October 19, 2024
8 mins read

የኦሮሞ ሽማግሌውች የጭካኔ ፍርድ: በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን በአደባባይ በገበያ እንጨት ላይ ታስራ መገረፏ ብዙዎችን አስቆጥቷል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን ወጫሌ ወረዳ አንዲት ሴት በአደባባይ የቆመ ግንድ ላይ ተጠፍራ በመታሰር ስትደበደብ በማህበራዊ ሚዲያ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡
በባለቤቷ በአደባባይ ታስራ ስትደበደብ የሚያሳየው ይህ ድርጊት ስሜትን እጅግ የሚረብሽ ሲሉ ብዙዎች እያወገዙት ይገኛል።

69869554 1004

የአከባቢው ሽማግሌዎች ጉዳያችሁን በቤታችሁ እናይላችኋለን ተመልሰሽ ግቢ አሏት፡፡ እሷ ግን ለህይወቴ እሰጋለሁ በደንብ ታይቶ ችግሬ ካልተፈታልኝ አልገባም በማለቷ ሽማግሌዎቹ በእንጨት ላይ ታስራ እንድትገረፍ ፈረዱባት” የተጎጂ ቤተሰብ

ተበዳይዋን ለአደባባይ አሰቃቂ ድብደባ ያበቃት ውሳኔ

ምስራቅ ቦረና ዞን ወጫሌ ወረዳ ቀቀሎ ቀበሌ ውስጥ ኩሹ ቦነያ ጉዮ የተባለች ሴት በአደባባይ በገበያ  እንጨት ላይ ታስራ ክፉኛ ስትገረፍ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በስፋት ከመጋራቱም አልፎ የበርካቶችን ስሜት እጅግ የሚረብሽ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ተከሰተ የተባለው ይህ ድርጊት ሚስት ከባለቤቷ ጋር በነበራት አለመግባባት የተነሳ ለመታረቅ ዝግጁ አይደለችም ተብላ በአከባቢው ሽማግሌዎች ታስራ እንድትገረፍ ተወሰነባት። እናም በአደባባይ ተገረፈች። ይህ አሰቃቂ ድርጊት ብዙዎችን አስቆጥቷል።

የተጎጂዋ ወንድም ጃርሶ ቡሌ የሶስት ልጆች እናት የሆነችው እህታቸው እንዲህ በሚያሳቅቅ መልኩ በአደባባይ ታስራ የተደበደበችው በባለቤቷ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አክለውም “እሱ ውትድርና ሄዶ ስለነበር ለአራት ዓመታት ገደማ ልጆቿን ብቻዋን ለማሳደግ ላይ ታች ስትል ነበር፡፡ እሱ ከውትድርናው ከተመለሰ በኋላም ስለቤተሰብ ማስተዳደር አሳስቦት አያውቅም፡፡ ሰርቶ ያገኘውን ጫት ይቅምበታል ጠላ ይጠጣበታል በቃ፡፡ ከዚያን ሌሊት እየገባ ይደበድባታል ተመክሮም ማንንም ልሰማ አልቻለም፡፡ በዚህ በመሰላቸቷ ከቤቷ ትወጣለች፡፡ የአከባቢው ሽማግሌዎች ጉዳያችሁን በቤታችሁ እናይላችኋለን ተመልሰሽ ግቢ አሏት፡፡ እሷ ግን ለህይወቴ እሰጋለሁ በደንብ ታይቶ ችግሬ ካልተፈታልኝ አልገባም በማለቷ ሽማግሌዎቹ በእንጨት ላይ ታስራ እንድትገረፍ ፈረዱባት” ብለዋል፡፡

ተበዳይዋን ፍትህ ለማሰጠት የተጀመረው የህግ ሂደት
የተበዳይ ወንድም አቶ ጃርሶ እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የሽማግሌዎች ውሳኔ በቦረና ያልተለመደ አይነት ክስተትም እንደነበር በአስተያየታቸው አስረድተዋል፡፡ እህታቸው በገበያ ውስጥ እንዲያ ታስራ ስትገረፍ የሚያሳይ ቪድዮ ሲሰራጭ ቁጭትና ንዴት እንደተሰማቸውም አልሸሸጉም፡፡ “ስትደበደብ ማንም እንዳያስጥላት ሲከለክሉ ነበር፡፡ ሴቶች ምነው የሰው ልጅ አይደለች ተውአት እንጂ ሲሉ ሰሚ አጥተዋል፡፡ ለማስጣል የመጣውን ሰው እንኳ ስለሚመቱ ሰው ሁሉ በፍርሃት ቆመው ሲመለከቱም ነበር፡፡ መጨረሻ ላይም እሷም ክፉኛ በመደብደቧ ለህይወቷም ፈርተን ሆስፒታል ወሰድናት፡፡ ለፖሊስና አቃቤ ህግም አሳወቅን፡፡ እነሱም ወንጀሉን መርምረው በድርጊቱ የተሳተፉትን 8 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው በዋጪሌ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ አሁን ከባለቤቷ ውጪ ሌሎቹ በፍርድ ቤት በዋስ ተለቀዋልም” ነው ያሉት፡፡

ወንጀሉ ከተፈጸመ በሳምንት በኋላ ጥቆማውን መስማቱን የሚገልጸው የወረዳው አቃቤ ህግ ቪዲዮው ከተሰራጨ በኋላ የወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ይገልጻል፡፡ አቶ ጉዮ አሬሮ የወረዳው አቃቤህግ ኃላፊ ናቸው፡፡ “አሰቃቂው ድርጊት ውስጥ ተሳተፉ የተባሉ በቁጥጥር ስር ውለው የምስክሮችም ቃል ለማሰባሰብ ጥረት ተደርጎ ነበር፡፡ እሷም እንድትታከም ሆኖ የህግ ሂደቱ እስከተቻለ ድረስ እንዲሄድ ተደርጓል፡፡ አሁንም የተበዳይዋ የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ክስ ተመስርቶ ፍትህ እንድታገኝ እየጣርን ነው” ብለዋል፡፡

የሴቶች መብት ጥሰት ክትትል

በወረዳው የሴቶች ጉዳይን ጨምሮ የባህል፤ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያቅፈው የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ሊበን ጉዮ በፊናቸው ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት በጥፋቱ የተሳተፉትን አስቀድሞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ከማድረግ ጀምሮ ጽህፈት ቤታቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “ይህቺ ሴት በጣሙን ተጎድታለች፡፡ እንዴትስ እነዚህ ሰዎች የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው ይወጣሉ ብለን ሞግተናል፡፡ አቃቤህግም ሽማግሌ የተባሉትና በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ በፍርድ ቤት በመለቀቃቸው አልረካም፡፡ አሁንም ግን የህክምና ማስረጃዋን በማቅረብ ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰጥ መክረናል” ነው ያሉት፡፡

የወረዳው አደረጃጀት ኃላፊው አቶ ሊበን እንደሚሉት መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በቦረና ባህልም ሆነ በገዳ ስርዓት ቦታ የለውም፡፡ “እንዲህ ያለ ባህል በቦረና ውስጥ የለም፡፡ በተለይም እንዲህ በአደባባይ ሰው አውጥተው ሰብዓዊ መብት ገፎ ማስደብደብ አንግዳ ነው የሆነብን፡፡ እናም በባህልም በህግም የሌለው ነገር በህግ ውሳኔ ፍትህ እንዲያገኝ ነው አቋማችን” ብለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop