ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡
ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ መጠን ከፍ እንደሚል አምናለሁ፡፡ ግሎባል አላያንስ፤ ቤተ አማራና ሌሎች የሚያደርጉት መዋጮ ተስፋ ይሰጣል፡፡ እንድረስላቸው፡፡ ከአክብሮት ጋር፤ አክሎግ

ምነው አምላክ ሆይ ይህን ያህል ጠላኸን፤ ተጠየፍከን፡፡ የሠራሃትን አገር፣ የፈጠርከውን ሕዝብ ለሠራዊተ አጋንንት አጋልጠህ መሠወርህ ለምን ይሆን? ምን እስክንሆን ነው ለኦነግሸኔ የመከራ ውርጅብኝ አጋልጠህ የተውከን?

አዲስ አበባ እየጠፋች ነው፡፡ ሕዝቧ ብቻ ሣይሆን ታሪኳም ቅርሷም ቅርጿም ወዳልነበርነት እየተቀየሩ ነው፡፡ አንበሣ አውቶቡስ መልኩንም ስሙንም ቀየሩት፡፡ አመልካች ሥራ ፈላጊዎችን በአማርኛና ኦሮምኛ ፈትነው የኦርምኞቹን ሲያሣልፉ ያማርኞቹን ጣሏቸው፡፡ አቤት ግፍ! የኑሮ ውድነቱን ከጣራ በላይ ሰቀሉት፡፡ ቤቱን የሚያፈርሱበትን የአዲስ አበባ ኗሪ ለማፍረሻ ገንዘብ ያስከፍሉታል፡፡ ካልከፈለ ዕቃውን ይቀሙታል ፤ አፈናቅለውም የትም ይጥሉታል፡፡

እነዚህ ወፍዘራሾች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየከመሩበት ያለው ከፍሎ የማይዘልቀው የታሪክ ዕዳ ከአሁኑ ያሣስበኛል፡፡ አይነጋ መስሏቸው በተለዬ እሽቅንድር አድርጓቸዋል፡፡ ጥጋብ ትቢታቸው ይሠሩት አሳጥቷቸዋል፡፡ የዕብሪተኞችን መጨረሻ ከደርግና ከወያኔ ሊማሩ አልቻሉም፡፡ የሁሉም ነገር መፍትሔ ጥይት ብቻ መስሏቸው ሕዝብን በጥይት አረር እየቆሉ አገር ማፍረሳቸውንና በተለይ አማራን መጨፍጨፋቸውን፣ ማፈናቀላቸውን፣ ማሳደዳቸውን፣ አግቶ ብዙ ገንዘብ ማስከፈላቸውን … በስፋት ቀጥለዋል፡፡ ያቺ ቀጭን የፍርድ ጊዜም አትቀርም፤ እየመጣችላቸው ነው፡፡ ያኔ ነው ጉዱ፡፡ ትልቁ ችግር የዐረመኔ አምባገነኖች ዳፋ ወይም ጦስጥምቡስ ለየዋሁ ዜጋ መትረፉ ነው፡፡

ኦነግሸኔ አቢይና ሽመልስ ሆይ! ሌላ የምላችሁ የለም፡፡ መልካም የግድያና የውድመት ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ወደአባታችሁ ቤት ወደ ሲዖል እስክትሸኙ አባታችሁ ሣጥናኤልን ቶሎ ቶሎ አስደስቱ፡፡ ከምታፈሱት የአማራ ደም ጅረት ደግሞ እያንደቀደቃችሁ ጠጡ፤ ሥጋውንም ብሉ፡፡ የቀረቻችሁን አጭር ጊዜ በደምብ ተጠቀሙባት፡፡ ግን ይብላኝ ለልጆቻችሁና ለቀሪው ምሥኪን ኦሮሞ፡፡
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡
ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ መጠን ከፍ እንደሚል አምናለሁ፡፡ ግሎባል አላያንስ፤ ቤተ አማራና ሌሎች የሚያደርጉት መዋጮ ተስፋ ይሰጣል፡፡ እንድረስላቸው፡፡ ከአክብሮት ጋር፤ አክሎግ

Ynegal Belachew