አህጉራችን እና እኛ

January 26, 2025

January 26, 2025

ጠገናው ጎሹ

ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ የሚያስቸግር የድህነት/የጉስቁልና ማሳያ ሆኖ በቀጠለው አህጉረ አፍሪካ  ላይ ያተኮሩ  በመፃፍ የታወቀው (አሁን በህይወት የለም) ፕሮፌሰር   George B.N. Ayittey  Africa  Betrayed (እኤአ 1992) በተሰኘው መጽሐፉ  ለዚህ ሁሉ ዋነኛ ምክንያት ከነፃነት  በኋላ በሥልጣነ መንበር ላይ የተፈራረቁና የሚፈራረቁ የራሱ የአህጉሩ ጨቋኝና ሁሉንም እንወስንና እንቆጣጣጠር በሚሉ ገዥዎች  (oppressive native autocrats ) ክህደትና ውድቀት መሆኑን እንደ ሚከተለው ይገልፀዋል።

“The freedom never came to much of Africa after independence. Despite the rhetoric and vituperations against colonialism, very little change in the years immediately following independence. For many countries independence meant only a change in the color of administrations from white to black. The new leaders began to act in the same manner as the colonialists . In fact, in many places they were worse than the colonialists.”

ወደ አማርኛ ሲመለስ፦ ” ከቅኝ ግዛት ነፃ መውጣት (independence) በኋላ ነፃነት (freedom) አፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው ወይም ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ/ሁኔታ ፈፅሞ እውን ሊሆን አልቻለም/እውን አልሆነም ። በቅኝ ገዥዎች ላይ ከሚደረግ ድርጊት አልባ ዲስኩርና ስድብ አዘል ውግዘት ባለፈ የታየው ለውጥ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ለበርካታ አገራት ከቅኝ ግዛት ነፃ መሆን (independence) ማለት አስተዳደሮችን ከነጭ ወደ ጥቁር የሚደረግ የቀለም ለውጥ እንደ ማለት ተደርጎ ተወሰደ። አዲሶቹ መሪዎች ኮሊያኒያሊስቶች በሄዱበት ተመሳሳይ መንገድ ሥራቸውን ማስኬድ ጀመሩ። እንደ እውነቱ ከሆነ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች/አካባቢዎች ከቅኝ ገዥዎችም የባሱ ነበሩ።

የአህጉሩ ህዝብ ከብዙ ዓመታት የቅኝ ግዛት ሰለባነት ነፃ መውጣትን (independence) መልካም የታሪክ ኩነት በቅጡ ለመረዳትና ለማጣጣም ሳይችል በገዛ ወገኖቹ ጨቋኝና ጨካኝ ቀንበር ሥር ወድቆ የእርሱ ያልሆኑትን አያሌ ዘመናት እየቆጠረና እያስቆጠረ መቀጠሉን በመሬት ላይ ከሆነውና እየሆነ ከቀጠለው ግዙፍና መሪር እውነት በላይ ማስረጃ ፈፅሞ የለም።

የአስከፊነቱ ደረጃ ሊለያይ መቻሉ እንደ ተጠበቀ ሆኖ የአህጉረ አፍሪካ ህዝብ ባለው የተፈጥሮና የሰው ሃብት ተጠቅሞ እንደ ሰው ሰው ሆኖ ለመኖር እና እንደ ዜጋ የአገር ባለቤትነት መብትን አጣጥሞ እንዳይኖር የሆነበትን ግዙፍና መሪር እውነት ለሁለንተናዊ የህይወት ጉስቁልናው  ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው ባልተገነቡና እዚህና እዚያ በሚታዩ  የመሠረተ ልማት ማሳያዎች እና ለመግለፅ በሚያስቸግር ሁኔታ በድህነት/በጉስቁልና ታጭቀው እያሉ እንዲብለጨለጩ በተደረጉ ከተሞች እየሸፋፈኑ ከምድረ ሲኦል (ከቅኝ አገዛዝ) ወደ ምድረ ገነት (ድህረ ቅኝ አገዛዝ )  እንዳሸጋገሩት የሚሰብኩት  የገዛ ራሱ ጉዶች (ገዥዎች) ናቸው።

የድህረ ቅኝ አገዛዝ አፍሪካዊ መሪዎች ራስን አግዝፎ የማሳየት እና የማይናወጥ ሥልጣነ መንበር የማንበር እጅግ አስቀያሚ ፍላጎት ያላቸው የመሆኑ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ  ከአጠቃላይ መርህና ከዘላቂ አህጉራዊ ትብብር አንፃር ጊዜውና ሁኔታው በፈቀደው መሠረት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU)  እኤአ በ1963 መመሥረት አሳድሮ የነበረው አፍሪካን ከግዙፍና ሁለንተናዊ ኋላ ቀርነት የማውጣት ተስፋ ቀላል አልነበረም። በተለይ በወገኖቹ መሪነት ነፃነት፣ ፍትህ፣ ሰላም፣ ሥልጣኔና ልማት እውን የሚሆንበት አህጉር ይኖረናል በሚል ተስፋ በነበረው የዋህ ህዝብ ዘንድ። ይህ አይነት የቢሆንና የይሆናል ተስፋ እንኳንስ ትርጉም ባለው ሁኔታ ወደ እውነትነት እመርታ ሊያሳይ አንፃራዊ ነው በሚያሰኝ  ሁኔታም ለውጥ ሳያሳይ ከአራት አሥርተ ዓመታት በኋላ እኤአ በ2002 ከአውሮጳ ህብረት (EU) በተኮረጀ ይዘትና ቅርፅ የአፍሪካ ህብረት (AU) በሚል ስያሜ መጠራት ከጀመረ ይኸውና ከሁለት አሥርተ ዓመታት በላይ ሆነው።

ሃምሳ አምስት አገራትን በአባልነት የያዘው ይህ አህጉራዊ አካል የራሱን ዋና ጽህፈት ቤት (headquarters) በራሱ ማቆም አቅቶት የአህጉሪቱን ውድ የተፈጥሮ ሃብቶች ገደብ በሌለው ማስያዣነት ለቻይና መንግሥትና ኩባንያዎቹ   አስይዞ እና መከረኛውን ህዝብ ለርካሽ ሸቀጦች ማራገፊያነት አሳልፎ ሰጥቶ እንዲያንፁለት ያደረገ የሸፍጠኛ ፖለቲከኞችና አምባገነን መሪዎች ክለብ ሆኖ የቀጠለ አካል ነው። አዎ! በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን በመዋጮ ስም ከመከረኛው ህዝብ በሚሰበስበው ገንዘብ እና አህጉሩን በክለቡ አሻንጉሊትነት አማካኝነት ለመከታተልና ለመቆጣጠር ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል ብለው ከሚያምኑ ለጋሽ መንግሥታትና ድርጅቶች (donnors) በሚገኘው የገንዘብና ሌላም ልገሳ የየራሳቸውን ቅምጥል አኗኗር የሚኖሩ አባላትና ተቀጥላ ተጠቃሚዎች አህጉሩን ለእውነተኛ ነፃነት ያበቁታል ማለት በእጅጉ የተሳሳተ ወይም ከፍፁም ድንቁርና የሚመጣ ወይም ከመሪሩ ሃቅ ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ከንቱ ተስፋ መሆኑን አህጉሩ አሁን የሚገኝበትን ሁለንተናዊ ቀውስና ጉስቁልና 62 ዓመታት (እንደ ኦኤዩ 40 + እንደ ኤዩ 22 =62) በላይ ያስቆጠረውን እድሜ ማነፃፀር በቂ ነው።

በአጠቃላይ እንዲህ አይነቱን ለዘመናት የዘለቀና አሁንም በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን  አህጉራዊ ድርጅትን የአምባገነኖችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው የሸፍጥ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ እና የጥቅም ማጋበሻ አድርጎ  የቀጠለውን የተበላሸና አሳፋሪ መሪር እውነት መጋፈጥ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ሃላፊነት መሆን አለበት። በየአገሩ የገዛ ህዝባቸውን የምድር ላይ ሲኦል ሰለባ ያደረጉና እያደረጉ ያሉ አምባገነኖች (ሥልጣን ከሚያስገኝላቸው ልክ የለሽ ጥቅም ውጭ ሌላ ምንም የማይታያቸው) በክለብ አባልነት ከታደሙበት የድርጅት አውድ የተሻለ ነገር ይገኛል ብሎ ከመጠበቅ የባሰ ትውልዳዊ ቂልነት የለምና በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል።

 

ስለ እኛ በጭሩ  የሚከተለውን ብየ ላብቃ

ለመሆኑ እኛስ የት ነበርን?

አዎ! እኛማ  የውስጥ ስህተቶቻችን፣ ድክመቶቻችንና ፈተናዎቻችን የማይካዱ የታሪካችን አካሎች የመሆናቸው ጉዳይ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፦

Ø  የቅኝ ገዥዎችን  የቅኝ አገዛዝ ወረራ በማይናወጥ የአርበኝነት (የአገር ፍቅር) ተጋድሎ በመመከትና ድል በማድረግ ለአህጉራችን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የነፃነት (የፀረ ቅኝ አገዛዝ) ተጋድሎ ወርቃማ አርአያነትን ያሳየን፤

Ø  ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት (AU) መመሥረት እጅግ ጉሉሁን ሚና የተጫወትን፤

Ø  ከምሥረታውም በኋላ በእውቀትና በሥራ ልምድ የዳበረ ዲፕሎማሲያዊ ማንነት የነበረን ነን።

Ø  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለፀረ አፓርታይድ ትግሉ አስተዋፅኦ ያደረገን ነን።

ከዚያስ?

Ø  ከዚያ በኋላማ ያንን ድንቅ የታሪክ ማንነታችን ወደ ውስጣዊ የነፃነትና የፍትህ ሥርዓተ ፖለቲካ  ለመለወጥ (ለማሸጋገር) የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር  ይቻል ዘንድ በፍፁማዊ የዘውድ አገዛዝ ቤተሰቦችና የቅርብ አጋሮች  ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ባለመቻላችን  ሌላ ምርጫ በማጣቱ ከሁለቱ የዓለም ርእየተ ዓለም ካምፖች ሶሻሊዝምን በመረጠው ያ ትውልድ እና በጠመንጃ የታጀበ የራሱን ሶሻሊዝም ስም መፈንቀለ መንግሥት አካሂዶ የቤተ መንግሥት ፖለቲካውን በተቆጣጠረው ባለ ጠመንጃ ቡድን (ወታደሩ) በተደረገ ትንቅንቅ  አገር በደም እንድትጨቀይ ተደረገ፤

 Ø  ከዚያም እንደ ህዝብ (እንደ ማህበረሰብ) አይወድቁ ውድቀት ከወደቅንበት የ17ቱ ዓመት መከራና ውርደት ከምር ተምረን የተሻለ ሥርዓታዊ ለውጥ እውን ከማድረግ ይልቅ እጅግ መርዘኛና አደገኛ የሆነን የዘር/የጎሳ ደምና አጥንት  ስሌት ፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ለማስመሰል ያህል በታወቁ የዓለም አቀፍ መርሆዎችና ህጎች አሽሞንሙነው ወደ ህገ መንግሥትነት በመለወጥ “የምሥራች” ሲሉን “ምሥር ያብላልን” ብለን በመቀበል ራሳችንን ከቅኝ ግዛት እንዲላቀቁ ከረዳናቸውና አርአያ ከሆናቸው በታች አውርደን ትቢያ ላይ ጎተትነው። እናም ድፍን ሩብ ምዕተ ዓመት ከተከለለልን ክልል (ከተበረተልን በረት) ብንወጣ ምንም አይነት መብት/ነፃነት/ዋስትና የሌለው እንስሳ ሆነን ተገዛን (ተዋረድን)፤

Ø  ከዛሬ ስድስት ዓመታት በፊት ተመልሰን አይወድቁ ውድቀት የወደቅንበትንና ኦሆዴዶች/ኦነጎች የፈጣሪያቸውንና የአሳዳጊያቸውን የህወሃትን የበላይ ጠርናፊነት በስሜት በተነዳ ህዝባዊ ተቃውሞ አስወግደው ሥርዓቱን ግን  እንኳንስ ለማመን ለማሰብም በሚከብድ ሸፍጥና ጭካኔ ያስቀጠሉበትን “ተሃድሶ” “የአብይ አህመድ መሴነት የወለደው” ብለን የተቀበልንበትን እኛነት ከምር ለታዘበ የአገሬ ሰው የውድቀታችን አስከፊነትና አሳፋሪነት የሚገልፁ ቃላት የሚያገኝለት አይመስለኝም። እናም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የዘለቅንበት ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት መሪር ትምህርት (ተሞክሮ) አልበቃን ብሎ ሌላ የግማሽ ምዕተ ዓመት መከራና ሰቆቃ (የመቃብር ሥር እና የቁም ሞትን) በመለማመድ ላይ ያለን ይመስላል ማለት መሪሩን ሃቅ ተጋፍጠን ፍቱን መፍትሄ እንድፈልግ የሚያደርገን እንጅ ማጋነን አይመስለኝም።

 

ለመሆኑ አሁንስ የት ነን?

Ø  አሁን ያለንበት ሁኔታ እንኳንስ በእንደኛ አይነት እጅግ ዘመን ጠገብና ውስብስብ በሆነ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሞራላዊና ሃይማኖታዊ ሁኔታ ውስጥ በአንፃራዊነት የተሻለ ነው በሚባል አገር (ሁኔታ) ውስጥም ፈታኝ ሁኔታዎች የመኖራቸው ጉዳይ እንደ ተጠበቀ ሆኖ እጅግ እልህ አስጨራሽ ከሆነ ትእግስት በኋላ በቃ በማለት ህልውና፣ ነፃነት፣ ፍትህ፣ ሰላምና የጋራ እድገት የሚረጋገጥበትን አገር በጋራ እውን ለማድረግ አልሞ የተነሳው የፋኖ ተጋድሎ  ከሌሎች ወገኖች ጋር በሚያደርገው ምክክርና ቅንጅት ከተመራ ወደ ታሪካዊ ለውጥ የሚወስደውን ጉዞ ማሳጠር እንደሚቻል እያየንና እየሰማን ያለንበት እውነታ ነው።

Ø  እንደ ህዝብ (እንደ ማህበረሰብ) መመለሻና ማገገሚያ ከሌለው የውድቀት አዙሪት (ቅርቃር) ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መዳንና የመከራና የውርደት ፖለቲካ ሥርዓትን ያለፈ ታሪክ ማድረግ ካለብን ብቸኛው መውጫ መንገድ ይኸውና ይኸው ብቻ ነውና ከምር ሊያሳስበን ይገባል።

Ø  ለዚህ እውን መሆን ደግሞ ቀደም ሲል በከፈሉት ዋጋ እየታበዩ አሁን ላይ ያለውን እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ (ተጋድሎ) ተመካክሮና ስህተትን አርሞ በአንድነት የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከማድረግ ይልቅ ግዙፍና መሪር መስዋእትነት በመክፈል ላይ ከሚገኙት ወገኖች ጀርባ ከገዳይ፣ አስገዳይና አገዳዳይ ጋር እና ለህዝብ ዘላቂ ሰላም ሳይሆን በለመዱት የሸፍጥና የሴራ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ የገዥውን ቡድን እድሜ ከሚያራዝሙት እንድ ኢጋድ ተብየ (ወርቅነ ገበየሁ)፣  የአፍሪካ ህብረት እና ለአምባገነኖች ነፍስ አድን እርዳታ ለጋሽ ከሆኑ አካላት ጋር በሰላም ስም የክንፍ አልባ መላእክትነት የሥልጣን ጥማቸውን ለማርካት የሚሞዳሞዱትን ከምር በቃችሁ ማለት የግድ ነው። ከፈልነው የሚሉትን ውድ ዋጋ አሁን በሚያደርጉት የሸፍጥና የሴራ ፖለቲካ አቋምና ቁመና ምክንያት በዜሮ እያባዙ ዋጋ ከፍለናልና አይደፈሬዎች ነን ማለት ፈፅሞ ስሜት አይሰጥም። የነበረ መልካም እሴት በመልካምነቱ ሲቀጥል እንጅ በየፈርማታው እንደ እስስት ከተለዋወጠና ከተንጠባጠበ  የበጎ ሰውነት ዋስትና ሆኖ ሊቀጥል ፈፅሞ አይቻለውም።

Ø  በሌላ በኩል ከእነዚህ ወገኖች የሸፍጥና የሴራ ባህሪና ተግባር በተቃራኒ የቆሙትም ከጋግርታሙ የፖለቲካ ባህላችን የሚመነጩ አጉል መታበዮችና ልክ የሌለው የግል ዝና እና ጥቅም ፈላጊነት ሰለባ የሆኑ ወይም ለመሆን የሚዳዳቸው  ካሉ ተገቢና ገንቢ በሆነ ሂሳና ግለ ሂስ እንዲያርሙ እና እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ንፁሃን ቤተሰቦቻቸውና  ወገኖቻቸው የከፈሉትንና እየከፈሉት ያሉትን መስዋእትነት ለፍሬ እንዲያበቁ ሊነገራቸው ይገባል።

ስለሆነም ስለ ዘመን ጠገቡና በእጅጉ ስለተበላሸው የፖለቲካ እኛነታች እንዲህ በግልፅና በቀጥታ እየተነጋገር የጊዜንና የአቅምን ወሳኝነት መሠረት ባደረገ ሁኔታ የማያዳግም መፍትሄ ካላበጀንለት አሟሟታችንም ሆነ ለቅሷችን (ሃዘናችን) ፈፅሞ ትርጉም የማይሰጥ ሆኖ ይቀጥላል። እናም ልብ ያለው ልብ ይበል!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop