አንድነት ፓርቲ በመድረክ ስር ያሉ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ጠየቀ

ላለፉት 5 ወራቶች የመድረክን የስራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት የመድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ ጠየቀ፡፡

ብሔራዊ ም/ቤቱ ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ብሔራዊ ም/ቤቱ በሰየመው ገምጋሚ ኮሚቴ አማካኝነት የመድረክ አጠቃላይ ሁኔታ በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተገምግሞ ሚያዝያ 19/2005 ዓ.ም ለብሔራዊ ም/ቤቱ በግምገማው ሪፖርት ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከጠዋቱ 3፡00 – 1፡00 ሰዓት ስብሰባውን ያካሄደው የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት በዚሁ የግምገማ ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት የመድረክ ጉዞ በውህደት እንዲጠናቀቅ ወስኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የወደቀችበት ሁኔታ በመኖሩ መድረክ ጉዳዩን በጥልቀት ገምግሞ ራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈልገው የለውጥ ደረጃ በማጠናከርን አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተገቢውን እንቅስቃሴ በማድረግ ሕዝቡን በዙሪያው የማሰባሰብ ተግባር እንዲያከናውን የላቀ ጥረት እንዲያደርግ ብሔራዊ ም/ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
አንድነት ፓርቲ መድረክ ሊወስዳቸው የሚገባቸውን የመፍትሔ ሃሳቦች በጥልቀት የተወያዩት የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት የግንባሩ አባል ፓርቲዎች የፕሮግራምና የስትራቴጂ አንድነት በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ በመፍጠር በቀጣዩ ሂደት በአስቸኳይ ወደ ውህደት መምጣት እንዳለባቸው ወስኗል፡፡ መድረክ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውን የፖለቲካ ለውጥ ማሳካት በሚያስችለው ቁመና  እራሱን እንዲያዘጋጅ ለአንድነት ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ብ/ም/ቤቱ መመሪያም ሰጥቷል፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የቀረበው የግምገማ ሪፖርትና በውይይቱ ላይ የተነሱት ተጨማሪ ሃሳቦች የም/ቤቱ ሠነድ ሆኖ እንዲመዘገብ በመወሰን ይኸው ሰነድ ለግንባሩ አባል ድርጅቶችና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን  በመወሰን ብሔራዊ ም/ቤቱ የዕለቱን ስብሰባ አጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  9 የትግራይ ተወላጆች በአሶሳ ተገደሉ

ምንጭ፡  ፍኖተ ነፃነት

2 Comments

  1. The ‘opposition parties’ in Ethiopia have to make a choice. They have to act like opposition and do what they are supposed to do. ACT LIKE AN OPPOSITION PARTY , TALK LIKE AN OPPOSITION PARTY.

    So far most of them are happy to remain ‘LOYAL OPPOSITION” as the woyane would like to call them. The woyane call them ‘LOYAL OPPOSITION’ because the woyane know that these parties are weak, useless, incompetent who roll their heads and lie down as soon as the woyane threatens to lock them up in jail.

    In fairness, people are justified to be frustrated by the behaviour of some of the ‘LOYAL OPPOSITION’. What is the point of calling yourself an opposition if you cannot even hold a party meeting, if you cannot hold meeting with the people who support you, if you cannot hold a mass rally, or a demonstration.

    Some of the LOYAL OPPOSITION do not even protest when women and children, poor farmers are evicted from their villages to make way for arab, indian, chinese and pakistani land grabers who are out to makke a quick buck out of the misery of our people.

    The ‘LOYAL OPPOSITION’ should remove their label of ‘LOYAL’ and be a true and genuine opposition serving the interests of the Ethiopian people.

  2. Here we go again! Another useless meetings. What is wrong with this people? Opposition by definition means, political parties that are opposed the government but they never did that or never will.When woyane told them they can’t hold a demonstration they complain about it and move on, never opposed it. I’m sick of it. “Loyal opposition” well said my friend “titann” They need to learn to say NO. They have to say NO. All these useless people want is woyane to hand them their power like a gift. What a waste! they need to be ashamed of themselves. They need to leave politics alone or start saying NO. They are good ONLY for one thing, NOTHING!

Comments are closed.

Share