አሰፋ አበበ
- ታሪካዊዳራው
የጎጃም አማሮችና የወለጋ ኦሮሞዎች ለዘመናት ጎን ለጎንና አብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው:: በዝህ የጉርብትናና አብሮ መኖር ሂዴትም ግጭቶችና ትብብሮች ሲታዩ ቆይቷል:: የጎጃም አማሮችና የወለጋ ኦሮሞዎች ለዘመናት ጎን ለጎንና አብረው ኑረዋል:: በዝህ የጉርብትናና አብሮ መኖር ሂዴትም ግጭቶችና ትብብሮች ሲታዩ ቆይተዋል:: ከተጠቃሽ ግጭቶች ውስጥ አንዱ የጎጃም ብቸኛው ንጉሥና የአፄ ዮሐንስ 4ኛ (እ.አ.አ. 1872-1889) ሎሌ በነበረው ንጉሥ ተክለሐይማኖት (አዳል ተሰማ) ትዕዛዝና በራስ ደረሱ አባጣቦ መሪነት ወደ ሆሮ ጉድሩ ዘምቶ በአብሼ ገርባ ሁሩባ በተመራው የአከባቢው ኦሮሞዎች ጋር ተደርጎ የነበረው ውጊያ ነው:: በራስ ደረሱ የሚመራው የጎጃም ጦርና በአብሼ ገርባ በተመራው የሆሮ ጉዱሩ ኦሮሞ ጦር መካከል እ.አ.አ. ፌብሩዋሪ 13, 1877 በሆሮ ጉዱሩ ውስጥ ኮኮር በሚባል ቦታ ላይ ውጊያ ተደርጎ የጎጃም ጦር አሸንፎ አብሼን ማርኮ ወደ ጎጃም ወስዶ አስሮ ካቆየ በኋላ ገድሎታል::
የንጉሥ ተከለሐይማኖት የጎጃም ጦር እ.አ.አ. በ1882 እንደገና በራስ ደረሱ መሪነት ወደ ሆሮ ጉዱሩ ሲዘምት ተቀናቃኛቸው የነበረው የሸዋ አማራ መሪ የሆነው የንጉሥ ምንልክ ኃይል በኦሮሞው ራስ ጎባና ዳጬ የሚመራ ጦር ወደ ሆሮ ጉድሩ አዘመተ:: ሆሮ ጉድሩን ለመቆጣጠር የሚደረገው ፉክክርና ውጊያ በመበርታቱ ንጉስ ተከለሐይማኖትና ንጉስ ምንልክ ጦራቸውን ለማበርታት ወደ ቦታው ሄዱ:: እ.አ.አ. ጁን 6, 1882 የጎጃምና የሸዋ ኃይሎች በሆሮ ጉዱሩ ኢምባቦ ላይ ገጥመው ውጊያው በሸዋ አማራ ኃይል አሸናፊነት ተደመደመ:: ንጉስ ተክለሐይማኖትም በንጉሠ-ነገሥት (አፄ) ዮሐንስ ጃንዋሪ 20, 1881 የጎጃም ነጉሥ ተብሎ በተሾመ አመት ከአራት ወሩ ቆስሎ የተማረከ ሲሆን የጎጃም ኃይልም ለሸዋ ኃይል ገበረ::
ንጉስ ተክለ ሐይማኖት ለንጉስ ምንልክ ከገበረ በኋላ ለአፄ ዮሐንስ የነበረው ታማኝነትና ታዛዥነት ቀነሰ:: በተለይ በ1888 የሱዳን ማሃዲስቶች ወደ ጎጃምና ጎንደር ገብተው አገር ሲያቃጥሉ እንደ ጥሩ ዕድል ቆጥሮ የንጉሥነት ሹመት የሰጠውን የትግራይ ሰው የሆነውን ዮሐንስን ከሥልጣን ለማውረድ ከምንሊክ ጋር መዶለት ጀመረ:: አፄ ዮሐንስ የንጉሥ ተከለ ሐይማኖትንና የንጉስ ምንልክን ዱለታ ሰምቶ ወደ ጎጃም ዘምቶ ንጉሥ ተከለ ሐይማኖትን በድጋም ያስገበረ ቢሆንም ምንልክ ላይ ግን ለመዝመት አልደፈረም:: ወደ ሸዋው ምንልክ ከመዝመት ይልቅ ወደ ሱዳኑ ማሃዲስት ለመዝመት መርጦ ሄዶ መተማ ጋላባት ላይ ማርች 9 እና 10, 1889 በተደረገ ውጊያ ውስጥ ተገደለ:: የንጉሠ ነገስሥትነት ሥልጣንም በዝያው ወርና አመት በሸዋው ምንልክ ተወሰደ:: ምንልክ የንጉሠ ነገስሥትነት ሹመት ሥነ-ሥርዓቱን ኖቨምበር 3, 1889 አድርጎ ሥልጣኑን በመላው ኢትዮጵያ አጸና:: መላውን ኢትዮጵያ አንድ አድርጎ የገዛ የመጀመሪያ ንጉሥም ሆነ:: አንዳንድ ወገኖች የኢትዮጵያን የአገርነት ዕድሜ ከ1889 ጀምሮ የሚቆጥሩትም ከዝህ የተነሣ ነው::
ባህሩ ተፍላ የተባሉ ጸሐፊ “Two of the Last Provincial Kings of Ethiopia” በተባለ ጽሁፋቸው ውስጥ እንደገለጹት የአደል ተሰማ ጎሹ አያቶች ኢቢዶ ከተባለ የአሙሩ ሜጫ ኦሮሞ ጎሳ አባል የሆኑና ወደ 1850 (እ.አ.አ.) አከባቢ ከብቶቻቸውን ነድተው ወደ ጎጃም ዳሞት ወደሚባልና ልዩ ስሙ ጃቢ፡ታሃን ወደ ተባለ ቦታ ከሄዱት ኦሮሞች ውስጥ አንዱ ነበሩ ይላሉ:: ኦሮሞዎች ወደ እነርሱ የመጣ እንግዳን ተቀብለውና አስለምደው አባል አድርገው እንደሚኖሩ ሁሉ እነርሱም ወደ ሌሎች አከባቢዎች ስሄዱ ቶሎ ተቀላቅሎ፥ ተላምዶና ተመሳስሎ የመኖር አመል አላቸው:: ይህም አመል አማራና ትግራዋይ እንዲሁም የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች የበዙበት አከባቢ የሄዱት ኦሮሞዎች ማንነታቸውን እንዲቀይሩና እንዲዋጡ አድርጎአቸዋል::
የንጉሥ ተከለሐይማኖት ጦር አባሎች ሁነው ወደ ሆሮ ጉዱሩና አከባቢው ከዘመቱ ጎጃሜዎችና ጎንዶሬዎች አንዳዶቹ ሳይመለሱ እዝያው ወለጋ ውስጥ መኖር ጀመሩ:: የወለጋ ኦሮሞም የመጣችሁት ልትወጉን ስለነበረ ውጡና ሂዱ አላሉአቸውም:: ሆኖም ግን አንዳንዶቹ በአፄ ምንልክና በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ስካሄድ በነበረው የአማራ የበላይነት ፖሊሲ ተደፋፍረው ችግር በመፍጠራቸው በአሁኑ ምሥራቅ ወለጋ ዞን የሊሙ አካባቢ የኦሮሞ መሪ የነበረው አቶ ዱጉማ ጃልደሶ የአማራ የበላይነት ማስፈንና መጠበቅ የሚለውን የአፄ ኃይለ ሥላሴን ፖሊሲ የሻረውን የጣሊያን ጊዜን ተጠቅሞ ከሊሙ እስከ ሻምቡ ያሉ ችግር ፈጣሪ የጎጃምና የጎንደር አማሮች ተበታትነው በየቦታው ችግር እየፈጠሩ ህብረተሰቡን ከምያስቸግሩ ሆሮ ውስጥ ጫብር ወደተባለ ቦታ ሄድው አንድ አካባቢ እንዲኖሩ አደረጉ:: ያም ለችግሩ ጊዜያዊ መፍትሔ ሁኖ ነበር:: ከ1936-1941 የነበረው ጊዜ የምዕራብ ኦሮሞች የአማራ አገዛዝና ጭቆና መሮናል ራሳችንን ችለን አገር መስርተን የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል ሆነን በነጻነት መኖር እንፈልጋለን ብለው የምዕራብ ኦሮሞ ኮንፌዴሬሽን የተባለውን ድርጅት አቋቁመው የተንቀሳቀሱበትና የኢንግሊዝን ጨምሮ ከተለያዩ አገር ወክሎች ጋር ግንኙነት የፈጠሩበት ጊዜ ነበር:: የኮንፌዴሬሽኑ እንቅስቃሴም ለኦሮሞና ኦሮሚያ ነጻነት ትግል የሐሳብ ጥንስስ የጠነሰሰ ነው::
በምሥራቅ ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የአማራ ሰፋሪዎች በብዛት የሰፈሩት እ. አ. አ በ1970 የተመሰረተውን የአንገር ጉቲን እርሻ ልማትና በ1977 በአንገር ጉቲን የተጀመረው የመንግሥት ሠፈራ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ነው:: በአብርሃም ኢቦር የሚመሩ ሶስት የዳች (ኒዜርላንድስ) ተወላጅ የሆኑ ወንድማማቾች እ. አ. አ በ1970 “Solidarite et Development” (አንድነትና ልማት) የተባለ እርሻ ልማት እስኪመሰርቱ ድረስ የአንገር ጉቲን አካባቢ ከፍተኛ የወባ በሽታ ያላበት በመሆኑ የአከባቢው የኦሮሞ ነዋሪዎች ለረዥም ጊዜ ኑሮ ሳይሆን ለአጭር ጊዜ እርሻ፥ ግጦሽና አደን የሚገለገሉበት አከባቢ ነበር:: የአንገር ጉቲን አከባቢ አንገር፥ ኢንጂሮ፥ አንዶዴ የመሳሰሉ ወንዞች: ሰፊና ለም ቦታ ያሉት አከባቢ ነው::
ከ1970-1977 አንገር ጉቲንን ለ7 አመት ኮንትራት ወስደው እርሻ የጀመሩ ዳቾች በበቆሎ፥ በዘንጋዳ፥ በሰሊጥና ሌሎች እርሻዎች ላይ የጉልበት ሥራ የምሰሩ የቀን ሰራትኞችን ከጎጃም፥ ከሸዋና ከተለያዩ የወለጋ አከባቢዎች አምጥተው አንገር ጉቲን አሰፈሩ:: በ1977 ኮንትራታቸው አልቆ ዳቾቹ ሲወጡ በ1976 በግብርና ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው የሰፈራ ባለሥልጣን የእርሻ ቦታውንና ታያያዥ ንብረቶችን ተረክቦ በቦታው መቆየት የፈለጉትን የእርሻው ሰራትኞች የነበሩትን በህብረት እርሻ አደራጅቶ በቋሚነት አሰፈራቸው1:: ከደርግ ዘመን በፊት በድርቅ ጉዳት የደረሰባቸው የወሎ ሰዎች ገባር ለማብዛት ፍላጎት ካላቸው የአቤ ዶንጎሮው የኦሮሞ ባላባት ፊተውራሪ አበራ ዊርቱን ከመሳሰሉት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአቤ ደንጎሮ፥ በቱሉ ጋናና በሌሎች የሆሮ ጉዱሩ አካባቢዎች ከሰረፈራ ፕሮግራም ውጪ የሰፈሩ ነበሩ::
እ. አ. አ ከዴሴምበር 29, 1979 (ታህሣሥ 19, 1972 E.C.) ጀምሮ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የደረሰባቸውን፥ የእርሻ መሬት የሌላቸውን፥ መሬታቸው የጠበባቸውን ወይም ያረጀባቸውንና ሥራ አጦችን ወደ አንገር ጉቲንና ሌሎች ቦታዎች ወስዶ የሚሰፍረው የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋያ ኮሚሽን (ዕማማኮ) በአዋጅ 173/1972 (173/1979) ተቋቁሞ የሰፈራ ባለሥልጣንን ተክቶ የሠፈራ ሥራውን አጠናክሮ ቀጠለ2:: ዕማማኮ ከ1979- 1985 (1972-1978 E.C) በድርቅ የተጎዱ ናቸው የተባሉትን 1,000 አባወራዎችን ከወሎ፥ 1,800 አባወራዎችን ከትግራይ ወስዶ አንገር ጉቲን አሰፈረ:: ከወሎ የመጡት በመንደር 1 እና 2 ሲሰፍሩ ከትግራይ የመጡ ደግሞ መንደር 3፣ 4 እና 5 ሠፈሩ:: በ1984/85 (1977 E.C) በአማራና ትግራይ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በጉቲን የሰፋሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አንዲጨምር አደረገ:: በ1985 (1978 E.C) መጨረሻ አንገር ጉቲን ሄደው የሰፈሩ ሰፋሪዎች ቁጥር 29,217 ደርሶ ነበር:: በሌሎቹ የወለጋ ዞኖች ማለትም በምዕራብ ወለጋ ዞን ጃርሶ ከሰፈሩት 15,512 ሰፋሪዎች እና በቄላም ወለጋ ዞን ቄጦ ከሰፈሩት 37,024 ሰፋሪዎች ጋር ሲደመር በወለጋ እስከ 1978 ዓ/ም ብቻ መንግሥት ከሌላ ቦታ አምጥቶ ያሰፈራቸው ሰፋሪዎች ቁጥር 81,753 ደርሶ ነበር:: ይህ ቁጥር ከመንግሥት ኦፍሰላዊ የሰፈራ ፕሮግራም ውጭ በራሳቸው ፈቃድና ተነሳሽነት ወደ ወለጋ ሄደው በግል የሰፈሩትን፥ ታቦት ይዘው በቤተክርስቲያን ምስረታና አገልግሎት ስም ወደ ክልል የሄዱትንና በግለሰብ የእርሻ ሥራ ላይ ሰርቶ ለመጠቀም፥ የቡና ለቀማና ሌሎች የሥራ ዕድሎችን ፍለጋ ሄደው የሰፈሩትን አይጨምርም::
እ.አ. አ በ1990 የነቀምቴ ቡሬ መንገድ መከፈትና በ1991 የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን መያዝ ለሕዝቦች ከቦታ ቦታ ዝውውር ሁኔታዎችን በማሳለጥ ወለጋ ውስጥ የሰፈሩ ሰፋሪዎች ሀብት ማፍራትና የተሻለ ኑሮ መኖር የሰሙ ሰዎች ከጎጃም፤ ከወሎ፥ ከጎንደር: ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ወደ ወለጋ በተለይም ከጎጃም ጋር ወደሚዋሰኑ ወደ ምሥራቅ ወለጋና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች በብዛት በመጉረፍ ብዙ የእርሻ መሬቶችን ያዙ:: ይህ የዘፈቀደ የመሬት ወረራና ደኖችን በመሳሰሉ የተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደርሰው ጉዳት አዲሶቹን የአማራ ሰፋሮች ከአከባቢው ነባር የኦሮሞ ነዋሪዎች ጋር ማጋጨት ጀመረ::
- ለወለጋፋኖ ምሥረታ መሠረት የሆኑ ትርክቶች
ለወለጋ ፋኖ ምሥረታ መሠረት የሆኑ ትርክቶች ብዙ ሲሆኑ ጥቅቶቹ የሚከተሉት ናቸው::
- ኦሮሞከኢትዮጵያ መሬትም አገርም የለውም፥ ኦሮሞ ያለበት መሬት ሁሉ የአማራ ስለሆነ ከኢትዮጵያ መባረር አለበት –የወለጋ ክፍለ ሀገር (ቢዛሞ) ፋኖ ዕዝ ታህሳስ 8/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል፥ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፥ ኪራሙ ወረዳ፥ አሮ ቀበሌ የሰጠው መግለጫ “እኛ በቀድሞ ዳሞትና ቢዛሞ ግዛት በዛሬው ወለጋ ክፍለ ሃገር የምንኖር የአማራ ህዝቦች በአጠቃላይ ከባለፉት 450 ዓመታት ጀምሮ በእመቃ፣ በስልቀጣ ከፍ ሲልም የጅምላ ጭፍጨፋ እየተፈፀመብን በርካታ የመከራ ዘመናትን አሳልፈናል”ይላል3። መግለጫው “እኛ…የአማራ ህዝቦች” ሰለሚል በወለጋ አራቱም ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም አማሮች አቋም፥ እምነትና ፍላጎት ነው ተብሎ ይገመታል:: የዕዙን መግለጫ የምቃወም ሌላ ድምጽ ከእነዝህ በወለጋ የሚኖሩ አማሮች እስካልሰማን ድረስ ግምቱ ትክክል አይደለም ማለት አይቻልም:: ይህ ደግሞ የአማራና ኦሮሞ ሕዝቦችን ግንኙነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ያመራል፥ ከባድ ጉዳትም ሊያደርስ ይችላል::
መግለጫው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የታወጀ ግልጽ የጦርነት አዋጅ ነው:: መግለጫው ኦሮሞ ከሰለጠነው የአማራ ህዝብ ጋር ሊዋሃዱ አልቻሉም፥ ኦሮሞና አማራ ዘይትና ውሃ ስለሆኑ ሊቀላቀሉ አይችሉም፥ ብርሃንና ጨለማ ስለሆኑ በአንድነት ሊኖሩ አይችሉም፥ አማራና ኦሮሞ የሚኖሩባት ኢትዮጵያ በበቁሎ ትመሰላለች፥ በቅሎ ትውልዱን አይተካም፥ ምክንያቱም ፍጹም ከተለያየ ዘር ስለሆነ ይመክናል፥ ይሞታል፥ ኢትዮጵያም በኦሮሞ ምክንያት ሙታለች፥ ባለፉት 450 ዓመታት ወደ ቁልቁለት ሄዳለች:: ስለዝህ ተጻራሪ ህልምና የምይታረቁ ማንነት ያላቸው ኦሮሞና አማራን ይዛ ኢትዮጵያ የትም ሊትደርስ አትችልም፥ ስለዝህ ኦሮሞ ከኢትዮጵያ አንድም ጋት መሬት የለውም ተብሎ ከኢትዮጵያ መባረር አለበት በማለት “የዓለም፡አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ”4 የተባለውና በዋናነት በእነአቶ ጌታቸው በየነ፥ አቶ ተክሌ የሻው፥ አቶ ኢያሱ ሙላቱ፥ ዶ/ር ጋሻው ካሴ፥ አቶ ደሳለኝ ካሳ፥ ፕ/ር ሃብታሙ ተገኝ፥ አቶ አበባው ከበደና አቶ አቻምየለህ ታምሩ የሚገኙበት የአማራ ጽንፈኛ ቡድን የሚቀነቀነውን አደገኛና ሀሰተኛ የሆነ ትርክት ላይ የተመሰረት ነው::
ይህንን “ኦሮሞ መጤ ነው” የሚለውን ትርክት የአማራ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረውና ከእኔ ጋር ሁናችሁ የመንግሥት ሥልጣን የያዙ ኦሮሞዎችን አንወጋም ብላችኋል ያላቸውን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የነበረው ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በቢሮው ውስጥ ስብሰባ ላይ እያሉ ገብቶ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የረሸነው ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ በኋላ በብዛት የፋኖ አባል የሆኑትን የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ያስተምር ነበር:: ለምሳሌ ብ/ጄኔራል አሳምነው በ2011 በተደረገው የአማራ ልዩ ኃይል ምረቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተግኝቶ “በታሪካችን [በአማራ ታሪክ] ወደ ኋላ ሄደን 500 ዓመት በፊት እንዲህ ዓይነት ፈተና ገጥሞን ነበር:: በየትኛውም ቦታ በአማራ ላይ የሚደርስ ጥቃት የመቀልበስ ኃላፊነት አለብን” ብሎ የአማራ ልዩ ኃይል ከአማራ ክልል ውጭ የትም ሄዶ ከ500 ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጣ ብሎ የሚገምተውን ኦሮሞን ለውጋት እንዲዘጋጅ ስነግረው ነበር:: “የትርክት ዕዳና በረከት” በተሰኘው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ገጽ 272 ላይ ከብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ማስታወሻ የተገኘ ነው ተብሎ ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት ሰውዬው በኮምቦልቻ ዘይት ፋብሪካ በምመረተው ዘይት ውስጥ መርዝ በመጨመር የሆነ አካባቢ ያሉትን ሕዝቦች ማጥፋት ይቻላል የሚል ዕቅድ የነበረው ጨካኝ ሰው ነበር5:: ኦሮሚያ ለጥፋት ታጭተው ከነበሩ አካባቢዎች ውስጥ አንዱ ሊሆን እንደምችልም ይገመታል፥ ስለዝህ በጦርነት መጨረስ ያልተቻለውን የኦሮሞ ሕዝብ በመርዝ ለመጨረስ ዕቅድ ነበር ማለት ነው::
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (የመላው አማራ አንድነት ድርጅት) ፕሬዝዳንት የሆነው አቶ ማሙሸት አማረ የኢትዮጵያ ጠባቂና አዳኝ አማራ ብቻ እንደሆነ፥ አማራ ጎጃም ውስጥ ተደራጅቶና ተጠናክሮ ወደ ኦሮሚያ ወለጋ፥ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከልና ትግራይ ወልቃይት መዝመት እንዳለበት ይቀሰቅስ ነበር:: ለምሳሌ መጋቢት 22/2011 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ በተካሄደው የአማራ ወጣቶች ማህበር ላይ ተግኝቶ እኛ አማሮች የባለልጣን፥ የባለወንበር ልጆች ነን፥ ነፍጠኞች ነን፥ ጠመንጃ አንጋቾች ነን፥ ትምክህተኞች ነን፥ ኢትዮጵያን የምናድነው እኛ አማሮች ብቻ ነን፥ አክሱም የአማራ ነው፥ አዲስ አበባ የአማራ ነው፥ እኛ ቀድመን እዝያ ነበርን፥ ሌሎቹ ከየት መጡ? ጎጃም ያለው አማራ ስደራጅና ስጠናከር ወለጋ ያለውን አማራ፥ መተከል ያለውን አማራ፥ ወልቃይት ያለውን አማራ ማንም አይነካውም እያለ በኋላ በብዛት የአማራ ፋኖ አባል የሆኑትን የአማራ ወጣቶች ህብረት አባላትን ለወለጋ፥ ለመተከል፥ ለወልቃይትና ለአዲስ አበባ ወረራ ይቀሰቅስ ነበር::
የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ድጋፍ ሰጭ ግብረ ኃይል መሪ የነበረው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ኦሮሞ መጥቶ የሰፈረበት ወለጋ የአማራ ነው፥ አማራ ጥሩ አመራር ካገኘ ወለጋን ለአማራ ያስመልሳል: ኦሮሞ የሰፈረበት መሬት ግማሹ የአማራ ነው፥ ኦሮሞ ወሰን የለውም፤ ድንበሩም አይታወቅም፥ ኦሮሞ ጎረቤታችን ሁኖ በሰላም መኖር ስለማንችል ጥቃት የሚመጣበትን አቅጣጫ ለይተን ሄደን ጠላታችንን ማጥፋት አለብን ብሏል:: ወለጋን ለመቆጣጠር በወጣው ስትራቴጂ መሰረትም በመጀመሪያው ዙር ሃያ (20) የወለጋ ወረዳዎች የአማራ ልዩ ዞን ሆነው ተደራጅተው በአማራ ቁጥጥር ሥር እንዲገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል:: እነዝህ በአማራ ቁጥጥር ሥር እንዲገቡ የተጠየቁ ወረዳዎችም የሚከተሉት ናቸው::
1. ኪረሙ |
6. ኢባንቱ ወረዳ |
11. ስቡ ስሬ |
16. አይራ ጉልሶ |
2. ጊዳ አያና |
7. አሙሩ ወረዳ |
12. ሳስጋ |
17. ባቦ ገምቤል |
3. ሊሙ |
8. ጃርደጋ ጃርቴ |
13. ዋዩ ጡቃ |
18. ሌቃ ዱሌቻ |
4. ጉቴ ጊዳ |
9. አቤ ደንጎሮ |
14. ብሎ ቦሼ |
19. ጎቡ ሳዮ |
5. ዲጋ ወረዳ |
10. ጉደያ ቢላ |
15. ጊምቢ |
20. አንፍሎ |
ተጨማሪ “የኦሮሞ መጤና ወራሪ ነው ትርክት” አራማጆችን መዘርዘር የሚቻል ቢሆንም ለማሳያ ግን ይህ በቂ ነው:: ለ450 እና 500 ቁጥሮች መነሻ የሚያደርጉት ኦሮሞ የተወሰደበትን መሬቶች ለማስመለስ በገዳ ሥራዓት ሥር ተደራጅቶና በአባገዳዎችና በአባዱላዎች ተመርቶ የተንቀሳቀሰበትን የተወሰዱ መሬቶች የማስመለስ ዘመቻን እነርሱ ግን የኦሮሞ ፍልሰት ወይም መስፋፋት የሚሉትን የ16 ኛውን ምዕተ ዓመት እንደመነሻ በመውሰድ ነው:: ያልነገሩን ግን ሐበሻ በተለይም አማራ ከየመን መምጣቱን፥ ንግሥታችን የሚሏት ንግሥት ሳባም በእውን የሌለችና በታሪክ ውስጥ የተጠቀሰችው የሳባ (የዛሬው የመን) ንግሥት (Queen of Saba) እንጂ Queen Sheba አለመሆኑዋን: ከአይሁዶች ጋር ያያይዘናል የሚሉት ቀዳማዊ ምንልክ የተባለ ንጉሥም በእውን የሌለ መሆኑን፥ ስርወ መሰረቱንና ታሪኩን ከየመንና ከአይሁድ (ኤስያ አህጉር) ጋር የሚያያይዘው የሴም ሕዝብ አካል የሆነው አማራ ስርወ መሰረቱንና ታሪኩን ከአፍሪካ አህጉር ጋር ከሚያያይዘውና የኩሽ ሕዝብ አካል ከሆነው የኦሮሞ ሕዝብ የተሻለ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንደማይችል ነው::
- የርዕሰመን ግሥትነት ቦታም፥ በየደረጃው ያሉት ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ቦታዎችም በአማራ ብቻ መያዝ ይኖርባቸዋል– የወለጋ ክፍለ ሀገር (ቢዛሞ) ፋኖ ዕዝ መግለጫ “ቅድመ አያቶቻችን ባቆዩት ሀገር አገዛዙ በንቃት[በንቀት] በፌደራሉም ሆነ በክልል ምክር ቤቶችም ሆነ ስራ አስፈፃሚነት ቦታ እንዳይኖረን በማድረግ ሁለተኛ ዜጋ አድርጎን ቆይቷል” ይላል። በመግለጫው እንደተጠቀሰውና የወለጋ ፋኖ ዕዝ ሰብሳቢ ነኝ ያለው አቶ ንጉሤ ዋለለኝ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከአማራ ፋኖ መዋዕለ ዜና ዘጋቢ ሚዲያዎች ውስጥ አንዱ ከሆነው ከአንከር ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ውስጥ እንደገለጸው የቡድኑ አንዱ ዓላማ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ጥሎ አዲስ መንግሥት ማቋቋም እንደሆነ ገልጿል:: ይህም የጎጃም አማራ ፋኖ ሰብሳቢ ነኝ ያለው አቶ ዘመነ ካሴና ሌሎች የፋኖ መሪዎች፥ አባላትና ደጋፊዎች የመንግሥት ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት አስመልክተው በተለያዩ ጊዜያት ከተናገሩትና ትርክቶች ጋር የሚጣጣም ነው:: ለምሳሌ የጎጃም መራዊ ተወላጁና ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ተለይቶ ወደ አገር ተመልሶ ፋኖን ተቀላቅሎ እነማስረሻ ሰጤንና እስክንድር ነጋን እያባረረ በፋኖ አመራርነት ስሙ ጎልቶ የሚሰማው የጎጃም አማራ ፋኖ መሪ ዘመነ ካሴ የሚከተለውን ብሏል:
- ቢያንስቢያንስ ከአቢይ አናንስም፥ ታግለናል ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚኒስትር ያለውን ሥልጣን መያዝ አለብን::
- እኔእያለሁ ሌላው ዘውድ አይጭናትም፥ አራት ኪሎ አይገባትም: ዘመነ አጥናፉ አባተ አይደለሁም: አጥናፉ አባተ አብዮት መርቶ አብዮት አደራጅቶ አገር በመምሪያው ጊዜ መንጌ የተባለ ቀልጣፋ ቀስ ብሎ ገፋው፥ ከዝያም ከዝህ ምድር ላይ አጠፋው:: ዘመነ አጥፉ ይመስለሃል? አይቻልም፥ ሥልጣን እንወስዳለን፥ ቀበሌን፥ ወረዳን፥ አራት ኪሎን እንወስዳለን:: ሥልጣን እንይዛለን፥ ለመቶና ሁለት መቶ አመት ትውልድ እንገነባለን::
- አራሽ፥ተኳሽ፥ ቀዳሽ ብቻ ሳንሆን ነጋሽም ነን፥ እንነግሳለን::
- በጥንቆላጥበብ የዳመና ጋላቢ የሆኑ ወላጆች ልጆች ነን፥ የፖለቲካ ሥልጣን እፈልጋለሁ፥ ያም የሚገኘው በመሳሪያ ኃይል ነው:: የትጥቅ ትግሉ የተፈለገው የፖለቲካ ግባችንን በመሳሪያ ለማሳካት ነው፥ ከእኛ የተሻለ ሰው ደግሞ አይመጣም (በጥንቆላ ለማመኑ ደግሞ አንገቱ ላይ የሚያንጠለጥለው ከተለመደው መጠን በላይ የሆኑ ትላልቅ መስቀሎች፥ በትክሻው የሚያነግተው የዳዊት መጽሐፍና በግራ የእጅ ጣቶቹ ላይ የደረደረው የብር ቀለበቶች ፍንጭ ይሰጣሉ) ::
- እኛሞተን ሥልጣኑን አሳልፈን አንሰጥም፥ ትግሉንም ድሉንም እንጠብቃለን፥ የጎጃምን ትግል ለመከፋፈል የምፈልጉትን በእሳት ነው የማቃጥላቸው፥ በጥይት አልመታም:: ይህም ከዝህ በፊት የአማራ ባንዳዎች እጅና አንገት መቆረጥ አለበት ብሎ ካስተላለፈው ማስፈራሪያ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የሽብር ቃል ነው:: ዘመነ ካሴ ኮሎኔል ጌታሁን መኮንን የተባለውን የአማራ ፋኖ አመራር የነበረ ሰው ከእስክንድር ነጋና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር ትገናኛለህ በማለት ጎጃም ቁንዙላ በሚባል ቦታ ከበው እንዲገድሉት ገዳይ ቡድን ልኮበት ሲያስለቅስ የነበረና ኮሎኔሉ በኋላ ትግሉን ትቶ እንድወጠ ያደረግ አምባገነንና ጨካኝ ሰው ነው::
የሥልጣን መያዝ ጉዳይን በሚመለከት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “መነሻችን አማራ፥ መድረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለውን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ግንባር ዓላማ ሲያብራራ ኢትዮጵያ የአማራ ነች፥ አማራ ስነሳ ሌላው ይርበደበዳል፥ አማራ ተቆጥቶ ተነስቶ አራት ኪሎ ቤተ-መንግሥት መግባት አለበት፥ አራት ኪሎ ስንገባ በእኛ ደንብና መመሪያ (terms and conditions) እኛ በምንፈልገው ሁኔታ የሚመቸንን ሥርዓት እንገነባለን ብሏል:: “መነሻችን አማራ፥ መድረሻችን ኢትዮጵያ” ማለት አማራ ብለን ተነስተን ኢትዮጵያን እንቆጣጠር ማለት ሲሆን ይህ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የሸዋ አማራ ፋኖ መፈክር ነው:: የ”መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ” መፈክር/ፖሊሲ ዓላማዎች:
- የመንግሥትሥልጣንንአማራ 100% ጠቅልሎ እንድይዝ ማድረግ
- አሁንያለውንሕገ-መንግሥት ቀዳዶ መጣል
- ክልላዊፌዴራሊዝምንማጥፋት
- የሕገ፡መንግሥቱንአንቀጽ39 ገደል መክተት
- ከአማርኛበቀርሌላውን ቋንቋ ማገድና ማጥፋት
- አማራየኢትዮጵያብቸኛው ታማኝ ብሔር መሆኑንና ሌላው ብሔር ታማኝ አለመሆኑን ማስረዳት
- ፋኖአሸንፎየምንልክን ቤተ መንግሥት ወስዶ እንድነግሥና ኢትዮጵያን እንዲያስተዳድር ማድረግ ናቸው ስል ዶ/ር ደረጀ ከበደ የተባለ የአማራ ፋኖ ብርቱ ደጋፊ ሰው አብራርቷል:: በዘመነ ካሴ የሚመራው የጎጃም አማራ ፋኖ ደግሞ “መነሻችን አማራ፥ መድረሻችን አማራ” የሚል መፈክር ያለው ሲሆን እርሱ ደግሞ ከዝህ የጠበበና የከፋ ነው::
- አማራ የውሃ ልክነትና የበላይነት እንጂ እኩልነት አይመጥነውም –የአንዳንድ የአማራ ልህቃንና ፖለቲከኞች አስተሳሰብ “ሁሉም አንስሳት እኩል ናቸው፥ ግን አንዳንዶቹ እንስሳት ከሌላው የበለጠ እኩል ናቸው” ከሚለው ከጆርጅ ኦርዌል ልበ ወለዳዊ አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይ ነው:: ለምሳሌ የአብን አመራሮች “ሰው በተፈጥሮው ፈጣሪውን ማክበር እንዳለበት ሁሉ፥ ኢትዮጵያም ፈጣሪዋን አማራን ማክበር አለባት” ብለው በጽሑፍና በቃል ስናገሩ ኢትዮጵያ መሬቱ ማለታቸው ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች አማራን ማክበር አለባቸው ማለታቸው ነው:: አቶ ክርስቲያን ታደለን የመሳሰሉ የአብን አመራሮችም “አማራነት የሰውነት ውኃ ልክ ነው” ብለው አንደሚያምኑ ገልጸዋል:: ይህም ዋለልኝ መኮንን የገለጸው ከ1966 በፊት በኢትዮጵያ የነበረው የአማራ የበላይነት ተመልሶ እንድመጣ ይታገላሉ ማለት ነው:: በ1987ቱ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መግቢያ ውስጥ “መጪው ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረም” ነው የሚለው አገላለጽ እንድወጣ የምፈልጉበት ምክንያትም ድሮ የነበረው የሕዝቦች የበላይነትና የበታችነት ተመልሶ ሥራ ላይ ውሎ ኢትዮጵያ ተመልሳ የአንድ ብሔር ማንነትና ባሕል የሚገንባት አገር እንድሆትን በመፈለግ ነው::
- አማራሐያል ሕዝብ ስለሆነ ልጆቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የትም ቦታ ሄደው የፈለጉትን በኃይል ማስገበርና መግዛት ይችላሉ— የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መሪ የነበረው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ኦክቶቤር 5/2018 ከኤል ቲቪ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አብን የተቋቋመው አማራ በአንደኛ ደረጃ ዜግነት የምኖርበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው፥ አብን አገራዊ ፓርቲ ነው፥ 40% የአብን መሥራች አባሎች ከአማራ ክልል ሲሆኑ፥ 60% ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል፥ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፥ ከደቡብ ክልልና ከአዲስ አበባ ናቸው: አብን ከአማራ ክልል ውጭ ላሉ አማሮች ዘብ ይቆማል ብሏል:: ይህም በኦሮሚያ የሚኖሩ አማሮች ትስስራቸው ከአማራ ክልል ጋር መሆኑንና የሚመሩትም አማራ ክልልን ማዕከል ባደረገው የአማራ ፖለቲካ መሆኑንና ለሰላምና ደህንነታቸው የሚተማመኑበት የኦሮሚያ ክልል መንግሥትን ሳይሆን የአማራ ክልል መንግሥትንና በአማራ ክልል ያሉ እንደአማራ ልዩ ኃይልንና ፋኖን እንደሆነ ያሳያል:: ይህ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ አማራዎች መብት ጠባቂው የአማራ ክልል መንግሥት ወይም የአማራ ድርጅቶች ናቸው የሚለው አስተሳሰብ የኦሮሚያ ክልል መንግሥትን የሚያዋርድና በኦሮሚያ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው::
የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደንነት አማካሪ የነበረ ዶ/ር ገዱ አንደርጋቸውም ዴሴምበር 27, 2024 ከኢቲዮ፡ንውስ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ–ምልልስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቶ ሥልጣንና አገር ጥሎ የወጣበት ዋናው ምክንያት ወደ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ገብቶ እንዲዋጋና የአማሮችን መብት እንድያስከብር የተገነባነው የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ እንዲፈርስ በመወሰኑ ነው ስል ገልጿል:: ይህ ማለት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚኖሩ አማሮች ላይ ያለው የማስተዳደር ሥልጣን የተሟላ አይደለም ማለት ነው:: የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ኦነሠን ለማጥፋትና የኦሮሚያን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በ2014 ዓ/ም መስማማታቸው ይታወሳል:: ግንኙነታቸውንም ለማጠናከር በዝሁ በ2014 ዓ/ም የኦሮሚያ ክልል መንግስት በአማራ ክልል ህወሓት በከፈተው ውጊያ ለተፈናቀሉ ወገኖች መርጃ የሚሆን የ100,000,000.- (አንድ መቶ ሚሊዮን) ብር ድጋፍ ማድረጉም ይታወሳል፡፡የኦሮሚያና አማራ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮችም ተመሳሳይ ስምምነት አድርገዋል::
አንዳንድ የአማራ ልህቃን ኢትዮጵያ የተሰራቸው በአማራና በትግራይ ሕዝቦች ነው፥ ባለቤቶቹም አማራና ትግራዋይ ናቸው፥ ኦሮሞና ሌሎች በኋላ የመጡ እንግዶች ናቸው: በታሪካዊው ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ የላቸው ብለው ያስባሉ:: በመሆኑም የአገሩ ባለቤቶች የሆኑት አማሮች የትም ሄደው አንግዶቹን ኦሮሞዎች በፈለጉት መንገድ ማስተዳደር ይችላሉ ብለው ያምናሉ:: አማራ ታሪካዊ ቦታውን መልሶ መያዝ አለበት እያሉም ይቀሰቅሳሉ:: በወለጋ አማራ ፋኖ ዕዝ የመመሥረቻ የአቋም መግለጫ ውስጥ “አያት ቅደመ አያቶቻችን ያቀኑት አገር” ተብሎ የተጠቀሰውም ይህንኑ የአማራን “የአገር ባለቤትነት”ና የኦሮሞን “እንግዳነት” ለመግለጽ፥ ነው:: ኦሮሞ የአገሩ እንግዳ አለመሆኑና የአገሩ ባለቤት መሆኑን ማሳወቅ ይኖርበታል:: የአንዱን ክልል የመንግስት መዋቅር ወደ ጎን በመተው ሌላ ለመዘርጋትና በመንግስት ላይ ሌላ መንግስት ለመመሥረት መጣር ስራዓተ አልበኝነትን የማስፈን አሰራር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም::
ዶ / ር ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ፕሬዝዳንትነት እንድነሳ ጥቅም ላይ ከዋሉ ዜዴዎች ውስጥ አንዱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አቶ ደመቀ መኮንን የመሳሰሉ አማራ የሆኑ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት የጉጂ ኦሮሞና የጌድኦ ብሔረሰብ ግጭትን የመሳሰሉ የሕዝብ ግጭቶችን በመፍጠር የኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎችን በመወንጀል መሆኑን ስለ ጉዳዩ የሚያውቀው ዶ/ር ሚልከሳ ሚዳጋ አጋልጧል:: ልክ በቡራዩ በ2010 በኦሮሞና በጋሞ ወጣቶች መካከል እንደተፈጠረው ግጭት፥ በ2010 በጎጂና በጌዴኦ መካከል እንደተፈጠረው ግጭት በወለጋ በተላዩ ቦታዎች በአማራና በኦሮሞዎች መካከል የተፈጠሩት ግጭቶች የፖለቲካ ግብን ለማስፈጸም ሆን ተብለው የተፈጠሩ ግጭቶች ናቸው፤፤
- የወለጋፋኖ ዕዝ መመሥረትና የዓላማው አደገኝነት
የወለጋ አማራ ፋኖ ምሥረታና ዕድገት ፓላስታይን ውስጥ ከአረብ ፍልስጤማውያን መሬትን በግዥና በሌላ መንገድ እየወሰደ: ቀስ በቀስ እየተስፋፋና አተደራጀ ሄዶ ኢስራኤልን መስርቶ ከነባር ፍልስጤም አረቦች ላይ አገር ከቀማው ከጽዮናዊነት እንቅስቃሴ ጋር ይመሳሰላል:: ሁለቱም ተለሳልሰው በመግባት የአያቶቻችን መሬት እናስመልሳለን ብለው መጀመሪያ በህቡዕ፥ ከዝያም ራስን መከላከል በሚል ሽፋን በትናንሽ የሚሊሻ ቡድኖች ከዝያም ከፍ ባለና ይበልጥ በተጠናከረ ተዋጊ ኃይል ተደራጅተው ውግያ የጀመሩ ናቸው::
በኢሕአዴግ ዘመን ወለጋ ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች “ጋላ ገዳይ” በሚልና ዋና መቀመጫውን ነቀምቴና አንገር ጉቲን ከተሞች ያደረገ ኦሮሞን በአካልና በስነ ልቦና የመግደል ዓላማ ባለው የህቡዕ ድርጅት ሥር ተደራጅተው ይንቀሳቀሱ ነበር:: በ2010 ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ የተከሰተውን የሕግ መላላትና የጸጥታ መደፍረስ ችግር እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በህቡዕ ስንቀሳቀስ የነበረው የጋላ ገዳይ ቡድን አማራዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በአካባቢ ሚሊሻ መልክ ተደራጅተውና ታጥቀው ራሳቸውን እንዲጠብቁ በመቀስቀስ እንድደራጁ ረዳቸው:: አዲስ አበባ፥ ጎጃምና በተለያዩ ቦታዎች ካሉት የአማራ ባለሀብቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋርም ግንኙነት በመፍጠር የበለጠ ትጥቅና ስንቅ እንዲያገኙ ረዳቸው:: በተሰጣቸው ዕርዳታና ድጋፍም በአንገር ጉቲን በአቤ ደንጎሮና በኪረሙ የማሰልጠኛና የትጥቅና ስንቅ ማከማቻ ማዕከላትን (ዴፖዎችን) ማቋቋም ቻሉ::
በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የአማራ ተወላጁ አቶ ደመቀ መኮንን በወለጋና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሉ አማሮች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማስታጠቅ አለብን ብለው በይፋ ከተናገሩ በኋላ የማስታጠቁ ሥራ ተጠናክሮ ቀጠለ:: በወለጋ ያሉ የአማራ ሰፋሪዎች ራሳችንን እንዲንጠቅ አስታጥቁን እያሉ ያደረጉት እንቅስቃሴና የማስታጠቁ ሂዴት በደርግ ዘመን የደርግ ደጋፊዎች አስታጥቁን አታስጨርሱን ብለው የጦር መሳሪያ ታጥቀው ተቃዋሚያቸው የነበሩትን የኢሕአፓ አባላት ከጨፈጨፉበት ሂዴት ጋር ተመሳሳይ ውጤት አመጣ::
የጦር መሳሪያዎችን ወደ ወለጋ የማስተላለፍ ሂዴትም እነአቶ ውብሸት ወርቅአለማሁን የመሳሰሉ የአማራ ባለሀብቶች ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመቀናጀት ወደ ሰሜን ሸዋ አጣዬ የጦር መሳሪያዎችን ካስተላልፉበትና በኢትዮ ፎረም ሚዲያ “ብናልፍ ያሳለፉት፤ አጣዬ፣ አማራን ከትግራይ ማጋጨት” በሚል ርዕስ ዴሰምበር 3/2024 ከተገለጽው ሂዴት ጋር ተመሳሳይ ነው:: ያገኘውን ትጥቅ፥ ስንቅ፥ ስልጠናና የሞራል ድጋፍ በመጠቀም በምሥራቅ ወለጋና በሆሮ ጉዱሩ ዞኖች ውስጥ በየቦታው በሻምበልና በሻለቃ የተደራጀው ፋኖ በአከባቢው የኦሮሞ ነዋሪዎች ላይ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት እጀግ ብዙ ጉዳት አደረሰ:: ሰው ገደለ፥ ቤት አቃጠለ፥ አፈናቀለ፥ ንብረት ዘረፈ፥ ከፍየል እስከ ከብት የቤት እንስሳትን ነድቶ ወሰደ፥ ሴት ደፈረ:: እ. አ. አ. በ2022 በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ጥቃቱ ሲበዛ ሕዝቡን እከላከላለሁ ብሎ ወደ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ የተሰማራውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) አባላትን ገጥሞ በማሸነፍ የሁለቱን አንገት ቆርጦ ወደ ጎጃም ቡሬ ከተማ በመውሰድ በብረት ዘንግ ላይ ሰክቶ እየጨፈረበት ጨካኝነቱንና አሸባሪነቱን በአደባባይ አሳዬ:: በወለጋ ውስጥ የተደራጀው የአማራ ፋኖ በተለያዩ ጊዜያት ከኦነሠና ከኦሮሚያ የፖሊስ ኃይል ጋር ተዋግቶ እንዳሸነፈና የመከላከያ ኃይልን ለመግጠም እየተዘጋጀ መሆኑን የወለጋ አማራ ፋኖ ዕዝ ሰብሳቢ ንጉሤ ዋለልኝ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ከአንከር ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ውስጥ አረጋግጧል::
በአጭሩ የወለጋ ክፍለ፡ሀገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) ከላይ እንደተገለጸው ቀስ በቀስ እየተደራጀ መጥቶ አሁን በታህሣሥ ወር 2017 ዓ/ም ድርጅታዊ አቋሙን ይፋ ያደረገ ነው እንጂ በአጭር ጊዜ ዝግጅት የተደራጀ አይደለም:: በተለይም ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ጎጃም ውስጥ በተስፋፋው የአማራ ወጣቶች ማህበር እና የአማራ ልዩ ኃይል ጋር ግንኙነት በመፍጠር፥ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀናጀ ሥራ በወለጋ ውስጥ በተካሄደው የሚሊሻ ሥልጠና በመሳተፍና ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም የተጀመረው የትግራይ ጦርነት የፈጠረውን የተጨማሪ ሥልጠናና ትጥቅ የማግኘት ዕድል በመጠቀምና በጎጃም አማራ ፋኖ ድጋፍ እዝህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል::
የወለጋ ክፍለ፡ሀገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) መመሥረት በኦሮሞና በኦሮሚያ ላይ የደቀነው አደጋዎች 9 ነጥቦች ባለው የምሥረታው የአቋም መግለጫ ውስጥ ተገልጸዋል፥ እነርሱም:
- የኦሮሞስም ያላቸውን አከባቢዎች ሰም በመለወጥ የኦሮሞን ታሪክ ማጥፋት— ለዝህም ወለጋን “የቀድሞ ዳሞትና ቢዛሞ በአሁኑ የወለጋ ክፍለ ሀገር” ብሎ መጥራት ጀምረዋል:: ቀጥሎም በተያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የአማራ ፋኖ ዕዝ ለመመስረትና ኢሉ አባቦራን እናሪያ፥ አርሲን ፈጠገር፥ ሐረርን ዳዋሮ፥ ሰላሌን ግራሪያ፥ ወሎን ላኩመልዛ፥ ፊንፊኔን በረራ በማለት ለመለጥ አደገኛ ዕቅድ ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ::
- ተደራጅተውናተጠናክረው እንድንወጡ ሁለተናዊ ድጋፍ አደርጎልናል ካሉት ከጎጃም አማራ ፋኖ ጋር በመስራት ጦርነትንና ሽብርን ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል በወለጋ በኩል በስፋት ለማስገብት እየሞከሩ ነው፥
- ሰፊውንየኦሮሞ ህዝብ በሥልጣን ላይ ካሉ የፖለቲካ ቡድኖችን በጠላትነት የፈረጅነውን ያህል እንደ ህዝብ በጠላትነት አናይህም፥ ስለሆነም በሁለትኛ ደረጃ ጠላትነት የመድብንህ ስለሆነ ልናጠፋህና አ ርህን ለመውሰድ በምናደርገው ጦርነት አግዘንና ራስን ለማጥፋት ተባበረን እያሉ ያላግጡበታል።
- ኦሮሚያአያት ቅደመ አያቶቻችን ያቀኑት (በጠመንጃ ኃይል በጉልበት አስገብረው ይዘውት የበረ) ስለሆነ አሁንም መልሶ ለማቅናት (ለማስገበር) የኦሮሞን ሕዝብ ታግሎ ከማሸነፍ ውጭ አማራጭ የለንም በማለት የወረራ ፍላጎታቸውን በግልጽ አሰታውቀዋል።
- ትጥቅ፥ስንቅና ሃሳብ (መመሪያ) የሚሰጣቸውም ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጭ አገር ጭምርም መሆኑ ን በመግለጫቸው ውስጥ አምነው ባንዳነታቸውን አረጋግጠዋል::
- የአማራወጣቶች ወደ ወለጋ ዘምተው የወለጋ አማራ ፋኖ ዕዝን ተቀላቅለው ኦሮሞዎችን እንድወጉ የክተት ጥሪ አስተላልፏል::
- በወለጋበተለያዩ አደረጃጀቶች ታቅፈው በመታገል ላይ ያሉ አማራዎች ዕዙን ተቀላቅለው ኦሮሞን እንዲወጉ ጥሪ አድርጓል::
- ወለጋውስጥ ከአማራ ተወልደው ከመንግሥት ጋር የሚሰሩትን እንደፀረ አማራ ቆጥሮ አስጠንቅቋል::
- የኦሮሞጎጂውን የመውደድ ጸባይና ዝምታ
የኦሮሞ ሕዝብ አቃፊ ሕዝብ እንደሆነ በብዛት ይነገራል፥ በጉደፈቻም፥ በሞጋሳም፥ በሌላ የማቀፊያ መንገድም የሌላ ብሔር ብሔረሰብ ተወላጆችን አቅፎ አብሮ ይኖራል:: በጉድፈቻና በሞጋሳ ባቀፋቸው ላይም ምንም ልዩነት ሳያደርግ እንደራሱ ልጆችና ቤተሰብ ይይዛቸዋል:: ለምሳሌ በ16ኛ ምዕተ ዓመት መጨረሻ አከባቢ አባቱን በጦርነት ውስጥ የገደሉበትን የጎንደሩን የአማራ ተወላጅ ሱስንዮስ ፋስልን ኦሮሞዎች በጉድፈቻ ወስደው አሳድገው፥ የጦር ሥልታቸውን አስተምረውት፥ አቅፈውና ደግፈው ለጎንደር መንግሥት ሥልጣን አብቅተውታል:: ሆኖም ግን ሱስንዮስ ማርች 10/1607 ሥልጣን ከያዘና ኃይሉን ካጠናከረ በኋላ ኦሮሞዎቹ ላይ ዞሮ ፈጃቸው:: ምንልክ ሐይለመለኮት (በኋላ አፄ ምንልክ)፥ ከአፄ ቴዎድሮስ እስር ቤት ጁላይ 1/1865 ከመቅደላ በወሎ ኦሮሞዎች እርዳታ አምልጦ ወደ ሸዋ ስመለስ የሸዋው ገዥ የነበረው አቶ በዛብህ ይገድለኛል ብሎ ስለፈራ ወደ ቢሾፍቱ ሄዶ በኦሮሞዎች መካክል ነበር የተደበቀው:: ኦሮሞዎችም ምንልክ ጎን ተሰልፈው አቶ በዛብህን በመውጋት ምንልክ በ1866 የሸዋ ንጉሥ እንድሆን፥ ከዝያም በ1889 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እንድሆን ረዱት:: በሰጡት ወታደራዊ አገልግሎት ሥልጣን የያዘው ምንልክ ኦሮሞዎቹን መልሶ ክፉኛ ቀጣቸው፥: እነ ራስ ጎበና ዳጬ፥ ፊተውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲናግዴ፥ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ለአፄ ምንልክ የሰጡት አገልግሎት፥ እነ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ለንጉሥ ኃይኃለ ሥላሤ የሰጡት አገልግሎት፥ እነ ኃይሌ ፊዳና ዶ/ር ሰናይ ልኬ ለደርግ የሰጡት ድጋፍና አገልግሎት: እንዲሁም አንዳንድ የኦህዴድ አመራሮች ለሕወሐት ያሳዩት ታማኝነትና የሰጡት አገልግሎት ለኦሮሞ ያመጣው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል:: ከዝህ የተነሳ ይመስላል ዶ/ር ገመቹ መገርሳ “ኦሮሞ አቃፊ ነው ይላሉ፥ ኦሮሞ ለምን ያቅፋቸዋል? ሕግ ይቀፋቸው እንጂ፥ ሕግ የማያከብሩትን ኦሮሞ ለምን ያቅፋል?” ያሉት:: ኦሮሞ ሌሎችን ከማቀፍም አልፎ እርሱ ውስጥ ሆነው ተንኮልና ደባ ስሰሩበት አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ሕዝብ ነው:: የኦሮሞ ሕዝብ ተኩላዎች ሊበሉት እየከበቡት ትኩረት ባለመስጠት እያለፈ ሆዱ ውስጥ ገብተው አንጀቱን በልተው እንደምጥሉት ዝሆን ነው::
ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችም አቀፍን ባሉት ለሌላ ብሔር ብሔረስቦች ታማኝ በሆኑ ግለሰቦች ተተብትበው ተይዘው ወደፊት መራመድ እንዳይችሉ ስደረጉ ይታያሉ:: ፊ/ ርሻል ብርሃኑ ጁላ ኦነሠ አሸናፊ ጎንደሬን በመሳሰሉ አማራዎች ይመራል ያሉት ዝም ብሎ እንደቀልድ የምታለፍ ጉዳይ አይደለም:: አሸናፊ ጎንደሬ (ጃል ጫላ) የተባለ ሰው በኦነሠ ውስጥ ኖረም አልኖረም ገጸ ባሕርው የሚወክለው የአማራ ተወላጆች ግን በድርጅቱ ውስጥ እንዳሉ በሰፊው የሚወራ ጉዳይ ነው:: የአማራ ፋኖ በምሥራቅ ወለጋና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ያን ሁሉ ጉዳት ሲያደርስ ኦነሠ መንግሥት ባለመሆኑ ሕዝቡን ከአማራ ፋኖ ጥቃት የመከላከል ግዴታ የለበትም የሚል አቋም እንድራመድ የሚያደርጉትም እነዝሁ አሸናፊ ጎንደሬዎች ናቸው:: ኦነሠ ሕዝቡን ከአማራ ፋኖ ጥቃት የመከላከል ግዴታ ከለሌው የሕዝቡን ሰላምና ደንነት ሊጠብቅ የነበረውን መንግሥታዊ ተቋም አፍርሶና ሕዝቡን ትጥቅ አስፈትቶ ለአደጋ አጋልጦት6 ፋኖ ሲመጣ ጥሎት የሚሄደውን ኦነሠን የመቀለብ ግዴታ የለበትም ማለት ነው::
አንዳንድ የኦሮሞ ልህቃንም ኦሮሞ ላይ በደል ላደረሱ ወገኖች ጥብቅና ቁመው ስከራከሩ ታይተዋል:: የፋኖ ኃይሎች ከመነሻው የራሳቸውን ትይዩ መዋቅር ዘርግተው መንግሥትን የመገዳደር ፍላጎት አሳይተው ነበር:: የፋኖ ኃይሎች ወደ ኦሮሚያ ወለጋና ደራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዘምተው ለመቅጣት ያላቸውን ፍላጎት ደጋግመው ገልጸው እያሉ የወጣት ደረጄ አማረ አንገት የተቆረጠበትና የዘሩ ሹመቴ ዶዮ እጅ በካራ የተቆረጠበት የነሐሴ 21/2016 ዓ/ም የደራ የፋኖ ጥቃትን በመንግሥት ሠራተኞች/ኃይሎች ላይ ያላክካሉ:: ደራ ሁለት ነው አንዱ የአማራ ክልል ደራ ሌላው የኦሮሚያ ክልል ደራ በማለትም በውሸት ውዥንብር ለመፍጠር ሞክረዋል:: አንዳንድ የኦሮሞ ልህቃን የስቶክሆልም ስንድሮም (Stockholm Syndrome) ተጠቂዎች ናቸው:: አፋኛቸውን፥ ጨቋኛቸውን፥ በዳያቸውን ይወዳሉ፥ያቀርባሉ:: የኦሮሚያን ድንበር/ ወሰን ሰብረው ገብተው ኦሮሞን የምገድሉትን ራስቸው መደገፋቸው ሳይበቃ ሌላውም እነርሱን ተከትሎ እንዲደግፍ ይቀሰቅሳሉ:: የአማራ ፋኖ በግልጽና በአደባባይና በተደጋጋሚ የክልል አወቃቀርንና ፌዴራሊዝምን እየተቃወመ በኦሮሚያ፥ በቤኒሻንጉልና በትግራይ ያለውን አያቶቻችን ያቀኑትን መሬት/ አጽመ ርስት መልሰን በአማራ ቁጥጥር ሥር እናስገባለን ብለው እየፎከሩ እየተሰማ ፋኖ የሸፈተው ሥልጣን የያዙ የኦሮሞ ተወላጆች አማራን ስለበደሉ ነው፥ እነዝህ ሥልጣን ላይ ያሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ከሥልጣን አባረን ከፋኖ መሪ ዘመነ ካሴ ጋር ተደራድረን በፍቅርና በሰላም እንኖራለን ይላሉ:: በኦሮሞ በዳዮች ዘንድ ለመወደድ ተበዳዩን ኦሮሞን መልሰው ይከሳሉ:: አይናችን እያዬ ጆሮአችን እየሰማ የአማራ ጽንፈኛ የሚባል የለም አቢይ አህመድን፥ ሽመልስ አብዲሳን፥ አዳነች አቤቤንና ሌሎች ኦሮሞዎችን ከሥልጣን ካባረርን ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል: አይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ፥ ይሉናል::
እነዝህ የስቶክሆልም ስንድሮም ተጠቂዎች ናይሮቢ ኬንያ ላይ በኦሮሞ ስም በመንግሥት ሥልጣን ላይ ያሉት ልፍስፍስ አምባገነኖች (anocracy) እና ጠማማዎች ኢትዮጵያን ይዘው ገደል እንዳይገቡ ወይ እንደጠማማ እንጨት በእሳት ለብልበን ማቃናት ወይም ከመንገድ ዘወር ማደረግ አለብን ብለው ኑሬንበርግ ጀርመን ላይ ደግሞ መንግሥትን ከሥልጣን የማባረር/ መንግሥት የመገልበጥ ዓላማ የለንም ወደ መስመር እንዲመለሱ የመለመንና የመማጸን እንጂ እያሉ የፖለቲካ ዥዋዥዌ ይጫወታሉ:: አንዴ ኢትዮጵያ የቀነጨረች አገር ስለሆነች ልትፈርስ አትችልም እያሉ፥ ሌላ ጊዜ ደግሞ ኢትዮጵያ ሥሩ እንደተበላ ዛፍ ነች ወድቃ ልትበታተን ነው፥ ከጣሪያ ላይ እንደወደቀ ጀበና ብትንትኗ ልወጣ ነው እያሉ በየጊዜው የታያቸውን ቅዠት ሚዲያ ላይ ወጥተው እያወሩ ሕዝቡን ግራ ያጋባሉ:: የትግላችን ስትራቴጅካዊ ዓላማ ኢትዮጵያን አገራዊ ዕይታ ከሌለው ከአቢይ ለማዳን ነው በማለት ራሳቸውን የኢትዮጵያ ብቸኛ አዳኝ አድርገው ያቀርባሉ::
የአማራ ኤሊት ፀረ-ኦሮሞ ትርክት ሲፈበርክ፥ የአማራ ፋኖ የኦሮሞን አገር ሲወር ፤ የኦሮሞን ፖለቲካ ማንም ግራና ቀኝ ሲያላጋውና ሲያቦካው ብዙሃኑ የኦሮሞ ኤሊት ዝም ማለቱም ይገርማል:: ጅብ እግሩን ቆርጥሞ ጨርሶ፥ የሆድ ዕቃውን እያንቦጫረቀ እየበላው አብሮ የተኛውን ጓደኛውን “ዝም በል እኔን እየበላ ነው (Ishaa na boqqaa)” እንዳለው ፈሪ ሰውዬ ሌላውንም ዝም በሉ፥ ከተናገራችሁ ደግሞ አማራ በሕወሐት ምክንያት የትግራይ ሕዝብን እንደቀጣ ነገ እኛን በእነርሱ ምክንያት እንዳይቀጣን ሥልጣን ላይ ያሉትን የኦሮሞ ተውላጆችን መርጣችሁ አውግዙ ይላሉ:: ይህ የኦሮሞ ኤሊት ዝምታም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል::
- የአማራፋኖ ወረራን የመቀልበስ አስፈላጊነት
በ2008 ዓ/ም በአገር አቀፍ ደረጃ በኢሕአዴግ ላይ ተጠናክሮ ተነስቶ የነበረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ የፋኖ ስምም እንደቄሮ ስም ጎልቶ ስሰማ እንደነበር ይታወሳል። የ2010 ዓ/ም የመንግሥት ለውጥን ተከትሎ የቄሮ ንቅናቄ እየተዳከመ ሲሄድ በተቀራንው የፋኖ ንቅናቄ እየተጠናከረ ሄዶ ነሐሴ 06/ 2013 ዓ/ም የአማራ ህዝባዊ ኃይል (የአማራ ፋኖ) በጎጃም ፍኖተ ሰላም ከተማ ተመሰረተ:: ለአማራ ህዝባዊ ኃይል ምሥረታው ቀዳሚ ምክንያት ነው የተባለውም የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መገስገስ መጀመር ሲሆን የድርጅቱ ስምም ከትግራይ መከላከያ ኃይል ጋር ተወደዳዳሪ እንድሆን የተሰየመ ነው:: የፋኖ መሠረታዊ ዓላማ የአማራ ሕዝብ ሕልውናን መጠበቅ ነው ቢባልም የመሬትና የሥልጣን ጉዳይም የፋኖ ዓላማዎች ናቸው። “የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጎጃም ፍኖተሰላም ሲመሰረት ዓላማዉም የአማራ ሕዝብ በህልዉና አደጋ ላይ መዉደቅ አንገብጋቢዉ ጉዳይ ከመሆኑ በተጨምሪ የአማራ ሕዝብ ወሳኝ የማንነት እና የአጽመርስት እንዲሁም የፖለቲካ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ እንዲያገኙ ሁሉም የአማራ ልጆች በአንድ የትግል ማዕከል ተሰባስበዉ ወሳኝ ትግል እንዲያደርጉ ነበር”7። እንደተመሰረትም ሕዝብን ማንቃት፣ ማደራጀት፣ ማሰልጠንና ማስታጠቅ የጀመረ ሲሆን ከመነሻው የራሱን ትይዩ መዋቅር ዘርግቶ መንግሥትን የመገዳደር ፍላጎት አሳይቶ ነበር:: በጥቅምት 2013 ዓ/ም የተጀመረው የትግራዩ ጦርነት የፋኖ አባላትን ለማሰልጠንና ለማስታጠቅ ጥሩ ዕድል ፈጠረላቸው :: በ2015 ዓ/ም የትግራይ ጦርነት እንድቆም የፌዴራል መንግሥቱና ሕወሐት ለድርድር ስጋጁ የፋኖ ኃይሎች መንግሥት የሚወክላቸው ተደራዳሪዎች የአማራን ጥቅም ያስጠብቃሉ ብለን አናምንም በማለት 1) ብ/ ጀነራል ተፈራ ማሞ 2) ዶ/ር ደስአለኝ ጫኔ 3) ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ 4) አቶ ቴወድሮስ ትርፌ በአባልነት የያዘ የራሳቸውን የአማራ አደራዳሪ ቡድን ሰይመው ነበር:: ጥቅምት 23 ቀን 2015 በፕሪቶርያ ስምምነት ተፈርሞ የሁለት ዓመቱ ጦርነት እንድቆም ስደረግ ፋኖዎቹ የእኛ ተወካዮች አልተሳተፉበትም፥ ፍላጎታችንም በስምምነቱ ውስጥ አልተካተተም በምል ቅሬታ አሰሙ::
በ2015 አጋማሽ ላይ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የልዩ ኃይል አደረጃጀቶችን መልሶ የማደራጀት ተግባር ሥራ ላይ ስውል የአማራ ልዩ ኃይልም እንደሌላው ክልል እንድፈርስ ስወሰን የልዩ ኃይሉን መፍረስ የተቃወሙ አባላት የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ)ን በብዛት ተቀላቀሉ:: የጦር መሣሪያውና የሰው ኃይሉ ብዛት እጨመረ ስሄድ የፋኖ በክልልና በማዕክል ደረጃ ሥልጣን የመውሰድ ፍላጎትም እየጨመረ መጣ፥ በሥልጣን መያዣ መንገድ ላይ ቁመው እንቅፋት ሆነዋል ወይም ሊሆኑ ይችላሉ ያሉትንም በጭካኔ መቅጣት ቀጠሉ:: ይህ አካሄድ ጎጂና አደገኛ በመሆኑ መቀልበስን ይፈልጋል::
ከደጋፊዎቻቸው ማቴሪያል የሆኑና ያልሆኑ ድጋፎችን ለማግኘት ወይም ግዛት በማስፋፋት ታሪክ ሰሪ ለመሆን የሌላውን ድንበር ጥሶ መግባት ወይም ወረራን መፈጸም: ሥልጣንን ከሕግ ውጭ በኃይል ለመውሰድ ከመሞከር እኩል ወይም የበለጠ አደገኛ ነው:: የሌላውን ክልል ወይም ብሔር ብሔረሰብ ድንበር ጥሶ ወረራን መፈጸም የሕዝቦችን ግጭት የሚፈጥርና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ መቀልበስ ይኖርበታል::
- ኦሮሞመማር ያለበት ትምህርቶችና መውስድ የሚገባቸው እርምጃዎች
ኦሮሞ ወደ አከባቢው ለሥራና ኑሮ የሚመጡትን የሌላ ክልልና የሌላ ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆችን እንደተለመደው በፍቅር ተቀብሎ አብሮ መኖርን መቀጠል ይኖርበታል:: ሆኖም ወደ አከባቢው የሚመጡ ሰዎች ከወንጀል ድርጊት ነጻ መሆናቸውን፥ ከነበሩበት አከባቢ መሸኛ ያመጡ መሆናቸውን፥ በአከባቢው መጥተው የሚሰሩት ሥራም ሕጋዊ መሆኑን: የአከባቢውን ነዋሪ ሕዝብ የማያውክ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸውዋል:: የኦሮሞ ሕዝብ የበለጠ ሊያጠቁት ለሚዘጋጁ ሽፍቶችና ወንጀለኞች አቃፊና መደበቂያ መሆን የለበትም:: አከባቢውም ሕገወጥ ታጣቂዎች ራሳቸውን የሚያደራጁበት፥ የሚሰለጥኑበትና የሚታጠቁበት መሆን የለበትም:: ኦሮሞ በሐሳብ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዴት ራሱን ለዛሬው ጥቃት ተጋላጭ እንዳደረገ ሂዴቱን ማስታወስ፥ እንዴት እዝህ እንደደረሰ፥ ምን ማድረግ እንደነበረበትና ምን ማድረግ እንዳልነበረበት ድርጊቱን መገምገም ይኖርበታል:: የአከባቢው፥ የቀጠናውና የዓለም አቀፉ እንቅስቃሴም ምን አንደሚመስልና ምን ይዞ ሊመጣ እንደምችል መገመትና ለዝያ መዘጋጀት ያስፈልጋል::
ኦሮሞንና ኦሮሚያን ከተጋረጠበት የፋኖ አደጋ ለመታደግ የሚከተሉት እርምጃዎች መወሰድ ይኖርባቸዋል:
- በአማራፋኖ ግንባር ቀደም ተጠቂ የሆኑ በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ወለጋ፥ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፥ የሰሜን ሸዋና የምሥራቅ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች- – በአማራ ጽንፈኛ ፋኖ ታጣቂዎች ባለፉት አምስት አመታት በኦሮሞዎች ላይ የደረሰውን ከእናንተ በላይ የሚያውቅ የለም:: ያላቸው ዕቅድና ዕቅዱን ለመፈጻም በማድረግ ላይ ያሉት ዝግጅት የበለጠ ጉዳት ሊመጣ እንደሚችል ግልጽ ነው:: በመሆኑም የአማራው ጽንፈኛ ፋኖ ኃይል መሬታችሁንም፥ ሃብት ንብረታችሁንም ወስዶ በአገራችሁና በቄዬአችሁ በሰላምና በክብር እንድትኖሩ የምፈቅድላችሁ አለመሆኑን አይታችኋል:: በመሆኑም በቻላችሁ መንገድ ሁሉ ወደቄዬአችሁ መጥቶ ከሚረብሻችሁ አሸባሪ ራሳችሁን መከላከል ይኖርባችኋል::
- ለመላውየኦርሞ ሕዝብ– የወለጋ ፋኖ ዕዝ ኦሮሞ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የዛሬ 450 ዓመት ነው፥ ወራሪና እንግዳ ነው በሚለው ትርክት ላይ ተመስርቶ የተቋቋመ መሆኑን በመግለጫው ውስጥ በግልጽ አስቀምጧል:: ወለጋ አያቶቻችን ያቀኑት (አስገብረው የያዙት) መሬታችን ነው፥ ስሙም ተለውጦ ዳሞትና ቢዛሞ መባል አለበት ብሎ አውጇል:: በተጨማሪም የፌዴራልና የክልል አወቃቀሩን በመጣስ ወደ ኦሮሚያ ክልል በኃይል ገብቶ ወደ ድሮ ሥርዓት ለመመለስ ባለው ፍላጎት የተነሳ “የወለጋ ግዛት” ወይም “የወለጋ ክፍለ ሀገር” እያለ ይጠራል:: የወለጋ አማራ ዕዝ የተቋቋመውም በሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የየራሳቸውን የአማራ ፋኖ ዕዝ እንዲያቋቁሙ ለማበረታትና ለመቀስቀስ ነው በማለት የዕዙ ሰብሳቢ አቶ ንጉሤ ዋለለኝ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአንከር ሚዲያ ላይ ቀርቦ በይፋ ገልጿል:: በመሆኑም የወለጋ አማራ ፋኖ ዕዝ በወለጋ ኦሮሞዎች ላይ ብቻ የተደቀነ አደጋ ሳይሆን በሁሉም የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተደቀነ አደጋ መሆኑን በማወቅ አደጋውን ለመቀልበስ መወያያትና አብሮ መሥራት ያስፈልጋል:: ፋኖዎቹ በ1996 ዓ.ም በድርቅ ምክንያት ከሐረር ተፈናቅለው በሆሮ ጉዱሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ሐርር ሳሞ እና ሐረር ጃርሶ ቀበሌዎች የሰፈሩትን ሰላማዊ የሐረር ኦሮሞዎችንም ቤት እያቃጠሉ፥ ንብረታቸውን እየዘረፉ ከቦታው እያፈናቀሉ አ ባረዋል::
- በወለጋና በሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች ለሚገኙ የአማራ ሕዝቦች– ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም የወጣው “የወለጋ ክፍለ፡ሀገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ)” ምስረታ መግለጫ “እኛ በቀድሞ ዳሞትና ቢዛሞ ግዛት በዛሬው ወለጋ ክፍለ ሃገር የምንኖር የአማራ ህዝቦች” በማለት በእናንተ በሕዝቡ ስም የወጣ መግለጫ ነው:: ይህ ኦሮሞን ከ450 ዓመት በፊት የመጡ እንግዶች የሚል፥ የአገራቸውን ስም ቀይሮ “ዳሞትና ቢዛሞ” የሚል፥ ኦሮሚያን አያቶቻችን “ያቀኑት” ብሎ የድሮ ቁስልን የሚነካካ፥ የፌደራሊዝሙንና የክልል አወቃቀሩን የሚጥስ: በስማቸሁ የወጣ የአቋም መግለጫ የእናንተ አቋምን ይገልጻል ብሎ ማመን ያስቸግራል:: ሆኖም ግን በተደራጀ ቡድን ተወካዮች በመገናኛ ብዙሃን በይፋ የተነገረ በመሆኑ አይደለምም ብሎ ለመውሰድ ያስቸግራል:: ይህ የፋኖ ድርጊት ሰፊውን የአማራና የኦሮሞ ሕዝብን ወደ ግጭት የሚገፋፋ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ፥ በግልም ሆነ በጋራ እንድታወግዙት እናሳስባለን:: የአማራ ጽንፈኞች ወጣቶችን መልምለው፥ አበል ክፍለው ከአማራ ክልል አዲስ አበባ አስገብተው ለመረበሽ ካደረጉት ሙከራ የበለጠ ወደ ኦሮሚያ አስገብተው ለመረበሽ ሞክረዋል:: የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦችን ለማጋጨት ለፖለቲካ ዓላማቸው ብለው ሕዝብ የሚያፈናቅሉና የተፈናቀሉት እንዳይመለሱ የሚያደርጉ የአማራ ተወላጆችንና ቡድኖችን ማጋለጥ ያስፈልጋል::
- የኢትዮጵያፌዴራል መንግሥት — የፋኖ የትጥቅ እንቅስቃሴ ከአማራ ክልል መንግሥት አቅም በላይ በመሆኑ የፌዴራል መንግሥቱ የመከላከያ ኃይል እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠርና አደጋውን በመቀልበስ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ወደ ክልሉ ተሰማርቶ በመሥራት ላይ መሆኑ ይታወቃል:: ሆኖም ግን የጽንፈኛው ኃይል በአማራ ክልል እያረፈበት ያለውን ምት ለመሸሽ ወደ ኦሮሚያ ክልል እየገባና መሰረት እየጣለ ይገኛል:: በመሆኑም ይህ ታውቆ በፍጥነት አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድበትና ከኦሮሚያ ተጠራርጎ እንድወጣ ማድረግ ያስፈልጋል:: የጽንፈኛው ኃይል እዝህ የደረሰው በመንግሥት ሥልጣን ላይ ካሉ አማራዎች በተደረገላቸው ድጋፍ፥ ከውጭና ከአገር ውስጥ በምደረግላቸው የሎጂስቲክ ድጋፍ መሆኑን ገልጿል:: የመንግሥት ክፍተኛ ባለሥልጣን የነበረውና መንግሥት ፋኖ ላይ የወሰደውን እርምጃ በመቃወም ሥልጣኔንና ኢትዮጵያን ትቼ ወደ አሜሪካ ተሰደድኩ ያለው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህንን አባባል ያጠናክራል፥፤ በመሆኑም የፌዴራል መንግሥቱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሁነው ለዝህ ሕገ ወጥና ጽንፈኛ ቡድን ድጋፍ የሚሰጡትን ተከታትሎ የእርምት እርምጃ መውሰድና ከውጭና ከአገር ውስጥ የሚተላለፈውን የገንዘብና ሎጅስቲክ ፍሰት ለማቆም እርምጃ ወስድ ይኖርበታል::
- የኦሮሚያክልል መንግሥት — እነዝህ የአማራ ፋኖ ጽንፈኞች ጦርነትን፥ ሁከትንና ሽብርን ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል የማስገባት ዕቅድ ይዘው ወለጋ ላይ የተደራጁ መሆኑ ይታወቃል:: ስንዝር ስሰጣቸውም ክንድ የሚጠይቁ አልጠግብ ባዮችና ትምክህተኞች መሆናቸውም ግልጽ ነው:: የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እስከ አሁን የአማራ ፋኖን ከኦሮሚያ ጠራርጎ ለማውጣት የቋንጃ ቁስል ሆኖ ቆይቷል ያሉት እንቅፋት በእነ አቶ ሰኚ ነጋሳ ከክልሉ መንግሥት ጋር ተስማምተው የትጥቅ ትግል አቁመው መግባት እንደተወገደ ይገመታል:: በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ድንበር/ ወሰን የማስከበርና በክልሉ ውስጥ የሕዝቡን ሰላምና ደንነት የመጠበቅ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል:: የፋኖ ዓላማ መሬት መውረር፥ ሀብትና ንብረት መዝረፍ ብቻ ሳይሆን የመንግሥት መዋቅርንም አፍርሶ የመቆጣጠር መሆኑ መታወቅ አለበት:: ስለዝህ ሳይቃጠል በቅጠል ማለትና በሩቁ ማክሸፍ ያስፈልጋል:: ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነውና የክልሉ መንግሥት መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ሕገ ወጥ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት፥ የክልሉ ሕጋዊ ነዋሪ ያልሆኑ ሀብት ለመዝረፍና ሁከት ለመፍጠር ወደ ክልሉ በዘመቱት ላይ ሕጋዊ አርምጃ መውሰድ ለወደፊትም ወደ ክልሉ ለሥራና ለኑሮ የሚሄዱ ግለሰቦች መከተል ያለባቸውን ሕጋዊ ሥርዓት ማበጀት ይሆርበታል:: የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሰላምና ጸጥታ እንዲያስጠብቅ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 52(ሰ) የተጣለበትን ግዴታ መወጣት ይኖርበታል::
- በኦሮሞናበኦሮሚያ ስም የምንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች– የወለጋ አማራ ፋኖ ዕዝ መቋቋም ፋኖ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ግልጽ፥ተጨባጭና ሊሆን የሚችትል አደጋ መደቀኑን ያረጋግጣል:: አደጋው የፖለቲካ አመለካከትን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ሁሉንም የኦሮሞ ሕዝብ አባል እንደ ኦሮሞ ሊጎዳ የምችል ነው:: ፋኖ የሚመራባቸው ትርክቶች ፈጣሪዎች እንደአቀዱትና እንደምመኙት ተአምር ተፈጥሮ ኦሮሞን የኛ ብቻ ነች በሚሏት ኢትዮጵያ ውስጥ 450 ዓመት ለኖረበት ግብር አስከፍለው መጣ ወደሚሉት ኬኒያ፥ሶማሊያና ማዳጋስካር ቢያባርሩ ወይም በኃይል አባረው ወደ ሕንድ ወቅያኖስ ቢጨምሯቸው እናንተ በድርጅታቸሁ አባልነት የምታደራጁት፥ የሚታስተዳድሩት ወይም ነጻ የሚታወጡት ሕዝብ አይኖርም ማለት ነው:: የተደራጁና የታጠቁ ኃይሎች ሕዝብ አፈናቅለው በማባረር መሬታቸውንና ሀብት ንብረታቸውን እንደሚቀሙ ከማይናማር ከተባረሩ የሮህንጋ ሕዝቦችና ከፊልስጤም ከተፈናቀሉ አረብ ፊልስጤማውያን አይተናል:: ከኦሮሚያ ክልል ኪረሙ፥አሙሩ፥ደራና ፈንታሌ ወረዳዎች ከቄዬአቸው በኃይል ተፈናቅለው መሬታቸው ከሌላ ክልል በመጡ ታጣቂዎች በመያዙ መልሰው ማግኘት ያልቻሉ የኦሮሞ ተፈናቃዮችም አደጋው የኦሮሞ ሕዝብንም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያጋጥም እንደሚችል ማሳያ ሆነዋል:: ስለዝህ አያጋጥምም ከማለት ሊያጋጥም ይችላል ብሎ መዘጋጀቱ አስፈላጊ ነው::
እ. አ. አ. በ1931 የጃፓን ወራሪ ኃይል የጃፓን አንድ የጦር ክፍል መሪ የሆነው ሉቴናንት ሱኤሞሪ ካዋሞቶ የተባለ ሰው በቻይና ማንቹሪያ ውስጥ በጃፓን በሚተዳደር ባቡር ጣቢያ ላይ ፈንጂ እንዲያፈነዳ በማድረግ፥ ራሳቸው ያፈነዱትን ፈንጂ ምክንያት በማድረግ የጀፓንን የባቡር መስመርና ጥቅም እንጠብቃለን በማለት ቻይናን ስወሩ: እርስበእርስ ሲዋጉ የነበሩት በቻይና የመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበረው የቻይና ብሔርተኛ ፓርቲ (ኮምንታግ) እና ኮምንታግን ክሥልጣን ለማውረድ በሽምቅ ስዋጋ የነበረው የቻይና ኮሙኒስት ቀዩ ጦር ግዜያዊ ሰላም አውርደውና ትብብር ፈጥረው ወራሪውን የጃፓንን ጦር ከአገራቸው ለማባረር ችለዋል:: የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ከኮምንታግና ከቀዩ ጦር ልምድ ትምህርት ወስደው የመጣባቸውን የጋራ ጠላት በጋራ መመከት ይኖርባቸዋል:: የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጊዜ፥ ቦታና ሁኔታ በፖለቲካ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ተረድተው እንደጊዜው፥እንደሁኔታውና እንደቦታው የፖለቲካ አካሄዳቸውን መቃኘት ይኖርባቸዋል::
- የኦሮሞናየኦሮሚያ ልሕቃን –የአማራ ልህቃን በተለያዩ ዘርፎች ትርክቶችን ፈጥረው በቃል፥ በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በማሰራጨት፥ የትርክታቸው ማስፈጸሚያ ፕሮጄክቶችን ቀርጸው፥ አስፈጻሚና በጄት መድበውላቸው በመተግበር ላይ ይገኛሉ:: የአማራ ፋኖ አንዱ የትርክታቸው ማስፈጸሚያ ፕሮጄክት ነው::የኦሮሞ ልህቃን እነዝህ በየጊዜው የምፈበረኩትን የውሸትና አደገኛ ትርክቶችን ተከታትለው ማክሸፍና ተጸራሪ ትርክት ፈጥረው መልቀቅ ይኖርባቸዋል:: እነዝህ ትርክቶችና ተጻራሪ ትርክቶች የፕሮፓጋንዳና የካውንተር ፕሮፓጋንዳ መርህን ተከትለው መካሄድ ይኖርባቸዋል:: በኦሮሞ ምሁራን መካከል የፖለቲካ አስተያየትን/መስመርን ተከትሎ የሚታየው ልዩነት ጠቦ በጋራ ጠላት ላይ በጋራ ማተኮር ጊዜውና ሁኔታው የሚጠይቀው ጉዳይ ስለሆነ ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው::
- ማጠቃለያ
የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ድጋፍ ሰጭ ግብረ ኃይል መሪ የነበረው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በኦገስት 2023 በዩ. ኤስ. ኤ. ኮሎራዶ ከተማ የአማራ ፋኖ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ የወለጋ አማራ ተነስቷል፥ እኛ ልንረዳቸው ይገባል በማለት የፋኖ እንቅስቃሴ ወለጋ ውስጥ መኖሩን በመግለጽ የወለጋው የአማራ ፋኖ ዕዝ ሊቋቋም እንደምችል ፍንጭ ሰጥቶ ነበር:: የወለጋ ፋኖ ዕዝ መመሥረት የጎጃሙ አማራ ፋኖ ከተመሰረተበት ከነሐሴ 06/2013 ዓ/ም 3 ዓመት ከአራት ወር በኋላ፥ የትግራዩ ጦርነት በፕርቶሪያው የሰላም ስምምነት በመጠናቀቁ መንግሥት በአማራ ክልል ያሉ ኢመደበኛ ታጣቂዎች እንዲፈቱ እና እንዲበተኑ በመወሰኑ ትጥቅ አንፈታም ያሉት ታጣቂዎችና የመንግሥት ኃይሎች ሐምሌ ወር 2015 ዓ/ም መጨረሻ ግጭት ከተነሳበት ጊዜ ደግሞ አንድ ዓመት ከአራት ወር በኋላ ታህሳስ 8/2017 ይፋ የሆነ ቢሆንም ላለፉት አምስትና ስድስት አመታት ወለጋ ውስጥ በሻምበልና በሻለቃ ተደራጅቶ በተለያዩ አከባቢዎች ውስጥ በተናበበ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ችግር ስፈጠር ነበር:: በወለጋ የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት በሌሎች ቦታዎችና ሕዝቦች ውስጥ ማደራጀት እንደሚቀጥል የወለጋ ፋኖ ዕዝ ሰብሳቢ ንጉሤ ዋለልኝም፥ የጎጃም አማራ ፋኖ ሰብሳቢ ዘመነ ካሴም ገልጸዋል:: አቶ ዘመነ ፋኖ ከውጭ አገር ኃይሎች ጋርም እየሰራ መሆኑን አምኗል:: የጎጃሙ አማራ ፋኖ በጦርነት ላይ የማረካቸውን እንደ ሌተናል ኮሎኔል ያሬድ ኪሮስ የመሳሰሉትን ወታደሮች ለተለያዩ አካላት በመሸጥ በጎጃም መሸንቲ መምህራንን በጎጃም መሸንቲ መምህራንን በማፈን፥ ጋዜጠኛ በማፈን ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ በማስከፈል ገቢ የሚያመነጭ ወንጀለኛ ቡድን ነው::
አሁን አገር እያመሰ ያለው የፋኖ እንቅስቃሴ መታወቅ የጀመረው በ2017/2008 ዓ/ም በአማራ ክልል ውስጥ በተቀሰቀሰው ፀረ- መንግሥት የተቃውሞ ሰልፍ ጊዜ ሲሆን እንቅስቃሴውም ሲደረግ የነበረው ልክ እንደ ኦሮሚያው የቄሮ እንቅስቃሴ ባልታጠቁ ወጣቶች ነበር። የታጠቀው እና በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው ፋኖ በአብዛኛው የተመሠረተው እና ያለበትን ቅርጽ የያዘው፣ በክልሉ ውስጥ እና ከክልሉ ውጪ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙን “ጥቃቶችን ለመመከት” በሚል በተሰባሰቡ ግለሰቦች ከ2010 ዓ/ም ወዲህ ነው:: ዓላማውን ለማሳካት የመረጠው የትግል ሥልት ደግሞ የትጥቅ ትግል ነው:: ለፋኖ ወደ ትጥቅ ትግል መግባት የመግሥት አስትዋጽኦ መኖር አይካድም:: የየጎጃም ፋኖ ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆነው አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ እንደገለጸው የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በገቡበት ጊዜ የአማራ ክልል መንግሥት ፋኖ ለሚባለው አደረጃጀት በሚዲያ ጥሪ አድርጎ እውቅና እየሰጠ ያታግልም ነበር። ነገር ግን መንግሥት ትግሉን የሚፈልግበት ዓላማ እና እኛ ፋኖዎች የምንፈልግበት ዓላማ የተለያየ ነበር ብሏል::
ፋኖ የምመራበት ትርክትና አካሄድ የመግሥት ሥልጣንን በኃይል ወስዶ ብቻ የሚያቆም አይደለም:: የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በትግላቸው ያገኙትን ራስን በራስ የማስተዳደር፥በቋንቋቸው የመጠቀም፥ ባሕልና ታሪካቸውን የማሳደግ፥ የመረጡትን ሃይማኖት የመከተል መብት ነጥቀው ወደ ፊውዳላዊ ሥርዓት ልመልሱት ይፈልጋሉ:: ይህ አደጋ እንዳይደርስ ሁሉም የፋኖን እንቅስቃሴ ለማክሸፍና ለመቀልበስ መተባበር ይኖርበታል::
አባሪ 1: ማጣቀሻዎች
- Resettlement, Food Security and the Problem of Forest Resource Depletion in Western Ethiopia: The Case of Angar Gutin Resettlement Site in Eastern Wollega, By Zelalem Teferra1
- Relief and Rehabilitation Commission Establishment Proclamation No. 173/1979. 1979. pdf
- ፋኖልሳን Fano Lisan – የወለጋ ክፍለ-ሀገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) ምስረታን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ – Fano Lisan
- International Fano Coordinating Committee (IFCC), የማይጠይቅትውልድ” የፖለቲካ ኑዛዜ በአዲስ አመት ( ክፍል 2 ) | ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም.
- ዳንኤልክብረት “የትርክት ዕዳና በረከት” 2016 E.C.
- Katharine Houreld, Rebel or bandit? His life illuminates Ethiopia’s hidden insurgency. The Washington Post, May 21, 2023 Ethiopia insurgency in Oromiya region a threat to country’s stability – The Washington Post
- አንተነህ ሽፈራዉ: የአማራፋኖ አንድነት እንዴት፣ በማን እና መቼ? August 18, 2024 የአማራ ፋኖ አንድነት እንዴት፣ በማን እና መቼ??
አባሪ 2: በአማራ አስተዳደር ሥር እንድሆኑ የተጠየቁ ሃያ የወለጋ ወረዳዎች ዝርዝር
