December 17, 2024
5 mins read

የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ ታወቀ

GfAK SEXsAAHO3vበአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተሻለ ቢዝነስ ያንቀሳቅሳሉ የሚመባሉ የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ ታውቋል።

እነዚህ በአብዛኛው የአማራ ተወላጅ የሆኑ ባለሀብቶች እየተመረጡ ተንቀሳቃሽ ሒሳባቸው በህግ እየታገደ ወይም Legal Restriction እየተደረገባቸው እንደሆነ የባንኮች ምንጮቻችን ተናግረዋል።

መሠረት ሚድያ ባደረገው ማጣራት በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ ለታጣቂዎች ድጋፍ ሊያደርጉ ይችላሉ የተባሉ ሁሉ ‘ከላይ በመጣ ትእዛዝ) በሚል በጥርጣሬ ባንካቸው እየታገደባቸው ይገኛል።

ንግድ ባንክ ላይ ብቻ ቢያንስ 200 የሚሆኑ የእነዚህ ባለሀብቶች አካውንቶች እንደታገዱ ታውቋል፣ የግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ቁጥራቸው ያልታወቀ እገዳዎች መደረጋቸው ታውቋል።

“አብዛኞቹ የፍርድ ቤት እግድ እንኳን የሌለባቸው ናቸው፣ በጥርጣሬ በሚል በርካታ አካውንቶች ተዘግተዋል” ያሉት ምንጫችን ሁኔታው የዛሬ ሶስት እና አራት አመት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የትግራይ ባለሀብቶች ላይ ከተደረገው ጋር ተመሳሳይነት አለው ብለዋል።

ሚድያችን በዚህ ዙርያ አካውንታቸው የታገደባቸውን አንድ ነጋዴ እነጋግሯል።

“አካውንቱ መታገዱን የሰማሁት ከቢሮዬ ተደውሎ ክፍያ መፈፀም አልቻልንም ሲሉኝ ነው” የሚሉት እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነጋዴ ወደ ንግድ ባንክ ሄደው ሲያጣሩ “ለግዜው እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ ተጥሎበታል ተባልኩ፣ ሌላው ቀርቶ በወረቀት ላይ የተፃፈ ማብራርያ ወይም ለእግዱ ማረጋገጫ አልሰጡኝም” በማለት አስረድተዋል።

በተመሳሳይ እርሳቸው የሚያውቋቸው የአራት የአማራ ተወላጅ የቢዝነስ ባለቤቶች አካውንታቸው እንደታገደባቸው እንደሰሙ ጠቅሰው ወንጀል ባልፈፀሙበት እና ክስ እንኳን ባልቀረበበት ጉዳይ ለ40 አመት የሰሩበትን የንግድ ስራ እንዲያቆሙ እንደተገደዱ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙርያ ከብሄራዊ ባንክም ሆነ ከሌላ የመንግስት አካል የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራርያ የለም።

(መሠረት ሚድያ)

መረጃን ከመሠረት!cks on civilians. The world must act now to stop the atrocities.


በሀረር ለኮሪደል ልማት 2 ሚልየን ብር አላዋጣችሁም የተባሉ የግል ባንኮች ታሸጉ

GfAY3iEWAAAOeSM(መሠረት ሚድያ)- ከከተማው የሚደርሰን መረጃ እንደሚጠቁመው ሐረር ከተማ ላይ እየተሰራ ላለው የኮሪደር ልማት ብር አልከፈላችሁም በሚል ሰበብ ባንኮች ላይ የማሸግ ድርጊት ተፈፅሟል።

“የህዝብ አገልጋይ የሆኑ የባንክ ቅርንጫፎች እንደሱቅ ታሽገዋል” ያሉን አንድ የባንክ ሰራተኛ በተለይ የግል ባንኮች እንዲዘጉ ተደርገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግን ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ታውቋል።

ከተዘጉት ባንኮች መሀል ወጋገን፣ አባይ እና ኦሮሚያ ባንኮች ይገኙበታል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኮሪደር ልማት መንገዱን ቀድሞ ከነበረበት 7 ሜትር ስፋት ወደ 30 ሜትር በማስፋት ግንባታው እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

ይሁንና የግል ባንኮችን ኢላማ ባደረገ መልኩ ለምን እንዲዘጉ እንደተደረጉ የክልሉ ባለስልጣናት እስካሁን ማብራርያ አልሰጡም።

መረጃን ከመሠረት!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop