November 8, 2024
15 mins read

የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ ፍትህን የሚከላከልበት ጊዜ አሁን ነው-.ትራምፕና ኢትዮጵያዊያን

ኞቬምበር 8፣2024

ደራሲው አክሎግ ባራራ (ዶ / ር)

“የአሜሪካ ዶላር ያለን ዶላር ለዘላለም የተጠባባቂ ምንዛሬ እንደሆነ የሚናገሩ ኢኮኖሚያዊ ሕግ ወይም ፊዚክስ የለም.”

የአርቫንድ ንዑስ ክፍል, ፒተርሰን ተቋም

የማይቀየሩ እና የማይለወጡ በሕይወታቸው ውስጥ ጥቂት ጉዳዮች ብቻ አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የዓለም አኗኗር ሕንፃው (ፕላትፎርም) ፈጣን መለወጫው እና ይህንን የሚያግዙበት የመሣሪያ ስርዓቶች  (ህግጋት) ናቸው።  አንደኛው ኃያል አገር በበላይነት ሊገዛና ሊሠራ፤ መላውን ዓለም ለዘላለም ሊቆጣጠር ይችላል የሚል  ሕግ የለም። ታላቋ ብሪታንያ ታሪክ ሆናለች፤ አልፋለች። የሮማን ኤምፓየር፤ የኦቶማን ወዘተ ኤምፓየር አልፈዋል።

ዲሞክራት ሆነ ሪፐብሊካን፤ ተከታታይ የአሜሪካ ባለሥልጥናት ለመላው ዓለም እንደሚናገሩት ከሆነ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ የሚንጸባረቀው በሕገመንግሥቱ መሰረት የሕግ የበላይነት ሲከበር ነው። ይህንን ስኬታማ የሚያደርጉ ተቋማት አሉ–ገለልተኛ ፍርድ ቤቶች፤ ገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን፤ ነጻና ገለልተኛ ማህበረሰባዊ ድርጅቶች፤ ፍትሃዊ፤ ጫና የሌለበት፤ ግልጽነት ያለው፤ ተፎካካሪነትን የሚያሳይ ወዘተ ምርጫና የሕዝቡን የምርጫ ውጤት የሚያከብርና የሚቀበል፤ ለይስሙላ ብቻ ያልሆነ ምርጫ። ባለፈው ሳምንት የታዘብኩት የአሜሪካ ምርጫ ይህንን ያንጸባርቃል።

ካሜላ ሃሪስ ተሸንፈው ዶናልድ ትራምፕ መመረጣቸው የአሜሪካ ዲሞክራሳዊ ስርዓት የሚሰራ መሆኑን ያሳያል። የሕዝብ ድምጽ ወሳኝ ነው። ትራምፕን ለምን መረጡ? ወደሚለው ለመሄድ አልችልም። ውሳኔው የአሜሪካ ሕዝብ እንጅ የኔ ሊሆን አይችልም። ውጤቱን ግን አከብራለሁ።

እንደ እኔ ፍትሃዊ ካልሆነ በየወቅቱ ምርጫ ማካሄድ በተናጥል ዲሞክራሳዊ አያደርገውም። የሕዝብን ድምጽ፤ ብሶትና ተስፋ የማያንጸባርቅ ምርጫ ዲሞክራሳዊ አያደርገውም። ዲሞክራሲ ተቋም ነው። ባህል ነው። ልምድ ነው። እሴት ነው።

ዲሞክራሴ እሴት ነው ከተባለ የአሜሪካ የውስጥ ዲሞክራሳዊ እሴት፤ አስተዳደር እና አፈጻጸም ከአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ጋር መያያዝ ይኖርበታል። የአሜሪካ መንግሥት ግን ለዓለም ሕዝብ የሚሰብከው ብሂል ከአገሪቱ የዲሞክራሲ ስርዓት፤ እሴት፤ ባህል ወዘተ ጋር አብሮ ሲሄድ አላየሁም። ባለፉት አምሳ ዓመታት የአሜሪካ መንግሥት በዓለም ደረጃ ብዙ ጦርነቶችን አካሂዷል—ቬትናም፤ አፍጋኒስታን፤ ኢራክ፤ ሶሪያ ወዘተ። አምባገነኖችን ደግፏል፤ ችሌ፤ አርጀንቲና ወዘተ።

ይህ ታሪክ የሚያሳየው ፕሬዝደንቱ ዲሞክራት ወይንም ሪፕብሊካን ቢሆን ፖሊሲው የአሜሪካን ጥቅም ብቻ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ነው። እርግጥ መጠኑ ይለያያል።

