ግርማ ካሳ
በአማራ ፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ሰባት እዞች ነበሩ፡፡ በዘመነ ካሴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ በምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ፣ በኢንጂነር ደሳለኝ የሚመራው የአማራ ፋኖ በሸዋ፣ በሻለቃ ባዬ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ በሻለቃ ሃብቴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ፣ በሻለቃ መከታው የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝና በኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ፡፡
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የሚባለው፣ ከአምስት ወራት በፊት ሲቋቋምና መሪዉን እስክንድር ነጋን አድርጎ ሲመርጥ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎና የአማራ ፋኖ በሸዋ እዝ ተወካዮች አልተቀበሉትም፡፡ እነዚህ ሶስት እዞች፣ በእዝ ደረጃ አንድነታቸውን አጠናክረው ሲቀጥሉ፣ በሌሎች አራት እዞች ዘንድ ግን ችግሮች ተፈጠሩ፡፡
አንደኛው እዝ የአማራ ፋኖ በጎንደር ነው፡፡ በስብሰባዎች የዚህ ዕዝ ተወካይ የነበሩት ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ፣ ዕዙን ወክለው ድምጽ ለእስክንድር ሰጥቻለሁ ቢሉም፣ የዕዙ መሪ ሻለቃ ባዬ፣ አዲሱ ድርጅት እንደተቋም ያልተወሰነበት ውሳኔ እንደሆነ በመግለጽ፣ ውሳኔዉን በመግለጫና በቃለ መጠይቆች እንደማይቀብሉ አሳውቀዋል፡፡ ያንን ተከትሎ በፋኖ ሰለሞን አጣናው የሚመራ “እኛ ነን የአማራ ፋኖ በጎንደር” ብለው ወጡ፡፡ በአማራ ፋኖ በጎንደር መካከል ክፍፍል ተፈጠረ፡፡ አስቡት፣ ይህ ክፍፍል የመጣው ፣ አማራን አንድ ለማድረግ ነው የተቋቋመው ያሉትን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትና የእስክንድርን መሪ መሆንን ተከትሎ ነው፡፡
ሁለተኛው ዕዝ በሻለቃ ሃብቴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ነው፡፡ ይህ ዕዝ ለእስክንድር ነጋ ድምጽ በመስጠት፣ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን የተቀላቀለ ዕዝ ነው፡፡ በቅርቡ ይፋ በሆነው ዘገባ መሰረት፣ የዕዙ የበላይ ጠባቂዎች፣ ይህ እስክንድር ነጋ መሪ ነኝ ያለውን አማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን እንደማይቀበሉ አስረድተዋል፡፡ መጀመሪያ የጎንደር ፋኖዎች አንድ መሆን አለባቸው በሚል፡፡ እንግዲህ ይህ ክፍፍል የመጣው ፣ አማራን አንድ ለማድረግ ነው የተቋቋመው ያሉትን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትና የእስክንድርን መሪ መሆንን ተከትሎ መሆኑንም በድጋሜ እናያለን፡፡
ሶስተኛው በኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ የሚመራው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ነው፡፡ ኮሎኔሉ የክፍለ ጦር አዛዦችን ሳያማክሩ ፣ እስክንድር ነጋ የሚመራውን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን በመቀላቀላቸው፣ ከጅምሩ ነበር ተቃውሞን ያስተናገዱት፡፡
ኮሎኔሉ በስራቸው አራት ክፍለ ጦሮች ይመሩ ነበር፡፡ በርሳቸው ስር የነበረው ግዙፉ የላስታ አሳምነው ክፍለ ጦር (አሁን ኮር ሆኗል)፣ የኮሎኔሉን ውሳኔ እንደማይቀብል ገልጾ፣ በምሬ ወዳጆ የሚመራውን የአማራ ፋኖ በወሎ ተቀላቅሏል፡፡ ሌላው ሰፊ ቦታ ይሸፍን የነበረው የእስክንድር ነጋ ክፍለ ጦር ይባል የነበረው፣ ለሶስት ክፍለ ጦሮች እንዲሸነሸን ተድርጎ፣ ሁለቱ ክፍለ ጦሮች፣ የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦርና፣ የንጉስ ሚካኤል ክፍለ ጦር፣ ከአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ወጥተው በምሬ ወዳጆ የሚመራውን የአማራ ፋኖ በወሎ ተቀላቅለዋል፡፡ መካነሰላምና ወግዲ አካባቢ ያለው፣ እስክንድር ነጋ ከሚል ወደ መብረቅ ክፍለ ጦር ራሱን የቀየረና በሻለቃ ሃምታሙ የሚመራ ክፍለ ጦር ብቻ ነው በምእራብ ወሎ በአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ስር ያለው፡፡ ሶስተኛው ክፍለ ጦር የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን አልቀበልም ብሎ ለብቻው የወጣው፣ በደሴ አቅራቢያ የሚንቀሳቀሰው የልጅ እያሲ ክፍለ ጦር ነው፡፡ የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር አሁን ወደ ኮር ተሸጋግሯል፡፡ ከነምሬም፣ ከነኮሎኔል ፋንታሁን ጋር አይደለም፡፡ አራተኛው ክፍለ ጦር የመቅደላ ጽናት ክፍለ ጦር በአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ስር ቀጥሏል፡፡
እንግዲህ እዚህ ጋር የምናየው ኮሎኔል ፋንታህኑን ሙኸባ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የክፍለ ጦር አዛዦችን ሳያማክሩ በመቀላቀላቸው፣ በእርሳቸው ስር የነበሩትን 75% ፋኖዎች አጥተዋል ማለት ነው፡፡ ከዚህ አማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ጋርም በኮሎኔል ፋንታሁን ይመራ የነበረው የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ በጣም አንሷል ማለት ነው፡፡
አራተኛው የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የተቀላቀለው፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ነው፡፡ ይህ ዕዝ የወሰነውን ውሳኔ ሲወስን፣ እነ ሻለቃ መከታውም የክፍለ ጦር አዛዦች ሳያማክሩ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በርካታ በዕዙ ያሉ ብርጌዶች፣ የዕዙ መሪ ሻለቃ መከታውን በመቃወም፣ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን እንደማይቀበሉ እያሳወቁ ነው፡፡ “እኛ የሸዋ ህዝብ ፋኖዎች እንጂ የግለሰብ ዘብ አይደለንም፡፡ እኛ የሸዋ ፋኖዎች አንድነት ነው የምንፈልገው” ሲሉ ጠንከር ባለ መልኩ የዕዙን አመራሮች እየሞገቱ፡፡
እዚህም የምናየው፣ ከዚህ እስክንድር ነጋ ከሚመራው አማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ጋር በተገናኘ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መታመሱን ነው፡፡ ይህ ዕዝ በሽዋ ብዙ ዘመቻዎችን የሚያደርግ ጠንካራ ዕዝ ነበር፡፡ ሆኖም ላለፉት አምስት ወራት ግን በዕዙ ውስጥ ግሪድሎክ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ፣ አልፎ አልፎ ካልሆነ፣ ያን ያህል በፊት ሲያደርግ እንደነበረው እንቅስቃሴ ሲያደረግ አይታይም፡፡
እነዚህን እንደ ማስረጃ የማቀርበው፣ ይህ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የሚባለው እንኳን የተቋቋመለትን ዓላማ ሊያሳካ ቀርቶ፣ እንደው የበለጠ በፋኖዎች መካከል ችግሮች እየፈጠረ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡
ይህን ድርጅት ያልተቀበሉ ፣ አንድነታቸውን ጠብቀው ብዙ ስራዎች እየሰሩ ነው፡፡ ይህ ድርጅት የተቀበሉ ግን ውስጣዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል፡፡
ይህ ድርጅት እነ እስክንድር ነጋ እንዳሉት፣ ሌሎችንም አካቶ አንድ ሆኖ ቢወጣ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ያም እንዲሆን፣ በርካታ ምክረ ሃሳቦችን አቅርበን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይኸው አምስት ወር አለፋቸው፡፡ ምንም ነገር የለም፡፡ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የሚባለው ያመጣው፣ የፈየደው ምንም ነገር የለም፡፡
ስለዚህ፣ መሰረትን የሚሉትን ድርጅት ወደዚያ ጥለው፣
#እነ ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ ከነሻለቃ ባዬ ቀናው ጋር በመሆን፣ ልክ እንደ ጎጃም፣ አንድ የጎንደር እዝ መመስረት ነው ያለባቸው፡፡
#ኮሎኔል ፋንታሁን ሙኽባም፣ ለብቻው ካለው የልጅ እያሱ ኮር ፣ እንዲሁም ከነ ምሬ ጋር ቁጭ ብለው ለመነጋገርና፣ አንድ የወሎ እዝ እንዲመሰረት ለማድረግ መዘጋጅት አለባቸው፡፡
#ሻለቃ መከታው ማሞ እስክንድር ነጋን ሳይሆን የሸዋ ህዝብ የሚለውን ማዳመጥ መጀመር አለበት፡፡ የየአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የሚለውን የሸዋ ፋኖዎች አይቀበሉትም፡፡ ስለዚህ በስሩ ያሉትን ፋኖዎች ጥያቂ ሰምቶ፣ ከወንድሞቹ ከነኢንጂነር ደሳለኝ ጋር በመነጋገር፣ ሸዋን አንድ ለማድረግ መዘጋጀት አለበት፡፡ ያንን ማድረግ ካልፈለገ፣ ከሸዋ ህዝብ ይልቅ እስክንድርን የሚል ከሆነ፣ ከሃላፊነቱ ይልቀቅ፡፡ የሸዋ ፋኖዎች አንድ የሚያደርጋቸው መሪ እንጂ፣ የሚከፋፍላቸው፣ ከነርሱ ይልቅ ሌላ ሶስተኛ አካል የሚከተል መሪ አይፈለጉም፡፡
እስክንድር ነጋስ ምን ይሆናል ? በፊትም አንዱን እዝ ተቀላቅለህ ፣ ስራ ስንለው እንደነበረ፣ አሁንም አንዱን እዝ ተቀላቅሎ ቢስራ የበለጠ ጥሩ ይሆናል፡፡ “የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት” የሚለውን ነገር ከዚህ በኋላ ማቆም አለበት፡፡ ግትርነቱን ማቆም አለበት፡፡ ሜዳ ላይ ፋኖዎች በቃ ይህ “የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት” የሚባለውም የአማራ ህዝብ ግንባር፣ በኋላ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የሚባለው እንዳልተቀበሉት አይቀበሉትም፡፡ እስክንድር ነጋ ሜዳ ላይ ካለው እውነታ ጋር መታረቅ መቻል አለበት፡፡
Mr. Girma Kassa!
You are tottaly wrong. You’ve no idea about the real FANO s of Shoa and Bete Amhara ( Wello) either. What is indeed the reality on the grond? The truth of the matter is that so called Gojam and Wello Misraq of Zemene Kasse and Mire Wedajo were and are ANDM/ BEadean surrogates. These nasty paid agents are bragging and oppening their bad mouth against all Shoans in genaraeal and especiallay Eskindir Nega, Meketawu Mamamo. As they are good for nothig, we do not mind. We are dead sure they are wicked persons. So hand off from patriot Eskindir and Meketawu Mamo of Shoa. We alone liberate our capital and crush Galla invaders! Beaden’s agents of Gojam, Gondere and Welloye are traitors. Shoa and all Shoans in Harergehr, Arusi, Bale, Sidamo, Keffa, Gamo Gofa , Ilubabor and Wellega prevail.