አረመኔው የበሻሻ ደላላ #አብይአህመድና የብልጽግና/የብልግና ካድሬዎቹ ተደናግጠውል ፣ ተደናብረዋል። #የአዲስአበባን ህዝብ በግፍ እያፈናቀለ በ 13 ቢሊዮን ዶላር ቅንጡ ቤተ መንግስት በ 500 ሄክታር የዜጎች የእምባና የደም መሬት ላይ በመገንባት ፣ እንዲሁም በርካታ ብልጭልጭ ግንባታዎችን በመደረደር “እየበለጸግን ነው፡ ህልማችንን እየኖርን ነው” እያሉ ህዝብንም ሆነ አለም አቀፍ ማህበረስቡን ሲያደናግሩ፣ ሲያጭበረብሩ እንደነበር የሁላችንም የታዘብነው ነው። ዛሬም እንደ እንደ በፊቱ በደመ ነፍስ በለመዱበት ድሪቶ “ሪፎርም እያደረግን ነው፣ በልጽገናል” የሃስት መግለጫዎች፣ ማጭበርብሪያና ፣ ማደናገሪያ ሃቁን ለመሸፋፈን እየሞከሩ መሆኑን እየታዘብን ነው።
ከ 120 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ውስጥ 76% የሚሆኑት 86 ሚሊዮን ዜጎች በከፋ ድህነት የሲኦል ኑሮ እየገፉ መሆናቸው የተመድ የልማት ድርጅትና ኦክስፎርድ ዪንቨርሲቲ አመታዊ “የዘርፈ ብዙ ድህነት መገለጫዎች” በሚመለከት ያወጣው ይሄው አመታዊ ሪፖርት 2024 ያሳያል። የመሰረታዊ የህልውና እና የልማት ፍላጎቶች እንደ ምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፣ መብራት፣ ትምህርትና የጤና እገልግሎቶች እንደማያገኙ የተመድ ልማድ ድርጅትና የኦክስፎርድ ሪፓርት ያመላክታል።ሪፓርቱን ብዙ ኢትዮጵያውና ዜጎች፣ ተመራማሪዎች ፣አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ ቲንክ ታንኮች የሚያገኙትና የሚመለከቱት ነው። የአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከወለል በታች በነጭ ድህነት በመመማቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ሌሎች ልዩ ልዩ አለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም አለም አቀፍ የመገናኛ አውታሮች ኢትዮጵያ የምትገኝበትን፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚገኝበትን (86 ሚሊዮን/120) ሚሊዮን የተዘፈቀበትን ከድህነት ወለል በታች/ነጭ ድህነት፡ በረሃብ፣ በእርዛት፣ መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶች እንዲሟሉ ማድረግ ያልቻለ አገዛዝ መሆኑኑ በየግዚው ዘግበዋል። የአብይ አህመድ ፋሽታዊ አገዛዝ በህዝብ ላይ የሚያካሂዳቸው የመንግስታዊ ሽብር ተግባራት፣ ማንነት ላይ ያነጣጠረ የጅምላ እስሮች ፣ ግድያዎች፣ በአማራና በኦሮሞ ክልሎች የሚያደርጋቸው ጦርነቶች ሳቢያ የሚጠፋው የሰው ህይወት፣ የሚወድመው የህዝብ ሃብቶችና ንብረቶች በሚመለክትም ዘግበዋል፣ አጋልጠዋል። በመላ አገሪቱ የዜጎች መብቶችና ነጻነቶችና መብቶች ገፈፋና ረገጣ እየተስፋፋ መሆኑን በሰፉው ዘግበዋል። አነዚህ ተአማኒ፣ ታዋቂና፣ ቅቡል የአለም ተቋማት በመረጃና በጥናት በተከታታይ ይፋ ያደረጉትን ሀቆችና አውነታዎች እጅግ አስክፊ፣ አሳፋሪ ገጽታዎች በለመዱት ሃስቶችና ማደናገሪያዎች ሊሸፋፍኑ ቢሞክሩም ቅሉ አይሳካላቸውም።
1ኛ ኢትዮጵያ ከ 120 ሚሊዮን ህዝብ 86 ሚሊዮን ከድህነት ወለል በተች ዜጎቿ የሚኖሩባት። ከአለም የመጨረሻው ተርታ የድሃ ድሃ ሀገሮች መካከል (የተመድ የልማት ድርጅት ሪፓርትና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ 2024 ሪፓርት – hdr.undp.org/content/2024-g…)
2ኛ፣ በሺዎች ዜጎች በድሮን፣ በታንክና በመድፍ እየተጨፈጨፉ ህይወታቸው የሚበለጽግባት (አልጃዚራ፣ ቢቢሲ ወዘተ፡
3ኛ። ከአለም ሀገራት የፕሬስ መብቶች ነጻነት ከመጨረሻዎቹ እንዷ (ፍሬደም ሃውስ Freedom House: freedomhouse.org/country/ethiop…)
4ኛ። የህግ የበላይነት ፣ ህገ መንግስታዊነት፣ ፍትህ ደብዛው የጠፋበት፣ ዜጎች በሺዎች ፣ በመቶ ሺዎች በ”ልማት” ሰበብ የሚፈናቀሉበት፣ ሰብአዊ መብቶች፣ የዜግነት ነጻነቶች በአብይ አህመድ ኮሬ ነጌኛ፣ ፌደራል ፓሊስ፣ ደህንነት ሃይሎች ፡ያለህግ አግባብ የሚገደሉባት ፣ በአዋሽ አርባ፣ በፌደራል ፓሊስ ሜክሲኮና ፣ በልዪ ልዩ ማጎሪያ ቦታዎች ሰቆቃ የሚፈጸምባት (የቢቢሲ ልዩ የምርመራ ዘገባዎች፣ በርካታ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች (አልጃዚራ፣ ቢቢሲ ወዘተ፡
ሃቆቹ በጥቂቱ እነዚህ ናቸው። አረመኔው የበሻሻ ደላላውና ካዲሬዎቹ ምን ቢፍጨረጸሩ መፋቅ ፣ መሸፈን ያማይቹሉት መራራ ሀቅና አስከፊ እውነታዎች።