ይህ ሁኔታ ወደ ሚዛናዊ ፍትህ፤ ሰብአዊ መብቶች ስኬት ያመራኛል።  በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግሥታት የተመሰረተበት ዋና ምክንያት ጦርነትን ለመግታት ነው። ቢቻል ለማቆም። በዚህ መስፈርት የተባበሩት መንግሥታት ወድቋል ለማለች እችላለሁ። እንደ አሜሪካ ያሉት ኃያላን አገሮች የሚመሩት የዓለምን ሕግና ደንብ ተከትለው ሳይሆን የራሳቸውን ሥትራተጂክ ፍላጎት ስኬታማ ለማድረግ ሆኖ ይታያል። ሰብአዊ መብቶችን፤ በተለይ ብሄር/ዘውግ/እምነት ተኮር እልቂቶችን እንዴት ይመለከቷቸዋል? ለምሳሌ ፤ጋዛን፤ ዳርፉርን፤ አማራውን?

በዓለም ደረጃ ክፍተቱ በማን ይሞላል?

የአሜርካ መንግሥት በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ተጽኖ ያለው መንግሥት ነው። እልቂትን (ጀኖሳይድን) በሚመለከት የአሜሪካ መንግሥት፤ የአሜሪካ ምክር ቤት ወይንም ኮንግሬስ የማያሻማ አቋም አላቸው።

አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (The UN sanctioned International Criminal Court/ICC) አይዳኘንም፤ አያገባውም የሚል።

አያገባውም ከተባለ የብሄር/ዘውግ/እምነት እልቂትን በሚመለከት የተጎዱት ግለሰቦች ወይንም አካላት አቤቱቷ የሚያቀርቡት በተባበሩት መንግሥታት በኩል ለጸጥታው ምክር ቤት ይሆናል። ይህ ተቋም ከተስማማ ወደ አይሲሲ ይመራዋል።

አሜሪካ ወይንም ሩሲያ ወይንም ቻይና ወዘተ አሉታዊ ድምጽ ከሰጡ ግን አይሲሲ ስራውን ሊሰራ አይችልም።

የአሜሪካ መንግሥት አይሲሲ ሃላፊነቱን እንዳይወጣ ለምን ጫና ያደርጋል? ብየ ራሴን ስጠይቅ፤ የአሜሪካ ዜጎች፤ ወታደራዊና የደህንነት ተቋማት ጦርነትና እልቂት ባከሄዱባቸው ቦታዎች በተከሰቱ ግድያዎች የአሜሪካ ዜጋዎች እንዳይከሰሱ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ይህንን ሃቅ መቀበል አለብን። የዓለም ሕግጋት፤ ተቋማትና አስተዳደር፤ የፍትህ ስኬት ተለውጧል።

ሌላ አማራጭ አለ?  

በፍጥነት እየተደራጀና አባላትን እያሰፋ ያለው የብሪክስ እንቅስቃሴ እንደ አማራጭ ይታያል (The BRICS Platform as an alternative)::

ይህ እንቅስቃሴ የሚጋራው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የተመሰረቱት የፋይናንስ፤ የንግድ፤ የዓለም አቀፍ ህግጋትና ተቋማት ለመላው ዓለም ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነ ደረጃ ለማገልገግል አልቻሉም የሚል ነው። ለምሳሌ ዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ፤ የጸጥታው ምክር ቤት ወዘተ። የአሁኑ ሞዴል መፍረስ አለበት የሚል መሆኑ ነው። ለምሳሌ አፍሪካ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት አባል መሆን አለባት የሚለው።

የኃብትና የኢኮኖሚ ጥንካሬውንና እንቅስቃሴውን ስመለከተው እመርታዊ ለውጥ በግልጽ ይታያል። እ.ኤ.አ. በ 2024 አምስቱ የመጀመሪያዎቹ  የብሪክስ አባላት– ብራዚል፤ ሩሲያ፤ ህንድ፤ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ – ብቻ ጠቅላላ ገቢያቸው (Cumulative GDP) $ 29 ትሪሊዮን ዶላር ነበር::  አዲስ አባላት ከተቀላቀሉ ጀምሮ የጨመረውን አቅም ስመለከት እመርታዊ ለውጥ ( Tectonic)  ለውጥ ነው ለማለት እችላለሁ። ይህ አውነታው  ሂደት አስተሳሰባችን እንዲለወጥ ያስገድደናል።

ግን፤ ብሪክ ስሰብአዊ መብቶችንና እልቂቶችን በሚመለከት ያላቸው አቋም ምንድን ነው? ብየ ራሴን ስጠይቅ፤ ፍይዳቸው ግልጽነት የለውም። በአምባገነን መሪዎች የሚመሩ አገሮች ለሰብአዊ መብት ደንታ እንደሌላቸው እናያለን። ይህንን ሁኔታ የማስተካከል ግዴታ አለባቸው ብሪክሶች።

የማያሻማው የዓለም አቀፍ ተቋማት፤ ሕግጋትና አካሄድ ሃቅ ግን አንድ ነው። ይኼውም የተባበሩት መንግሥታትና ተቋማት ብዙም ሳይቆይ የተሻሻሉ እና የተስተካከሉ ካልሆኑ በስተቀር የተባበሩት መንግስታት ስርዓቱ ከዓለም ሕዝብ ግማሽ የሚሆኑ ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ምኞት ያላቸውን፤ ፍትሃዊ፤ ሚዛናዊ እና ውክልናን (Fair representation) የሚያንጸባርቅ ካልሆነ ችግሮችን በጦርነት ብቻ እንፈታዋለን የሚለው አደገኛ መርህ ይቀጥላል። የሰው ክብር፤ ደህንነትና ህያውነት ፋይዳቢስነት ይባባሳል።

ብዙ የአፍሪካ አገሮች የሚሳተፉበት ብሪክስ ራሱን ዲሞክራሳዊና አሳታፊ ካደረገ፤ ግልጽነት ካለው፤ ወደፊት የዓለምን ሕግጋትና፤ የኢንቨስትመንት፤ የፋይናንስ፤ የንግድና የሕዝብ ግንኙነቶችን ተቋማት መቀየሩ አይቀርም።

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን፤ እኔን የሚያሳስበኝ፤ ባለፉት አስር ዓመታት ብቻ  የዘር ማጽዳት፤ የጅምላ ወረርሽኝ፤ የጅምላ ሥልጣን ነጣቂነት፤ የጅምላ ጭንቀት፤ የጅምላ እሴቶችና ቅርሶች አፍራሽነት (De-construction and start from zero model)፤ የመገመናኛ ብዙሃና የመንግሥት ያልሆኑ የማህበረሰብ ድርጅቶች መዳከም  ወይም ፈጽሞ መውደም፤ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ያለውን አደገኛ ሁኔታ ያንጸባርቃዓል።

ሃላፊነቱ የምእራብ አገሮች ወይንም የብሪክስ ብቻ አይደለም። የሁሉም ነው፤ በተለይ ተግዳሮት በተከሰተባቸው አገሮች የሚኖረው ሕዝብ በአንድነት ሆኖ ለመታገልና ድምጹን ለማሰማት አለመቻሉ። ለፍትህ መታገል ያለበት ሕዝቡ ነው።

ድምጸአልባ ለሆኑት ማን ይናገራል?

ደጋግሜ የምጠይቀው  የምእራብ ሚዲያ የት አሉ? የብሪክስ ሚዲያዎች የት ናቸው? ለእልቂት ለምን ሺፋን አይሰጡም?

እኔ በምእራብ ሀገር ውስጥ እኖራለሁ። ተጠቃሚ ነኝ። በምርጫው ጊዜ በየዕለቱ የሚተኮሩ የነበሩትን ሚዲያዎች ተከታትያለሁ። ስለ ዘር፤  ብሄር/ዘውግ/እመነት ተኮር እልቂት ለምሳሌ ሱዳን፤ ጋዛ፤ ኢትዮጵያ አንዴም ቢሆን ውይይት ሲደረግ አላየሁም። ድምጻቸው እንዲጎላ የተደረጉት በጉብኝት ላይ የነበሩ መሪዎች የኢስራኤል መሪ ኔተንያሁና የዩክሬን ፕሬዝደንት ዜለንስኪ ብቻ ናቸው፤ ይህም ሚዛናዊና ፍትሃዊ ባልሆነ ደረጃ። ሚዛናዊ አይደለም የምለው ፓሌስትንያንን ያላቀፈ ስለሆነ ነው።

የአሜሪካ መንግሥት በእልቂት ላይ አቋም የማይወስድ ከሆነ አማራጩ ምንድን ነው?

የተጎዱት ያላቸው የአቤቱታ ምርጫ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው። የአፍሪካውን ለጊዜው እንርሳው። አማራጩ አለም አቀፍ የወንጀል ፍ / ቤት (ICC) ነው።

ደቡብ አፍሪካ የጋዛን እልቂት በሚመለከት ለአይሢሲ አቤቱታ አቅርባለች። ምስጋናየን እገልጻለሁ።

ለመደምደም፤ ዋናው መመለስ ያለበት ጥያቄ አይ.ሲ.ሲ ን በሚመለከት የአሜሪካ መንግሥት ለምን ICCን ይቃወማል የሚለው ነው?

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ካልቻልን “ላም አለኝ” በሰማይ ሆኖ አየዋለሁ።

ፕሬዝደንት ትራምፕ የአሜሪካን የውጭ አቋም ከቀየሩት፤ ለእልቂት ቦታ ከሰጡት፤ ድምጽ ካሰሙ በታሪክ ከፍተኛ ቦታ ይኖራቸዋል።

November 8, 2024

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop