December 17, 2024
6 mins read

በግርግር 5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ቅርጥፍ አድርጎ የበላው የትናትናው የቲቪ ሪፖርተር ያዛሬው ሚሊኒየር የግሩም ጫላ አስቂኝ ቃለ ምልልስ

470222985 988241926684242 7031984139796941723 n
“30 አመት አሜሪካ ውስጥ ታክሲ እየነዳህ እዚህ መጮህ አይቻልም” አነጋጋሪው የግሩም ጫላ ቃለ ምልልስ
***
የቻይናው “ሴጂቲኤን” ቴሌቪዥን ጣቢያ ወኪል ጋዜጠኛ (correspondent) የሆነው ግሩም ጫላ ለብዙዎች አነጋጋሪ የሆነው ቃለ ምልልስ ከሰሞኑ አካሂዷል፡፡
አላይቭ ቶክ ከተሰኝ ፖድካስት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው ይህ ጋዜጠኛ የብልፅግና መንግስት ታማኝ ሰው ነው በሚል ስሙ ይነሳል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከጥቂት አመታት በፊት “GTNA” የተባለ አፍሪካን የሚወክል ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመስረት አዲስ አበባ ውስጥ 5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከቡን እና እስካሁን የቴሌቪዥን ጣቢያው ነገር የውሀ ሽታ ሆኖ መቅረቱን በማሳያነት ያነሳሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ ግሩም በዚህ ቃለ ምልልሱ የልማት ተቃዋሚ ናቸው በሚል የፈረጃቸውን ሀይሎች በጠንካራ ቃላት ተችቷል፡፡ በዚህ ትችት በዋነኝነት ዲያስፖራው ተቆጥቷል፡፡
“አሜሪካ ውስጥ እጅግ በተደጋጋሚ ሰልፍ በመውጣት የሚታወቁት ኢትዮጵያዊያን ናቸው” ሲል የሚናገረው ግሩም – “በተለያዩ መሪዎች ዘመን የተቃውሞ ሰልፎች በተደጋጋሚ ተደርገዋል” ሲል ይሞግታል፡፡ “አሳዛኙ ነገር ሰልፍ ስንወጣ ብዙ የሆንን መሰለን እንጅ አሜሪካ ውስጥ ሰፊ የዳያስፖራ ቁጥር ካላቸው 10 የአፍሪካ ቀዳሚ ሀገራት ተርታ እንኳን አንመደብም” ሲል ሞግቷል፡፡
“እረ ተዉ – ሰው ይታዘበናል” ሲል ሰልፍ የሚወጡትን ዳያስፖራዎች የሞገተው ግሩም “በመሰረቱ ለውጥ የሚመጣው በዚህ መንገድ አይደለም፡፡ ጀግና ሰው የሚያወራውን ይተገብራል፡፡ በኢኮኖሚ ሀገራችን አልተለወጠችም ብሎ የሚሞግት ዳያስፖራ ሀገር ውስጥ ግባና ሰርተህ አሳየን” ሲል በእልህ ሲሞግት ይታያል፡፡
ጋዜጠኛው “30 አመት በአሜሪካ ታክሲ እየነዳህ እዚህ መጮህ አይቻልም” ሲል ክልከላ ያስቀምጣል፡፡ አክሎም “ይሄን በድፍረት የምናረው ከ0 – Hero የደረስኩ ሰው በመሆኔ ነው” በማለት ይገልፃል፡፡ “ዛሬ የአሜሪካን ህልም እዚህ ሀገር ውስጥ መኖር ጀምረናል” የሚለው ግሩም ጫላ “ብዙ ሰው እንዲለወጥ መንገድ መክፈት አለብን፣ አነሱ የሚኖሩበትን ምእራባዊያን ሀገራት መንግስታት ያማከርን ሰዎች አለን፣ ሰርተን የተለወጥን – ያገኝን ሰዎች አለን፣ ይሄንን ዋጠው እመነው” ሲል ሞግቷል፡፡
“ይሄን ያሳካነው የጠቅላይ ሚንስትሩ ጓደኛ ስለሆንኩ፣ የከንቲባው ዘመድ ስለሆንኩ ሳይሆን ስለቻልኩ ነው ያደረግኩት” ሲልም ተደምጧል፡፡ ኢትዮጵያው ውስጥ የሚሰራ ሰው ይወረፋል እንጅ አይደነቀም ሲል የሚከራከረው ግሩም ጫላ – በሌላ አፍሪካ ሀገር ግን ሰርቶ የተለወጠ ሀብታም እጅግ ይከበራል ሲል ቁጭቱን ገልጾአል፡፡
“ሀገር የጋራ ነው፡፡ የምንለወጠው በጋራ ስንሰራ ነው” በማለት ለዚህ ደግሞ ሁለት አማራጭ እንዳለ ይጠቁማል፡፡ አንደኛው “ለውጡ እንዲቀጥል ማገዝ ሁለተኛው ከማደናቀፍ ተቆጥቦ አፍን መዝጋት ነው” ሲል መክሯል፡፡
“የኮሪደር ልማትን መቃወም ጤነኝነት አይደለም – በዚህ ልማት የፖለቲካ እና አስተዳደራዊ በደል የሚደርስባቸውን – ቤት እና የንግድ ሱቃቸው ለሚያጡት ወገኖች መከራከር ግን ወንጀል አይደለም” ሲልም ተከራክሯል፡፡
“በደፈናው አሜሪካ ተቀምጦ ካዛንችስ ፈረሰ – ቄራ ፈረሰ የሚለው እና የኮሪደር ልማት የሚቃወም ሰው ግን ጤነኛ አእምሮ የለውም” በማለት የተቸው ግሩም ጫላ “ዱባይ ሄደን የምንዝናና ሰዎች እስከ መቼ በቆረቆዘ (ghetto) ከተማ እና ሀገር ውስጥ እንድንኖር ትፈልጋላችሁ” በማለትም ነው የገለጸው፡፡
(ሸገር ታይምስ)

4 Comments

  1. አረ ወዳጄ እንዲህ ያለ እብሪት አወዳደቅህን ያከፋዋል ከቀን ጅቦች ትምህርት ብታገኝ መልካም ይመስላል።

  2. ጃሌ ግሩም ጫላ ይህ የሚሰድቡት ታክሲ ነጅው ቤተሰብ አስተምሮ እርሶ ከወያኔ ጋር ተመቻችተው ሲቀመጡ ለሃገሩ በበረዶና በጸሃይ ኡኡ ሲል የነበረ ነው፡፡ እንዳሉት አልቅሷል ያለቀሰው ግ ን ለሃገሩ ነው እንዲህ በማድረጉ ቤተሰብ በድለሏል ሃገሩን ግን አድኗል፡፡ እንደ እርሶ ለክልሉ ብሎ አገሩ ላይ አልዶለትንም እንደ አቶ ጁዋር መሃመድ በማስተዋል እጥረት ብዙ ህይወት እንዲቀጠፍ አላደረገም እንደ አብይ መሃመድና ለማ መገርሳ ክፉ ስራ ኢትያጵያ ላይ አልድዶለተም፡፡ዘረ ከጎሳ ሳንለይ ለሁሉ ጩዃል፡፡

    እንደሚያስታውሱት ፓስተር በቀለ ገርባ ይፈታ ብለን ላንቃችን እስኪደርቅም ጩኸን ነበር ታየ ደንዳም እንዲሁ ካልተፈታ ብለን ነበር ሚኒስቴር ከመሆኑ በፊት፡፡ ፓስተሩ ከተፈቱ በኋላ አማርኛ አትናገሩ በኦሮሞኛ ካልተናገረ እቃ አትሽጡ ግደሉ አባርሩ ካሉ በኋላ ለቃላቸው ሳይቆሙ በማያውቁት በማይመሳሰሉበት አገር እስከ ቤተሰባቸው ስደት ጠይቀው ተከብረው መኖር ጀመሩ፡፡ ቋንቋችሁን ካልተናገሩት ላሉት በጠሉት ቋንቋ አማርኛ መጽሃፍ ሽጠው መቸብቸብ ያዙ፡፡ ምንድነው እናንተ አካባቢ ያለ ሰው አቅሉን ሳተ እርሶም እንዲህ መስመር የሳተ እብሪት ውስጥ ገቡ የቀበጡ እለት ሞት አይገኝ አለ ለመሆኑ ማን አይዞት ብሎት ነው እንዲህ የናጠጡት? ጊዜው ሲደርስ እሳት ያኮማተረው ፌስታል ይመስላሉ አይቀሬ ነው ይህን ይጠብቁ፡፡

  3. ቱልቱላ! ከዜሮ ወደ ሂሮ ትላለህ እልፍ በሚያለቅስባት ምድር ተቀምጠህ። መኖርህን የምትለካው በአንተ ጊዜአዊ ስኬት ነው እንዴ? ጅላጅል! ባይመስልህ ነው እንጂ ጊዜ ሲጨልም በህይወት እያለህ ከተጠቀምክበት ንዋይ ይልቅ ለበላተኛ ጥለህ የምትሄደው ነው የሚበልጠው። ያም የሰውን ከንቱነት ያሳያል። እንዳንተ እድልና ጊዜ ሰምሮላቸው በከፍታ ላይ ብቻቸውን ቁመው እኛ ብቻ ከኖርን ያሉ ዛሬ የሉም። አሉ ከተባለም እንደሞቱ ይቆጠራል። እርግጥ ነው የሃገር መሻሻልን ማንም ቢሆን ይፈልጋል። ግን ሰው እንባ እያፈሰሰና በዘርና በጎሳ ተለይቶ ቤቱና ንብረቱ እየወደመ የሚፈጸም መሻሻል ለማንም ለምንም አይበጅም። አሁን የተጠለልክበት የብልጽግና ከለላም በጊዜ ሲሽቀነጠር የአንተና የመሰሎችህ ከፍታ ይናዳል። በታሪክ ያየነው ይህን ነውና! ሰው ሆኖ እንዲህ በትቢዕት በድፍረት መናገር መታመም እንጂ የጤና አይደለም። ግን የቁስ አካል ፍቅር ልቡን ያነደደው የዘርና የቀን ነጋዴ ከራሱ ሌላ ማንንም አያይምና አልፈርድብህም። መቼ ነው እንደ ሰውኛ ማሰብና መኖር የምንጀምረው? ለምን ይሆን ስኬትና እድገት በዘርና በቋንቋ በብሄር የሚለካው? ይህ ጉራና የተጋነነ ወሬ ነው ዛሬ ምድሪቱን የጦር አውድማ ያደረጋት።
    ከገባህና ከተረዳህ ሰው ታክሲ ነዳ ጫማ ጠረገ ጥሮ ግሮ የሚያገኘው በመሆኑ እንቅልፉ የሰላም፤ ምግቡም የጤና ነው። በሰው ደም ጠቅሎ እንጀራውን አይጎርስምና! ህይወት የአደራ እቃ መሆኗ ለገባው የሌላው ሰቆቃና እንባ ይገደዋል እንጂ እንዲህ አይበጣጠስም። ልብ ይስጥህ ወንድሜ…. ብሄር፤ ቋንቋ ሳትል የወገን መከራና እንባ ይረዳህ!

    • ተስፋ “መኖርህን የምትለው ባንተ ጊዜያዊ ስኬት ነው ” ላልከው ማስተካከያ ቢደረግበት ያመጣው ስኬት ሳይሆን ዘግናኝ ዘረፋ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop