ሄርናንዴዝና ኦዚል የዘንድሮው ሲዝን በአውሮፓ ምርጥ ግዢዎች ተባሉ

BUYS OF THE SEASON
ባለፉጽ ሁለት የዝውውር መስኮቶች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ፓወንዶች፣ ዩሮዎችና ዶላሮች ለተጨዋች ግዢ ውለዋል፡፡ በዚህ ከፍተኛ በጀት በመላው ዓለም በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨዋቾች ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላው ዝውውር አድርገዋል፡፡ የጣሊያን ሴሪ አ እና ሴሪ ቢ ክለቦች ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ የተጨዋቾች እንቅስቃሴ ተካሂዶባቸዋል፡፡
በእንግዝና በስፔንም ባለፉት ሁለት የዝውውር መስኮቶች የበርካታ ተጨዋቾች እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡ ይህንን ከግምት በማስገባትም ጎል ዌብሳይት የፉትቦል አናሊስቶች የ2010-11 ሲዝን 10 እጅግ ተደናቂ የዝውውር ውሎችን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዳስሷቸዋል፡፡ አናሊስቶቹ የዘንድሮው ሲዝን 10 ተደናቂ የዝውውር ውሎችን ያወጡት ተጨዋቾችን የዘረዘሩት ለክለባቸው ካበረከቱት አስተዋፅኦ አንፃር እንዲሁም በአዲሱ ክለባቸው የጨዋታ ስታይል በምን መልኩ ለመዋሀድ ችለዋል የሚሉት መስፈርቶች ከግምት በማስገባት ነው፡፡
1/ ናስር ቺዲሲ /ኤፍ.ሲ.ቲዎንቴ/
የተገዛበት ዋጋ፡- 500 ሺህ ፓውንድ
ቺዲሊ በሆላንድ ኤሪ ዲቪዚዮን በተደናቂ ኳሊቲያቸው ግንባር ቀደም ስፍራ ከተሰጣቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱነው፡፡ ነገር ግን አያክስ አምስተርዳም ይህንን በአጥቂ መስመር በሁሉም የጨዋታ ሚናዎች ለመሰለፍ የሚችል ተጨዋችን ለኤሪዲቪዚዮ ውድድር ተሳትፎ በትክክል አይመጥንም በሚል በአግባቡ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም የኤፍ.ሲ.ቲዌንቲ ኃላፊዎች የዘንድሮ ሲዝን ከመጀመሩ በፊት አስፈርመውታል፡፡ ይህንን ውሳኔ ማድረጋቸውም ተገቢነት ያለው መሆኑ ተመስክሮለታል፡፡ ምክንያቱም ከዝውውሩ ወዲህ ቤልጂየማዊው ኢንተርናሽና አጥቂ አሚር በጅራሚ ጋር ያደረገው ፉክክርን በማሸነፍ በበርካታ ግጥሚያዎች በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመሰለፍ ዕድልን አግኝቷል፡፡ በዘንድሮው ሲዝን በሆላንድ ሊግ በተደናቂነቱ አቻ ያልተገኘለት የዝውውውር ውል ውሳኔም ሆኗል፡፡ ቺዲሊ በዘንድሮው ሲዝን የኤሪዲቪዚዮ ብቻ ሳይሆን በቻምፒየንስ ሊግ ውድድርም ታላቅ ፕሮፎርማንስን ለማበርከት በመቻሉ ወደ ትልቅ ክለብ ዝውውር ለማድረግ የሚጠብቀው የዘንድሮው ሲዝን እስኪጠናቀቅ ድረስ ብቻ እንደሚሆን ይታመናል፡፡
በቲዌንቴ የተሰለፈው፡- በ45 ግጥሚያዎች
ያስቆጠረው ጎል፡- 13
አሊስትስ፡- 5
2/ ኬቪን-ፕሪንስ ቦውቴንግ /ኤሲ ሚላን/
ግጥሚያ፡- 29
ጎል፡- 3
አሲስት፡- 3
የተዛወረው፡- ከጀኔዋ በ3 ሚሊየን ዩሮስ ጋናዊው ኢንተርናሽናል በመጀመሪያ ላይ ፖርትስማውዝን በመልቀቅ በጄኔዋ በኩል ለኤሲ ሚላን የፈረመበት የዝውውር ሂደት ትልቅ ውዝግብን ፈጥሮ ነበር፡፡ በዛኑ መልኩም በፍጥነት ከጣሊያን ሴሪ አ የጨዋታ ስታይል ጋር ለመላመድ መቻሉ አጠራጣሪ መስሎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቦውቴንግ ከደረሰበት ጉዳት ካገገመ በኋላ ለኤሲሚላን በቁልፍ ግጥሚያዎች ሳይቀር ታላቅ ፕሮፎርማንስን ማበርከት ችሏል፡፡
በተለይም ኤሲ ሚላን ከሜዳው ውጪ ከቶተንሃም ጋር ባደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያ ተደናቂ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡ በኤሲ ሚላን የሚድፊልድ ዲያመንድ ፎርሜሽን የሰውነት ጥንካሬውን በመጠቀም ተደናቂ እንቅስቃሴን የማበርከት አዝማሚያውም እጅግ ተደናቂ ነው፡፡ በተለይም የቡድኑ አማካይ ክፍል ያማረ ቅንጅትን የመፍጠር አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው፡፡
3/ ሲኒጂ ካጋዋ /ዶርትሙንድ/
ግጥሚያ፡- 25
አሲስትስ፡- 2
የተዛወረው፡- በ350 ሺህ ዩሮስ ከሴሮዝ ኦስካ
እስከ ሲዝኑ መጋመስ ድረስ ካጋዋ በመላው አውሮፓ እጅግ ተደናቂው የተጨዋች ግዢ ውሳኔ መሆኑ ተመስክሮለታል፡፡ ነገር ግን ለጃፓን ብሔራዊ ቡድን በኤሺያ ካፕ ውድድር ተሳትፎ ሲመለስ በእግሩ ላይ የማታታርሳል ጉዳት ተከስቶበታል፡፡ ይህ ጉዳቱ ጠቅላላውን የሲዝኑ 2ኛው አጋማሽን ከሜዳ ለመራቅ እንዲገደድ ምክንያት ሆኖታል፡፡ ዶርትሙንድ ጃፓናዊው ኢንተርናሽናልን ያስፈረመው በቡድኑ ፕሌይ ኬከርነት ሚና ትክክለኛው ሽፋንን ይሰጣል ብሎ ስላመነበት ነበር፡፡
ነገር ግን በፕሪ ሲዝን የዝግጅት ግጥሚያዎች ከሚጠበቀው በላይ ታላቅ ፐሮፎርማንስን ለማበርከት መቻሉ በአሰልጣኝ የርጌን ክሎፔ ቡድን የመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት እድልን እንዲያገኝ ምክንያት ሆኖታል፡፡ ከዋጋው ከፍተኛ ወሳኝነት ያላቸው ጎሎችን ለዶርትሙንድ ከማስቆጠሩም በላይ ውጤታማ ፓሶችን እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ቦርሺያ ዶርትሙንድ የዘንድሮው ሲዝን የጀርመን ቡንደንስሊጋ ውድድርን የበላይነትን እንዲይዝ ምክንያት ሆኗል፡፡ በቀጣዩ ሲዝንም ለዶትርሙንድ በቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ቁልፍ ሚናን ለማበርከት እንደሚችል ይታመንበታል፡፡
4/ ሞሳ ኮአዋ /ሊል/
ግጥሚያ፡- 39
ጎል፡- 22
ኢስትስ፡- 1
የተዛወረው፡- ከሬኒስ በነፃ ዝውውር የሊል ያለፈው ሲዝን ትልቁ ችግር የማጥቃት እንቅስቃሴን በጠንካራ ሁኔታ የማድረግ ባህል የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሲሉ አሰልጣኝ ሩኒ ጋርሲያ ሞሳ ኮአዋን በነፃ ዝውውር ውል ከሬኒ ክለብ ያስፈረሙበት ተግባራቸው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ፈረንሳዊው የፊት አጥቂ ለሊል ከመፈረሙ በፊት በጠቅላላው የፉትቦል ሕይወቱ ያስቆጠራቸው ጎሎች ብዛት 18 ብቻ መሆናቸው ነው፡፡ ነገር ግን የፈረንሳይ የምስራቅ ጫፍ ለሚገኘው ሊል ክለብ እጅግ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡ ከወዲሁም የ25 ዓመቱ አጥቂ እስካሁን በተደረጉት ግጥሚያዎች 21 የሊግ ጎሎችን ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል፡፡ በእርግጥ በአንዳንድ ግጥሚያዎች ጎል የማስቆጠር ችግር ይታይበታል፡፡ ያም ሆኖ ግን የሊል የአጥቂ መስመር ችግርን በመቅረፍ ቁልፍ አስተዋፅኦ ለማበርከት ችሏል፡፡
5/ ሪካርዶ ካርቫልሆ /ሪያል ማድሪድ/
ግጥሚያ፡- 42
ጎል፡- 2
አሲስትስ፡- 0
የተዛወረው፡- ከቼልሲ በ8 ሚሊዮን ዩሮስ በጆሴ ሞውሪኖ ስር ለፖርቶና ለቼልሲ ሲሰለፍ የቡድናቸው ቁልፍ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዘንድሮው ሲዝን ከመጀመሩ በፊት ከሞውሪኖ ጋር ዳግም ለመገናኘት የቻለው በ8 ሚሊዮን ዩሮ ሂሳብ ከቼልሲ ወደ ሪያል ማድሪድ ዝውውር በማድረግ ነው፡፡ ከዝውውሩ ወዲህም የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ክፍልን በማጠናከር ቁልፍ አስተዋፅኦን በማበርከት ላይነው፡፡ ካርቫልሆ ከዚህ በፊት ያልተረጋጋ አቋም በነበረው በሪያል ማድሪድ የኋላ መስመር ታላቅ ፐርፎርማንስን ማበርከት የጀመረው ከስፓኒሽ ላ ሊጋ የጨዋታ ስታይል ጋር ለመላመድ ያንን ያህል ሰፊ ጊዜ ሳይወስድበት በፍጥነት ነው፡፡ ምንም እንኳን ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ዕድሜው 32 ቢደርስም በአሁኑ ወቅት የያዘው ጥሩ አቋም ግን ለቀጣዮቹ ዓመታትም ሪያል ማድሪድን በትልቅ ደረጃ ለመጥቀም እንደሚችል የሚጠቁም ነው፡፡ የሪያል ማድሪድ የተከላካይ መስመርን የማጠናከር ኃላፊነቱን በአግባቡ ለማከናወን ከመቻሉም ባሻገር በዘንድሮው ሲዝን ሶስት ጎሎችን ለማስቆጠር ችሏል፡፡ ከእነዚህ ጎሎቹ ውስጥ በኦሳሱና ላይ ያስቆጠራት ወሳኝ የማሸነፊያ ጎል ጎልታ ትጠቀስለታለች፡፡
6/ ራውል ጎንዛሌዝ
ግጥሚያ፡- 43
ጎል፡- 19
አሲስት፡- 6
የተዛወረው፡- ከሪያል ማድሪድ በነፃ ዝውውር
የ33 ዓመቱ ስፔናዊ አጥቂ ሪያል ማድሪድን የለቀቀው ባለፈው ሲዝን በበቂ ተሰላፊነት የመጫወት ዕድልን በማጣቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ለሻልካ በተሰፈለባቸው 30 የቡንደስሊጋ ግጥሚያዎች 12 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ እስካሁንም ድረስ ውጤታማ የአጥቂ መስመር ተጨዋች መሆኑን አስመስክሯል፡፡ በተለይም በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አምስት ጎሎችን በስሙ በማስመዝገብ ሻልካ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የውድድር ግማሽ ፍፃሜን እንዲያሳካ ምክንያት ሆኖታል፡፡ በቅርቡ ራውል በሰጠው መግለጫም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የፉትቦል ህይወቱ ባማረ ሁኔታ የተገኘለት የዘንድሮው የውድድር ዘመን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ይህ አባባሉ ራውል ለተጨማሪ ዓመታት የሻልካ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ እንደሚዘልቅ ያረጋገጠ ነው፡፡
7. ኤዲንሰን ካቫኒ /ናፓሊ/
ግጥሚያ፡- 44
ጎል፡- 32
አሲስት፡- 5
የተዛወረው ከፓሌርሞ በመጀመሪያ በውሰት ከዛም በ16 ሚሊዮን ዩሮ
ኡራጉዋዊው አጥቂ በፓሌርሞ ቆይታው ጎሎችን የሚያስቆጥረው በአንዳንድ ግጥሚያዎች ነበር፡፡ ለናፖሊ ከፈረመ ወዲህ ግን ከጣሊያን ሴሪአ ውድድር የተዋጣላቸው ጎል አስቆጣሪዎች አንዱ ለመሆን ችሏል፡፡ እስካሁን ከመረብ ያሳረፋቸው 25 የሴሪአ ጎሎቹ ናፓሊ የዘንድሮውን ሲዝን በስኮዲቶ ድል ለማጠናቀቅ በሚደረገው ፉክክር እንዲገባ በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት ሆኖታል፡፡ ከእነዚህ የሴሪአ ጎሎቹ ውስጥ በሶስት የተለያዩ አጋጣሚዎች ሀትሪክሄሮ የሆነበት ይገኝበታል፡፡ ካቫኒ የሲሲሊ ደሴቱ ክለብ ከ20 ዓመታት በኋላ ለጣሊያን ሴሪአ ሻምፒዮንነት ለመብቃት በሚደረግ ፉክክክር እንዲገባ ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር እስከሲዝኑ አጋማሽ ድረስ ለናፖሊ በዩሮፓ ሊግ ውድድር ሰባት ጎሎችን ለማስቆጠር ችሏል፡፡ ይህ ከወዲሁ ስሙ ከታላላቅ ክለቦች ዝውውር ጋር በመያያዝ ላይ ያለው ካቫኒ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ለመሳተፍ የሚመጥን አስተማማኝ ብቃት እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡
8/ ራፋኤል ቫንደርቫርት /ቶተንሀም/
ግጥሚያ፡- 30
ጎል፡- 12
የተዛወረው፡- ከሪያል ማድሪድ በ8 ሚሊዮን ፓውንድ
ቫንደርቫርት ወርልድ ክላስ ፉትቦለር በመሆኑ በፕሪሲዝን ዝውውውር የመጨረሻው ቀን በቶተንሃም በ8 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ብቻ መገዛቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሆላንዳዊው ስታር ከቶተንሃም ጋር የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ሳይሰራ በፍጥነት ከቡድኑ የጨዋታ ስታይል ጋር ለመላመድ መቻሉ የአሰልጣኝ ሀሪ ሬድናፕ እጅግ ተደናቂ የተጨዋች ግዢ መሆኑን ለማስመስከር ችሏል፡፡ ቶተንሃም የዘንድሮውን ሲዝን 4ኛ ደረጃን በማግኘት ለማጠናቀቅ በሚያደርገው ጥረት ቫንደርቫርት ቁልፍ ተዋናዩ ሆኗል፡፡ ከዚህ ባሻገር በቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ከፍተኛ ወሳኝነት ያላቸው ጎሎችን በማስቆጠር ቶተንሃም በውድድሩ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገው ተሳትፎው እስከ ሩብ ፍፃሜው ድረስ እንዲዘልቅ በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርሰናል በመክፈቻው ጨዋታ ከኒውካስትል ጋር ነጥብ ተጋርቶ ወጣ

/ ሀቪዬር ሄርናንዴዝ /ዩናይትድ/
ግጥሚያ፡- 38
ጎል፡- 18
የተዛወረው፡- ከቺቫስ ጉዋዳላሀራ በ8 ሚሊዮን ፓውንድ
በብዙዎች ዘንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከታዩት ተደናቂ ተጨዋች የመግዛት ተግባሮች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቺቻሪቶን ያስፈረሙት ወደ ፊት ለቡድናቸው ትልቅ ግልጋሎትን ይሰጣል በሚል እምነት ነው፡፡ ነገር ግን ኦልድትራፎርድ በደረሰበት ገና በመጀመሪያው ሲዝኑ በርካታ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር የማንቸስተር ዩናይትድ መደበኛ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ችሏል፡፡ በዚህ በመደሰት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቡድናቸው ኦሎምፒክ ማርሴይን 2ለ1 በረታበት የቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያ ሁለቱንም ጎሎች ያስቆጠረላቸው ቺቻሪቶን ያሞካሹት ‹‹በፕሪ ሲዝን የዝውውር መስኮት ገዝተነዋል ሳይሆን ሰርቀነዋል ማለትን እመርጣለሁ፡፡ ምክንያቱም ቺቻሪቶ ውስጡ በጎሎች የተሞላ ልጅ ነው…›› በማለት ነበር፡፡
10/ ሜሱት ኦዚል /ሪያል ማድሪድ/
ግጥሚያ፡- 45
ጎል፡- 10
አሲስት፡- 18
የተዛወረው፡- ከዌርደር ብሬመን በ15 ሚሊዮን ዩሮስ
ኦዚል በ2010 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ውጤታማ ፉትቦልን ለማበርት ቢችልም በፍጥነት ግን ከሪያል ማድሪድ የጨዋታ ስታይል ጋር በመዋሀድ ታላቅ ፐርፎርማንስን ያበረክታል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አልነበረም፡፡ በዘንድሮው ሲዝን ለሪያል ማድሪድ 10 ጎሎችን ከማስቆጠሩም ባሻገር 18 አሲስቶችን አድርጓል፡፡ ብዙውን ጊዜም የጆሴ ሞውሪኖ ቡድን ተደናቂ ውጤቶች ሲገጥሙት የሚታየው ጀርመናዊው ፕሌይ ሜከር በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ነው፡፡ ለዚህ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን ያስተናገደበት የኤል ክላሲኮ ግጥሚያን 1ለ0 ከመመራት አንሰራርቶ በ1ለ1 ውጤት ለማጠናቀቅ የቻለው ኦዚል ተቀይሮ ከገባ በኋላ የሆነበት ሁኔታን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
ሪያል ማድሪድ የዘንድሮውን ሲዝን በሶስት ውድድሮች የዋንጫ ድል ለማጠናቀቅ እንዲጓጓ ቁልፍ አስተዋፅኦን ካበረከቱለት ተጨዋቾች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ገና የ22 ዓመት ወጣት በመሆኑም ሞውሪኖ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሪያል ማድሪድን በትልቅ ደረጃ ማገልገል የሚቀጥልበት ብቃት እንዳለው አምነውበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Bjorklund men's record shattered in ideal conditions
Share