January 20, 2025
22 mins read

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

the lawless land of east africaመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። 

  — መክብብ 75

እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ እንደሚመጣ ማስተዋልስ ለምን ተሳነን  ? ኧረ እባካችሁ ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለምን አንማርም ? ክብሩን  ሰው በረሮ  ( cockroach )  ብሎ በመበየን ፣ሰው ፣ ሰውን በጅምላ ፣ በጭካኔ   መጨፍጨፉን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኢሊቶች  እንዴት በአጭር ዓመታት እንዴት  ዘነጉት   ? ( “ ቱሲዎች “  “ ለሁቱ “ ጎሣ  በረሮ ነበሩ ። በዛን ወቅት ሁቱዎች   800 ሺ ንፁሐን  ቱሲዎችን  ጨፍጭፈዋል ።  )

እኛስ ፣ ኢትዮጵያውያን  ከዘመን በኋላ በሰው የተፈጠረው የጎሣ እና የዘውግ አጠራር ለምን ሰውነታችንን ያጠፋብናል ? ሰው መሆናችንን ይሰርዘዋል ? ለምን ከተሳሳተ የታሪክ ትርክት  በዘመኑ ንቃተ ህሊና ዝቅተኝነት የተነሳ ከተፈጠረ ቆዳ መዋደድ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ተሳነን ? ለምን ይሆን በሚገርም መልኩ ዛሬም በአስተሳሰብ ደረጃ ፣  አመድ በዱቄት ሲስቅ ጀንበር የሚጠልቀው  ?  በተግባር ውሃ ጠብ አድርገን ብንፈትሸው እኮ የአመድ ከንቱነት የዱቄት ምግብነት ይገለጽልናል ።

እውነቱ ይኽ ይሁን እንጂ ፣ በአስተሳሰብ ደረጃ ፣ ዛሬም በአገራችን አመድ በዱቄት መሳቁን ለማቆም አልቻለም ? ከቶስ አመድ በዱቄት መሳቅ አለበት ወይ ? ዱቄት እኮ ምግብ ይሆናል ። ሰውነት ያደረጃል ። እምብዛም ጥቅም የማይሰጠው አመድ ዱቄትን በመምሰሉ ብቻ  እንዴት ህይወት ያለውን የዱቄት ተግባር ሊሳለቅበት ቻለ ?   እንዴት ፈርሃ እግዚአብሔር ያለውን ጠቃሚ አስተሳሰብ እና አመለካከት   ከልቦናችን ለማስረፅስ ብዙዎቻችን  አቃተን ? ዛሬ እየተጎዝንበት ያለው ሰው መሆናችንን የመርሳት እና የመገዳደል አባዜስ  እየበረታ ፣ እየጎለበተ እና እያየለ የመጣው ጥቂት የማንባለው “ በአስተሳሰብና በአመለካከት ደረጃ “ አመድ “ ሆነን ሣለ ጠቢብ በሆኑት ፣ አገርን ወደ ብልፅግና የሚወስድ አስተሳሰብና አመለካከት ባላቸው ጠቢባኖቻችን ( ልሂቃን ) መዘበታችንን በመቀጠላችን  አይደለምን  ?

ይህ ሁሉ ስደት ፣ መፈናቀል ፣ መጠላላት ፣ እርስ በራስ  መገዳደል በዚህ ዘመን አይሎ የታየው ፣ ሁሉንም መልካም ነገር ፣ ሁሉንም የዕድገት ጉዞ ፣ በጥላቻ ጠንሳሾቹ  ፤ የአይጠረቄነት መንፈስ በተጠናወታቸው ፣ የነዋይ ፍቅርም ባሰከራቸው ፣ የግብዝነት አስተሳሰብ በህሊናቸው በገዘፈ  የአገር ልጆች እና  ለጥቅማቸው ብቻ በቆሙ የፈረጠመ ጡንቻ ባላቸው የውጪ ኃይሎችና እንዲሁም  ህሊናቸውን በሸጡ በግራና ቀኝ ባሉ ምናገበኝ ባይ ፖለቲከኞቻችን እና ልሂቃኖቻችን ተባባሪነት አይደለም እንዴ ? ይኸው ዛሬም ከዕድገትና ብልፅግና አንፀር ፣ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ እየተጓዝን ያለነው ፣ “ ከራስ በላይ ነፋስ “ የሚል መርህን ስለምንከተል አይደለምን ? ኩንን ከሆነው “ አመድ በዱቄት የመሳቅ  አባዜ ያልተላቀቅነውስ ቆም ብለን “ እኔ በፍጥረት ማን ነኝ ? “ ብለን መጠየቅ ተስኖንን አይደለም እንዴ ?

ይኽ ኩንን አመድ በዱቄት ላይ የመሳቅ ተግባራዊ ሂደትስ   ከ33 ዓመት በፊት አይደለም እንዴ በረቀቀ ሤራ የህገመንግስት ሽፋን ተሰጥቶ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ? (የአውሮፓ ሀብታም መንግስታት ፣ አሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ቻይና   እና ኤሜሪት …  ለምን ወደብ ይገዛሉ ? አሜሪካስ ከናዳን እና የፓናማ ግዛት ለመጠቅለል ለምን ፈለገች ? ሩሲያስ ለምን ዩክሬንን ወረረች ? ለየአገራቸው ጥቅም አይደለምን ? )

በአፍሪካ እና በእኛ አገር ግን አገራቸውን ለመጥቀም ባላቸው ዕውቀት እና ተሰጥኦ  በብርቱ እየተጉ ፣ ያለመታከት  በጎ ምክር እና ተግፀስን የሚለግሱን እና   ሲለግሱን የነበሩትን ሊቃውንቶች መቼ ሰማናቸው ? ቆም ብለን ብናስተውል ከ30  ዓመት በፊት የታተሙ መፅሐፍት ፣ መፅሔቶችና ጋዜጦች ሰው ጠል አመለካከትና አስተሳሰብ መጨረሻው ውድመትና ዕልቂት መሆኑንን አስጠንቅቀውን ነበር እኮ ። ሲቀጥል አራተኛው መንግስት ፕሬስስ ዛሬ የት ነው ያለው ? ብሎ መጠየቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ።

አራተኛው መንግስት ( ከህግ  አውጪው ፣ ከህግ ተርጓሚው እና ከህግ አስፈፃሚው ቀጥሎ ፕሬስ ቀና  ምክር ፣ ሂስ እና ተግፃስን በማቅረብ ፣ መንግስትን አጋዥ የሆነው ፣ አራተኛው ወሳኝ የመንግስት አካል ይባላል ። ) ኢህአዴግ ሥልጣንን በያዘ ማግስት እጅግ ገኖ እንደነበር እናስታውሳለን ።  ህትመታቸው አነስተኛ ቢሆንም   ፣ የወቅቱን ሶሾ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የሚዘግቡና የሚተቹ የተለያዩ  ጋዜጦቸ ና መፅሔቶች በየቀኑ ፣ በየወሩ እና በየሳምንቱ ለአንባቢ ይቀርቡ ነበር ። ያለፈውን የሆነ ሰገነት  ዘመን ዞር   ብሎ መቃኘት ጠቃሚ ነው ። በዛን ዘመን የተፃፉትን ፣ በሳል ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚየዊ እና ማህበራዊ ይዘት ያላቸውን  ፅሑፎች መልሶ በማንበብ ፣ ቆም ብሎ በማስተዋል ለሀገር ታላቅነት መስራት የሚበጅ ይመስለኛል  ።

በአናቱም ፣ ህሊናችንን ፈፅሞ ከማይገነባ ከከንቱ ውዳሴ ይልቅ ፣ የጠቢባንን ተግፀስ መስማት ከግብዝነት ለመፅዳትና ህይወትን በማስተዋል ለመምራት እንደሚጠቅምም እንገንዘብ ።  ተገንዝበንም በማስተዋል  በተሰማራንበት የሥራ መስክ እና የኃላፊነት ቦታ  ብቻ ሳይሆን ለአገር ብልፅግና  የምንችለውን  ሁሉ  መሰዋት እንክፈል  ። ሁሉም ዜጋ በሰውነት እኩል መሆኑን ተገንዝቦ  በከንቱ  ውዳሴ ሳይፈነድቅ ፣ ገንቢ ተግፃስን እና ትችትን በጆሮው አዳምጦ ፣ አንብቦና ተመልክቶ እራሱን በመውቀስ በቀና ጎዳና ሲጎዝ አገር ልትበለፅግ ትችላለች ። ብዬ አምናለሁ ።

ጎበዝ ፣ እያንዳንዳችን ሰዎች ነን ። በአገር ደረጃ ደግሞ ዜጎች እንባላለን ። በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዳችን  ፣ የጠቢባንን ተግፃስ ሰምተን  እራሳችንን እንደምንወቅስ ሁሉ መንግስትም ትችት ፣ ወቀሳና ተግፃስን የማዳመጥ ከባድ ኃላፊነት እንዳለበት እና ይህንንም ኃላፊነት የሰጠው የመረጠው ይኸው  የሚተቸው ህዝብ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ። ለዚህም ነው መንግሥት ገንቢ ትችቶችን አዳምጦ ፣ “ ዜጎች ጠንክረን እንድንሰራ   የሚያሰራ ፖሊሲና የፖለቲካ መንገድ በተጠና መልኩ መቀየስ  ፤ በተግባር ላይ የዋሉትንም በድጋሚ መመርመር ና ማሻሻል  ይገባዋል    ። “  የሚባለው ።

አዲስ ፣ ጠቃሚና ሁሉንም ዜጋ አሳታፊ ፖሊሲዎች ፣ በወጉ ተመርምረው  በተግባር ላይ ከዋሉ እና የፖለቲካ ምህዳሩና የመጫዎቻ ህጉ እና የተሳታፊዎች   መድረክ ግልፅ ፣ ፍትሐዊ እና ጠልፎ መጣል ከሌለበት ፤  እኛም ዜጎች ፣ ዘወትር ጠንክረን እየሰራን ጎን ለጎን ሳንታክት እንደሃይማኖታችን ለፈጣሪ በመፀለይ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ያለአንዳች ሥጋት ኑሯችንን ለመለወጥ   ጠብ እርግፍ በማለት ለአገር ልማት የበኩላችንን አስተዋፆ ለማድረግ እንችላለን ። …

ሁላችሁም እንደምታስተውሉት   ፣ ዛሬ እና አሁን   ገሮች እየከፉ መጥተዋል ። በዓለም ዙሪያ የሚታየው ነገር ሁሉ አስፈሪ ነው ። አስደንጋጭ ነው ። በሽታ በዝቷል ። ቸነፈር በዝቷል ። ረሐብ በዝቷል ። ጦርነት በዝቷል ። በዛው መጠን ደግሞ አስረሽ ምችው  በዝቷል ። ሰማይን በርግጫ የሚል ደልቃቄም ቁጥሩ ትንሽ አይባልም ። … ሰማይን በርግጫ ካላልኩ በሚለው፣ በፈጣሪ በተፈጠረው ሰው እኩይ እና ዘግናኝ ድርጊት ዓለም   ዘወትር ትገረማለች ። እኩይ ድርጊቱ ሲገዝፍም ምድሪቱ ደም ታነባለች ። የሰው መጨካከን ምድሪቱን በሰው ደም እያጨቀያት ነው ። ነገሩ በማስተዋል ለተመለከተ  ይዘገንናል ። አንዳንዴ ሳስበው ሰው የመጨረሻ ጅል ነው እንዴ ? እላለሁ ። ለዚች ሰባ ዓመት  ለማትሞላ የምድር ቆይታው በፍቅር ከመ ኖሮ ይልቅ  መገዳደልን መመረጡ ፤ ጥላቻን ገንዘቡ ማድረጉን እና አመድ በዱቄት እየሳቀ ጀንበሯ መጥለቋን  ሳስተውል   በሰው ሞኝነት በአያሌው  እደመማለሁ  ። ( ልብ አድርጉልኝ ከሰው ተርታ ሁላችንም አለን ። )

በመገረምም “ ሰው ጅል ነው ። ሲሞት አስከሬን ሲሆን ነው ጅልነቱን የነገ ሟቾቹ የሚረደቱ ። ሰውን ሞቶ ስትመለከቱት ብቻ ነው ፣ ‘ ለካ ሰው እንዲህ ጅል ነው ። ‘  የምትሉት ። ምንም እንኳን  ራሳችሁን እንደንጉስ የምታዩ ብትሆኑ  ፤ በህይወት ሳላችሁ ፣  ቁጡ ፣ ሀይለኛ ፣ አትኩኝ  ባይ ወዘተ ። ብትሆኑም ፤ ስትሞቱ ፣ ምንም ማድረግ የማትችሉ ፣ በድን ስለምትሆን የመጨረሻ ጅል ሆናችሁ  ለተራ ሟቹ የምትታዩት  ።

“ ይህንን የምትረዱት ዛሬ በህይወት ሳላችሁ ማስተዋልን ገንዘብ ስታረጉት እና የጠቢባንን ተግፃስ  ሥትሰሙ ብቻ ነው ።

“ የጠቢባንን ተግፃስ ሰምታችሁ ፣ ማስተዋልን ገንዘብ ካደረጋችሁት  ፣  ሰው ሲወለድ ሞት አብሮት እንዳለ ትገነዘባላችሁ ። ይሁን እንጂ እስከዛሬ በህይወት ያለ ሰው ሁሉ  የሚሞተው ሞቶ ያየው ሰው ብቻ  ይመስለዋል  ።  በዚህ  ጅል  ዕውቀት የተነሳም ፣  ሰው  ፣  አምሳያውን ሰው  በጅምላ ለማጥፋት  የሚችልበትን መሳሪያ ዘወትር  መፈልሰፉን እንሆ ቀጥሏል ።

“ በአውዳሚ ጦር መሳሪያ ረገድ ፣ ዛሬ ፣ ዛሬ ኃያላኑ ሀገራት አንድን ከተማ ለይቶ እንዳልነበረ የሚያደርግ አውቶሚክ ቦንብ ወይም የኒኩለር ሚሳኤል አላቸው ። በፈለሰፉት ጅምላ ጨራሽ የጦር እና የባዮሎጂ ገዳይ መሳሪያዎችም   ዛሬ  መፈራታቸው ከወትሮ ይልቅ ዛሬ በእጅጉ  አስደንጋጭ ሆኖ እናገኘዋለን ። “ እናም ለጥቅማቸው ሲሉ የትኛውንም የማደግ ፍላጎት ያለውን አገር እንዳያድግ የዕድገት መንገዱን መዝጋት ይችላሉ ። በእጅ ጥምዘዛም ” እስከምድር ፍፃሚ ይበዘብዙታል ።” እያስተዋልን ያለነውም ይህንኑ እውነት  ነው ።

“ እያስተዋልን ያለነው ብዙኃኑ የማደግ ፍላጎት ያለው ሀገር ፣ በተለይም “የመብልፅግ  ጥማቱ ከፍተኛ የሆነው መላው አፍሪካ   ” እስከዛሬ    እንኳን ሊበለፅግ  ፣ በእነሱ ምፅዋት ድጋፍ ይኸው ወደ ሦስተኛው ሚሊኒየም እየገሰገሰ ነው ። “ በማለት እብከነከናለሁ ።

የአፍሪካ ሊሂቃን እና የዓለም አሳቢያን እንደሚመሰክሩት ፣ አፍሪካዊው  በምፅዋት የሚኖረውም ከበቂ በላይ የሚታረስ ለም መሬት እያለው ነው ። ይኽንን ለም  መሬትም የእንስሳት  ፣ የእፅዋት  ፓርክ እና የማዕድን አካባቢ  በማለት ፣ ለብዝበዛ እንዲያመቻቸው “ወፍ ዝር የማይልበት  ጥብቅ አካባቢ ” ብለው  በህግ ና በመሳሪያ  የሚያስጠብቁት ። በዚህ ረቂቅ  ድርጊታቸውም አፍሪካዊያንን በረሃብ እና በችጋር  ይቀጣሉ ። በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ ታጥረው የተቀመጡ  ጥበቅ ሥፍራዎቹ  እጅግ ለም ናቸው  ። በኢትዮጵያ እንኳን በሁሉም ክልሎች ጥብቅ ሥፍራዎች የበዙ ናቸው ። የአገርን ኢኮኖሚ  በፓርክነታቸው ፣ በዕፅዋት ሥፍራነታቸው  ከድህነት እያላቀቁ  ግን አይደለም  ።

በነገራችን ላይ ለዕፅዋት የተከለሉትን ሰፋፊ መሬቶችን አጥሮ ከማስቀመጥ ፣ ጎን ፣ ለጎን ፍራፍሬዎችን በማልማት የአገርን ኢኮኖሚ በጥቂቱ እንኳን መገንባት  ይቻል ነበር ። ኢትዮጵያ በሜዳማ አካባቢዎች ፣ እጅግ ለም በሆኑ ሰፊ ለም መሬቶች ያውም ወንዞች በውስጧ  እየፈሰሱ    በሰፋፊ መሬቶቿ  ላይ ለአገር ጠቃሚ በሆኑ የግብርና ዘርፎች መሰማራት አዋጪ ሆኖ ሆና ብታገኘውም   የተከለከሉ ጥብቅ ሥፍራዎች በመሆናቸው  ሰበብ በምግብ ሰብል ራሷን ለመቻል አዳግቷታል ። ።

በአገራችን ላይ ፣ በገዛ አገራችን  ከስንዴ ልመና የሚያወጣንን መንገድ ወይም  ፖሊሲ መቀየስ ለምን አቃተን ?  የተሻለ ጥቅም የሚሰጠውን እና ከተረጂነት የሚያወጣንን የእርሻ እና የእርሻ መሬት ፖሊስ በማውጣት በለሀብቶች በዚህ አዋጪ ሥራ እንዲሰማሩ በማድረግ የምግብ ፍላጎታችንን  ሙሉ ለሙሉ ለማሞላት ለምን ተሳን ? በነገራችን ላይ ፣በከርሰ ምድር ውሃችን ላይስ ለምን የተለየ ፖሊሲ አልተጠቀምንም ? ከከርሰ ምድር ውሃ በማውጣት የሚጠቀም ሁሉ የከርሰ ምድር ውሃ ተጠቃሚነት ግብር ለምን አይከፍልም ? በከርሰ ምድሩ ” የአገር ውሃ ” አምርቶ እየተጠቀመ አይደለምን ? የውሃ አቅራቢዎች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የከርሰ ምደር ተጠቃሚዎች  ለውሃችን የመክፈል ግዴታ ሊጣልባቸው ይገባል ። …

ማጠቃለያ

ቆም ብሎ ማሰብና ራስን በራስ ወቅሶ ወደጠቃሚው መንገድ መምጣት ለራስም ፣ ለቤተሰብም ፣ ለአገር ይበጃል ። ሁሉም ያልፋል ። የማያልፍ የለም ። ከማለት ፣ ከማብቃቱ  ፊት ግን በትክክለኛው ፣ ሰው ፣ ሰው ፣ በሚሸተው  በህይወት መንገድ ላይ መገኘት ያስፈልገናል ። የትኛውንም  ያህል ሀብት ብናከማች ስንሞት ይዘነው አንሄድም ። ራቁታችንን መጥተናል ።  ራቁታችንን እንሄዳለን ። ያለን ሀብት ፣ ያለን ሥልጣን ከሞት አያድነንም ። ከመቀባር በላይ በክብር ሥማችንን የሚያስጠራውና በትውልዱ ህያው የሚያደርገን መልካም ፣ ቅን እና በጎ ሥራችን ብቻ ነው ። እናም ይህንን እውነት ቆም ብለን ካላሰብን ፣ ግራና ቀኝ አይተንም  ካላስተዋልን ፤ ከጠቢባኖቻችንም ለመማር አላዋቂነታችንን ካልተረዳን ፣ አገራችንን ወደ ብልጽግና መውሰድ ከቶም አንችልም ። አበቃሁ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

Go toTop