እየተስተዋለ – በወንድስን ገ/ህይወት (ቪ.ሚ)

ላለፉት 22 ዓመታት በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ሀገራችን በጉልበት መመራት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በህዝባችንና በሀገራችን ላይ በመፈጸም ላይ የሚገኘው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ሁኔታዎች ተባብሰው ይገኛሉ።

ይህ የወንበዴ ስብስብ ይህን ሁሉ ግፍ እየፈጸመ የሚገኘው በሀገራችን ውስጥ ምንም ዓይነት ነጻ የፍትህና የነጻ ፕሬስ ተቋማት እንዳይኖሩ በማድረጉ ነው።የህዝባችን መብት መረገጥ፣የሀገራችን ህልውና እጅግ ያሳሰባችው ቆራጥና ደፋር ጥቂት ኢትዮጵያውያን ይህን ዘረኛ የወንበዴ መንግስት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ታግለዋል፣ህዝቡን በማስተባበር ሥርዓቱን ለመጣል ሞክረዋል፣ለዓለም ህብረተሰብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማስረዳት ጥረዋል።ይህን በማድረጋቸው በገዢው የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን መታሰር፣መደብደብ፣የአካል መጉደል፣መሰደድና መገደል ደርሶባቸዋል።በተለይም ዛሬ በሀገራችን ውስጥ በነጻነት ተምሮ ሰርቶ መኖር የማይቻልባት ሀገር በመሆንዋ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ወገኖቻችን ጨምሮ ህዝባችን በብዛት እየተሰደደና ሀገሩን እየተወ በመሸሽ ላይ ይገኛል።
የሀገራችን ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሉዓላዊነትዋ አሳሳቢ ደረጃ ደርስዋል።በውጭ ወራሪዎች እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተደፈረችው ሐገራችን የናት ጡት ነካሽ በሆኑ የማሕጸነ መርገምት ልጆችዋ በውጭ ሐይል እርዳታ በተደራጀ ተገንጣይና አስገንጣይ ቡድን በግልጽ ለጨረታ ቀርባ እየተቸበቸበች ትገኛለች።ይህን ድርጊት ተባብረን ካላቆምነው አባቶቻችን ድማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በነጻነት ሐገራችንን ጠብቀው ለኛ ያስተላለፉልንን አደራ እኛም ለተተኪው ትውልድ ሣናስተላልፍ ብንቀር ታሪክ ተጠያቂና ተወቃሽ ከመሆን አንድንም።

ይህ ስርዓት ላለፉት 22 ዓመታት ያለ ምንም ተቀናቃኝ በሥልጣን ላይ የቆየው በሱ ጥንካሬና ሀይል ሳይሆን በኛ ያለመተባበር፣ከሁሉም በላይ በፍርሀት፣በሽሽት፣በልዩነትና ሀላፊነትን ለመወጣት መስዋዕትነትን ለመክፈል በመፍራታችን ጭምር ነው።ካለፉት ህዝባዊ እምቢተኝነትና በዘረኝነት ላለመገዛት ህዝብ የወሰደውን የጋራ ትግል ስሜት ትግሉን በሚመሩት አካሎች ቆራጥ አመራር ለመስጠት አለመቻል፣መስዋዕትነትን በመፍራታቸው ምክንያት አሸናፊ ለመሆን አልቻልንም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው

በሀገራችን ውስጥ በየክፍለ ሀገሩ፣በየቀበሌው እየደረሰ ያለው በደል መጠኑ ይለያይ እንጂ በሁሉም የሀገራችን ክፍል ተመሳሳይ ነው። በየዕለቱ ከሐገር ቤት የምንሰማው ዜና ሁሉ እጅግ አሳዛኝና የወገን ያለህ የሚያሰኝ ሁንዋል።ገዢው የወያኔ ሐይል ይህንን ሁሉ በደል በሕዝባችን ላይ የሚፈጽመው ባለው መሳሪያ፣መረጃና ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ሚድያ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩና በነጻው ፕሬስ ላይም እገዳ በማድረግ ሕዝባችን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኝ በመዝጋቱ ነው።

በውጭ ሐገር በስደት የሚኖሩ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የሐገራቸውን ህልውና ለመታደግና የሕዝቡን ጭቆና ለማስወገድ በድርጅት፣በቡድንና በግል ጭምር ብዙ እየጣሩ ይገኛሉ።በተለይም ሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ወደ ሐገር ቤት የሚተላለፍ የሬድዮ አገልግሎት ለመስጠት ሲሞክሩ ረጂም ጊዜ አሳልፈዋል።ብዙዎቹ ሬድዮኖች ተጠናክረው መቀጠል ባይችሉም ጥቂቶቹ አሁንም እየሞክሩ ይገኛሉ።እስካሁን ያደረጉት አስተዋጽኦ ቀላል ባለመሆኑ ሊደገፉና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።

