“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)
4 Comments
Leave a Reply
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ
ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ
እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! –
“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) (ታህሳስ 19፣ 2017) December 28, 2024 መግቢያ እንደተነገርን ኢትዮጵያን “ከዕዝ ወይም ከሶሻሊስታዊ” ኢኮኖሚ አላቆ ወደ “ ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ” እንድትሸጋገር ከተደረገ ይኸው ከ31 ዓመት በላይ ሊያስቆጥር ነው። በጊዜው ስልጣንን የተቆናጠጠው የህወሃት አገዛዝ
ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት መሰረት የሚጥል ህግ፣ ወይስ የኢትዮጵያን ሀብት የሚያዘርፍና ህዝብን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ አዲስ የባንክ ህግ- ከኒዎ-ሊበራሊዝም ወደ ባሰ ኒዎ-ሊበራሊዝም የዝቅጠት ጉዞ!
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)
መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል
“መካር የሌለው ንጉስ እንዳይሆኑ” ፤ ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተፃፈ አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም
“መካር የሌለው ንጉስ እንዳይሆኑ” ፤ ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተፃፈ አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ጊዜው ይከንፋል፡፡ ይሄውና ከዘመነ ወያኔ ድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ወደ ለዬለት ሲዖል ከገባን ድፍን ስድስት ዓመት ከስምንት ወር ከ11 ቀናት ሆነን – ዛሬ ታኅሣስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም፡፡ የሲዖላዊው መርዶ
YAmaran hezb maleteh newu? Gedu,Juwars,Bekele Gerba,Yayeh sewu Shimles, Bekalu Alamrewu,Berhanuley Nega,Belete Mola yemisetuachihun eyebelachihu btedebqu yishalachihual.
ከሰሞኑ አቶ ገድና ጃዋር በየፊናቸው ቱልቱላ ይነፋሉ። የሚያስገርም ነው። ለነገሩ በሁለቱ መካከል ያለው ልዪነት በRiver Rat (Water rat) እና በBeaver እንስሳት መካከል እንዳለው ነው። ሁለቱም መሰሪዎች ናቸው። የሚያወሩትና የሚለፉት በጥቂቱ ይለያይ እንጂ ገድና ጃዋር ስልጣን ናፋቂዎች ናቸው። የሁለቱ አይጥ መሰል እንስሳትም ተግባር መሰርሰርና ውስጥ ለውስጥ መጓዝ ነው። ጃዋር የፓለቲካ ሳይንስን ተምሬአለሁ በማለት ባልተማረ ህብረተሰብ መካከል ቆሞ የአኖሌን ሃውልት ተደግፎ ፎቶ የሚነሳ ደንቆሮ ነው። አኖሌ ሰዎች እንዲጨራረሱ ሆን ተብሎ በብሄር ፓለቲካ በጠነበሩ የኦሮሞ የዝንት ዓለም አልቃሾችና በወያኔ ሴራ የቆመ የፈጠራ ሃውልት ነው። ዓለም እየጨለመበት እያለ እነዚህ የፓለቲካ ውታፎች ከያሉበት ስርቻ ብቅ ብቅ በማለት ዛሬ ድምጻቸው እንዲሰማ የሆነበትን ሁኔታ ስፈትሽ ጥቂት ነገሮች ትውስ አሉኝ። 