የባርሴሎናውን ፈርጥ ወይንም ”አቶሚክ ቦምብ ” በእንቅስቃሴ ላይ ያለውን ልዩ የቴክኒክ : የኳስ ቁጥጥሩ : ድሪብል እያደረገ መጓዙ : ብልሀቱ : ፍጥነቱ ወዘተ …. እያለ የቀድሞ የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አንግል ማርስ የሊዮኔል ሜሲን ብቃት በዝርዝር ገልጾታል :: እርሱን ለዛሬ እንደሚከተለው አቀናብሬ አቀረብኩት ::
የገዘፈ ቴክኒክ
ኳስ ይዞ ሲገፋ ወዲያው የሚታወሰኝ ወይም በአእምሮዬ የሚመጣው ዲያጎ ማራዶና ነው :: እግሩ ላይ ኳሱን በማስቲሽ ለጥፎ የሚንቀሳቀስ ይመስላል :: ሜሲ ያልገዘፈውን ሰውነቱን ሲታይ ኳሱ ለእርሱ ትልቅ ይሆናል የሚል እምነት ቢያሳድርም በእንቅስቃሴ ላይ ግን ለእርሱ በጣም ትንሽ ናት :: እንደፈለገውም ያደርጋታል ::
በደንብ የተሰራ ጭንቅላት
ከእድሜው በላይ የበሰለ ነው :: በዚህ ላይ ራሱን ላይ አያስቀምጥም :: ከሜዳ ውጭ ሌላ አያዳምጥም :: ሚዲያ ምን አወራ ምን አለ ለእርሱ ምንም ማለት አይደለም :: ለእነርሱ ጆሮም የለው :: ለእርሱ ትልቅ ቦታን የሚሰጠው ሜዳ ውስጥ መዝናናቱን ነው :: እስካሁን ድብቅ ነገሩ ከሜዳ ውጪ ምን አይነት ሕይወት አለው ? ሴቶችን ያውቃል ? በርካታ ጓደኞች አሉት ? በዚህ በኩል እስካሁን ድብቅ ነው :: ትልቅ ተጫዋች እንዲሆን ከተፈለገ ግን በዙሪያው ያሉ በሙሉ ሊገፉት ይገባል ::
እንደብርሀን ፈጣን ነው
ከጥንካሬው ይልቅ በጣፍ ፈጣን ነው :: በ 30 ሜትር ውስጥ ቦምብ አይደለም :: በተቃራኒ በመጀመሪያዎቹ አምስት ሜትሮች ውስጥ በጣም ጠንካራ ነው :: ትልቁ ብቃቱ ሪትሙን የመቀየር ኳሊቲው ነው :: ኳስ በአንድ ጊዜ በእግሩ ከገባች የሚወስደውን አክሽን በፍጥነት ያስባል :: ከማንም ተጋጣሚ አእምሮ በጣም ፈጣን ነው :: ከእምሮ ፈጣን በመሆኑ እንቅስቃሴዎቹ በአብዛኛው ስኬታማ ናቸው ::
ያበደ ድሪብለር
በኳስ የፈለገውን ነገር መስራት ይችላል :: ያበደ ድሪብለር ነው :: ለብቻው አንድን ተከላካይ ሚዛን ማሳጣት ይችላል :: በማንኛውም ጊዜና ስአት ልዩነት መፍጠር ይችላል :: ድሪብል ሲያደርግ አቅጣጫው ወደፊት ነው :: በዚህ ላይ ወደ ውስጥ እየገባ ነው የሚሄደው :: በፍጹም ወደ መስመር አይጓዝም :: ለእርሱ ሁሉ ነገር ስኬታማ ነው – ድሪብሉ ሳይቀር ::
ሚስጢሩ
ከማንም በላይ ለሜሲ ስኬታማ እንቅስቃሴው ዋናው ምስጢር ኳስ መቆጣጠሩ ነው :: ከዚዳን ጋር አመሳስለዋለሁ :: ሜሲ ኳሱ ወደ እርሱ ስትመጣ በቴክኒኩ እርግጠኛ ሆኖ ነው የሚጠብቀው :: ስለዚህ በተጋጣሚ ተከላካዮች ላይ ብዙም አይጨነቅም .:: ትኩረትም አያደርግም :: ማንም ቢሆን ለእርሱ ቦታ የለውም :: ተከላካዮች ከእርሱ ብዙ ኪሎሜትሮች ርቀት ያሉ እስከሚመስለው ድረስ ነው የሚታይበት ስሜት ::
_________________