የ’ልማታዊው አርቲስት’ ሠራዊት ፍቅሬ የኢቲቪ ፕሮግራም ታገደ

/

(ዘ-ሐበሻ) በሕዝብ ዘንድ “ልማታዊ አርቲስት” በሚል የመሽሟጠጫ ስያሜ ከሚጠሩት አርቲስቶች መካከል የቀድሞው የደርግ ወታደርና የአሁኑ የወያኔ ስርዓት ዋነኛ አቀንቃኝ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ ለመንግስት በሚያደርጋቸው የአጎብዳጅነት ተግባራት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የቶክ ሾው ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ የዓየር ሰዓት ተፈቅዶላት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደጠቆሙት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ያቀርበው የነበረው ቶክ ሾው ውለታው ተዘንግቶ እንዲታገድ ተደርጓል።
“ግራና ቀኝ” የሚል ቶክ ሾው ከሌላኛው ‘ልማታዊ’አርቲስት ሽመልስ በቀለ ጋር ላለፉት 6 ወራት ሲያቀርብ የቆየው የደርጉ ወታደር ሰራዊት ፍቅሬ ይህን የዓየር ሰዓት ያገኘው ለመንግስት ባለው ታማኝነት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ድንገት ያቀርበው የነበረው ፕሮግራም በወያኔ ካድሬዎች በሚመራው ኢቲቪ እንዲታገድ መዳረጉ አስተተያየት ሰጪዎችን “ፍቅር አለቀ ወይ?” የሚሉ ግምቶችን እንዲሰጡ በር ከፍቶላቸዋል።
የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ አርቲስቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው “ባለ ራዕዩን መሪ” እንዲቀብሩ በማስተባበር እንዲሁም ጥቁር በጥቁር አንለብስም ያሉና ለቅሶ አንደርስም ያሉ አርቲስቶችን “ሲያስጠቁር” (ለመንግስት በማቃጠር) ነበር እየተባለ የሚተቸው አርቲስቱ 6 ወር በቴሌቭዥን ያቀረበው “ግራና ቀኝ” ቶክ ሾው እንዲታገድ የተደረገው “አዝናኝ ፕሮግራም” አይደለም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ይህ እገዳ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል እንደማያውቁ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ መታየት አቁሟል ብለዋል።
ኢቲቪ ወትሮም አዝናኝ ፕሮግራም አቅርቦ የት ያውቅና ሲሉ የሚተቹ አስተያየት ሰጪዎች አዝናኝ ፕሮግራም አይደለም በሚል ቶክ ሾው እንዲታገድ መደረጉ በቂ ምክንያት አይደለም በሚል ከእገዳው በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ይገምታሉ። በተለይም እንደሪፖርተርን ያሉ አፍቃሬ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ያሉ ጋዜጦች “በአቶ መለስ ስም መነገድ ይቁም” በሚል በረዥሙ ሲተቹ የከረሙት እንደሠራዊት ያሉትን ሆዳም አርቲስቶች ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢቲቪ ካድሬ መሬዎች የሰራዊትን ማንነት በግልጽ ተረድተው ይሆናል ያገዱት ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በቅርቡም በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ እንደቀረበበት መዘገቡ ይታወሳል።
የአስገድዶ መድፈር አቤቱታውን ዜና ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖ ባህርዳር ሊገባ ነው | በአዲስ አበባ ገብርኤል አስደንጋጭ ነገር ተፈፀ | 50ሺ ሠራዊት አማራ ገብቶ አልቋል›› ጄኔራሉ

ለግንዛቤ ደግሞ የታገደውን የሰራዊት ፍቅሬ ሾው አቅርበናል።

10 Comments

  1. ሰራዊት ለሆዱ ሲል ለወያኔ አደረ “አርቲስት” መሆኑ እርግጥ ነው። ቢሆንም ገናለገና እሱን ለማጣጣል ሲባል የደርግ ወታደር ማለቱ ደስ አይልም። የወያኔ ወታደር ቢባል ያስኬዳል፣ ምክንያቱም የዛሬ ወታደሮች የወያኔን ሥልጣን ከመጠበቅ በቀር ሌላ ምንም ሚና የላቸውምና። ባለፈው ስርዐት ሀገራቸውን ያገለገሉ ወታደሮች ግን ለሀገራቸው ዳርድንበር መከበር የተዋደቁ ጀግኖች ናቸውና የኢትዮጲያ ወታደር ቢባሉ አይበዛባቸውም።

    • ሙሴ እርግጥ ነው እኔም ሙሉ በሙሉ ሃሳብህን እደግፈዋለሁ። በየትኛውም መለኪያ ይሁን የደርግ ወታደር ከወያኔ ወታደር ጋር በእኩል ሚዛን አይሰፈርም። የደርግ ወታደር ለሃገሩ፤ ለባንዲራው፤ ለዳር ድንበሩ፤ ሲል ደረቱን ለጥይት ህይወቱን ለእሳትና ለሞት አሳልፎ የሰጠ ስለነበር ። ከምንም በላይ ደሞ ሃገሩን በጥቅም አሳልፎ አይሰጥም ነበርና እውነትም ሙሴ እንዳልከው የደርግ ወታደሮች የ ኢትዮጵያ ወታደሮች ቢባሉ አያንሳቸውም ። ሌላው ወደዚህ አድር ባይ እና አጎንባሽ አጎብዳጅ አርቲስት ነኝ ባይ ሰራዊት ፍቅሬ ስመለስ እሱ ተው ባይ ያጣ ጡረተኛ የዎያኔ ቅጥረኛ አሽቃባጭ፤ ደም መጣጭ፤ ውርደታም ቆሻሻ ሰው ነው ። እንደው ለእንደዚህ አይነቱ ሰው ስም መጥራቱም ይቅር በለኝ ነው። በሰው ደም የሚከብር ራሱን ከመውደድ ብቻ የተነሳ የሃገርን ጥቅም ለገዛ ራስ ለማዋል በመስገብገብ የሚያጋብስ ሆዳም ሰው ነውና ሁሉም የራሱን ቅጣቱን ያገኛል ።

  2. ከላይ የተሠጡትን ሐሳቦች እየደገፍኩ ግለሰቡ ባለፈውም ሥርዓት (ለደርግ) ማደሩ ጉዳይ ከቤተሰብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው በወታደርነት በፍፁም አልነበረም። ካዛንችስ ቀበሌ ፲፭ ይመስክር ። በእርግጠኝነት ግን በጆሮ ጠቢነት፣ በጠቋሚነት፣ (በአስጠቋሪነት) ቤተሰቡ ሁሉ በእየተራ ተሳትፏል። ግለሰቡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የነበረበትን የድህነት ዕድገት ዘንግቶታል። በሚሊኒየም ችግር ደህና ሰንብት ያለው ችግር መልኩን ቀይሮ ከተፍ አለ። እነ ከተፌንም ይኸው ዘብጥያ እየከተታቸው ነው። አሁን በካድሬዎች ፣በኢንቨስተሮች፣በኤምባሲ ሹማምንትና ቤተሰቦች፤…. በሰውዬው ለቅሶ ላይ በጣም የዘነጡ ድንኳን ውስጥ የፀሐይ መነፅር ያደረጉ፤ለአልቃሽ የከፈሉ፤የሰውዬው ፎቶ በካኒቴራ፣በቁልፍ መያዣ፣መበሸጥ ታማኝ መስለው የከበሩ አስመሳይ አድርባይ ሁሉ ቀረጥ ያልከፈሉ… በሰውዬው ሞት በግንባር ቀደም አዛኝ አስተዛዛኝ ከተማውን ቀወጠው…መክረማቸው በጣም አነጋጋሪና የሚያስጠረጥራቸው ይሆናል። እንደዕንባቸው ፍሠትና በጣም የተለጠጠ ሽርጉዳቸው መጠን ጀርባቸው ይጠናል፣ ይጋለጣሉ፣ በሕግም በሕዝብም ፊት ለፍርድ ይቀርባሉ፤ለአዲሱ ትውልድ በዕውቀትና በሥራ መተማመን እንጂ በግለሰቦች ጥላ መክበርና ማጭበርበር አሳፋሪ መሆኑን ማስተማሪያም ይሆናሉ። እነኝህም ሆድአደሮች “ግራና ቀኝ” ሳይሆን “መሐል ሰፋሪ” የተሰኘ የቲቪ ፕሮግራም ቢኖራቸው ኖሮ የበለጠ እራሳቸውን ይገልፃቸው ነበር። ህዝባችን ፸፪ ከመቶ ማንበብና መፃፍ አይችልም፡ ሀገሪቱ ነፃ ሚዲያ የላት፡ መብራትን በተራ፣ ለኮዳ ውሃ በወረፋ የሚሸጥባት፤ አለቅጥ ያደገች የሙሰኖች ሀገር ፤ የጤናው ነገር ከሚታከመው ሆስፒታል አግዳሚ ወንበር ላይ የሚሞተው ይበልጣል። ይህ ጊዜውን አገኝን ብለው የሚቀሳፍቱና የሚቀላምዱ ሁሉ የትውልድ ፀር ናቸው። የአየር ሰዓቱን ባለሙያዎች ትምህርት እንዲሰጡበት ይተውላቸው። ስንት ምሁራን ካድሬና የፓርቲ አባል ስላልሆኑ የቴሌቪዥን የአየር ሰዓት ዕድል ተነፍገውና አቅም አንሷቸው በእየቤቱ በእየቡና ቤቱ ዕውቀታቸው ይባክናል። እንደዜጋ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊዋጋ የሚገባው ሌላው የሀገሪቱ ‘የዕውቀት ብክነት’ እና ‘የወሬኞች ልቀትን’ ነው በለው ! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን!

  3. I knew they will do that after I saw the first show. Serawit may have helped to build weyane’s image but his talk show raised many issues which could help to rebuild the detoriating Ethiopian culture. Its way of substantiating his points with Ethiopian culture and norms definately are against weyane’s interest of undermining Ethiopiawinet. Gerana kegn, balageru idol, Meaza biru’s programs on sheger fm and voice of awassa some of the radio/tv programs that are cenered on Ethiopiawinet and Ethiopian culture and history. Abraham Welde’s balageru ideol will servive this epsoid atmost!!!

  4. if you hate Sarawit You can fix your problem with him .Don’t Cry to Say (Darg darg) This word is we know 21 years from wayanes.Ayamrebacehum.

  5. It has nothing to do with being Derge or TPLF solider . He is victim of narcissism” and needs psychological treatment. He deeply fail in love with himself. However, I disagree on the comments that Derg were serving the people and TPLF army is guarding TPLF. Sorry, we never have an army standing for the people but for the leaders including that of Derg army. The TPLF army serve TPLF agenda. period.

  6. ከዚህ በላይ አስተያየታችሁን ያሰፈራችሁ ስዎች በጣም ቀናተኛ ናችሁ። ቅናት ደግሞ በቀላሉ የሚድን በሽታ አይደለም። ስው ለምን ስርቶ አለፈለት እያላችሁ ስትጽፉ ትንሽ እፍረት የላችሁም፡ ስዉን ሁሉ ደርግና ወያኔ የምትሉ ለመሆኑ እናንተ ማን ናችሁ?

  7. Drink Buna in mender-with ye sefer setoch- is to to eat” ye sew Sega’ tongue melas”
    to eat ye sew sega–alubalta…most of the time ye mender setoch-no education
    no work-prostitue- most of the time-to eat sew–alubalta…destroe yesefer buna–

  8. dear editor
    please stop the Blu Party -demonstration in front Africa Building
    the day when we celebrate __the of 50 years of African Union celebreation__
    We want to remember our King Haile Selasse-and Kwame Nkruma etc…
    if you want to fight the Woyane-fight them with GUNS–not with ” tongue ”
    Woyane fight colonel Mengestu with 10 guns…not with tongue-cry or choose
    another day another please–celebration of AU 50 years in peace..Go to hell with your ” La La La la…”

Comments are closed.

Share