1. የብልጽግናው መንግስት የንግስና ማብቂያ ዓመት በመሆኑ – እኔን ስሙ ለማለት 2. በዚህም በዚያም የውጭ ሃይሎች ክፍያና ግፊት በመታከሉ 3. በሃገርና በውጭ ያሉት የት ገባችሁ ለሚሏቸው አለን ለማለት የራስን የመኖሪያ ብልሃት ካሳመሩ በህዋላ የሩቅ ተዋጊ ለመሆን የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ነው። ሌላው ሁሉ አሻሮ ሃሳብ ነው።
እውቋ ጋዜጠኛ ቤተልሄም ታፈሰ እንዳስቀመጠችው ጀዋር ፈሪና ነገር አደባላቂ ሰው ነው። ተከበብኩ ድረሱልኝ በማለት ያስጨረሳቸው ንጽሃን ዜጎች ደም ለፍትህ እየጮኸ “አልጸጸትም” የሚል የአፍ ጀብደኛ በተግባር ግን የሌለበት በየጊዜው የፓለቲካ አቋሙንና ቀለሙን የሚቀያይር ሰው ጀዋር ማለት እሱ ነው። ከእስር ቤት ከወጣ በህዋላ እይታውን ሁለገብ አድርጎ፤ የሰላም መንገድን ተከትሎ፤ ባለፈው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሰራውን በደል አራግፎ ሰው ይሆናል ስንል ራሱን ናይሮቢ ላይ አስጠግቶ እንሆ አሁን ደግሞ በጀርመንና በሌሎች ከተሞች በመገኘት ለደነዘዘ ህዝብ ይዘላብዳል። ለመሆኑ በማን ፓስፓርት ነው ጀርመን የገባው? የአሜሪካ ፓስፓርቱን መልሷል ተብለን አልነበረም። ግን አሜሪካኖች የሚታመኑ አይደሉም። የወያኔ መሪዎችን ለማይሰምር የሰላም ድርድር በራሳቸው ወታደራዊ አውሮፕላን በየስፍራው እንደ ታክሲ ሲያመላሉሷቸው የነበሩት ለኢትዮጵያ አስበው አልነበረም። ሌሊት ሌሊት በሱዳን በኩል ከግብጽ የተላከ የጦር መሳሪያ በአውሮፕላን ትግራይ ውስጥ ሲራገፍ ደጋፊዎች ነበሩ። ያው የኢትዪጵያ አየር ሃይል በለስ ቀንቶት አንድን መቶ ከጣለ በህዋላ ነገሩ ቆመ እንጂ! አሁንም ወያኔ በድንበር በየብስ መሳሪያ በማጋዝ ላይ ይገኛል። አሜሪካኖች በወያኔ ዘመን ወያኔዎች ያደረጉላቸውን ውለታ ለመመለስ በጦርነቱ ጊዜም ሆነ አሁን ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም! ለጀዋርም በስውር ፓስፓርቱ ተመልሶለት ይሆናል። የጥቁር ህዝቦች እንዲበለጽጉና በሰላም እንዲኖሩ ነጩና ዓረቡ አለም አይፈልግም። ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች እድል ፈንታ ሁለት ነው። ሞትና ግዞት! የድሃ አድግ ልጆችን ለመከራ ማግዶ በውጭ ሃገር በሰርቁትና ከውጭ ሃይሎች በተቀበሉት ገንዘብ መኖር። ግን ያ መኖር ሳይሆን በቁም መሞት ነው። ለገባው የሃበሻ ፓለቲካ እቦጭ ነው። የውሃ ወቀጣ። አንድ ግን ሌላ አማራጭ የማይገኝለት መንገድ የሰላሙ መንገድ ብቻ ነው። መገዳደሉን አይተነዋል። የብሄር ነጻነት ታጋዮችንም አይተናቸዋል። የእድሜ ልክ ጨካኝ መሪዎች ሲሆኑ፤ ለራሳቸው እንጂ ለህዝብ የማይገዳቸው የማፍያ ስብስብ እንደሆኑ። ጦርነት የእብዶች የእውቀት መለኪያ ማስመሪያ ነው። 12 ኢንች ብቻ! አርቆ ማየት የተሳነው!
የብሄር ፓለቲከኞች በጥቅሉ ድውያን ናቸው። ከላይ በቪዲዪው የበለጠ ይደራጃል፤ ወደ ኋላ አይልም። እየተናፈቀ እየተጠበቀ ነው የሚባለው የፋኖ ክምችት ነጻ አወጣሃለሁ የሚለውን ህዝብ መከራ ውስጥ የዘፈቀ፤ የጠራ የፓለቲካ ጥያቄ የሌለው፤ እርስ በእርሱ የሚሸራገድ የቀማኞች ስብስብ ነው። ይህ ማለት በአማራ ህዝብ ላይ ግፍ በወያኔም በብልጽግናውም አልተሰራም ማለት አይደለም። የአማራ ህዝብ ተለይቶ ተጠቅቷል። እየተጠቃም ነው። ግን በአማራ ክልል ነፍጥ አንስቶ ት/ቤትና መንገድ ዘግቶ የአማራን ህዝብ ወደኋላ መልሶ አማራን ነጻ እያወጣን ነው ማለት መጃጃል ነው። ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም። በዘር የተሳከረው የሃበሻ ፓለቲካ ሳይደርሱብኝ የሚበቃኝ ልያዝ እያለ ይኸው መንገድም፤ ት/ቤቱም፤ የመገናኛ አውታሩም የሚሰራው በሌሎች ክልሎች ሆኗል። ስለዚህ ፋኖና ብልጽግና በጋራ የአማራን ህዝብ አግተው እንደያዙት ቁልጭ ብሎ ይታያል።
በመጨረሻም የትግራይ ህዝብ የይቅርታ ጋጋታ አይደለም የሚፈልገው የሚበላው ዳቦና ሰላምን እንጂ። የትግራይ ህዝብ መከራ ወያኔ ራሱ ነው። ወያኔ እያለ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም። ለማን ተብሎ ነው በወርቅ ፍለጋው ሳቢያ መሬቱ እየታረሰ፤ ያለምንም Land Remediation and Rehabilitation እቅድ አፈሩ፤ እንስሳትና እጽዋት እየተመረዙ ያሉት? የትግራይ ህዝብ ከምሲን ይደርሰዋል? መንገድ፤ ት/ቤት፤ የህክምና ተቋም እነዚህ ቆፋሪዎች ሰርተውለታል? ግን የወያኔ መሪዎች ዛሬ በአውሮፓ/በሰሜን አሜሪካ በየሥርቻው ተሸጉጠው በዘረፉት የሃገር ሃብት ሲፍነሸነሹ ማየት መፈጠርን ያስጠላል። የትግራይ ህዝብ የገድ አንዳርጋቸውንም ሆነ የማንንም ይቅርታ አይፈልግም። በሰላም ሰርቶ ጥሮ ገሮ እንዲኖር ግን ወያኔ መጥፋት አለበት። የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራም፤ ሻቢያም፤ ብልጽግናም አይደለም። ወያኔ ሃርነት (ባርነት) ትግራይ እንጂ! በቃኝ!
ጎበዝ ችሎታ ያለው ሰው የጁዋር መሃመድን መጽሃፍ (ተረት) ኮፒ አድርጎ በኢንተርኔት ቢለቀው መልካም ነው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ የመሰለች ብዙ ታሪክና ባህልም ያላት አገር በፖለቲካ ስም የሚነግድ ሰው እየተነሳ ሲዘላብድ፣ በተለይም አማራውን እወክላለሁ በማለት የባጡን የቆጡን ሲዘላብድ መስማት በጣም ያበሳጫል። ደርጉ አንዳርጋቸው ከደመቀ ጋር በመሆን በወጣትነት ጊዜው በህወሃት ተመልምሎና የእነሱ ካድሬ በመሆን ወያኔ 27 ዓመት ያህል ስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን እንደ ጓደኞቹ ወያኔን ያገለገለ ነው። ወያኔ ስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን በአማራውም ሆነ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሲፈጽም አብሮ የተባበረና ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንድትገኝ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካደረጉት ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ነው። በአጠቃላይ ሲታይ ገዱ አንዳርጋቸውና ጓደኞቹ የአማራውን ክልል በሚያስተዳድሩበት ዘመን ሰፊውን የአማራ ህዝብ የሚጠቅም፣ እንደሰው እንዲኖርና ራሱንም እንዲችል የሚያደርገው አንዳችም የልማት ስራ አልሰሩም። በአንፃሩ ራሳቸው የሆቴልቤት ስራ እንዲስፋፋ በማድረግና እዚያ ገብተው በመዝናናት እንወክለዋለሁ የሚሉት የአማራ ህዝብ የተቦጫጨቀ ልብስ ለብሶ ሲሄድ ይታያል። እንደ ኦርቶዶክ ሃይማኖት የመሳሰሉት ተቋማት በአንዳንድ መነኩሴዎች ጥረት ራቅ ያሉና በቀላሉ ሊደረስባቸው የማይችሉና ጥንታዊ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት ባሉበት አካባቢ ሰፊው አማኝ ህዝብ በቀላሉ በመጓጓዣ መጥቶ በሃይማኖት ስርዓት ላይ ይካፈል ዘንድ መንገድ ይሰራልን ብለው ሲያመለክቱ አይቻልም በማለት በአካባቢው የልማት ስራ እንዳይካሄድ ያደረጉ ናቸው። ከዚህም በላይ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ሰፋ ያለ የገበያ ቦታና ከአቧራ በስተቀር ምንም መቀመጫና መጠለያ የሌለው ቦታ ገበሬዎችም ሆኑ ነጋዴዎች በዚያ በጠራራ ፀሀይ ከስምንት ሰዓት በላይ ሲቃጠሉ የገበያ አዳራሽ መስራት አለብን በማለት አንዳችም ዕርምጃ ለመውሰድ ያልቻሉ ናቸው። ሃሳቡም በፍጹም የመጣላቸው አይደለም። እኔ ራሴ እንዳየሁት ከገጠር እየመጡት የተለያዩ ሰብሎችንና ሽንኩርት፣ እንዲሁም ፍራፍሬዎችን የሚሸጡ መጠለያ የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ መጸዳጃም በአካባቢው የለም። እንደምንም ብለው ከስምንት ሰዓት በላይ በጠራራ ፀሀይ ከተቃጠሉ በኋላ እንደገና በእግራቸው ብዙ ኪሎሜትር ተጉዘው ወደ ቢታቸው ይመለሳሉ። በመሰረቱ በአካባቢው ለገበያ አዳራሽ መስሪያ የሚሆን ለጡብ መቀቀያ አፈር ባለበትና ዲንጋይም በተትረፈረበት ቦታ ሰፋ ያለና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊያስተናግድ የሚችል የገበያ አዳራሽ መስራቱ ይህንን ያህልም የሚከብድና ብዙ ወጪም የሚጠይቅ አይደለም። ከተሰራም በኋላ ከገበያ አዳራሹ በሚገኝ ገቢ ዋጋውን እንደገና መሸፈን ይቻል ነበር። ሌላም ባህር ዳርን ውስጥ ውስጡን እየተዘዋወረ ለጎበኘ ሰው የሚገነዘበው ነገር ከተማዋ በሚገባ በዕቅድ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የተገነባ ከተማ አይደለም።
ለማንኛውም ይህንን ወንጀል የሰራና ምንም ዐይነት የፖለቲካ፣ የፖለቲካል ኢኮኖሚና የሶስዮሎጂ ዕውቀት የሌለው ሰው በፖለቲካ ስም እየወጣ ድምጹን ሲያሰማ መስማት በጣም ያሳዝናል። ገዱ አንዳርጋቸው ከቤልጂግ ወደ አሜሪካ ካቀና በኋላ ከይልቃል ጋር ጌቶቹን ለመለማመጥ ነው ወደ ስቴት ዴፓርትሜንት ያቀናው። እንደሚታወቀው ወያኔን ስልጣን ላይ ያወጣውና አገራችንንም በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ እንድትወድቅ ያደረገው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ነው። ገዱ አንዳርጋቸውና ኢንጂነር ይልቃል እያለ ስሙን የሚጠራ ሰው አሜሪካን በኢትዮጵያና በተቀረው የሶስተኛው ዓለም አገሮች የሰራውን ወንጀል የተገነዘቡ ቢሆን ኖሮ አሜሪካንን ለመለማመጥ ወደ ስቴት ዴፓርትሜንት ባላቀኑ ነበር።በነገራችን አቢይ አህመድም ስልጣን ላይ የወጣው በአሜሪካኖች ታግዞና ወያኔ ያለገባደደውን እርኩስ ስራ እንዲያጠናቅቅ ተብሎ ነው። ይህም ማለት ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ ማዳከም፣ ህዝቡን አቅመ-ቢስ ማድረግና የአገራችንንም የጥሬ ሀብት ማስበዝበዝ ነው። ሀቁ ይህ ሆኖ ካለና አንድ ሰው ፖለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባው እየተነሳ የሚዘላብድ ከሆነ በምን መለኪያ ነው አማራውን ወይም ፋኖን እወክላለሁ በማለት ገዱ አንዳርጋቸውና ጓደኞቹ የሚዘላብዱት። ጋዜጠኛ ነን የምትሉም እንደዚህ ዐይነቱን ወንጀለኛ ሰው እየጋበዛችሁ ውዥብንር እንዲነዛ ማድረጋችሁ ከተጠያቂነት ልታመልጡ የሚያደርጋችሁ አይደለም። ከእንግዲህ ወዲያም ገዱ አንዳርጋቸውና ጓደኞቹ ውዥንብር መዝናታቸውን ማቆም አለባቸው። እንዘኢሁን ሰዎች የሚያስተናግድ በጋዤጠኝነት ስም የሚነግድ ሚዲያም ሆነ ግለሰብ ከተጠያቂነት በፍጹም ሊያመልጡ አይችሉም።
ወደ ጃዋር ልምጣ። ይህ ግለሰብ በከፍተኛ የውንጀል ስራ መጠየቅ ያለበትና እስርቤትም መወርወር ያለበት ነው። ጃዋር በሲአይኤና በአረቦች በመመልመል ወጣቱንና ምንም ዕውቀት የሌለውን በኦሮሞ ስም የሚነግደውን ወጣት እየሰበሰበ የሚዘላብድና ውዥንብር የሚነዛ ነው። ጃዋር ምንም ዐይነት ዕውቀት የሌለ ሰው ነው። እንደ ገዱ አንዳርጋቸው ለአንድ አገር ግንባታ በሚያስፈልጉ ዕውቀቶች ላይ ጊዜ በመውሰድና በማጥናት ጭንቅላቱን የገነባ ሰው አይደለም። ጊዜው አሁን ነው በማለትና በራሱ ኤጎ በመጠመድ ሰፊውንና ምንም ዕውቀት የሌውን ወጣት የሚያወናብድ ተራ የፖለቲካ ነጋዴ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥም ስድሳ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚያወጣ ቪላ ቤት ያስገነባና ምንም ሳይሰራ ወይም በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሳይሳተፍ የማጅራት መቺ ፖለቲካ በማካሄድ በአጭር ጌዜ ውስጥ የናጠጠ ሀብታም ለመሆን የበቃ ሰው ነው። ተስፋዬ እንዳለው ጃዋር የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሰው ሲሆን በመሰረቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቶ የመሳተፍ መብት ሊኖረው አይገባም። በህዝብም ዘንድ ተቀባይነት አለኝ እያለ የሚያወራው በምን ስራው ተቀባይነት እንዳገኘ በፍጹም ሊነግርን አይችልም። ይህ ግለሰብ እንደ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዐይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ የማንኛውም የአገር ወዳድ ተግባር መሆን አለበት።
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)