April 29, 2013
6 mins read

በአዲሱ ሃይማኖቷ “የኦርቶዶክስ እምነትን ስህተት ነው” ያለችው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች

“የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚል አዲስ እምነት እያራመደች ያለችውና ነብዩ ኤልያስ ወደ ምድር እንደመጣ የምታምነው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አዲስ ባቋቋመችው እምነት የተነሳ መታሰሯን ከአዲስ አበባ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ።
በተለያዩ የመድረክ ቴያትሮች፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ድራማዎች በተለይም “ገመና” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ የእናትነት ገፀ – ባህሪን ተላብሳ በመተወን የምትታወቀው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች፡፡ አርቲስቷ ማክሰኞ ማታ ተይዛ አራት ኪሎ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በኋላ ረቡዕ አመሻሽ ላይ ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መዛወሯንና ከእርሷ ጋር ሌላ አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች መታሰራቸውን በስፍራው ተገኝተን አረጋግጠናል ያለው የአዲስ አድማስ ዘገባ አርቲስት ጀማነሽና አብረዋት የታሰሩት ግለሰቦች ሃሙስ እለት አፍንጮ በር መንገድ አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ዘግቧል።

ጋዜጣው ዘገባውን በመቀጠል “አርቲስቷንና አብረዋት የታሰሩትን ሰዎች ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ከመጡ ግለሰቦች ለመረዳት እንደቻልነው፤ አርቲስቷና አብረዋት ያሉት ሰዎች የታሰሩት “ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ” ከተባለው ማህበራቸውና ከሀይማኖት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአርቲስቷ ጋር የታሰሩት አንድ የሃይማኖት አባት፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ፣ አሁን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽን ሊጠይቋት የመጡ ሰዎችን ለማነጋገር ስትወጣ በተመለከትናት ጊዜ በፈገግታ የታጀበች ሲሆን ጠያቂዎቿ “እንዴት ነሽ ተመቸሽ?” ብለው ሲጠይቋት “እግዚአብሔር ያለበት ቦታ ሁሉ ምቹ ነው” ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ አርቲስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ተዋህዶ” በሚል ሃይማኖት ውስጥ ተሣታፊ በመሆን አነጋጋሪ ሆና መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡” ብሏል።

“ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ በተገኘን ጊዜ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚለብሱት የቀስተደመና ቀለማት ያሉት ነጠላ አጣፍታ፣ ፀጉሯንም የቀስተ ደመና ቀለም ዙሪያውን ባቀለመው ሻሽ አስራለች፡፡ ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ “የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚሉትን የተለያዩ ጉባኤዎችን እያዘጋጀ የሚያስተምር ማህበር መሆኑን ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት ገልፀውልናል፡፡ በተለያዩ ገዳማትም የሀይማኖቱ አራማጆች እንደሚገኙና እንደሚያስተምሩ ያገኘናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ነግረውናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ ከመምሪያው የተፃፈ ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል የወረዳው ፖሊስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡” በማለት ዘገባውን አጠናቋል።

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop