December 1, 2024
26 mins read

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልተስተምሮም ቁ.2

GduIqzWXMAAO9M

ጠ/ሚ አብይ “ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ” የሚለው አባባል ላይ ትችት ሲሰነዝሩ ሰማሁ መሰል፡፡ አትሸወዱ አይሞቅም ነው… ያሉት፡፡ በዚህ አባባል ላይ እሳቸው እንዲህ አሉም አላሉም አባባሉን ለመረዳት ሳይንቲስት ወይም የቋንቋ ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በአጭሩ የዚህ አባባል ትረጓሜው በምንም ሁኔታ ውስጥ ሕይወት አለ፤ ይቀጥላልም ማለት ነው፡፡

እውነት ነው፡፡ ሃገር በጦርነት ውስጥ ባለችበት ግዜ ሰዎች መጋባታቸውን አያቆሙም፤ ፍቅርም እንዲሁ፡፡ በግርድፉ የመቃብርን ቀዝቃዛነት ወስደን ብልመከተው የኢትዮጵያ መቃብር ቅዝቃዜ በጥቅምት ቁር እኩለ ለሊት ላይ በደጋማው አካባቢ -4 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መድረሱን እጠራጠራለሁ፡፡ እኔ በምኖርበት ሰሜን አሜሪካ ግን ክረምት ላይ በመስታወት ውስጥ ፀሐይ ፍንተው ብላ እየታየች ፀሐይ ወጣች ተብሎ ውጭ ሲወጣ ቅዝቃዜው ከ -35 – -40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡

እንግዲህ ጠ/ሚ ምን እያደረጉ ነው ያሉት? ከእነዚህ በትእምርትና ምልክት ከተሞሉ ዘይቤዊ አነጋገሮችሰ ጋር ምነው አልላቀቅ አሉ? ብለን ብንጠይቅ፣ መልሱ እሳቸውና መሰሎቻቸው አፍርሰው በራሰቸው አምሳል ማዋቀር የሚፈልጉት  ሰሜናዊ የተባለ የስነልቦና ውቅር ስላለ ይሆናል፡፡ ዘመቻው መልከ ብዙ ገጽታ ያለው ነው፡፡

የሰሜኑን ህዝብ ስነልቦናዊ መዋቅር ለማወቅ ጥንታዊ ግብጽን፣ የእብራውያን ታረክን አረቦችን ማጥናት ይጠይቃል፡፡ ይህ ህዝብ በዘመናት የዳበረ ባህል ባለቤትና ውስብስብ የሆነ የስነልቦና መገለጫ ባለቤት የሆነ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን አፍሪካዊነታችንም መረሳት የለበትም፡፡ ይህ ደግሞ ለአፍሪካ በረከት እንጂ እርግማን አይደለም፡፡

አማራ ሲተርት “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” ይላል፡፡ በነገራችን ላይ አስመራ በአፄ ኃይለ ስላሴ ግዜ የታተመ የትግረኛ ተረትና ምሳሌ መጽሐፍ ላይ እንደተመለከትኩት በጣም አብዘኞቹ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች በተዛማች ትርጉማቸው በትግረኛም ይገኛሉ፡፡ ታዲያ እንደ ጠ/ሚ አብይ ያለ ሰው ይህን ምሳሌ ሲሰማ እንዴት አማርኛ ውድ የሆነውን የእራስን ልጅ ህይወት ከምንናገረው ቃል ይመዝናል ይላል፡፡

ውስብስብ የሆነውን ማህበራዊ አደረጃጀት፣ ተውፊትና ባህላዊ እሴት በአባባሉ ውስጥ አስገብተን ስንመለከት ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ነገሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ መጽሐፈ መሣፍንት ም. 11 ቁ. 30 -40 ዮፍታሔ  የአሞንን ልጆች ለመዋጋት ወጣ፡፡ ስእለትም አደረገ፡፡ ድል ከቀናኝ በመጀመሪያ ሊገናኘኝ የሚወጣውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋእት አቀርባለሁ አለ፡፡

ከድል በኋላም ወደ ቤቱ ሰለመጣ ድንግል የነበረች አንድዬ ልጁ ከበሮ ይዛ እየጨፈረች ልትገናኘው ወጣች፡፡ ዬፍታሔም አለቀሰ፡፡ በኦርቶዶክስ ትርጓሜ መጽሐፍት ላይ እንደሚነበበው፤ ዬፍታሔ ሁል ግዜ እርቆ ሄዶ ሲመለስ ሊቀበለው የሚወጣ አንድ በግ ነበረው፡፡ እሱን እያሰበ ነው ስለቱን የተሳለው፡፡ ነገር ግን ሴት ልጁ ልትገናኘው ወጣች፡፡ እሷን አስፈቅዶ የተናገረውን ፈጸመባት፡፡ ስለዚህም ታሪክ ተረቱ “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ” ተባለ፡፡ አትዮጵያውያንም ለዮፍታሄ ልጅ በየአመቱ አራት ቀን በእስራኤላውይን ዘንድ ይደረግላት የነበረውን ማስታወሻ ሙሾ ለቅሶ ወደ ተረትና ምሳሌ ቀይረው ዝንተ አለም ሲዘክሯት ይኖራሉ፡፡

ይህን ቁ. 2 መጣጥፍ ለመጻፍ ምክነያት የሆነኝ ህዳረ 12፣ 2017ዓ.ም. (Nov 21, 2024) በዚሁ በዘሐበሻ ላይ “ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልተስተምሮም” በሚል ርዕስ በወጣው መጣጥፍ ላይ ንግስቲ የተባለች ልጅ በኮመንት መስጫው ላይ የጠየቀችው ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄዎቿም ለአብይ አህመድ ማን ዶክትሬቱን ሰራለት የሚልና በአማርኛ ባህላዊ ዘፈኖች ውስጥ ሌላ ታሪክን ያጣቀሱ ግጥሞች እንዳሉ ብትነግረን የሚሉ ናቸው፡፡

ለአብይ አህመድ የዶክትሬት ድግሪ ጽሑፉን ከየመጽሐፉ ላይ ገልብጦ ማን እንዳዘጋጀላቸው አላውቅም፡፡ ነገር ግን እሳቸው ይህን ትምህርት ተማርኩበት በሚሉት ወቅት የነበረውን የትምህርት ሂደት ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አቀርበዋለሁ፡፡

1983ዓ.ም. ኢህአዲግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይና በአማራ ክልል ይነቀሳቀሱ የነበሩና በአብዛኛው ትምህርታቸውን ከ1ኛ ደረጃ ያቋረጡ ታጋዮች ለትምህርት ልዩ ሁኔታ ተመቻችቶላቸው ነበር፡፡ በተዘጋጀላቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአመት ውስጥ ሶስትና አራት ክፍል እያለፉ ለ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በቅተዋል፡፡

ለምሳሌ ጀነራል ሰአረ መኮንን የዚህ እድል ተጠቃሚ ነበር፡፡ ከዚያም ድግሪና ዲፐሎማ ያዙ ተብሎ በየመስሪያ ቤቱ ተመድበዋል፡፡ ከ7ክፍል በላይ የተማሩበት ትምህር ማስረጃ የለም የሚባሉት ጠ/ሚ አብይ የዚህ እድል ተጠቃሚ እንደነበሩ አላውቅም፡፡ ነገር ግን በእንዲህ ሁኔታ ተምረው ቢሆን ኖሮ ህወኻቶች ይናገሩት ነበር፡፡

የሆነው ሆኖ ኢህአዲግ አባላቶቹን ሲቪል ሰርቪስ በማስገባትና በውጭ ሃገራት ተማረ የተባለው ግለሰብ ቁጭ ብሎ የማይከታተለው ማሰተርስ ድግሪ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ የኦህዲድ አባለቶችም በተመቻቸላቸው ሁኔታ በመጠቀም የማሰትርስ ድግሪ ባለቤት የሆኑ ብዙ ናቸው፡፡

ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች የማስተርስ ድግሪ እያሰሩ በማሰተርስ ድግሪ የተንበሻበሹም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ እንግዲህ አሰሱም ገሰሱም በለማሰትሬት ሆኗል ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ ባለፈው ጥቅምት 10 ዲ/ን(?) ዳንኤል ክብረት በፌሰ ቡኩ  ፋኖ ላይ አላግጣለሁ ብሎ የለጠፈው የአስቻለው ጩልሌው ታሪክ አንድ አስቻለው ጀቱ ይባል የነበረን ከአስራ ሶስት አመት በፊት የማውቀውን ሰው ያስታውሰኛል፡፡ አስቻለው ጀቱ የሚሉት ፈጣን ልጅ ስለነበር ነው፡፡

የአስቻለው ስራ ደግሞ የማሰተርስ ድግሪ ቴሲስ መጻፍና ማገላበጥ ነበር፡፡ የመቀሌውን፣ ለባህርዳር፣ የባህረዳሩን ለመቀሌ፣ የአዲስ አበባ ዩንቨርሰቲን ለሌላ ዩንቨርሰቲ መመረቂያ ጽሑፍ እያዘጋጀ ያቀርብ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩንቨርሰቲዎች የሚሰሯቸው ቴሲስና የዶክትሬት ዲሰርቴሽን ከጓደኞች ጋር በዘረጋው ኔትወርክ ይደርሰዋል፡፡

ከዚያም ከስምንት ሺህ እስከ ሃያ ሺህ (ለዶክትሬት) እያስከፈለ የመቀሌውን ለአዲስ አበባ፣ የባህረዳሩን ለመቀሌ አዟዙሮ ገልብጦ ለዕጩ ተመራቂዎች ይሰጣቸዋል፤ በቃ ይመረቃሉ፡፡ ታዲያ አንድ ግዜ የባህረዳሩን ለመቀሌ ዩነቨርሰቲ መመረቂያ ሲያገላብጥ አንዲት ቃል ይረሳል፡፡ Here in Tana (እዚህ ጣና…) የሚል ቃል ነበር፡፡ መመረቂያው ወረቀት መቀሌ ላይ ሲቀርብ እዚህ ጣና ሃይቅ ላይ የሚለው ተነብቦ ጉድ ተባለ፡፡

እንግዲህ ዳንኤል አስቻለው ጀቱን መሰለኝ፣ አስቻለው ጩልሌ የሰነፍ አራዳ፣ ስሙን እስካባቱ ጨምሮ ሚቀዳ፣ ብሎ የጻፈበት፡፡ አሰቻለው ይህንን ስራውን የሚያከናውነው የወሊሶ ጫት እየቃመ ነበር፡፡ እኔ በአካል አግኝቼው አውቀለሁ፡፡ ለቤተመንግስት አራተኛ ክፍል  ወታደራዊ ደህንነቶች የማስተርስ ድግሪያቸውን ሲሰራለቸውም በግዜው መረጃው ነበረኝ፡፡ እንግዲ ጠ/ሚ አብይንም አስቻለው ጩልሌው ወይም ማህበርተኞቹ ቢያገኟቸው ይሆናላ እንዲህ ከ62%  በላይ ከሌላ ስራዎች የተቀዳ የዶክትሬት ዲሰርቴሽን ያቀረቡት፡፡ አንድ የዶክትሬት ድግሪ ከ15%  በላይ ከሌላ የተገለበጠ ከሆነ አያስመርቅም፡፡ ያውም የሌላን ሰው ስራ ራስ ጽሑፍ ውስጥ ሲያስገቡ ምንጭ ተጠቅሶ ነው፡፡

በኢህአዲግ ዘመን ዶክተር ሳይሆኑ ዶክተር ነን የሚሉ ብዙ ነበሩ፡፡ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ የተባለ በግዜው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የቦርድ አባል ለማድረግ ይሻሙበት የነበረ ሰው ነበር፡፡ በኋላ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ዶክትሬቱም ማስተርሱም ድግሪው የውሸት መሆኑን አጋለጠበት፡፡ ባለ ግዜ ስለነበር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዶ/ር እየተባለ መጠራቱን ቀጥሎበት ነበር፡፡ ሰውዬው ግን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩንቨርሲቲ አንድ ለናቱ የባዮሎጂ ድግሪ ብቻ ነበር የነበረው፡፡

እንዲሁም ኢህአዲግ አዲስ አበባ የገባ ሰሞን አንድ ዶ/ር አብዱ(?) ምናምን የሚባል ሰው ከእንግሊዝ ሃገር መጥቶ በቴሌቪዥን እንዲሁ መግለጫ ሲሰጥ ከረመና በኋላ የሚያውቁት ሰዎች ዶ/ር አለመሆኑን ሲናገሩ፣ ድግሪውን አምጣ ቢባል ከየት ያምጣ፡፡ ጭራሽኑ እናነተ ነችሁ እንጂ ዶ/ር ብላችሁ የጠራችሁኝ እኔ ነኝ መች አልኩና ብሎ አረፈው፡፡

እንግዲህ ዶ/ር አኒ-ሚኒ-ማኒሞ(ብርሃኑ) እነዚህን የውሸት ዶክተሮች የማጋለጥ ግዴታ አለባቸው፡፡ ምነው እሳቸው 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ብቻ ጨከኑሳ? እዚህ ላይ አሰመሳይ ሙህር ምሳሌ እንደሚያበዛ እዚህ ካናዳ ውስጥ የተሰራ የመርማሪ ጋዜጠና ዶክመንተሪ ፊልም የቱብ ላይ በሚከተለው አድራሻ ገብታችሁ ተመልከቱ፡፡ Fake degrees: Exposing Canadians with phoney credentials(Marketplace)  እዚህ ፊልም ላይ ያለው ዶ/ር(?) አልፍሬድ ኦጆ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ያመላክተኛል፡፡

ወደ ሁለተኛው የንግስቲ ጥያቄ ስመጣ መልሱ አዎን በሚነገሩ ታሪኮች ላይ ተመርኩዘው የሚዘፈኑ ዘፈኖች አሉ፡፡ ለምሳሌ

መሶብ ወርቄ ተሸከረከረች

አባይን ዞራ በደም ተነከረች፡፡

አበሉሽ ወይ፣ አጠጡሽ ወይ

እንኴን ሊያበሉሽ፣ እንኴን ሊያጠጡሽ፣

አስረው ገረፉሽ፡፡

ማን ነው ገራፊው?

ደጅ አሳላፊው፡፡

ሚስቱ ወለደች የጦጣ ግልገል

እሷን ይዞ ገደል ለገደል፡፡

ይህ ታሪክ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ያለ ቅድስት ድንግል ማርያም በግብጽ የነበራትን የስደት ታሪክ የሚተርክ ነው፡፡ አንቲ ውእቱ መሶብወረቅ… (አንቺ ከሰማይ የወረደ ህብስተ መና የያዝሽ መሶብወረቅ ነሽ) እንዲሉ መጸሐፍት፤ መሰብወርቋ ቅድስት ድንግል ማርያም ነች፡፡

አባይን ዞራ በደም ተነከረች ማለት በግብጽ የነበረውን ስደቷን  የሚያሳይ ነው፡፡ የእመአምላክ ማርያምን ስደት በሚያትተው የኦርቶዶክስ መጽሐፍ፣ ዮሴፍ፣ ሶሎሜና ማርያም ከነልጇ ትእማን የተባለች ሴት ቤት ደረሱ፡፡ በቆንጆዋ ስደተኛ የቀናች እመቤትና አገልጋይ በማርያም ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ አገልጋዩ ሁለት አመት ገና ያልሞላውን ህፃኑን እየሱስን ከእናቱ እጅ ነጥቃ መሬት ላይ ጣለች፡፡

ዮሴፍ የአምላክነቱን ፍርድ ቢጠይቅ፡፡ መሬት ተከፍታ ትእማንና አገልጋዩን ዋጠቻቸው፡፡ እመቤቲቷን ከበው የነበሩ ሁሉ ወደ ዝንጀሮና ጦጣ ተቀየሩ፡፡ በቤት ውስጥ የነበሩ ውሾችም ወደ ጦጣና ዝንጀሮ የተቀየሩት ሰዎችንም ገደል ለገደል ይሯሯጡ ገቡ፤ ይላል ታሪኩ፡፡ እንግዲህ ይህ በልጆች የሚዘፈን ዘፈን ታሪኩ የተቀዳው ከዚህ መጽሐፍ ላይ ነው፡፡

ኦርቶዶክ ቤ/ክ ከአይሁድ እምነት ጋር የነበራትን ግንኙነት በተመለከተ ዩቱዩብ ላይ የፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅን ቃለ መጠይቅ በሚቀጥለው አድራሻ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ፡፡  ጥሩ ግንዛቤ የሚሰጥ ቃለ መጠይቅ ነው፡፡The Ethiopian Orthodox Tawahdo Church: Ephrem Yishak, Library of Congress

በለፈው ጠ/ሚሩ ሊነግሩን እንደሞከሩት የኋላውን ዞረን ለማየት የግድ አንድ አይን ከፊት ሌላው ከኋላ መሆን የለበትም፡፡ እግራችንም፣ ፊታችንም እጃችንም ሲሰራ ወደ ፊት አመላካች ተደርጎ የተሰራ ነውና፡፡ እዚህ ላይ  ደግሞ  ሲሜትሪና ናቹራል ዲዛይን የሚባሉ ሃሳቦች አሉ፡፡ እንግዲህ የሃገሬ ሰው ሲተርት “አንገት የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው” ይላል፡፡ ዞረን እፁብ ድንቅ የሆነውን ታሪካችንን እንመልከት፡፡

ያዲያቆነ ሴይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ፡፡ ጠ/ሚ አብይ የሰሜኖቹን ስነልቦና በመስበር እንዲሁም ስንልቦናዊ ውቅራቸው ስልጣኔን ያማያዋልድ አድርገው ማሳይት ስላለባቸው የሰሜነኞችን አባባልና ተረቶች እያነሱ መጣል ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ሰሜቲክ የሆነው ህዝብ ላይ አናረኪዝምና ኒሂሊዝም ታውጆታል፡፡

“ኑሮ ዱሮ ቀረ” ለሚለው አባባል ላይ ደግሞ፣ መች የኖራቸሁበት ግዜ ነውና…ብለው ጠ/ሚ አብይ በአደባባይ ሲሞግቱ ተሰምተዋል፡፡ እኔም ብሆን ለኢትዮጵያውያን ኑሮ ዱሮ ቀረ ባይ ነኝ፡፡ ከሃያ አመት በፊት እኔ መምህር ነበርኩ፡፡ የማገኘውም ደሞዝ ከአንድ ሺህ ብር ብዙም አይበልጥም ነበር፡፡

እንግዲህ የማወራው 1997 ዓ.ም. መነሻ አመት(Base Year) አድርጌ ነው፡፡ ከምርጫ 97 በኋላ የጤፍ ዋጋ በኢህአድግ ሸር ከሶስት መቶ ብር በላይ ከማሻቀቡ በፊት፣ የኔ ደሞዝ ስድስት ኩንታል ጤፍ ይገዛ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ይከፈለኝ የነበረ ደሞዝ ነው፡፡ ከምርጫውም በኋላ ቢሆን ከሶስት እሰከ አራት ኩንታል ጤፍ ይገዛ ነበር፡፡

አሁን ለዘመን መለወጫ ሰሞን ሃገር ቤት አንደ የመምሪ ኃላፊ የሆነ ሰው ጋር ደውዬ ደሞዝህ ስንት ነው አልኩት፡፡ አስራ ስድስት ሺህ ብር ነው ብሎ ነገረኛ፡፡ ይህ ሰው እንግዲህ ማስተርስ ድግሪ አለው፡፡ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋስ ስንት ብር ነው ብዬ ጠየቅኩት፡፡ ከአስራ ስምነት ሺህ ብር በላይ ሆኗል አለኝ፡፡

እንግዲህ የመግዛት አቅም(Affordability) እና የነገሮች አቅርቦትና መገኘት መጠን(Availability ) የሚባሉ ምጣኔ ሃብታዊ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ ጠ.ሚ አብይና አስተዳደራቸው የብር የመግዛት አቅሙን አውርደው ጥለዋል፡፡ አቅርቦትም ቢሆን በተፈለገው መጠን የለም፡፡ ምክነያቱም የመላው ሃገሪቱ ሰላም መንግስት በጥብጧታልና፡፡

ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ እንዴት ሆኖ ነው ኑሮ ዱሮ ያልቀረው? እኚህ የኦሪት(የዱሮ) ፈላሰፋ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የአይን ኋላና ፊት መቀመጥ እንደሆነ ሁሉ ያላግጡበታል፡፡ የአስራ ሁለተኛ ክፍለዘመን የአውሮፓውያኑን ረብ የለሽ የፍልስፍና  ጥያቄ “በአንድ ሰፒል ጫፍ ላይ ምን ያህል መለአክት መደነስ ይችላሉ?” (How many angels can dance on the head of a pin?) አይነት ጥያቄ እያነሱ ህዝቡን ያደናግራሉ፡፡

እንግዲህ አማርኛ በታሪክ አጋጣሚ የሰሜኑና የደቡቡ ህዝብ በተፈጥሯዊ ሂደት ያዳበረው ታለቅ ቋንቋ ነው፡፡ ሁሉ ነገሩ ሰምና ወረቅ የሆነ አልማዝም የማይታጣው ቋንቋ ነው፡፡ ወለፈንዴነትን(Paradox) በውስጡ አይጠፋውም ምክነያቱም ነገር ሁሉ አግባብ አለውና፡፡

የጠ/ሚ ወገኖች ግን ይህን ከብሔር የበለጠ፣ ከኢትጵያዊነት ትንሽ አነስ የሚል ኢትዮጵያዊ የአማራን ማህበረሰብ ማፍረስና በእራሳቸው  አምሳል፣ አሳመን ወይም አደናግር በሚለው ኦሮሙማ ርዕዬት ዳግም ማነጽ ፈለወገዋል ፡፡ ስለዚህም ተዘምቶበታል፡፡ ባለው አጋጣሚ ሁሉ ምግቡን(ዶሮ ወጡን…) ተረቱን፣ አባባሉን፣ ኑሮውንና ባህሉን ሁሉ ማውደም አቅደው እየተገበሩት ይገኛል፡፡

እንዲህም አለ ብለን ስንጽፍ ደግሞ እንዲህ ያሉትን ታሪኮች የደብተራ ታሪኮች ናቸው ሊሉን ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ የደብተራ የተባሉ ታሪኮች ደግሞ በአለም ሊቃውንት ዘንድ የተረጋገጡና እየተረጋገጡ ያሉ ሃቆች ናቸው፡፡ ታዲያ በቃል ከትውልድ ወደትውልድ ሲተላለፍ የኖረ እያደመጡ ማውራት ላይ ብቻ ታሪካችንን እንወስን እንዴ? ያውም ለብዙ ሺህ አመታት የጽሑፍ ታረክ እያለን እንኴን በብዕር ድንጋይ ቀርጸው ሃውልት አንፀው ፊደላቸውን እውን ያደረጉ አባቶች እያሉን ይህማ አይሆንም፡፡

ለእንድ ሰው አንድን ነገር ነገረህው፣ ቀጥሎ ለሌላ ሰው፣ ያም ቀጥሎ ለሌላ ሰው ቢያወራ ከስድስት የስሚ ስሚ በኋላ ኀሳቡ ተቀይሮ ሌላ መልእክት ነው የሚደርሰው ፡፡ ለዚህ ምክነያቱ ደግሞ ሰሚው መልእክቱን የሚተረጉመው በራሱ ሰሜት ዳራ ስለሆነ ነው፡፡ ድፍን ጥላቻ ሊኖረው ይችላል፣ወገንተኝነት ሊኖረው ይችላል፣ ሃሰቡን እራሱን ከጥቃት ለመከላለከል ይሞክር ይሆናል፣ መልእክቱን ሲሰማ የሚረብሹ ድምጾች ሊኖሩ ይችላሉ…በዚህና በመሳሰሉ ምክነያቶች አዲስ አበቤ እንደሚለው “ለገሃር የሞተች ቁንጫ መዘጋጃ ቤት ጋር ስትደርስ ዝሆን ተሆናለች” ነው፡፡ ይህ በስነልቦና ሙህራን ዘንደም የተረጋገጠ ሳይንሳዊ ሃቅ ነው፡፡

ለማንኛውም፣ በቃል ያለ ይረሳል በጽሁፍ ያለ ይወራሳል እንዲሉ አበው፡፡ ማንም ምን አለ ዘመኑን በዋጀ ሁኔታ ታሪካችን በተሰራበት ዘመንና ሳይንሳዊ በሆነ ሁኔታ እየመዘን እንቀጥል፡፡ ከኛ ወገን ያለሆኑት የኛን ታሪክ የሚያዩት እንደ በሰባሳ ሸክላ ሲሆን፣ አፍርሰው አብኩተው ድጋሚ ሊሰሩን የእብደት መንገድ ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ ግን አይሳካላቸውም፡፡

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር፣ ካናዳ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop

Don't Miss

Abiys Fake PHD 1.jpg

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልተስተምሮም

The title of the document is The Importance of Ministry