰቡ አንድም ደስታ አንድም ፍርሃት ሲፈራረቅባቸው አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡

ይሄኔ አቶ መለስ ፈርሸው ዘየዱ፤ (ሁል ጊዜ ቁጭ ብለው አሰቡ… እያልንኮ ፍራሽ የሌላቸው አስመሰልናቸው… “ፈርቸው” ማለት ፍራሽ ዘርግተው እጅግ በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው…) አስበው አስበውም፤ “ለምን አባይን አንገድበውም…” አሉ እርሳቸው ብለው እምቢ… እንዴት… ለምን… በምን… አይባልምና እሺ እሺ ተብሎ ተጀመረ፡፡ የዛን ጊዜውን ግንቦት ሃያም መንግስታችን ለአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ ውጡልኝ፡፡ አለ… በዛውም የህዝቡ የተቃውሞ ሃሳብ ተገደበ፡፡

የአቶ መለስን ብልጠት በመኮረጅ ፈተናዎች ይታለፋሉ ብለው የሚያምኑት አቶ በረከት ደግሞ ዛሬ እነሆ በግንቦት ሃያው አባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ እነደሚሰራ በቴሌቪዥናቸው ብቅ ብለው ነገሩን፡፡

ጥሩ ኮርጀዋል…! አኮራረጃቸው ስም ሁሉ ሳይቀር እንደሚቀዳ አይነት ኮራጅ ነው፡፡

ህዝቡ ይህንን ዜና ሲሰማ ምን አላቸው… የሚለውን ቤት ለቤት ሄደን መጠየቅ ብንችል ጥሩ ነበር፡፡ መጠየቅ ባንችል ግን መጠርጠር እንችላለን እና አንዲህ እንጠረጥራለን፤

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” ሳይላቸው አይቀርም፡፡

 

 

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop