October 31, 2024
14 mins read

ለቀባሪው አረዱ ነውና ነውር እንዳይሆንባችሁ፣

GagAlEMXQAA320eከጥሩነህ ግርማ

ኢትዮዽያዊነትን ለአማራ ለማስተማር ግራና ቀኝ መዝለል ከድካም ውጪ የሚያመጣው የለም።  የኮነናችሁዋትን ያቆሰላችኋትን ሃገር የተከላከለላት፣ የቆሰላት፣ የሞተላት አማራው ነውና  በደሙ ስር ስላለችው  አማራ ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል እንደሚባለው ከእንቅልፍ ባኖ ባለቤቱን ቤትህ ነው ማለት ከንቱነት ነው። ኢትዮዽያ ማለት አማራ ነው በሚል ሂሳብ አማራን ለመውጋት ኢትዮዽያ ተውግታለች::

አማራ የአማራ ብሄርተኝነቱን ተላብሶ ለህልውናው በትጥቅ ትግል ሲነሳ የጠሏትን ኢትዮዽያ እኛ እናድናለን ብለው ሁለተኛ መዋሽት ባሳፈራቸው ነበር።  ኢትዮዽያን ለማዳን ልባዊ ፍላጎት ቢኖራቸ ኖሮ አማራ ምንም አይነት ተቃውሞ እንደማይኖረው ይረዱት ነበር።

አማራነትና ኢትዮዽያዊነት ለብዙ ሽህ ዓመታት ያለምንም ቅራኔ ኖረዋል:  ኢትዮዽያዊነት የተጫነብን አበሳ ነው ብለው ትርክት የፈጠሩት አማራን ከኢትዮዽያዊነት ጋር ስለሚያዛምዱት ነው::

አፍርሰን እንሰራታለን ያሉት  እነሌንጮ በአማራ መቃብር ላይ መሆኑ ነው: ያለ ሃፍረት ስለሚናገሩት ብዙ ማለት አያስፈልግም: በደሙና በአጥንቱ ጠብቆ ያቆያትን ሃገር አማራን ከኢትዮዽያዊነቱ ለመገንጠል ያልፈጠሩት የውሸት ትርክት የለም::

ወራሪ፣ ነፍጠኛ፣ አግላይና ጨቋኝ ተብሏል: አቅማቸው የሚፈቅድላችን የጥላቻ ቃላት አውርደውበታል ግን ተሳስተውም እንኳ ስለሃገር ገንቢነቱ የታሪክ ባለቤትነቱ አይተነፍሱም: ዛሬ ገንዘቡንም ጦሩንም በእጃቸው አስገብተውና ሃገር ተረክበው ማስተዳደር ሲሳናቸው ቀኝና ግራ እየተወራጩ ሃገሪቱን የዘመነ መሳፍንትን በሚያስታውስ መልኩ ስረዓተ አልበኝነትን አንግስውባታል:: በዘመነ መሳፍንት ከሰማንያ አመታት በላይ በጎንደር ቤተ መንግስት እየተቀያየሩ ነገስታት የነበሩ ቢሆንም ሃገሪቱ በየአካባቢው ደጃዝማቾች ተከፋፍላ መሪ አልባ ነበርች:

ዛሬም አብይ ሃገር ማስተዳደር ተስኖት ሽመልስንና አዳነችን በመጋራት የአዲስ አበባ ከንቲባ ተግባርን እያከናወነ ነው: ሶስት ሆነውም ቢሆን አዲስ አበባን ማስተዳደር ተስኗቸው ዘርፊያና ግድያው በከተማዋ የቀን ተቀን እውነታ ሆኗል: ገፍተው ገፍተው ያመጡትን የአማራ ብሄርተኝነት የሆድ ህመም ቢሆናቸውም የተመኙትን አግኝተዋል: ግን የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ሆነና በጥላቻ እየተናነቃቸው ያጥሏሏትን ኢትዮዽያን እነሱ አፍቃሪ ሆነው አማራውን ፀረ ኢትዮዽያ አድርጎ ለማቅረብ የሚያደርጉት ማላዘን  የወቅቱ ዜማቸው ነው:: ትንሽም ሃፍረት ስለማይኖርቸው የትናንቱና

የዛሬው ትርክታቸው ይዞ ሲያጋጫቸው አይሰሙትም::

ይህም ሆኖ ኢትዮዽያን እናድናት ሲሉ በማፈራረስ ላይ እንደተሰማሩ ተግባራቸው ያሳያል: አማራው ኢትዮዽያዊነቱ ማተቡ መሆኗን ድርቁናቸው ስላወራቸው ማየት አይችሉም:: ኢትዮዽያ የመቶ አመት ብቻ ነው ታሪኳ የሚሉት ግብዞች ሽህ አመታትን ያሻገራትን አማራ ኢትዮዽያዊነትን ከቶ ሊያስተምሩ እውቀቱም ሞራሉም የላቸውም::

እነሱ ብቻ አይደሉም አማራንና ኢትዮዽያዊነትን የሚያምታቱት: ልዩነቱ እነሱ ሆነ ብለው ሲሆን የአማራ አደናጋሪዎች ግን ስለተደናገሩ  ጥቂቶቹ ደግሞ ለኦሮሙማ ስላደሩ ነው።

ለኦሮሙማው ደቀዛሙርትና አገልጋዮች ምንም ማለት አያስፈልግም ተግባራቸው የተሻለ ስለሚገልፀው:: ተደናግረው የሚያደናገሩትን ግን ትንሽ ልበላቸው:

የአማራ ፋኖንም ሆነ የአማራን ህዝብ ኢትዮዽያዊነት ልትነግሩት ስትሞክሩ በራሳችሁ እምነት ላይ ችግር እንዳለባችሁ ያጋልጣል: የአማራ ህዝብ የሚቻለውን ሁሉ ሰላማዊ የትግል ለረዥም ጊዜ ተግባራዊ አድርጏል ሰሚ ግን አልነበረውም:: ኢትዮዽያዊነቱን በኩራት ተሸክሞ ብዙ ተጉዟል: ወራሪና ነፍጠኛ ከመባል ግን አላዳነውም: ይህም ሆኖ ዛሬ በአማራነቱ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ እየተከላከል ኢትዮዽያ የኔ አይደለችም አላለም:: በአማራነት ማዕቀፍ ስር ተደራጅቸ እራሴን ላድን ማለቱ የኢትዮዽያዊነት ሰባኪ ደብተሮችን ለምን አሳሰባቸው? አማራ አማራን ሳያድን ኢትዮዽያ እንደማትኖር ይረዳዋል። ኢትዮዽያ ያለ አማራ አማራም ያለ ኢትዮዽያ መኖር አይችሉም: ይህን የቆየ ሃቅ ለማሰቀጥል አማራ በሞት ሽረት ትግል ላይ ነው። ነገር ግን ቅድሚያው እራስን ማዳን ነው: የአማራ ተወላጆች በኢትዮዽያዊ ድንኳን ውስጥ ተደብቀው አማራዊ ትግሉን አለመቀላቀል በህልውና ላይ ያላቸውን ብዥታ ወይም አውቆ መሸሸግን ያሳያል:: መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮዽያ የሚለው ግልፅ ያለሆነ መፈክር አይሉት የትግሉ

መመሪያ ወይም ቃላ ማድመቂያ፣ አፍ ማሞቂያ ግራ አጋቢ ነው: በግርድፉ እንየው ከተባለ ፋኖን ይዞ ኢትዮዽያን ተቆጣጥሮ ስልጣን መያዝ ማለት ነው::

የአማራ ተቀዳሚ ጥያቄ ስልጣን መያዝ አይደለም በመጀመሪይ የህይወት ዋስትና ማረጋገጥ ነው: ስልጣን በኢትዮዽያ ያሉ ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ የጋራ አወቃቀር ነው:: መዳረሻችን ኢትዮዽያ እንደ ፕሪንሲፕል ለፋኖ ችግር የለውም: ኢትዮያዊነቱን በአፋቸው እናወድሳት ከሚሉት በላይ ያውቃልና:: ችግሩ እነሱም ያልመለሱት ወይም በሚገባ ያልተረዱት ኢትዮዽያ መዳረሻችን እንዴትና በማን እንደሚከወን ላይ ያለው ብዥታቸው ነው::

የአማራ ፋኖ ስልጣን ከያዘ ብሁዋላ ለሌሎች ጣልጣል(እንደወያኔ) ያድርግላቸው ነው? ወይንስ አዲስ አበባ ጫፍ ላይ አድርሶ የመዋጋት ተልዕኮውን ጨርሷልና ወደየመጣበት ይመለስ ይሆን? ኢትዮዽያ የዳር እስከዳር የኢትዮዽይውያን የሁሉም መዳረሻ ናትና አማራም እራሱን ይከላከል ሌላውም ኢትዮዽያዊ መሃል መንገድ ድረስ መጥቶ ከአማራ ጋር ሃገሩን በጋራ ይታደግ በጋራ ይምራ: በአማራ ትክሻ ላይ ተቆናጦ ኢትዮዽያ መዳረሻችን

የሚለው ጉንጫ አልፋ ክርክር ለስልጣን ጥመኞች መሰላል ለመሆን ካልሆነ የሚያመጣው ፍሬ አይኖርም: የዚህ ትርጉም የሌለው አባባል አቀንቃኞች ከፋኖ የተሻለ ኢትዮዽያዊ ግንዛቤም ሆነ ፍቅር ስላላቸው አይደለም: አንድም ከወጡበት ማማ ወረድ ብለው የመሬቱን ግለትና የሰዎቻችንን መስዋዕትነት ሊረዱት አልቻሉም ወይም አልፈለጉም: አለመቻልን ሃቀኛ ጥረት ከተደረገ ትምህርት ይገረዋል ከመሬትካለው እውነታ ጋር ያገናኛልና ጊዜ መስጠቱ ክፋት የለውም:። አለመፈለግ ግን አውቆ ማደናገርን ወይንም ተልዕኮን የሚያመላክት ነውና በቀላሉ የሚታለፍ አይሆነም: ከላይ እንደተጠቀሰው በአገልጋይነት የተሰለፋ ቀደም ሲል በወያኔ ዛሬም በኦሮሙማው የሚነዱ ተከፋይ አገልጋዮች ብዙዎች ናቸው::በኢትዮዽያዊነት ሙሉ እምነትን ይዘው የአማራ ብሄርተኝነትን ተጠይፈው በመሃል ለቀሩት ግን ከፋኖ የበለጠ ኢትዮዽያዊ ፍቅር ሊኖራችሁ የሚችለው በምን ሂሳብ ነው? ተብለው

ሊጠየቁ ይገባል።

የነዚህ አይነት ስብስብ ነው ዛሬ የአማራ ምድራችን በአብይ ቦምቦች በሚቃጠሉበት ወቅት በኩራት ስለኢትዮዽያ ሲጨቃጨቁ የሚውሉት በሰላሳና አርባ ድርጅቶች ተጠርንፈው አንድ ሃገር ለማዳን ስምምነት እንኳ የሌላቸው አማራዎችም ቢሆን ድርጅት ከመፈልፈል ያስቆማቸው የአማራ ደምና አጥንት  የለም::

 

ማጠቃለያ

አማራን ለአማራ ፋኖና አቅፎ ደግፎ እዚህ ላደረስው የአማራ ህብረተሰብ እንተወው:: የጋራ ሃገርችንን በጋራ ለማዳን ሁሉም ኢትዮዽያዊ እንዲሰለፍ የግድ ስለሚል በአማራ ላይ ብቻ ሃላፊነቱን መጣል ሃላፊነት የጎደለው ነውና  እንደገና ይታሰብበት: ሌሎች እትዮጵያውያን እጃችውን ያሳዩ።

ዛሬ በአማራ ላይ ያለውን ህመም ህመሜ ነው ብለው ካልተጋሩት ነገ  ብቻቸውን ይመታሉ። ኦሮሙማ ለነሱ ብቻ ሳይሆን ቆምኩለት የሚለውን የኦሮሞ ህዝብ አይምርም።  ኦሮሙሙ መስላል እንጂ ለኦሮሞ ደህንነት የቆሞ አይዲኦሎጂ አይደለም። ዛሬ እየፈሰሰ ያለው የአማራ ደም ነው።፣  ነገ ግን የሁሉም ነውና ሁሉም በያለበት የተቻለውን ድንጋይ በአብይ ላይ ይወርውር። አብይንና በዙሪያው የተኮለኮሉትን ድኩማን አባሮ የጋራ ሃገረ መንግስት ማቆም የሁላችንም ድርሻ ነው። አብይ ዘርም ሆነ እምነት የለውም ፣ እምነቱም ዘሩም ስልጣን ነው። ይህን የታመመ ሰው  በህብረት ተነስቶና ተረባርቦ ወደማይቀርበት የታሪክ አተላነቱ መመለስ የሁሉም የዚህ ትውልድ ሃላፊልነት ነው።

ስለዚህ ፋኖን ከመጠበቅ ይልቅ እራስን ለማዳን ወደ ፋኖ መጠጋት አትራፊ ነው። ከዚህ በተረፈ ልጅ ምጥ ለእናቷ አስተማረች እንዳይሆን ኢትዮዽያዊነትን ለአማራ ለመስበክ የሚደረገው ጩኸት ሰሚ የለውምና ይስተካከል:።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop