የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት መምህርት መስከረም አበራ በተከሰሰችበት የኮምፒውተር ወንጀል ጥፋተኛ ተብላ የ1 ዓመት ከ4 ወር እስር እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
ንቃት ሚዲያ የሚል የበይነ መረብ መገናኛ ዐውታር መስራች እና ባለቤት የሆነችው መስከረም አበራ “ኮምፒውተርን ተጠቅማ በሕብረተሰብ መካከል ዐመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” የሚል ክስ ነበር የቀረበባት።
ከሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 19 ወራት በእሥር ላይ የምትገኘው መስከረም አበራ በዚህ ክስ ጥፋተኛ የተባለችው ከሦስት ሳምንት በፊት ሲሆን የቅጣት ብይኑን ለማንበብ ከዚህ በፊት በነበሩ ቀጠሮዎች ዳኞች ሳይሟሉ በመቅረታቸው ምክንያት ሁለት ጊዜ ቀጠሮው ተራዝሟል።
ፍርደኛዋ ከዚህኛው ክስ በተጨማሪ 52 ግለሰቦች በተከሰሱበት የእነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የፖለቲካ አላማን በምያዝና በመደራጀት መንግሥትን ለመጣል በሚል የሽብር ድርጊት መፈጸም ወንጀል ክስ ተመስርቶባት ጉዳዩ በሂደት ላይ ይገኛል።
እንደ ዛሬ ሀገር ምድሩ አማራጭ አጥቶ ወይም በልቡ ሴራ ጎንጉኖ አማራ አማራ ሳይል በፊት፤ ከፊት ወተሽ ወያኔንም ፣ብልፅግናንም ፣ አስመሳይ ኢትዮዽያኒስት ነን ባዮችንም በአንደበትሽ እና በብዕርሽ የታገልሽ የዘመናችን እንቁ ሴት❤️
የልጆችሽ አምላክ… pic.twitter.com/B60WHOicBd
— Frita Samuel (@Fritasamuel1) November 28, 2024
ዘገባ፤ ሰለሞን ሙጬ DW ከአዲስ አበባ
ከዘመናት በፊት እንዲህ ተብሎ ተገጥሞ ነበር። ግን ጊዜ ጊዜን ቢተካውም የእኛው ነገር ያዘው ልቀቀው በመሆኑ የተለወጠ ነገር የለምና ለአሁኑ ጊዜም ግጥሙ ሥፍራ አለውና እንሆ።
በጊዜ ምንገባው ማምሸቱን የተውነው
ሌባ ወይም ሰይጣን አይደል የፈራነው
ማጅራት መቺዎች ጽልመት ተገን አርገው
ስላሉ ገዢዎች እነርሱን ፈርተን ነው።
ቁና ቁና ቃል ስለፍትህና ስለ ሃገር እየቦተለኩ ሰውን እንበለ ፍርድ ማሰቃየት ልማድ ሆኖብን አሁንም እንሆ ከሰባ ዓመት ሽማግሌ እስከ እሚያጠቡ አራሶች እስር ቤት በማጎር በማሰቃየት ላይ እንገኛለን። በብሄሩ የተሳከረው የሃበሻ ፓለቲካ እይታው ከመንደሩና ከጎጡ ስለማያልፍ መኖርና መሞቱ የሚለካው በራፉ ላይ ባለው ኑሮው ነው። ተምረዋል እከሌ ተብለዋል የምንላቸው ከስማቸው ጥግ ፕሮፌሰር፤ ዶክተር፤ ኢንጅኒየር፤ ፓስተር፤ ሃዋሪያ፤ ቄስ፤ ጳጳስ፤ ሸሁ ወዘተ ሁሉ አብሮ የሚተምበት ይህ ያለንበት እቡኝ ዓለም ለተጨቆኑና ለተጣሉ ድምጽ ማሰማት እንደሚገባው ዘንግቶ ዛሬ ላይ በቁሳ ቁስ ፍቅር ልብና አንጎሉ ስለተያዘ ማሰቡን ከተቀማ ቆይቷል። እይታችን ህዝባዊ መሆኑ ቀርቶ ዘረኝነትን በመቃመሱ ማን ታሰረ፤ ማን ሞተ ከእነማን ወገን ነው ብሎ መጠየቅና በሙትና በታሳሪ መሳለቅ በሃበሻ ምድር ልማድ እየሆነ መቷል። እንግዲህ በዚህ ሳቢያ ዛሬ ላይ በየጎራው ተገድሎ የሚጣለው፤ የሚታሰረው፤ ቤቱ ከውጭ ተዘግቶ በእሳት የሚጋየው አማራ የሚባለው እንደሆነ እማኝ አያስፈልግም። ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያዊነትን አጉልተው ብሄርተኝነትን አክ እንትፍ ብለው ወቀጣፊ ይደልዎ ጥፊ የሚሉትንም በጥቅል ለማምከን እየተሰራ ለመሆኑ በየጊዜው የሚሰደድ ወገኖቻች ምስክር ናቸው።
በምንም አይነት የህግ ሚዛን የወያኔ መሪዎችና ታጣቂዎች በህዝባችን ላይ ለ 27 ዓመት የፈጸሙት በደልና በሰሜን እዝ ላይ ያደረጉት የክህደትና የግድያ ወንጀል ተረስቶ ዛሬ በየስርቻው በብልጽግናው መንግስት ተከሰው መከራ ከሚቀበሉት የቁርጥ ቀን የሃገሪቱ ልጆች ሰሩ ከተባለው ወንጀል ወያኔ ከፈጸመውና በመፈጸም ካለው ጋር ቢነጻጸር የዝሆንና የጥንቸል ያህል ነው። ግን የወያኔ ደም አፍሳሾች ያን ሁሉ ወገን አስጨርሰውና ጨርሰው በነጻነት ሲፈላሰሱ ላየ አይ ኢትዮጵያ “የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የሚሉት የአበው ተረት ልክ መሆኑን ይረዳል። ለተጨቆኑ፤ ለተገፉ፤ ለተራቡ፤ ፍርድ ሲዛባ ድምጽን ማሰማት በደል አይደለም። ግን አቶ ታዲዪስ ታንቱን ለዘመናት የፈረደበት የብልጽግናው ፍ/ቤት በመስከረም አበራም ላይ እንዲህ ያለ የተዛነፈና ግራ የሚያጋባ ፍርድ መስጠቱ አለ የሚባለውን የፍትህ ስርዓት መርጦ ነካሽ መሆኑን ያሳያል። አሳዛኙ የሃበሻ ፓለቲካ እየተንገራገጨ፤ ሲሊለትም እየተገላበጠ፤ እየበላና እያስበላ፤ አዲሱ ያለፈውን ሲኮንን ነባሩ በሌላ የተራበ ጭራቅ እየተካ ዝንተ ዓለም ስናስር፤ ስንታሰር፤ ስንገድል፤ ስናገዳደል ሞት በወረፋ የቀደሙትን እንደወሰደው ሁሉ እኛንም በጊዜው ይሰበስበናል። በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ ማንም ሰው መታሰር የለበትም። ግን ፈሪዎች ከራሳቸው ጥላ ጋር የተጣሉ በመሆናቸው እንዲፈሩ የማያደርጉት የጭከና ተግባር አይኖርም። ያ ግን ፍጻሜአቸውን ያቀርበዋል እንጂ አያርቀም። የፍትህ መዛባትና እንበለ ፍርድ የሰው ልጅን ማሰቃየት ይቁም። የመስከረም አበራም በደል ለተገፉ ድምጿን ማሰማቷ ብቻ ነው። ሌላው ሁሉ ከእቃው መጠቅለያው እንዲሉ ብቻ ነው!