November 25, 2024
4 mins read

ኧረ ተው ሰጎን የሚዋደቅን ንሥር እርዳ!

60yoyoyo

የቀን ጅብ አለቅጥ ከፍቶ ቆሞ እየሄደ ሰውን ሲበላው ሲታመስ አገር፣
እርግቦች ተምድር ሲጠፉ ጆፌው ግን ልፋጩን ይዞ በሰማይ ሲበር፣
ዓለምን ንቆ ገዳም የገባ የእውነት መነኩሴ አንገቱን ደፊ መናኝ ለመምሰል፣
ኧረ ተው ሰጎን ኩምቢህን ተጉድጓድ ከተህ አንገትን ቀብረህ አትኑር፡፡
የአእዋፍ ስደት ዘር ፍጅት ለማስቆም ንሥር እንደ ጀት በሰማይ ሲበር፣
አንተ ተውሽንፍሩ ያመለጥክ መስሎህ ተድቡሽት ራስ ስትቀብር፣
ዶፍ ዝናብ ሲወርድ ተጉድጓድ የምትወጣውን ያይጧንም ያህል አታፍር?

ሰውም ከብቱንም አርዶ እሚበላ ሰይጣን የላከው ፋሽሽት ሲመጣ፣
ባምስቱ ዘመን አላየህም ወይ መናኝ መነኩሴ እንኳን እየፎከረ ሲወጣ፣
ምንይሽር ጓንዴ በልጅግ አንግቶ ጀበርና ዝናሩን ታጥቆ ሲቆጣ!

እረጅም አንገት እያለህ ዞር ብሎ ማያ አይምሮ እዝነ ልቡና ያጠረህ፣
በኩምቢህ ገጦች ገላልጠህ ብራና አንብበህ የዓለምን ታሪክ ማወቅ ያቃተህ፣
አንዳንድ እርግቦች የጠፉት በየዋህነት ስላልታገሉ መሆኑ ዛሬም ያልገባህ፣
ካጂው ጥንብ አንሳ መጥቶ በቁምህ ሆድህን እስቲዘረግፍ ትጠብቃለህ?

ኧረ ተው ሰጎን መስሎ ማደሩ አድርባይነት ይቅርብህ ታርዶ ሲጠፋ ወገንህ፣
ጆቢራው ጫጩቶችህን እየጨለፈ ተምድር ሲያጠፋ ተጅብ ጋር ሲቆምርብህ!

የሰጎን ዘሮች በጥንብ አንሳዎች ሲበሉ በባንዳ ጭልፊት መሪነት፣
ድምጥህን አጥፍተህ መኖሩ ይኸንን የማታውቅ መስለህ እንደ ሙት፣
ምን ያህል ህሊናን ብትፍቅ ብታደርግ ተአንገት ማተብን ቡጭቅጭቅ?
ምድሪቱ ቁና ስትሆን በድሮን ባሩድ እሩምታ በሰማይ ሲበር ወቢ የተፋው ጥንብ አንሳ፣
ይኸንን ያህል ዝምታ ኩምቢ ቀስረህ ተክልህ ተአሸዋ ምግብና መጠጥ ፍለጋ፣
እግዚኦ መሀርነ ክርስቶስ ያንተስ ሆድ እንደ ውቂያኖስ የሰፋ የሚስያቀረጥፍ ይሉኝታ፡፡

የንሥር አርበኛ ተፋልሞ የአእዋፍ ዘር ፍጅት ሲቆም የተሻለ ቀን ሲጠባ፣
አታፍር ይሆናል እኮ ራስክን ተደበክበት አውጥተህ አንገት ነቅንቀህ ስትመጣ፡፡

የአእዋፍን ቆሽት የሚያነድ ልብ የሚያደማ የሚያስተዛዝብ ቀን መሽቶ ሳይነጋ፣
ኧረ ተው ሰጎን እንደ አይጥ መደበቅ አቁመህ ሞረሽ ሲጠሩህ ከች በል ተጀግኖች ሥፍራ፣
በሰማይ በረህ መፋለም ባትችል በምድር እየሄድክ የሚዋደቅን ንሥር እርዳ!
 

በላይነህ አባተ ([email protected])

ህዳር ሁለት ሺ አስራ ሰባት ዓ.ም.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop