November 8, 2024
5 mins read

ክብር ለጋሼ ታዲዮስ ታንቱ !! (አሥራደው ከካናዳ)

Tadios Tantu« Et s’il n’en reste qu’un, je serai celui-là ! » Victor Hugo

  • « በመጨረሻ  አንድ ሰው ብቻ ቀረ ቢባል እንኳ፤  ያ ሰው እኔው እራሴ እሆናለሁ.. » !!  ቪክቶር  ሁጎ

ናፖሊዮን ሦስት በፈረንሳይ ( በ ዲሴምበር 2  1851 እ .ኤ.አ  ) መፈንቅለ መንግሥት አድርጎ  በነገሠበት ወቅት፤  ቪክቶር ሁጎ  ንግሥናውን በመቃወሙ፤ ናፖሊዮን ቪክቶር ሁጎን እንዲታሰር  ሲወስን፤ ቪክቶር ሁጎ አገሩን ፈረንሳይን ጥሎ ተሰደደ ::

በስደት ከሚኖርበት ቦታ፤  ጸሃፊና ገጣሚው ቪክቶር ሁጎ፤ የሚከተለውን ጽፎ ለህዝብ አሰራጨ፤

  • « ከሺህ በላይ ተቃዋሚ  ሰዎች ቢኖሩ ከነሱ መሃል አንዱ እሆናለሁ !!
  • መቶ ያህል ተቃዋሚ ሰዎች ብቻ ቀሩ ቢባል ፤ አሁንም ከመሃላቸው አንዱ ለመሆን ቆራጥ ነኝ !!
  • አሥር ተቃዋሚ ሰዎች ያህል ብቻ ቀሩ ቢባል እንኳን፤ አሥረኛው እኔው እራሴ እሆናለሁ !!
  • በመጨረሻ አንድ ሰው ብቻ ቀረ ቢባል ፤ ያ ሰው  እኔው እራሴ እሆናለሁ.. » !!

ብሎ ነበር ::

በአምባ ገነኑ የአብይ አህመድ ሥርዓት፤ ፍትህ መደፍጠጧ እየታወቀ፤ የጎሣ ካባ በተከናነቡ፤ ዳኛ ተብዬ ካድሬዎች፤ ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሀፊው፤ ጋሼ ታዲዎስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል ::

ይህ ውሳኔ፤ የሥርዓቱን ዝግጠት ወለል ብሎ ከማሳየቱም በላይ፤ ዘረኝነቱ ምን ያህል አፍጥጦ፤ ጥላቻው ምን ያህል አግጥጦ፤ መንሰራፋቱን ያሳየናል ::

መብት ረግጦ፤ ፍትህን ደፍጥጦ፤ ጎሠኝነትን አውጆ፤  ዘረኝነት አንግሶ፤  ህዝብን  እያፈናቀሉ  ሜዳ ላይ በመጣል፤ የኑሮ ዋስትና በማሳጣት ፤ በኑሮ ውድነት እያሰቃዩ ፤ በርሃብ ጭምር  ህዝብን ለመፍጀት፤  የሚደረገውን የሰባዊ መብት ገፈፋ፤ በቃ ልንለው ይገባል ::

በኢትዮጵያ ህዝብ፤ ግብር ከፋይነት የተመሠረቱትን ተቋማት ለባዕዳን እየቸበቸቡ፤  የጦር መሣሪያ በመሸመት ፤  ሕዝብን በጦርነት ፈጅቶ፤ እግርን አንፈራጦ ለመግዛት የሚደረገውን፤ ፋሽስታዊና ፀረ ሕዝብ  ድርጊት፤ ዜጎች በአንድነት በመነሳት ታግለው ሊያስወግዱት ይገባል ::

አሁንም ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ በመቀጠል ፤ ዕድሜ ሳይገድባቸው፤ ፍርሃት ሳይደፍራቸው፤  ለፍትህ ዘብ በመቆም ፤ የጎሣና  የዘረኝነት ሥርዓቱን ፊት ለፊት በመጋፈጥ፤

« በአገር ውስጥ፤ ለፍትህ ዘብ የሚቆም፤ አንድ ሰው ብቻ ቀረ ቢባል ፤  እኔው እራሴ  እሆናለሁ » እንዳለው፤  እንደ ቪክቶር ሁጎ፤ ለአገራቸውና ለወገኖቻቸው ክንር ፤ በቆራጥነት  ለሚታገሉት አዛውንት፤ ጋሼ ታዲዮስ ታንቱ ትልቅ ክብር ይገባቸዋል ::

ክብር ለጋሼ ታዲዮስ ታንቱ !!

ይችን አጭር ማስታወሻ ለምታነቡ  ወገኖቼ በሙሉ !!

ለፍትህ የበላይነት፤ ለሰብአባዊ መብት መከበር፤ ለአንድነት፤ ለወንድማማችነትና ለነፃነት መከበር  ስትሉ፤ በሃሳብ መስጫው ቦታ ላይ፤ የጋሼ ታዲዮስ ታንቱን ምስል በማስፈር፤  ከግርጌው : ክብር ለጋሼ ታዲዮስ ታንቱ !!

በማለት ድጋፋችሁን እንድታደርጉላቸው፤  በአክብሮት እጠይቃለሁ ::  አደረራ !!

ከራሴ ልጀምር   

 

ክብር ለጋሼ ታዲዮስ ታንቱ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop