ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል።
የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ አልያም በአሜሪካ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
መንግስት በዋናነት በእስክንድር ከሚመራው የፋኖ ክንፍ ጋር በቅርቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ እንደተወያየ እስክንድር ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልፆ ነበር። አክሎም በድርድሩ ላይ የኢጋድ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች መገኘታቸውን ገልፆ ነበር።
በውይይቱ ላይ በፋኖ ክንፉ በኩል የተነሱ ነጥቦች መከላከያ አካባቢውን በግዜያዊነትም ቢሆን ለቆ መውጣት፣ ክልሉን ማስተዳደር፣ በፌደራል መንግስቱ በስልጣን መወከል፣ የድሮን ጥቃት ማቆም፣ ለተጎዳው ህዝብ ለህይወት ሳይቀር ካሳ መክፈል እና የመሳሰሉት ናቸው ተብሏል።
በመንግስት በኩል ደግሞ ትጥቅ በመፍታት ወደ ማሰልጠኛ መግባት፣ ጎጃም አካባቢ ላይ ያለውን ነገር ማስተካከል፣ በየከተማው ያለውን አደረጃጀት መረጃ መቀበል፣ ተጠያቂ የሚሆኑ አባላቱን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም በምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ መካተት ናቸው ተብሏል።
“በመንግስት ዝግ ስብሰባ ላይ ሲያጨቃጭቅ የነበረው የነእስክንድር ክንፍ አቅም ጉዳይ ሲሆን ግምገማውም በሀገር ውስጥና በውጭ ተቀባይነትን ለማግኘት መነጋገሩ እንደ አማራጭ ተወስዷል” ያሉን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጫችን ሸዋ ላይ ድርጅቱ የተሻለ አቅም እንዳለው፣ ነገር ግን ጎጃም ላይ የለም የሚባል ደረጃ ላይ እንደደረሰ መረጃ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል ብለዋል።
“ቢያንስ ሸዋን ማቃለሉ እንደ ጥሩ እድል በመታየቱ እና የድርድር ዝርዝር መረጃም የሚቀበሉ አለም አቀፍ ተቋማትም በመንግስት የንግግሩ ቦታ ስለተጓጓዙ ውይይቱ ተደርጓል” በማለት ሂደቱን አስረድተዋል።
“ነገር ግን አሳሳቢው ጉዳይ አሁንም ልክ እንደነ ጃል ሰኒ እንዳይሆን ነው፣ ሙሉ ሰላም ለማምጣት የተወሰነ ቡድን ሳይሆን ሁሉንም አካታች መሆን አለበት” ያሉን ደግሞ በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት የሰጡን ተንታኝ ናቸው።
“መንግስት ነገሮችን ያቀሉልኛል ብሎ እየሄደበት ያለው ይህ ነው። ሁሉም ወደ ንግግሩ መግባት አለበት፣ አልያ እንደ ኦሮምያ አይነት ሁኔታ ይፈጠራል፣ ይባስ ብሎም በቀረው ፋኖ ታጣቂ እና በመንግስት መካከል የሚኖረው ሁኔታ ይባስ ሊካረር ይችላል” በማለት ለሚድያችን ተናግረዋል።
ምንጭ :- መሠረት ሚዲያ
“እነ እስክንድር ውይይት አደረጉ እንጂ አልተደራደሩም፣ ለምን ነገሮችን ጠምዝዛችሁ ታቀርባላችሁ” የምትሉ ወገኖች አላችሁ፡፡
ይህ ውይይት የተባለው፣ የተደረገው ፣ በሰሜን ወሎ ዳዎንት ነው፡፡ በብልጽግና እውቅና፣ ትብብርና ድጋፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል፣ አንድ ጊዜ አብይ፣ ሌላ ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን አራያም ከአንዳንድ የፋኖ አመራሮች ጋር እየተነጋገርን ነው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡ የውጭ ድርጅቶች ዳዎንት የመጡት ድርድር ለማስጀመር ነው፡፡ ስለዚህ ውይይት እንጂ ድርድር አልተደረገም፣ ከብልጽግና ጋር ምንን ንክኪ የለንም ማለት አይቻልም፡፡
በነገራችን ላይ እዚህ ጋር አንድ ትልቅ ነገር ላስቀምጥ፡፡ ይህ ራሱን የአፋህድ ብሎ የሚጠራው ስብስብ ፡
# 0% የጎጃም ፋኖዎችን ያቀፈ ነው፡፡ (መቼም እነ ማስረሻስ ብላችሁ እንደማታስቁኝ ነው)
# የጎንደር ፋኖዎች 90% የሚሆኑትን የሚሸፍነው፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደርን ያቀፈ አይደለም፡፡ እንደውም ይህ ቁጥር በቅርቡ ወደ 95% ከፍ ሊልም ይችላል፡፡
# በወሎ 95% የሚሆኑ የወሎ ፋኖዎች የታቀፉት በአማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አማራ ውስጥ ነው፡፡ በኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ ስር ወደ 5% የሚሆኑ አሉ፡፡ እነርሱም ቢሆኑ፣ ኮሎኔሉ ከአፋህድ ካልወጡ፣ “እኛ የወሎ ፋኖ እንጂ የእስክንድር ነጋ ፋኖ አይደለንም፡ ብለው ወደ አማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አማራ አደረጃጀት ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡ ያ ማለት ኮሎኔሉ ከአስር የማይበልጡ ታጣቂዎች ጋር ሆነው ብቻቸውን ይቀራሉ ማለት ነው፡፡ ከ95% ወደ 100% የወሎ ፋኖ አንድነት ይረጋገጣል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አፋህድ በጎጃም፣ በወሎና በጎንደር ምንም አይነት ድጋፍ የሌለው ነው ማለት ነው፡፡ እስክንድር ነጋ 90፣ 80% ድጋፍ አለን ያለው የለየለት ቅጥፈትና ውሸት ነው፡፡ በዚህ ልክ መዋሸት ለምን እንዳስፈለገው አይገባኝም፡፡
# ወደ ሸዋ ስንመጣ ትንሽ የተለየ ነገር ነው ያለው፡፡ በሸዋ ሁለት እዞች አሉ፡፡ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ በአፋህድ ስር ነው ያለው፡፡ ስለዚህ እስክንድር ነጋ ግማሹ የሸዋ ፋኖ ይደግፈኛል ብሎ ቢናገር ተሳሳተ ማለት አይቻልም፡፡
ሌላው እስክንድር በተለይም ዳዎንት ውይይት/ድርድር ሲያደርግ፣ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ስራ አስፈጻሚ አልተወያየበትም፡፡
ሆኖም ግን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ ታች ባሉ አመራሮችና ፋኖዎች ዘንድ፣ “እኛ የሸዋ ፋኖዎች እንጂ የእስክንድር ፋኖዎች አይደለንም” በሚል በእዙ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ውስጥ ውስጡን እየቀረበ ነው፡፡ ሻለቃ መከታው ማሞ ጥሩ መሪ ስለሆነ፣ ጦሩም ለርሱ አክብሮት ስላለው፣ “ትንሽ ጊዜ ስጡኝ፣ እናስተካከላን” ስላላቸው ነው ነገሮች አሁን ድረስ በእንጥልጥል ያሉት፡፡ እንደዚያም ሆኖ ደራ የሚንቀሳቀሰው የአሳምነው ብርጌድ፣ የ7ለ70 ክፍለ ጦር፣ የሚኒሊክ ክ/ር በይፋ አፋህድን እንደማይቀበሉ አሳውቀዋል፡፡ ሌሎችም መከታው ችግሮችን ይፈታል በሚል ትንሽ ጊዜ እንስጠው ብለው ነው እየጠበቁ ያሉት፡፡
ስለዚህ ምንም እንኳን የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ በይፋ ከአፋህድ ያልወጣ ቢሆንም፣ በእዙ ያሉ ፋኖዎች 90% የሚሆኑት ግን ይህን ሸዋ አንድ እንዳይሆን እንቅፋት የሆነ፣ የሸዋን መከራን ያስረዘመ ድርጅትን ማየት አይፈልጉም፡፡ የሚያከብሩት መሪያቸውም፣ መከታው ማሞም፣ የሻለቃ ሃብቴን ፈለግ ተከትሎ መስመሩን እንዲያስተካከል ፍላጎት አላቸው፡፡ ያንንም ነው እየጠየቁት ያሉት፡፡ ባለኝ መረጃ በአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ውስጥም በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ ያሉ ፋኖዎች፣ አንደኛ ቅድሚያ የሚሰጡት ነገር ፣ የሸዋ ፋኖዎች እንደ ጎጃም፣ አሁን ወሎና ጎንደር እንደሆነው፣ አንድ እንሁን የሚል ነው፡፡
ሻለቃ መከታው በስሩ ያለው ጦር ፍላጎትና ጥያቄ የማያከበር ከሆነ፣ የሸዋ አንድነት እንዲመጣ ቅድሜያ ሰጥቶ የማይሰራ ከሆነ፣ በተለይም ደግሞ ከብልጽግና ጋር እነ እስክንድር እያደረጉት ያለው ውይይት የሚሉት ድርድር ፣ እርሱም ሆነ የሚመራው እዝ እንደሌለበት የማያሳውቅ ከሆነ፣ ተቀባይነቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያሽቆለቁል ማወቅ አለበት፡፡
ግርማ ካሳ እናመሰግናለን ዘመድኩን እንዳይስማን እንጅ፡፡
ይሄ እስክንድር ማለት ቀላል ሰው አይደለም ፡፡ሆድ አደር ጋዜጠኛ ባዮችን ያዘ፡ ኤርምያስ ዋቅጅራን ያዘ፡ በባዶ እግሩ ፎቶ ተነሳ፤ ባልደራስን በተነ አሁን በወያኔ ፕላትፎርም ገብቶ ኢትዮጵያን ሊበትን ነው፡፡ ሰውየው በእርግጥ አላማው ትግል ቢሆን አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ መታገል በተገባው ነበር ለነ ሃብታሙ አያሌው የሚኒስትርነት ሹመትን ለመስጠት አስጎምጅቶ በማያውቀው ነገርና ቦታ ችግር ባልፈጠረ ነበር፡፡ የምትከተሉት ሰዎች በሰላም ወደ አዲስ አበባ ሸኙት መንግስትም የበለጠ ሞላን ቦታ ይስጠው እኛም እረፍት እናግኝበት፡፡