May 22, 2011
8 mins read

ማን.ዩናይትድ ከባርሴሎና (ላይቭ)

ምናልባት ስለባርሴሎና የማናውቃቸው 5 ነጥቦች

ዘንድሮ የላሊጋው ሻምፒዮን ሆኖ የጨረሰው ባርሴሎና ስፖርት ክለብ የተቋቋመው እንደአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በሺህ ስምንትመቶ ዘጠና ዘጠኝ (1899) አ .ም ነው :: ልክ ማን .ዩናይትድ ”ሬድ ዴቭልስ ” ተብሎ በቅጥያ እንደሚጠራው ባርሴሎናም ”ባርሳ ” ተብሎ በቅጥያ ስሙ ይጠራል :: ይህ ብቻ ሳይሆን ባርሳ ”Blaugranes (Blue-Maroon)” የሚል ቅጥያ ስም አለው :: ባርሴሎና እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በማሊያው ላይ ማስታወቂያ የማይለጥፍ ብቸኛው የአውሮፓ ትልቅ ክለብ ነበረ ::
የካታሎናዊው ክለብ ባርሴሎና ስታዲየም መጠሪያ ካምፕ ኑ (ኑ ካምፕ )ይሰኛል :: ስታዲየሙ 98 ሺህ 772 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በዚህ ስታዲየም ላይ ማን .ዩናይትድ የ 1998ቱን የቻምፒዮንስ ሊግ ድል አሳክቶበታል :: ባርሳ በኑካምፕ ካደረጋቸው የቻምፒዮንስ ሊግና የአውሮፓ ካፕ ጨዋታዎች ውስጥ በከፍተኛ ጎል አቸንፎ ሪከርድ የያዘበት ጨዋታ 2 ነው :: ባርሳ በ 1982 አ .ም Apollon Limassol FC የተባለውን ክለብ በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ላይ አግኝቶ 8ለ 0 አሸንፏል :: ከዚህ በኍላ 2003 ላይ KM Pú chov የተባለውን ክለብ 8ለ 0 እንደገና ኑካምፕ ላይ አሸንፏል :: ከዚህ በኍላ ሪከርዱን ማሻሻል አልቻለም :: ምናልባት ኑካምፕ ላይ in the future ማን .ዩናይትድን ባርሳ 9ለ 0 ካሸነፈ ሪከርድ ያሻሽላል ማለት ነው :: ባርሳ ኑካምፕ ላይ ተዋርዶ የተሸነፈበት ውጤት በዳይናሞ ኪየቭ በ 1997: በጀርመኑ ኮሎኝ 4ለ 0 በ 1980: 4ለ 0 የተሸነፈበት ነው ::
ባርሴሎናን የተለያዩ እንግሊዛውያን ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞች መርተውታል :: ባርሴሎናን ያሰለጠኑ እንግሊዛውያን አሰልጣኞች ቁጥር 5 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ቴሪ ቬናብልስ እና ሰር ቦቢ ሮብሰን ይጠቀሳሉ :: 2 እንግሊዛውያን ደግሞ ባርሴሎናን በፕሬዚዳንትነት መርተዋል :: የቀድሞው የፉልሀምና የዌስትብሮሚች ተጫዋች የነበሩት ቦቢ ሮብሰን በ 1996-97 ሲዝን ባርሴሎናን ካሰለጠኑ በኍላ ፒኤስቪን እና ኒውካስትልን አሰልጥነዋል :: ከዛ በፊት ግን ፖርቶን መርተው ነበር :: ከእርሳቸው ሌላ ባርሳን ከ 1984-87 ድረስ የመራው የቀድሞው የቸልሲ : የቶተንሀም : ክዊንስፓርክ ሬንጀርስ እና ክሪስታል ፓላስ ተጫዋች የነበረው ቴሪ ቬናብልስ ነው :: ቴሪ 1984-85 ሲዝን ባርሳን የላሊጋው ሻምፒዮን አድርጎታል ::
ባርሴሎና ውስጥ ከተጫወቱ እንግሊዛውያን መካከል እንግሊዛዊው አጥቂ ጋሪ ሊንከር ይጠቀሳል :: በሌስተር ሲቲ ክለብ አድጎ ወደ ኤቨርተን የተዘዋወረው ሊንከር ለኤቨርተን 41 ጨዋታዎችን አድርጎ 30 ጎል ማግባት የቻለ አጥቂ ሲሆን ወደ ባርሴሎና በ 1986 ተዘዋወሮ እስከቆየበት 1989 ድረስ 103 ጨዋታዎችን ለባርሳ አድርጎ 43 ጎሎችን ለካታሎናውያኑ ክለብ አበርክቷል :: ጋሪ ከባርሳ በኍላ ለቶተንሀም ተጫወቶ በ 105 ጨዋታዎች 67 ጎሎችን አግብቷል :: ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ከ 80 ጨዋታዎች 48 ጎሎችን ያገባው ይኸው የቀድሞው የባርሴሎና አጥቂ ጫማውን የሰቀለው በ 1994 አ .ም መሆኑ ይታወሳል ::
አሁን ያለው የባርሴሎና አሰልጣኝ ጋርዲዮላ ክለቡን በታሪኩ ካሰለጠኑት አሰልጣኞች መካከል 31ኛው ነው ::
ሜይ 22

ውድ የዘ-ሐበሻ ዶት ኮም ድረ ገጽ ተከታታዮች፡ ከዛሬ ጀምሮ ባርሴሎና ከማን.ዩናይትድ ሜይ 28 ቀን 2011 ስለሚያደርጉት የቻምፒዮንስ ሊግ ፋይናል ጨዋታ በየሰዓቱ አዲስ መረጃዎችን እንጽፍላችኋለን። ድረ ገጹን ቶሎ ቶሎ ይመልከቱት። አሁን ማራዶና እና ሜሲ በ20 ዓመታቸው ምን አከናወኑ የሚለውን እናንብብ።
በ 20 አመት እድሜያቸው ምን አከናወኑ ??
ኦንዝ ሞንዲያል የተሰኘው ሜጋዚን በአርጀንቲና እውነተኛው የማራዶና ወራሽ ስለሆነው ሊዮኔል ሜሲ እና ስለራሱ ማራዶና አንድ ነገር አቅርቧል :: መጽሄቱ ማራዶና እና ሜሲ ሁለቱም እድሜያቸው 20 አመት እያለ የሰሩትን ያወዳድራል ::
በክለብ ሜሲ ይበልጣል በ 20 አመቱ ዲያጎ ማራዶና ከአርጀንቲኖስ ጁኒየርስ ወደ ቦካ ጁኒየርስ ሲዘዋወር በ 1981 የመጀመሪያውን የክለቦችን ሻምፒዮን ክብርን ለመጎናጸፍ ችሏል :: ባጠቃላይ የአርጀንቲና ሻምፒዮን ላይ ማራዶና አምስት ጊዜ የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን ጨርሷል :: ይህ ሪከርድ ነው ::
በ 20 አመቱ ሊዮኔል ሜሲ ለባሴሎና ዋናው ቡድን ይጫወታል :: ከካታሎኑ ክለብ ጋርም ሜሲ በ 2005 እና በ 2006 ሁለት ጊዜ ላሊጋን በተለይ ደግሞ የአውሮፓ ግዙፉን የክለቦች ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማግኘት ችሏል ::

በብሔራዊ ቡድን – ማራዶና ኤልፕቤ ዲ ኦሮ (ማራዶና ) ለብሄራዊ ቡድን መጫወት የጀመረው በ 16 አመቱ 27 ፌብሩዋሪ 1977 ከሀጋሪ ጋር ሲጫወቱ ነው :: ከአንድ አመት በኍላ አርጀንቲና ላይ የተደረገውን የ 1978ቱ የአለም ዋንጫ ላይ ለመቅረብ ማለም ጀመረ :: ግን አሰልጣኝ ሴዛር ልዊስ ሚኖቲ ሳይመርጡት ቀሩ :: ለብሄራዊ ቡድን እንዳልተመረጠ አሰልጣኙ ሲናገሩት ማራዶና አይኖቹ በእምባ ጠፍተው ነበር :: (በጣም አልቅሷል ::
”ላ ፑልጋ ” (ቁንጮው ) ሜሲ ለብሄራዊ ቡድን መጫወት በ 18 አመቱ ሲጀመር እለቱም 17 ኦግሰት 2005 ነው :: እንደማራዶና ከሀንጋሪ ጋር ነው የጀመረው :: በዚህ ቀን ተቀይሮ ሜዳ ቢገባም ብዙም ሳይቆይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል :: ሜዳ ውስጥ የቆየው 90 ሰከንድ ብቻ ነበር :: ዳኛው ሜርክ ሜሲ ባልፈጸመው ስህተት ነው ያስወጡት :: ሜሲም ሜዳውን የለቀቀው በማልቀስ ነበር :: ቢሆንም ሜሲ በጀርመኑ የ 2006ቱ የአለም ዋንጫ ላይ የመሳተፍ እድልን አግኝቷል ::
ማራዶናን እና ሜሲን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ሁለቱም የአለም ወጣቶችን ዋንጫን ማግኘት ችለዋል ::

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop