ቅዳሜ Dec 14፣ 2024 የተካሄደው “የኢትዮጵያን ሥርዓተ ትምህርት ማዘመን ለዕውቀት ልኅቀት፤ ለሕዝብ አንድነትና፤ ለሃገር ግንባታ”የተሰኘው የዌቢናር ጉባዔ ቪድዮ የሚከተሉትን በዋናነት የሚየዝ ነው። (1) ዶር ፍስሃ መኮንን፣ “ዘመናዊ (ምዕራብውያን መሰል) ትምህርት በኢትዮጵያ፡ ታሪካዊ ዳሰሳ በሚል ርዕስ (2) ዶር አዳነ ገበያው፣ “አጠቃላይ ትምህርት ለአገር አንድነትና ለኢትዮጵያዊነት” በሚል፣ (3) ዶር በቃሉ አጥናፉ፣ “የግዕዝ ፊደልና የፌዴራል ልሣን ለአገር መግባቢያነትና ለሕዝብ መቀራረብ” በሚል ርዕስ ናቸው ። በተጨማሪም ቪድዮው፣ “አንድ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖረንና፣ የተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች ከግዕዝ ፊደላት ይልቅ ላቲን ፊደልን እንዲጠቀሙ የተደርጉት ስሁት ማበረታታቶች ያስከተሏቸውንና የሚያስከትሏቸውን ሃገራዊ ጉዳቶች ይዳስሳል።
የጸረ ኢትዪጵያና አማራ ትርክት ጅመራው የጣሊያን ወረራ ነው። ከአንዴም ሁለት ጊዜ በቀይ ባህር በኩል አቋርጠው ፊልሚያ የፈጸሙት ጣሊያኖች በተለይም በሁለተኛው ወረራቸው ኢትዮጵያን በዘርና በቋንቋ ልክ አሁን እንደምናየው በመሸንሸን አንድን ከሌላው ጋር በማላተም ህዝቡንና ምድሪቱን የቅኝ ግዛት ለማድረግ ጥረዋል። ከጣሊያን ጎን በመሆን ሃገራቸውን የወጉ ሲሸለሙና ሲሾሙ ለሃገርና ለድንበር በድር በገደል የተንከራተቱት ደግሞ በዚህም በዚያም እየተወነጀሉ በግዞት፤ አልፎ አልፎም በስቅላት በማስወገድ ኢትዮጵያን ለውስጥና ለውጭ አፍራሽ ሃይሎች ንጉሱ እኖራለሁ በማለት አመቻቿት። በእርግጥም ኖሩ። ግን መኖር በዘመን እርዝማኔ አይለካምና አወዳደቃቸው የሮም ሆነ! ይህን ተከትሎ የኤርትራው ጀበሃ በሻቢያ ሲበላ ነገር ሁሉ እየከፋ መጣና ኤርትራን ለመገንጠል ኢትዮጵያ ኤርትራን የቅኝ ግዛት አድርጋ ይዛለች በሚል ሰበብ ፍልሚያው ጦፈ። ሻቢያ ለ 30 ዓመት ከንጉሱ እስከ ደርግ ሲፋለም በዓለም ዙሪያና በሃገር ውስጥ የዘራው የፓለቲካ ትርክት “የኤርትራዊያን የመከራህ ሁሉ ምንጭ አማራ ነው” የሚል ነበር። ይህን የፈጠራ ትርክት በዓለም መድረክ ላይ በተለይም በዓረቡ ዓለም በሰፊው እንዲሰራጭ አደረገ። አሁን ከ 50 ዓመት የመከራ ዘመን በህዋላ የተፈነገለው የሶሪያ መንግስት ሻቢያን በማሰልጠንና በማስታጠቅ ከረድት ሃገሮች መካከል ተጠቃሽ ነው። ስልጣኔ ከእኛ በላይ ላሳር ነው ይሉ የነበሩት ኤርትራዊያን ምሁሮች ዛሬ ላይ አፋቸው ተለጉሞ የእድሜ ልክ ጨካኝ መንግስት በሩቅና በቅርብ ሲያበራያቸው ማየት ሰው በሰፈረው መስፈሪያ ይሰፈርለታል ያሰኛል። ሻቢያ ቆይቶ እባብ ጊንጥን ይወልዳል እንዲሉ ወያኔንም አማራና ኢትዮጵያን እንዲጠላ የፈጠራ ታሪኩን እንዲቀበል በማድረግ የሻቢያን መርዝ ስለጋተው ሲኦል ድረስ ወርደን እናፈርሳታለን የሚሉ ጉዶችን በዘመናችን እንድናይ አድርጎናል። ለገባው በሲኦል ፈራሽ እንጂ አፍራሽ የለም! ሻቢያና ወያኔ የተንኮል፤ የክፋትና የመከራ ዝናብ ገጽታዎች ናቸው። ዛሬ ላይ ለምናየው የፓለቲካ ምስቅልቅልና የሰዎች ፍልሰት፤ የመከራ ዶፍ ሁሉ ተጠያቂዎቹ የብሄር የፓለቲካ አራማጆችና ደጋፊዎቻቸው ናቸው።
ታዲያ የዓለም የፓለቲካ ንፋስ ተለውጦ ወያኔ በአዲስ አበባ ሻቢያ በአስመራ የሃገር መሪዎች ሲሆኑ ሞኝ የያዘውን አይለቅም እንዲሉ ወያኔ ኢትዮጵያን በብሄርና በቋንቋ ሸንሽኖ ለራሱ አበላል አመቻቻት። በዚህ የፓለቲካ ነውጥ በተፈጠረ እምነት የክልል ባንዲራውን ይዞ ሁሉም ሃገር ሆነና ነገርየው የባሰ ተሳከረ። ሙትን ሙት እየተካው ቆይቶም የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ኦሮሚያ የምትባል ሃገር እንመሰርታለን በማለት የስንቱን ቤት አቃጥለው የስንቱን ህይወት አጥፍተው አሸሸ ገዳሜ ሲሉ ማየት የተለመደ ሆነ። እነዚህ ሶስት ሃይሎች ሻቢያ፤ ወያኔና ኦሮሞ ፓለቲከኞችን ከብዙ ነጥቦች መካከል የበለጠ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ኢትዮጵያዊነትን መጠየፍ፤ አማራን መጥላትና የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማሳደድና ማጥፋት ጎልተው የታዪ የትርክት ውጤቶች ናቸው። ይህ የፓለቲካ ስልት በጣሊያኖችም ዘመን የተፈጸመ ነበር።
ጊዜ ሰጠን ብለው ያዙኝ ልቀቁን ያሉ ዛሬ ትቢያ ሆነዋል። በፈጠራ ትርክት የሰከረውም ከእነስካሩ በጊዜው ያንቀላፋል። ሰው የወል ስም ነው። ሰው የሚመዘነው በዘሩ ወይም በቋንቋው ወይም ባካበተው ሃብት አይደለም። በሰውነቱ እንጂ! የሃበሻው ፓለቲካ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሳከረና እየሰከረ ዝንተ ዓለም የባሩድ ሽታ እንዳሸተቱ መኖር ልማድ ሆኗል። እኔ ኤርትራዊ ነኝ። አንተ አማራ ነህ፤ አንቺ ኦሮሞ ነሽ እከሌ እና እከሊት እንዲህ ናቸው የሚባለው የከሰረ የፓለቲካ ስልት ሁሉ በሳይንስ ቢፈተሽ ፉርሽ ነው። Dr. Bruce Lipton – The Biology of Belief በተሰኘው መጽሃፉ ላይ የሰው ዘር ሁሉ የተሳሰረ ሰንሰለት እንደሆነ ይነግረናል። እኛ ግን በዘርና በጎሳ፤ እንዲሁም በቋንቋ ተሳክረን የበደላችን ሁሉ ምንጭ አማራና ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት በጨለማ ውስጥ እንዳክራለን። የመከራው ምንጭ እኛው ራሳችን ነን። ግን ሳይንሳዊ ግኝትን ከመቀበል ይልቅ የፈጠራ የጥላቻ ታሪክን ከሚሰለቅጥ ህብረተሰብ ሚዛናዊ ፍርድ አይገኝም። ለዚህ ነው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻላል ብለን እምነት የጣልንበት ነገር ሁሉ ከበፊቱ የከፋና የከረፋ የሚሆነው። የአማራ ህብረተሰብንና ኢትዮጵያን፤ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክ በመጥላት የራስን መኖር ማድመቅ አይቻልም። ለጊዜው ጋጋታና ጫጫታ ግን ማዳመቂያ ከበሮ ይሆናሉ። ፍጻሜው ግን ኦርማይ ነው። በቃኝ!
ተስፋ ከሚንጋ ይልቅ ያንተ ውስን ሀሳብ ገብቶኛል
Hailea is really school of thought and national treasure. Long live please keep up we need you as long as Ethiopia is in existence.