May 25, 2011
7 mins read

ወረፋ እስከመቼ?

(ethiopianreporter) ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ለስኳርና ዘይት ሸመታ በሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ሱቅ አካባቢ ወንድ ልጃቸውን ያሰለፉት ፈልገው ሳይሆን ለልጆቻቸው ብለው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

‹‹ስኳሩ ቢቀር ዘይት መግዛት ግድ ነው፡፡ እኔ ተሰልፌ መግዛት አልችልም፡፡ ወረፋው እንደምታይው ነው፡፡ ከ200 ሰው በላይ ተሰልፎ ማየቱ ተስፋ ያስቆርጣል፤ ባይገዛስ ያስብላል፡፡ ልጄን ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ለወረፋ ከመላኬ ቀደም ብሎ ባለው ቀን ንጋት ላይ ወረፋ ይዞ ስኳርና ዘይት እንዲገዛ ልኬው ነበር፡፡ ሆኖም ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ባዶ እጁን ተመለሰ፡፡ ለምን እንደሆነ ስጠይቀው ‹ባይበላ ይቅር ይህን ያህል ሰዓት ለምን እንሰለፋለን› ነበር ያለኝ፡፡››

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በዱሮው ቀበሌ 50 በግ ተራ አካባቢ በተለምዶ ጌጃ ሰፈር ከሚገኘው የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበር ለአራት በመሆን የገዙትን 20 ሊትር ዘይት ለመካፈል ሲሉ ያገኘናቸው እናት የነገሩን ነበር፡፡

‹‹የደርግን ጊዜ አስታወሰኝ፡፡ በወር አንዴ በራሽን እንድንወስድ በተወሰነልን ቀን ከቀበሌው የምንሰለፈው በጠዋት ነበር፡፡ በወቅቱ ስኳር፣ ዘይት፣ ጨው፣ ሻይ ቅጠል፣ ሳሙናና የመሳሰሉት እንደቤተሰብ ብዛት ይሰጠን ነበር፡፡ ቡና፣ ፓስታና መኮረኒ በግድ ውሰዱም ይባል ነበር፡፡ የፉርኖ ዱቄት፣ እህልና ጥራጥሬም እናገኝ ነበር፡፡ ለዳቦ ወረፋ የተደባደብንበት ጊዜ ዛሬ አልፏል፡፡ አሁን ደግሞ ለዘይትና ለዘይት ጀሪካን የምንደባደብበት ጊዜ ሆኗል፡፡››

በአካባቢው በለስ ቀንቷቸው ስኳርና ዘይት አግኝተው ከሚሔዱ ሸማቾች ለመገንዘብ የቻልነው፤ ሸማቹ በተደጋጋሚ እየመጣ የሚገዛበት ሁኔታ ወረፋውንና ችግሩን እንዳባባሰው ነው፡፡ አምስት ኪሎ ስኳር ለሚገዛ አንድ ሰው ለወረፋው 20 ብር ስኳሩን ለገዙበትም በድርድር ከፍለው የሚወስዱ አሉ፡፡ በተለያየ መታወቂያና ራሽን እየተጠቀሙም በየቀኑ ወረፋውን የሚያጨናንቁት፤ ራሽናቸውን በቀጥታ ለመጠቀም የሚመጡት እንዳሉ ሆነው፤ ወረፋውን ለመሸጥ የሚመጡ ናቸው፡፡

በሌሊት በወረፋ ተሰልፎ ዘይትና ስኳር መግዛት የአንድ ወር ጊዜን አስቆጥሯል፡፡ በቦሌ፣ በአራዳ፣ በየካ፣ ኮልፌ ቀራንዮና በሌሎቹም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትና በኢትፍሩት ሱቆች ደጃፍ ከወጣት እስከ አዛውንቱ ተሰልፎ ማየቱ እስካሳለፍነው ሳምንት ድረስ የነበረ ታሪክ ነው፡፡

በ22 ማዞርያ፣ ቄራ፣ ሜክሲኮና ዘነበወርቅ አካባቢ ደግሞ ስኳርና ዘይት ለመግዛት የተሰለፉ ሸማቾች ሰልፉን እንዳይረብሹ በፖሊስ እየተጠበቁ ሲሸምቱም ነበር፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ያገኘኋቸው ነዋሪ በግንቦት መጀመርያ አካባቢ የሚያዝያ፣ የግንቦትና የሰኔ ወራት የዘይትና የስኳር መግዣ ራሽን እንደተሰጣቸው ነግረውናል፡፡ ሆኖም ግን ወረፋ ጠብቀው ለመግዛት ሞራሉ እንደሌላቸው ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ዘይትና ስኳር ለመግዛት ብዬ አንድ ቀን አላጠፋም፡፡ በውድ ዋጋም ቢሆን አለ ከተባለበት ስፍራ እገዛለሁ፡፡››

አራዳ ክፍለ ከተማን ጨምሮ በአብዛኞቹ ክፍለ ከተሞች የዘይትና ስኳር መግዣ ራሽን ለሸማቹ ደርሶት የነበረ ቢሆንም ሸማቹን ከሰልፍ አላዳኑትም፡፡ በመታወቂያ መጠቀምም ቢሆን እንዲሁ፡፡

በሜክሲኮና 22 ማዞርያ አካባቢ በሚገኙ የኢትፍሩት መሸጫ ሱቆች ከተሰለፉ ሸማቾች የሰማነው ደግሞ ስኳር ሲገዙ በግዳጅ አንድ ኪሎ ቲማቲም ወይም ሽንኩርት ውሰዱ መባላቸውን ነው፡፡ ‹‹ይህ አግባብ አይደለም፡፡ ሰው የሚፈልገውን እንጂ ዕቅዱ ያልሆነውን በግድ ግዛ ሊባል አይችልም፡፡ ምርጫ ስለሌለ ከሁለት አንዱን እንወስዳለን፡፡ ሽንኩርቱ ግን የሚፈለግ ዓይነት አይደለም፡፡ መርጦ መግዛትም አይቻልም፡፡›› ያለችን ማርታ ውቤ የተባለች ሸማች ናት፡፡

ከሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ የሸማቹን የስኳርና የዘይት ፍላጎት ሊያስተነፍሱ ይችሉ የነበሩትና ላለፉት ሁለት ወራት በስኳርና ዘይት አቅርቦት እጦት ባዶዋቸውን የከረሙ የንግድ ሱቆች፤ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ የፈለጉትን ያህል ዘይትና ስኳር ከሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት መግዛትና በተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን ለኅብረተሰቡ መሸጥ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ሸማቹን ከሰልፍ ይታደጉት ይሆን?

በምሕረት ሞገስ

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop