January 5, 2025
1 min read

ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ”

 


 

1 Comment

  1. የሃበሻ የብሄር ሰካራም ፓለቲከኞች የዝንተ ዓለም ግብግብና መላላጥን ለመረዳት ብዙ ሞክሬአለሁ። ሰው እንዴት ተንጋሎ ሲተፋ ትፋቱ ከራሱ ላይ እንዳረፈ መረዳት ይሳነዋል? አሁን በትግራይ ውስጥ የምናየው የእብደት ፓለቲካ፤ በአማራ ክልል ያለው እንዘጥ እንዘጥ፤ በኦሮሞ ሃይሎች ያለው የእርስ በእርስ ሽኩቻና ነጻ እናወጣሃለን የሚሉትን ህዝብ ማስራብና ማሳደድ ረጋ ብሎ ላየው እብደት እንጂ ጤና እንዳልሆነ በቀላሉ ይረዳል። ታዲያ በዚህ ዙሪያ ላይ ሳይንሱ ምን ይለናል? የፓለቲካ ሳይንሱን እሳት ጨምሩት፡ የዋልጌዎች ትምህርት ነው። ፓለቲካ ሳይንስ ተምሬአለሁ የሚለን አቶ ጃዋር ለዚህ ክስተት ዋንኛ ማሳያ ነው። ቀለሙን እየለዋወጠ ይዘላብዳል። መማር ብቻውን ሰውን ወደ እውነት አያስጠጋም። እንዲያውም በስማቸው አካባቢ ዶ/ር፤ ኢንጂኒየር፤ ፓስተር፤ ሃዋሪያ፤ ቄስ፤ ሃጂ ወዘተ የሚሉት ሁሉ ለራስ መኖርን የሚያስቀድሙ፤ የሌላው እንባ የማይረዳቸው በጎጥና በጎሳቸው አስመሳይ ፍቅር የታሰሩ የቁም ሙቶች ናቸው።
    እኔ ሳይንስ የምለው Neuroscienceን ነው። ጭንቅላቱ ተቆርጦ ሲራመድ ያየነው የለምና ማለቂያው እሱ ነው። በዚህ ሳቢያ አንዳንድ Psychiatrists በዓለም ዙሪያና በሃገራችን ስላለው ጉዳይ ሳጫውታቸው እንዲህ አሉኝ። አሁን ላይ “Delusional Disorder” የሚያጠቃቸው መሪዎች በዝተዋል። እነዚህ ግለሰቦች በእውቀት የላቁ ወይም ያነሱ፤ በህብረተሰብ መካከል አንቱ የተባሉ ያለያም ለይቶላቸው ሰው የሚሸሻቸው ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህ በሽታ የሚጠቁ ሰዎች ከእነርሱ ውጭ ሌላ በጎ የሚያስብ እንዳለ አድርገው አያምኑም። ሞኝ የያዘውና ወረቀት የያዘው አንድ ነው እንዲሉ ወረቀቱና ሞኙ ሲጠፉ ብቻ ነው ነገርየውም አብሮ የሚያከትመው።
    ዛሬ ላይ ሰው ለመዘላበድ መንገድ ብዙ ነው። በተለይም Artificial intelligence (AI) ከሰው ተምሮና ራሱን አስተምሮ ይኸው እንሆ የሰውን ድምጽ አስመስሎ፤ ፎቶውን አጣሞና ያልሆነውን ሆነ ብሎ እያቀረበ እውነቱን ከፈጠራው ለመለየት እየተሳነን ነው። በቅርቡ ቴዲ አፍሮ፤ አስቴር አወቀ፤ ጂጂና ሌሎችም ዘፋኞች ስለ ፋኖ ዘፈኑ ተብሎ የቀረበው ዘፈንም የዚህ ቅመር ውጤት ነው። ያልገባው ሆይ ሆይ ሲል፤ የተረዳው ደግሞ አድነኝ በማለት ራሱን ያማትባል። አማቺው የዚህ ዓለም የስልጣኔ ዘርፍ ከሩቅም ከቅርብም የሰዎችን መብት ለመርገጥ፤ ጠላትን ተኮሶና ሳይተኩሱ ለመግደል መንገድን አመቻችቶታል። ግን ይህ ስልጣኔ ተብሎ ሲዘከር ሰው ደንዝዞ አሜን አሜን ይላል።
    ኢትዪጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም ነው። የሰላሟ እንቅፋቶች ደግሞ ብዙ ናቸው። ያኔ ድሮ ሰው በባዶ እግሩ ሲሄድ የነበረን ስብዕናና ልዕልና ዛሬ የለም። ሁሉም ነገር አስረሽ ምቺው ሆኗል። ሰውን የሚለብሰው የሚለውጠው ቢሆን ኑሮ ባለ ገበርዲንና ከረባቶቹ ሃገርን ባላወኩ ነበር። ህመማችን የጭንቅላት ነው። እስቲ ስሙት በትግራይ አለም ገብረዋህድ የሚለውን? እስቲ ረጋ ብላችሁ የጃዋርን መጽሃፍ አንብቡና በየከተማው እየዞረ ከሚናገረው ጋር ዛሬና ትላንቱን መዝኑት? ፍሬ ነገር አለው? እርስ በእርሱ አይማታም? ለኦሮሞ ህዝብ ይጠቅማል? እናንተው ፍረድ!
    ስለ ሰላም አስፈላጊነት ስንናገር ተከፋይ፤ የብልጽግና ካድሬ፤ ፎቅ የተሰጠው ወዘተ እያሉ ስም የሚለጥፉልን ድውያን ፓለቲከኞች አንድም እውነት የላቸውም። ሰው ስለ ሃገሩ መንግስትንም ተቃዋሚዎችን ሳይደግፍ መጻፍ፤ መናገር አይችልም ያላቸው ማን ይሆን? ሃገርና ህዝብን መውደድ ከዘርና ከቋንቋ ከክልል ጋር አይገናኝም። ማሰሪያው ሰው ሆኖ መገኘት እንጂ! ለዚህ ነው ነገር ሁሉ በጦርነት ይፈታል የሚለውን ሃሳብ ጭራሽ የማልስማማበት። ጦርነት ውስጥ የገባ ህዝብ የሞተው ሞቶ የቀረው ቆሞ ሲንገዳገድ የማይታይ የዝንተ ዓለም ጠባሳ በህሊናውና በአካሉ ላይ እንደሚኖር መረዳት ያስፈልጋል። የገደለም ገዳይም ሁለቱም የሞቱት ያኔ ነውና! እውቁ ጸሃፊና በቫዪኬምስትሪ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የነበረው Isaac Asimov ስለ ግጭት ሲናገር”Violence is the last resort of the incompetent.” ብሎናል። ለዚህ ነው የህዝባችን መከራና ሰቆቃ የማያባራው።
    በመጨረሻም Ethio Forum በወያኔ ፍቅር የተለከፈ ለመሆኑ የሴራ እርካብ፤ የደም መንበር የሚለውን መጽሃፍ ማንበብ ለበለጠ መረጃ ይጠቅማል። የጠፋው ሚዛናዊ የሆነ ድህረ ገጽና መጣጥፍ እንጂ በሬ ላም ወለደ ወሬማ ድሮም እንሰማው የነበረ ነው። የሰው መኖሩ የሚለካው በሚታይ በሚዳሰስ በሚዘገን ነገር ላይ ተመርኩዞ ሰው ሆኖ ሲገኝ ነው። ለብዙዎች ግን መኖር ከራስ ወዲያ እየሆነ ይኸው በውጭም በሃገር ቤትም ሰውን ያምሳሉ። ይብላኝ ለእናንተ ኖርን ብላችሁ ለምትሞቱት! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop

Don't Miss

251796460 1294644667631451 5867229753062882010 n

አርማሽ ይውለብለብ !

አርማሽ (ቀና በል) አዝማች: አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