በቅርቡ ደግሞ በእድሜ ለጋ የሆነው ኢሳት የቴሌቪዥንና የሬድዮ አገልግሎት ወደ ሐገር ቤት እየሰጠ ይገኛል።ይህ ድርጅት ወደ ሐገር ቤት በተለያዩ መንገድ ለሕዝብ የተጣራ መረጃ በማቀበል በኩል እያደረገ ያለውና በየሰዓቱ ሐገር ውስጥ የሚደረገውን ድርጊት ውጭ የምንገኘው ኢትዮጵያውያን እንድናውቅ የሚደረገው ጥረት ብዙ አድማጭና ተመልካች እንዲኖረው ከማስቻሉም በላይ ድጋፋችንን እንድንሰጠው አድርጎናል።

ይህ ለጋ ድርጅት እስካሁን በሚሰራው እሰይ እደግ ተመንደግ አስብሎታል።በዚህ ሥራ ላይ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውንም እየሰጡ ኢሳት እንዲጠናከር ለሚያደርጉት ኢትዮጵያውያን በግሌ አክብሮትና ምስጋና አቀርባለሁ። ድርጅቱ ገና ወጣት ተቋም በመሆኑ በስራው ሂደት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚደረጉ ጥቃቅን ስህተቶች እንደሚኖሩ ብገምትም አንዳንዶቹ ግን ሀገርም ሆነ ህዝብ የማይጠቅሙ ከመሆናቸው በላይ በኢሳት ደጋፊዎች ላይ እምነትን የሚያሳጡ እንዳይሆኑ እሰጋለሁ።

ከነዚህም ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን ለመጥቀስ እወዳለሁ።

፩ኛ። ካሁን በፊት በዜና ከተላለፈው ውስጥ አክራሪና ተገንጣይ የፖለቲካ አቋም ለመተግበር ሲል ሀገራችንንና ህዝባችንን ሲጎዳ የነበረው በተለይ በሀረር ጋራ ሙለታና አካባቢው ንጹሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ያደረገውን የእስላሚክ ኦሮሚያ መሪ ጃራ አባ ገዳን የኦሮሞ ሌጀንድ የሆኑት አረፉ ሲል በእሳት ቲቪ ያቀረበውን ዜና ስሰማ እኔን ያሳዘነኝን ያህል ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖቸዋል ብዬ እገምታለሁ። እኔም እንደ ኢሳት የሆላንድ ድጋፍ ሰጭ አባልነቴ ለኢዲቶሪያል ቦርዱ ቅሬታየን በወቅቱ በኢ፡ሜይል አሳውቄለሁ።

፪ኛ ሜይ 13 ቀን 2013 በተላለፈው እንወያይ ፕሮግራም በጋዜጠኛ ደረጀ ሀ/ወልድ፣ፋሲል የኔዓለምና አፈወርቅ አግደው የተካሄደው ውይይት ርዕስና በውይይቱም ሂደት የተንጸባረቀው ሀሳብ ፍጹም ግራ የሚያጋባ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። ምክንያቱም የውይይቱም ርዕስ እንደሚያስረዳው በሀገር ቤት ውስጥ በሰላማዊ ትግል ለመታገል በህጋዊነት ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ በ50ኛው የአፍሪካ ህብረት በዓል ላይ የአ.አ ህዝብ ጥቁር በመልበስ በገዢው ፓርቲ (ወያኔ) በህዝብና በሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በመቃወም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመመርኮዝ ነበር።በተደረገው ውይይት የተጠራው ሰልፍ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት፣የተመረጠው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ከሰላማዊ ሰልፉ ማን ሊጠቀም ይችላል? በሚል አብዛኛው በአፍራሽ እይታ የተሞላ ውይይት ነበር።ለመሆኑ የሁላችንም ፍላጎት የሆነውና ይህንን ሥርዓት ለመጣል በሀገር ቤት ውስጥ መሰረት ያደረገ ህዝባዊ ትግል መኖር ለትግሉ አስፈላጊ መሆኑ እየታወቀ ሀገር ውስጥ ያለውን መነሳሳት የሚያኮላሽና ሰልፍ እንዳይወጣ ጥርጣሬን የሚያጎላ ውይይት ጠቀሜታው ለማነው? የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም የቅድመ ትንበያው አተናተናዊ ሁኔታ ሰልፍ አትውጡ የሚል አንድምታ ያለው መልክት ለማስተላለፍ የተፈለግ አስመስሎታል።ይህ ሁኔታ ራሱን የህዝብ አይንና ጆሮ ለማድረግ ከሚሰራ ተቋም የማይጠበቅ ማስተዋል የጎደለው ዝግጅት ሁኖ አግኝቼዋለሁ።

በተለይ እንደ ኢሳት አይነት አማራጭ የሌለውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ህዝብ በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተለው የመረጃ ተቋም ላይ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች በሙሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል። አስገራሚው ደግሞ ጋዜጠኛ ፋሲል፣ አፈወርቅና ደረጀ ያደረጉት ውይይት እኛን እንጂ ኢሳትን አይወክልም ሲሉ ይሰማሉ።ግን ማወቅ ያለባቸው እነሱ የኢሳት ባልደረቦችና የሙያ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ጭምር ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባታቸውና ኢሳትንም ተጠያቂ የሚያደርገው መሆኑን አለመረዳታቸው ነው።

ለግንዛቤ እንዲረዳ አንድ የቆየ በBBC የተላለፈ ዜና ትዝ አለኝ።በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያው አካባቢ ዓለም ላይ ከፍተኛ ሥጋት ጥሎ የነበረው የኑክሊየር ፍጥጫ አስመልክቶ በመግቢያ ዜና ላይ ሰበር/Breaking news/ በሚል ዜና መሀል አንባቢው አዝናለሁ የእንግሊዝ ህዝብ በማለት ከሩሲያ የተተኮሱ የኑክሊየር ሚሳይሎች ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ለንደን ይደርሳሉ ብሎ በማስተላለፉ በእንግሊዝ ህዝብ ላይ ምን ያህል መደናገጥ አስከትሎ እንደነበረና ጥቂት ቆይቶ ዛሬ እኮ April the fool ነው በማለት እየሳቀ መናገሩ ብዙ ሰው ያስቆጣ ነበረ። ዜናውን ያነበበው ጋዜጠኛና ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ሀላፊ ከሥራ ከመወገዳቸውም በላይ በህግ ተጠያቂ ሁነዋል።

ለማጠቃለል ያህል በዚህ ምክንያት በሚድያ የሚቀርቡ ነገሮች በሙሉ ህዝብ እውነት ናቸው ብሎ ስለሚያምን በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል።ይህንን ጽሁፍ በምጽፍበት ሰዓት የኢሳት ጠንካራ ሥራዎች እንዲጎለብቱ ድክመቶች ደግሞ ሊታረሙ ይገባቸዋል ብዬ ስለማምን ነው።

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዕንቅፋትን አለማንሳት ለሞት መመቻቸት ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!


ወንድስን ገ/ህይወት (ቪ.ሚ)

4 Comments

  1. Endie ATO wondosen, yet tegneteh keremek? Ene Fasil ena Afework yetenagerut eko tekekel hono tegegne. Endeyawim betam lidenekuna lishelemu yegebal manem yalayewin asekedemew mayet balemechalachew.\

  2. Wondwossen,

    I understand you. Per your suggestion and in accordance with their daily coverages, it is better for ESAT to call itself the voice of Amhara TV from abroad rather than hoodwinking the general public.

  3. ወያኔ እድሜውን ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው ስልቶች ውስጥ አንዱ ህዝቡ መረጃ እንዳያገ በማፈን ETVንና ሌሎች የመንግስት ሚድያወችን ብቻ እንድከታተል ማድረግ ነው::እነዚህን ሚዳዎች የሚከታተል ህዝብ ደግሞ የወያኔ ታማኝ ውሻ ሆኖ ከመኖርውጭ ሌላ አማራጭ የለውም::እያንዳንዳችን ቢንስ አንድ ጀለሳችንን ኢንተርኔት ላይ የሚወጡ ፅሁፎችን እንዳነቡ እንጋብዛቸው::በማይታመን ፍጥነት ከጎናችን

  4. ተሰልፈው እናገኛቸዋለን::ሁላችንም ቢንስ ሁለትና ከዚያበላይ ጎደኖች ይኖሩናል::ሁሉንም ወደዚህ መድረክ ብናመጣቸው ያለጥርጥር ከወያኔ ጉያ ውስጥ ፈልቅቀን ከባርነት ነፃ ማውጣት እንችላለን::እኔ በራሴ ሞክሬው ከወያኔ አባልነታቸው ራሳቸውን ያገለሉ ብዙ ጀለሶች አሉኝ::ያባልነት ብር ሲቁዋርጡ ካድሬወች ቢስቸግራቸውም እነሱግን ከአቁዋማቸው ፍንክች አላሉም::እንሞክረውበአንድ ሚሊዮኖችንእናፈራለን

Comments are closed.

Share