Hiber Radio: አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

May 27, 2013
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
Hiber Radio: አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ 1

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ግንቦት 18  ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…በደቡብ አፍሪካ ፣በአንጎላ፣ በሞዛምቢክ እነዚህ ወንድሞቻችን ካሉበት የባርነት ቀንበርነጻ እስኪወጡ ድረስ መላው አፍሪካና  ኢትዮጵያዊያኖች በዓለም ሸኝጎ በዕኩልነት ድምጻቸው እንዲሰማ …የአፍሪካ አገሮች የአዲስ አበባ ጉባዔ…>>ቀዳማዊ አጼ ሀይለስላሴ እ.አ.አ በ1963 ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<ህወሃት ጣሊያን የሰራውን ነው በአማራ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለው። የፋሺስቱ ጣሊያንና አሁን ያለው የህወሃት አገዛዝ ጸረ አማራ አቁዋም አንድ ነው። አማራው ራሱን ማደራጀትና ከዚህ ሊያቀጠፋው ከተነሳ ድርጅት ጥቃት መከላከል አለበት። አማራ ልደራጅ ሲል ለምን ተቃውሞ ይቀርባል?…>>

አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀ መንበር በቬጋስ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<… አማራው እየተረገጠ ለመብትህ አትደራጅ ብትለው ማን ይሰማሃል? ማርቲን ሉተርን አትደራጅ ትለዋለህ? ማህተመ ጋንዲን እንግሊዞችን አትታገል ትለው ነበር? ህወሃት ከዚህ የባሰ ነው። አማራው በፖለቲካውም ሆነ በወታደራዊ መስክ ተደራጅቶ ራሱን መከላከል አለበት። አማራ ተደራጅቼ …ልግደል ቢል ግን እንታገለዋለን። ዛሬ ዘመኑ ሰልጥኗል ሰው ልግደል ብለህ ፓርቲ ብታቋቁም ሰው አይከተልህም።ለመብት ተደራጅቶ መታገሉን ግን እደግፋለሁ…>>ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር የቀድሞ ሊቀመንበር ስለ አማራ መደራጀት ከተናገሩት

<<…ወ/ሮ ትግስት ከሲና በረሃ ለሽፍቶቹ ገንዘቡ ተከፍሎ ተለቃለች።ዛሬ ካይሮ ግብጽ ነች።እዚያ ያሉ ግፍ የሚፈጸምባቸው ወገኖቻችንን በተመለከተ እያንዳንዳችን ሀላፊነት አለብን…>> ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ከሱዳን ታፍነው ተሽጠው በሲና በረሃ ሲሰቃዩ የቆዩትን ሴት ለማስለቀቅ ዕርዳታ ማሰባሰቡን ካስተባበሩት አንዷ ለህብር እንደተናገሩት

የአፍሪካ ህብረት እና የ50 ዓመት ክብረ በዓሉ ዳሰሳ  

ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን

ዜናዎቻችን

– የግብጹ ፕሬዜዳንት ሙርሲ አዲስ አበባ ላይ በአባይ ግድብ ዙሪያ መከሩ

– አንድነት የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በሕዝባዊ ንቅናቄ አከብራሉ አለ

– አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

– በጉዲፌቻ መልክ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የመጣች ህጻን ልጅ በአደጋ ሞተች

– የኤርትራ ጳጳሳት ለተመድ ዋና ጸሃፊ አቤቱታ አቀረቡ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

4 Comments

  1. ለኪዳነማሪያም፣ ለኦምሀራ መብት የሚታገል እንጂ የጠፋው ለአሮሞውማ ኦነግ አለለት። ስለትግራይ ላነሳኸው ደግሞ ከህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ የበለጠ ለትግራይ ህዝብ የሚያስብ ከየት ሊመጣ? ምንም የሚታገልለት ድርጅት ሳይኖር ለመከራ ለስደትና ለሞት እየተዳረገ ያለው እኮ አምሀራው ነው። እህ!

  2. If they form Amahara Democratic Fronf(ADF) I can support them as an Amahara ans I support SNEM of Obang Metho as an Ethiopian as far as ADF’s manifesto is not ethnocentric. I don’t negotiate on my ETHIOPIAWINET not even in the na me of Amahara. Go guys, form ADF and be incusive of others with similar objectives. The ultimate objective should be the respect of equal human right for all Ethiopians for HUMANITY BEFORE ETHNICITY and NO ONE IS FREE UNLESS WE ALL ARE FREE.

  3. Mr.Tekle is very correct why Amhara is not organised as organisation to fight for his national.but my question is who fight for Ethiopian unity?

Comments are closed.

Previous Story

ብአዴን ‹‹ሰለሞናዊ›› ስርወ መንግስት!? – (ሊያነቡት የሚገባ የአደባባይ ምስጢር)

Next Story

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” – ከአቤ ቶኪቻው

Go toTop