December 2, 2024
4 mins read

አቶ ታዬ ደንደዓ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ

ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደዓ የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእስር እንዲለቀቁ ዛሬ ተወስኗል፡፡
ከዚህ በፊት በሦስት ክሶች ተከሰው በሁለቱ ነጻ የተባሉትና “ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘት” የሚለውን ክስ እንዲከላከሉት ፍርድ ቤት መበየኑን ተከትሎ በዋስትና ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጪ ለመከታተል የጠየቁት አቶ ታዬ፤ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኖ ነበር፡፡ ይሁንና እስካሁን ውሳኔን በመቃወም አቤት ያሉት ተከሳሽ አቶ ታዬ ዛሬ ባስቻለው የፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ተወስኖላቸው የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ተብሏል፡፡
ዛሬ ጠዋት በፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርበው ጉዳዩን የተከታተሉት ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፤ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን የዋስትና መከልከል ውሳኔ ሽሮ አቶ ታዬን በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ “ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ግድም በተሰየሙ ዳኞች አቶ ታዬ እስካሁን ያቀረቡትን ቅሬታም ጠቃቅሶ ጠባብ የህግ ትርጉም ተሰጥቶ የዋስትና መብት መከልከል ትክክል አይደለም ብሎ ነው የዋስትና መብት እንዲጠበቅ የወሰነው” ብለዋል፡፡469090185 1010376177794249 7741721280859540925 n
ወ/ሮ ስንታየሁ አክለውም አቶ ታዬ 20 ሺህ ብር አስይዘው አሊያም የሰው ዋስ ጠርተው ከእስር እንዲለቀቁ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዛሬ መወሰኑን አስረድተዋል፡፡ “ፍርድ ቤቱ ዛሬ ጠዋት ባዘዘው መሰረት አሁን ከሰዓቱን ለዋስትና የተባለውን 20 ሺህ ብር በመክፈል በውሳኔው መሰረት ሂደቶቹን በመከታተል ላይ ነን፡፡ አሁን ቃለምልልሱን በምሰጥበት ሰዓት እስካሁን የተፈጠረ ነገር ባይኖርም በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት እየሄድን ነው ዛሬ በስራ ሰዓት የተቻለንን የህግ ሂደቶቹን እንሄድበታለን” ነው ያሉት፡፡ ዶቼ ቬለ ዜናውን እስካጠናቀረበት ዛሬ ከሰዓት ዘጠኝ ሰዓት ግድም አቶ ታዬ ከእስር አልተለቀቁም፡፡
የዛሬ አንድ ዓመት ግድም ከስልጣን የተነሱት አቶ ታዬ ደንደዓ ሁከት ማነሳሳት፣ ጸረ-ሰላም ኃይሎች መደገፍ እና ህገወት የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘት በሚሉ ሶስት የክስ ጭብጦች ተከሰው የመጀመሪያዎቹ
ሁለት ክሶች ውድቅ ተደርጎላቸው ሶስተኛውን የክስ ጭብጥ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እየተከታተሉ ነው ሲል ከአዲስ አበባ የዘገበው ሥዩም ጌቱ ነው፡፡ አቶ ታዬ እንዲከላከሉት የተባለውን ህጋዊ ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ጉዳዩን ያውቁልኛል ያሉትን አምስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተከላካይ ምስክርነት ጠርተው በመከላከልም ላይ ናቸው፡፡
ዘገባ ስዩም ጌቱ DW ከአዲስ አበባ

2 Comments

  1. Is he re instated again as Selam Minster and encourage ONG to kill more citizens? Or leave the country expose the state and find antidote for Juwars poison?

  2. አቶ ታየ ደንዳስ ተፈቱ እነ አቶ ታድዮስ ታንቱ፤ክርስቲያን ታደለ፤ መስከረም አበራ….. ምን ቢበድሉ ነው የፍርድ ቤቱ ስስ ልብ እነሱ ዘንድ ሊደርስ ያልቻለው ወይስ ነገሮች የሚታዩት በአባ ገዳ ፍርድ ቤት በቄሮ መስካሪነት ነው? አብይ መሃመድን ሲሰድቡ እንኳን አልተሰሙም እስቲ የፍርድ ጊዜ ሲመጣ ሰው ገድሎ የገፈፈ ሁሉ እንደ ናዚ የጦር ወንጀለኛ በወረንጦ እየተለቀመ ለፍርድ መቅረቡ የማይቀር ነው፡፡ ሰው ገድሎ ገፍፎ እንዲህ በነጻነት መኖር የለም ጁዋር መሃመድና መሰሎቹ ለጊዜው በቁም ቅዠት በኋላ ደግሞ በፍርድ ቤት ቅጣታቸውን ያገኛሉ፡፡ አቶ ታየም ሰላም በሌለበት ሃገር ያን ያህል ጊዜ ደሞዝ እየበሉ በቦታው ባይቀመጡ መልካም ነበር ዛሬ ምን ስራ ሰሩ ያ ሁሉ ህዝብ ሲታረድ ቢሏቸው መልስ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ በሳቸው ዳፋ ቤተሰባቸው መጉላላቱ ግ ን ያሳዝናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop