May 10, 2011
19 mins read

የአርሴናል ትልቁ ችግር ዴንን ማጣቱ ነው

አርሴን ቬንገር እርካታን ማግኘት ይሻሉ፡፡ ከፊዚዮ ትራፒስት ሳይሆን አርሴናልን ለማጠናከር ሁል ጊዜም አዕምሯቸውን የሚያስጨንቁበት ጉይን ለማቃለል የሚረዳቸው እንደ ዴቪድ ዴይን አይነት የክለብ አስተዳዳሪን ይሻሉ፡፡ አርሴናል በቦልተን 2ለ1 ተሸንፎ ለድፍን ስድስት ዓመታት የዋንጫ ሽልማትን እንደሌለው ባረጋገጠበት ማግስት ቬንገር በሰጡት መግለጫ ‹‹ሁልጊዜም የማስበው ስለ ፉትቦል ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ተኝቼም ቢሆን አርሴናልን በምን መልኩ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባኝ አይምሮዬን አስጨንቀዋለሁ›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ጭንቀታቸው ከ2005 ወዲህ ለአርሴናል የዋንጫ ድልን ሊፈጥርለት አልቻለም፡፡ እንደ ቀድሞው የአርሴናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኬይዝ ኤዴልማን እምነት አርሴናል የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት እንዳይችል በዋነኝነት የሚጠቀስ ችግሩ የሆነው እንደ ዴቪድ ዴይሊ አይነት የክለቡ አስተዳዳሪን ማጣቱ ነው፡፡
የአርሴናል ምክትል ቼርማን የነበሩት ዴይን ከክለቡ ቦርድ አባላት ጋር የሀሳብ ልዩነትን ፈጥረው ከኃላፊነታቸው ከተነሱ ወዲህ አርሴናል የዋንጫ ሽልማትን ለማግኘት እንዳልቻለ ይታወቃል፡፡ የአርሴናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሆነው ከ2000 እስከ 2008 ድረስ የሰሩት ኤዴልማን በኃላፊነት ዘመናቸውወቅት አርሴናል የተጨዋቾች ግዥ የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥመው ወቅት ከዴይን ጋር በተደጋጋ ግጭት ፈጥረው እንደነበር በማስታወስ መግለጫቸውን የሰጡት ‹አርሴናል የዋንጫ ሽልማቶችን በማግኘት ውጤታማ ዘመንን ለማሳለፍ እንዲችል ቁልፍ አስተዋፅኦን ሲያበረክቱለት የቆዩት ዴቪድ ዴን ናቸው፡፡ ‹‹ብኔ በዴንና በቬንገር መካከል የነበረው ተግባብቶ የመስራት መንፈስም እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡ እኔ የቢዝነሱ ጉዳይ በዋነኝነት ሳስፈፅም ዴቪድና ቬንገር በበኩላቸው በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦል ሙሉ ትረኩረትንሰጥተው ይሰራሉ፡፡ በተለይም ዴቪድ ዴይን ለአርሴናል ውጤታማነት ቁልፍ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ቬንገር ያጡት ትልቁ ነገርም ከዴን የተነሳሽነት መንፈስን ነው፡፡ ቬንገር ሁሉንም ነገሮች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ማከናወንን ይመርጣሉ፡፡ ዴይን ግን ለአርሴናል ውጤታማነት ከፍተኛ የሆነ ተቆርቋሪ በመሆናቸው አንዳንድውሳኔዎችን ስሜታዊነት በተሞላበት መልኩ ያደርጋሉ፡፡ ይህ በአብዛኛው ስኬታማ ይሆንላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ሶል ካምፕቤልን ትልቅ ደሞዝን በመክፈል ለክለባችን እንዲፈርምያደረጉበት ተግባራቸውን መጥቀስ እንችላለን፡፡ ካምፕቤል የአርሴናል ተሰላፊ በሆነበት ዘመን ክለቡ የበርካታ ዋንጫዎች ሽልማትን ለማግኘት ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ክለቡ እንደዚህ አይነቱ ተግባርን ሲፈፅም አይታይም፡፡ ከዚህ ባሻገር ዴቪድ ተደናቂ የኔትዎርክ እቅድ ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ ለአርሴናል ይጠቅማል ብለው ያመኑበት ተጨዋችን ለማስፈረም የማመንታት መንፈስንሲያሳዩ አይታዩም፡፡ በእኔ ኃላፊነት ዘመን በክለቡ የቦርድ አባላት ስብስብወቅት ቬንገር የፕሪሚየር ሊግ ክብሩን ለማግኘት የሚችለው ወርልድ ክላስ ግብ ጠባቂ ሲኖር ብቻ ነው ማለታቸው የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ፍላጎታቸውን ለማሟላጽ እስከ መጨረሻው ድረስ ግፊት ሲያሳድሩአይታዩም፡፡ ዴቪድ ዴይን እስካሁንም ድረስ በክለቡ ቦርድ ቢኖር ኖሮ ግን ይህንን ፍላጎቸውን በፍጥነት ያሟሉላቸው ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር አርሴናል የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት የሚረዳው ጠንካራ አቋምን ለመያዝ የግድ እንደ ዴይን ያለ ሰው በክለቡ አስተዳደር ያስፈልገዋል፡፡ የአዲሱ የክለቡባለቤት ስታን ክሮኤንኬ የቀድሞ አላማ ሊሆን ሚገባውም እንደዚህ አይነት ቁልፍ ሰውን ማግኘት ነው›› በማለት ነው፡፡
ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የአርሴን ቬንገር ረዳት ሆነው ከ1996 ጀምሮ የሰሩት ፓት ራይስ ራሳቸውን ከኃላፊነቱ ለማግለል በመወሰናቸው በክለቡ ኮቺንግ ስታፍ መሰረታዊነት ያለው ፍቅር ይኖራል፡፡ የአርሴናል ደጋፊዎች ምኞትም የቀድሞው የቡድናቸው አምበል ፓትሪክ ቪየራን ቬንገር ረዳታቸው አድርገው እንደሚቀጥሩት ነው፡፡ ከማንቸስተር ሲቲ ያለው ኮንትራት ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሚያከትመው ቪየራ የ2003-04 የአርሰናል ኢንቪዝብልስ ቡድን መንፈስን ዳግም ወደ ክለቡ እንዲመለስ ምክንያት ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ይህ አርሴናል ራሱን ለለውጥ እርምጃ እንዲያነሳሳ ምክንያት እንደሚሆንም ይታመናል፡፡ ነገር ግን አዲሱ የክለቡ ባለቤት አርሴናል የተጨዋች ግዥ ውሎችን ለመፈፀም የዝውውሩ መስኮቱ እስኪገባደድ ድረስ ከመጠበቅ ይልቅ ፈጥነው ውሳኔ ላይ መደረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክያቱም ባለፈው ፕሪሲዝን አርሴናል የፉልሃሙ ግብ ጠባቂ ማርክ ሽዋርዘርን ለማስፈረም ያልቻለው እስከ ኦገስት ወር ድረስ እቅዱን ተግባራዊ ከማድረግ መቆጠብን በመምረጡ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሴስክ ፋብሪጋስ ባለፈው ሳምንት ውስጥ እንደሰጠው መግለጫ ሁሉ አርሴናል ከሁለት ነገሮች አንዱን ለመምረጥ ዝግጁ መሆን ይገባዋል፡፡
ከእነዚህ ሁለት ጉዳዮ ውስጥ የመጀመሪያው ወጣት ተጨዋቾችን ማፍራትን መቀጠል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የዋንጫ ድሎችን ለማግኘት ከፍተኛ ትረኩትን ማድረግ ነው፡፡ በዚህ የፋብሪጋስ መግለጫ የተበሳጩት ቬንገር ግን ምርጫቸው ወጣቶችን ማሳደግ መቀጠል መሆኑን ከመናገር አልተቆጠቡም፡፡ ነገር ግን ቬንገር ቡድናቸው የዋንጫ ሽልማትን ለማጣት ዝግጁ ከሆነበት የዘንድሮው ሲዝን በኋላ በስኳዳቸው የሚገኙት ተጨዋቾችን ለማቆየት ትልቅ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡
ለምሳሌ የሳሚር ናስሪ ኮንትራት የሚጠናቀቀው በጁን 2012 በመሆኑ ከዘንድሮ ሲዝን በኋላ ውሎ ወደ መጨረሻው ዓመት ይገባል፡፡ በአሁኑ ስኳድ ከሚገኙት የሜዳ ተጨዋቾች የ2004 የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ሜዳልያን በማግኘት ብቸኛው የሆነው ጌይል ክሊሺም ኮንትራት የሚጠናቀቀው በ2012 ነው፡፡
የእነዚህ ሁለት ተጨዋቾች ኮንትራት በማስመልከት ቬንገር መግለጫቸውን የሰጡት ‹ከናስሪ ኤጀንት ጋር ከወዲሁ መነጋገር ጀምረናል፡፡ የክሊሺም ጉዳይ ተመሳሳይነት ባለው ሂደት ይገኛል፡፡ እነዚህም ሆነ ፋብሪጋስን ሮቢን ቫንፐርሲን የመሳሰሉት የቡድናችን ተሰላፊዎችን ለመልቀቅ አንሻም፡፡ በአሁኑ ወቅት ለተጨዋች ግዢ የሚውል ከ40 ሚሊየንፓውንድ ያላነሰ ሂሳብ አለን፡፡ ነገር ግን የቡድናችን አማካይ የዕድሜ ክልል 23 በመሆኑ በርካታ አዲስ ተጨዋቾችን የማስፈረም ግዴታ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ በስኳዳችን የሚገኙት ተጨዋቾች ለተጨማሪ አራትና አምስት ዓመታት የኮንትራት ማራዘሚያን ለመፈረም ዝግጁ ሲሆኑ የሚታዩት ከቡድናችን ጋር የዋንጫ ድልን ለመቀዳጀት እንደሚችሉ ስለሚያምኑ ነው፡፡ በዘንድሮው ሲዝን የውንጫ ሽልማት ላይኖረን ይችላል፡፡ በቀጣዮቹ ዓመታት ግን ክለባችን ይህንን ምኞቱን ለማሳካት የማይችልበት ምክንያት አይኖርም፤ ዋናው ለዚህ ክለብ ውጤታማነት እያንዳንዳችን የስራ ድርሻችንን በአግባቡ ለመፈፀም ተግተን መስራት መቀጠላችን ነው፡፡›› በማለት ነው፡፡ ራሽያዊው ስታር አንድሬ አርሻቪን ከዘንድሮው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ በአርሴናል ይለቀቃል የሚል ግምት ከተሰጣቸው ተጨዋቾች አንዱ ቢሆንም ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ግን የተሰማውን ጭምጭምታ አጣጥሎታል፡፡
የ29 ዓመቱ ራሽያዊ በዚህ መግለጫው ከቬንገር ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውም ተናግሯል፡፡ አርሻቪን በጃንዋሪ 2009 ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግን በመልቀቅ ለአርሴናል ከፈረመ ወዲህ የአቋም አለመረጋጋት ያሳየበት የውድድር ዘመን የዘንድሮው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፉት ሁለት የአርሰናል ተከታታይ ግጥሚያዎች የመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት እድልን ያጣበት ዋነኛ ምክንያት ይሄ ነው፡፡ አርሻቪንም የዘንድሮው ሲዝን አቋሙ ጥሩ አለመሆኑን ያምናል፡፡ ነገር ግን ከአርሴን ቬንገር ጋር የሀሳብ ልዩነትን ፈጥሯል በሚል የቀረበበት ዘገባን ያስተባበለበት መግለጫን የሰጠው ‹‹ከቬንገር ጋር መልካም ግንኙነት አለኝ፤ ከአርሴናል ጋር ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ያለኝፍላጎትም ከፍተኛ ነው›› በማለት ነው፡፡
አርሻቪን በዘንድሮው ሲዝን መሰረታዊ የሆነ የአቋም አለመረጋጋት ችግር ሲከሰትበት መታየቱ የተለመደ ቢሆንም ስታስቲክሱ የሚያሳየው ግን ያንን ያህል መጥፎ የሚባል ሪከርድን አለመያዙ ነው፡፡ ምክንያቱም በዘንድሮው ሲዝን በፕሪሚየር ሊግ ጥሚያች 11 አሲስቶችን በማድረግ ከሴስክ ብሪጋስ ቀጥሎ 2ኛው ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በሁሉም ውድድሮች ግጥሚያዎች 10 ጎሎችን ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል፡፡ ያም ሆኖ ግን ቬንገር ከአርሻቪን ይልቅ ቴዎ ዋልኮትን ለቡድናቸው በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጠቀም እድልን መስጠታቸውን ገፍተውበታል፡፡ ከቶተንሃምና ከቦልተን ጋር በተደረጉት ግጥሚያዎች ዋልኮት የመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት እድልን አግኝቶ ከተሰለፈ በኋላ በሰጠው መግለጫው በዘንድሮው ሲዝን ቡድናቸው የዋንጫ ሽልማትን ለማግኘት ያልቻለበት ምክንያት የቡድናቸው ተሰላፊዎች በወጣትነት የዕድሜ ክልል ስለሚገኙ ነው የሚለውን አመለካከት እንደማይቀበለው አረጋግጧል፡፡ አርሴናል በአሁኑ ወቅት ከሊጉ መሪ ማንቸስተር ዩናይትድ በዘጠኝ ነጥቦች ተበልጦ ቀሪዎቹ 4 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎችን ለማድረግ ዝግጁ እንዲሆን ምክንያት የሆነው ዋነኛ ችግሩ ጎል የማስቆጠር መምራት የጀመረው ግጥሚያዎችን በድል ለማጠናቀቅ አለመቻሉ ነው ብሏል፡፡ ዋልኮት በቅርቡቡድናቸው ከሊቨርፑልና ከቶተንሃም ጋር ያደረጋቸው ግጥሚያዎችን ጎል በማስቆጠር መምራት ጀምሮ ሙሉ ሶስት ነጥቦችን ለማግኘት ሳይችል የቀረበ ሁኔታን በማስገንዘብ መግለጫቸውን የሰጠው ‹የዋንጫ ሽልማት ለማግኘት የምንችለው ከስህተቶቻችን በአግባቡ ለመማር ዝግጁ ስንሆን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን አብዛኛዎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች በወጣትነት የዕድሜ ክልል በመገኘታቸው የልምድ እጥረት የዋንጫ ሽልማቶችን አሳጥቶናል የሚለውን ጉዳይ ከእንግዲህ በምክንያትነት ማቅረብ አይኖርብንም፡፡ ምክንያቱም ባለፉት ዓመታት በበርካታ ትላልቅ ግጥሚያዎች ላይ አብረን በመሰለፍ ሰፊ ልምድን ለማካበት ችለናል፡፡ ለቡድናችን ውጤታማነት እያንዳንዳችን ኃላፊነታችንን በእባቡ ለመፈፀም ችለናል ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በዘንደሮው ሲዝን ግን ይህንን ቁልፍ ኃላፊነታችንን በወሳኝ ግጥሚያዎች ወቅት በአግባቡ መፈፀም መቻላችንን በከፍተኛ ደረጃ እጠራጠረዋለሁ፡፡ ምክንየቱም ጎል በማስቆጠር የመራናቸው በርካታ ግጥሚያዎችን በሙሉ ሶስት ነጥቦች ለማጠናቀቅ አለመቻላችን ክፉኛ ጎድቶናል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ያልቻለ ቡድን ደግሞ ለሊግ ሻምፒዮንነት ለመብቃት አይታደልም›› ብሏል፡፡
የአርሴናል ለድፍን 6 ዓመታት ካለዋንጫ ሽልማት መቅረትን ተከትሎ የአርሴን ቬንገር ኃላፊነት ለትልቅ አደጋ መጋለጡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ዋልኮት ከቬንገር ያለውን ድጋፍ የገለፀው ‹‹በርካታ ሰዎች ለቡድናችን የዋንጫ ሽልማት አለማግኘት ቬንገርን ዋነኛው ተወቃሽ ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የክለቡ ውስጥ ያለን ሰዎች ተወቃሽ የምናደርገው ራሳችንን የቡድኑ ተሰላፊዎች ነው፡፡ ምክንያቱም የቬንገር ያላሰለሰ ጥረት ፍሬያማ እንዲሆን የሚጠበቅብን ኃላፊነትን ለመፈፀም እንደተሳነን ማመን ይኖርብናል›› ብሏል፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop