September 26, 2024
36 mins read

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

Esemecu©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.

ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቤት ለቤት በመፈተሽ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ፤ ቤት ታከራያላችሁ” እንዲሁም “የፋኖ አባላት ናችሁ” ብለው የጠረጠሯቸውን 10 ሲቪል ሰዎች በጥይት መግደላቸው ታውቋል።

©ከአማራ ክልል፣ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወንጀላ ቀበሌ ሰኔ 5 ለሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ሌሊት ላይ በመንግሥት ጸጥታ አካላት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የ“ፋኖ”ታጣቂዎች ቀበሌውን ለቀው ከወጡ እና ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቀበሌዋ በመግባት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ቤት ለቤት እየዞሩ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ” በማለት 5 ሰዎችን ከቤታቸው አስወጥተው የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከልም 1 የ75 ዓመት አረጋዊ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

©ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሞጣ ከተማ ወደ ቀራንዮ ከተማ መኪና አጅበው በመጓዝ ላይ እያሉ መንገድ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የደረሰባቸውን የደፈጣ ጥቃት ተከትሎ የሰራዊቱ አባላት ወደ ቀራኒዮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመግባት የዕድራቸው አባል የሆኑ መነኩሴ ሞተው የቀብር ቦታ በመቆፈር ላይ የነበሩ 6 የከተማው ነዋሪዎችን እንዲሁም 1 የአብነት ተማሪን የገደሉ መሆኑን የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል።

©ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ተነስተው ወደ ሰሜን ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ቀበሌ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያሉ መከኒ ዋርካ ቀበሌ አልቃ በተባለ ቦታ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በበቀል ስሜት በጉዟቸው ላይ ያገኟቸውን 10 አርሶ አደሮችን በጥይት የገደሉ፣ሌሎች 2 አርሶ አደሮችን ደግሞ ያቆሰሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ 12፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ አስተዳደር፣ “ጎህ” በተባለ ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 16 ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት አስተዳደር አካላት ገልጸዋል። አንድ የመንግሥት ኃላፊ የግድያውን መነሻ ምክንያት ሲያስረዱ “በዕለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ውጭ ቆይተው ሲመለሱ በተተኮሰባቸው ጥይት 2 አባላት መቁሰላቸውን እና 1 ወታደር ተደብድቦ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ‘ፋኖ ያለበትን አሳዩን’፤ ‘መረጃ ስጡን’፤ ‘ምን እንደተፈጠረ ተናገሩ’ በሚል በሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎች እና ተኩሱን ሰምተው በመሮጥ ላይ የነበሩ ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል” በማለት ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል 2 አእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም በሬስቶራንቱ ሲስተናገዱ የነበሩ የአቢሲኒያ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ይገኙበታል።

@በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ ላይ በተካሄደ የትጥቅ ግጭት አባትና ልጅን ጨምሮ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከ3 ወር በፊት ተይዘው ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ 3 የ“ፋኖ” አባላት በጸጥታ ኃይሉ ተገድለው አስከሬናቸው ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጥሎ መገኘቱን ኢሰመኮ ለማወቅ ችሏል።

በተመሳሳይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በበቀል ስሜት በቁጥጥር ሥር አውለዋቸው የነበሩትን የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደገደሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ጣርማ በር ወረዳ፣ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች ቦታ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን ለመክበብ ሲሄዱ ታጣቂዎቹ ቀድመው ይወጣሉ። ይህንን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በመንገድ ያገኟቸውን፣ ቤታቸው በር ላይ ቆመው የነበሩ እና ሻይ ቤቶች አካባቢ የተገኙ በድምሩ 15 ሲቪል ሰዎችን “ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ ፋኖን ትደብቃላችሁ” በሚልና በመሰል ምክንያቶች ግድያ እንደፈጸሙባቸው የሟች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

©ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ውርጌሳ ከተማ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል የተተኮሰ ከባድ መሣሪያ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቆ በ4 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና በሌላ 2 የቤተሰብ አባላት ላይ በድምሩ 6 ሰዎች ላይ 1 የሞት እና 5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ 4ቱ ሕፃናት ሲሆኑ ቀሪ 2ቱ ደግሞ የሕፃናቱ ወላጆች ናቸው።

በአማራ ክልል፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ አሊ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ መስጊድ ቆይተው ወደቤታቸው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

©ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አቶ ይመር መስፍን የተባሉትን ሰው “ፋኖ ነህ፤ ልጆችህም ፋኖ ናቸው” በማለት ከአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት አባይ ቀበሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው በባዶ እግራቸው ወደ አምቦ መስክ ቀበሌ ከወሰዷቸው በኋላ ገድለው አስከሬናቸውን ጥለውት የሄዱ መሆኑን፣ አስከሬኑም ሲታይ አካላቸው የተለያየ ቦታ ተወግቶና ተበሳስቶ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ መሆኑን እንደሚያሳይ ምስክሮች ገልጸዋል።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ውድመን ቀበሌ ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል በትጥቅ የታገዘ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ከባድ መሣሪያ ቢያንስ 7 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።+

በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ ዶማ በተባለ አካባቢ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ∙ም. 1 የ“ፋኖ” ታጣቂ አባል ቆስሎ 2 ወንድሞቹ ሊያነሱት ሲሄዱ 3ቱም ወንድማማቾች በመንግሥት የጸጥታ አባላት መገደላቸውን ኢሰመኮ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል።

©ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ገነት አቦ ከተማ ሲካሄድ የዋለው ውጊያ ከቆመ በኋላ የመንግሥት ጸጥታ አባላት ቤት ለቤት ፍተሻ እያካሄዱ በነበሩበት ወቅት አቶ ካሳ ምትኩ የተባሉ መስማት የተሳናቸውና የሚጥል በሽታ ተጠቂ የነበሩ ግለሰብን ከቤታቸው በር ላይ ከሕግ ውጭ ግድያ የፈጸሙባቸው መሆኑን ኢሰመኮ ለማረጋገጥ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 2 ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በር እንዲከፍቱ ጠይቀዋቸው በፍርሀት ባለመክፈታቸው በመስኮት በኩል ጥይት ተኩሰው የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ስለመሆኑ ኢሰመኮ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳት ችሏል።
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት ዓባይ ቀበሌና በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከነሐሴ 6 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተካሄደ ውጊያ ጋር በተያያዘ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በመንገድና ቤታቸው ውስጥ ያገኟቸውን በግጭቱ ተሳትፎ ያልነበራቸውን 7 ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾች ውስጥ 1 በአካባቢው የማኅበረ ሥነ ልቦና ጉዳት እንዳለበት የሚታወቅ ሰው እና 1 የ17 ዓመት ልጅ ይገኙበታል። በተጨማሪ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት አካባቢ ቄስ አወቀ መኮንን የተባሉ አረጋዊ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለማከናወን ወደ አቡነ ዘርዓብሩክ ቤተክርስቲያን በመጓዝ ላይ እያሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጥይት እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
©ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን፣ እስቴ እና አንዳ ቤት ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ለስብሰባ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ በጉዞ ላይ እንዳሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ባደረሱት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለመረዳት ተችሏል።

©ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረወርቅ ከተማ አካባቢ በመንግሥት ወታደሮች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ አቶ ዘውዴ ጫኔ እና አቶ እንቻለው መኮንን የተባሉ አርሶ አደሮች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ እራሳቸውን ለማዳን ሲሸሹ የመንግሥት የጸጥታ አባላት መንገድ ላይ ከያዟቸው በኋላ የ“ፋኖ ደጋፊ ናችሁ” በሚል በጥይት የገደሏቸው መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ የመንግሥት የጸጥታ አባላት የሟቾችን የእጅ ስልክ በመውሰድና ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ጸያፍ ስድቦችን እንደሰደቧቸው እንዲሁም “እናጠፋችኋለን” ብለው እንደዛቱባቸው ምስክሮች ገልጸዋል።
በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ አባይ ማዶ ዘንዘልማ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማእከል አካባቢ ሰሳ በረት በሚባል ቦታ 4 ወጣቶች እና አሽራፍ በሚባል አካባቢ 2 ወጣቶች በድምሩ 6 ወጣቶች ለጊዜው ባልታወቁ አካላት እጃቸውን የኋሊት ታስረው በጥይት እና በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ተገኝተዋል።
ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ ከ1፡00 እስከ 1፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ቀበሌ 5 በግ ተራ አካባቢ “ሜላት ካፌ” በመባል ከሚጠራው ስፍራ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ) በከፈቱት እሩምታ ተኩስ በጎዳና አነስተኛ ሥራ እና በልመና ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሲቪል ሰዎች ላይ 2 የሞት እና 10 የአካል ጉዳት እንደደረሰ ለማረጋገጥ ተችሏል። ሟቾች 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና ድንች ቅቅል ጎዳና ላይ በመሸጥ የምትተዳደር 1 ሴት ሲሆኑ ከቆሰሉት መካከል ደግሞ 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና 1 የሟቿ ሴት ሕፃን ልጅ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

©ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጠዋት በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የነበረውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ራያ ቆቦ ከተማ ዙሪያ የቆቦ ከተማ እና የዋጃ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 4 ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች ተገድለው የተገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

 

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ፣ ይነሳ እና ይባብ ቀበሌ የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት እና ሚሊሻ) በአካባቢው ምንም ግጭት ሳይኖር በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ለምሳሌ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወ/ሮ መብራቴ መኳንንት (61 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 10 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳደሪ) እና ወ/ሮ ነጻነት ምትኩ (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ከቤተክርስቲያን ተመልሰው መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ በጥይት የገደሏቸው ሲሆን፣ የሟች ልጅ የሆኑትን ወ/ሮ ውብእህል ተባባል (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ደግሞ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ የቀኝ እጃቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል። ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ጭንጫር ጎጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ስሜ የተባሉትን የ74 ዓመት አርሶ አደር በመኖሪያ ቤታቸው ቡና በመጠጣት ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤታቸው በኃይል በመግባት ግለሰቡና ቤተሰቦቻቸው ላይ ድብደባ ከፈጸሙ በኋላ፣ ግለሰቡን በመኪና ጭነው ወደ ካምፓቸው ወስደው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ መልሰው ወደ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በማምጣት ከመኪና ላይ ገፍትረው አስፓልት መንገድ ላይ በመጣል በ3 ጥይቶች ተኩሰው ገድለዋቸዋል። ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አቶ ታደለ እውነቴ (42 ዓመት፣ አርሶ አደርና 4 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የበቆሎ ማሳ ለማሳረም የቀን ሠራተኞችን መንገድ ዳር ቆመው በመጠባበቅ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ጭንቅላታቸውን በ2 ጥይቶች መተው ገድለዋቸዋል።

ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይነሳ ቀበሌ ድንጅማ በተባለ አካባቢ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ አቶ ላቀ ቢተው (46 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) ከብቶቻቸውን ወደ ቤታቸው እየነዱ በመሄድ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት 2 እግራቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት ሕክምናቸውን በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር። ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም.

ይነሳ ቀበሌ አማስሬ በተባለ አካባቢ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ሞት ባይኖር (የ70 ዓመት አረጋዊና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የጫት ማሳቸውን በማረም ላይ እያሉ በአድማ ብተና ፖሊስ 2 እግራቸውን በጥይት ተመተው ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር።

©በአማራ ክልል፣ ማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ አለፋ ወረዳ፣ ሻውራ ከተማ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገው ከባድ ውጊያ ከ10 በላይ ሲቪል ሰዎች ከየትኛው ወገን እንደተተኮሰ ባልታወቀ ተባራሪ ጥይት እንዲሁም ግጭቱ ከቆመና ታጣቂዎች ለቀው ከወጡ በኋላ “ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ”፣ “መረጃ ትሰጣላችሁ” በሚል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመሄድና መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች አስረድተዋል።

 

©ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ማራኪ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 16 ልደታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም ወደ ተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በኃይል በመግባት በአምላክ አብርሃም ከተባለች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ልጃቸው ጋር በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል። በእናትና ልጅ ላይ የተፈጸመው ግድያ ምን አልባት ጥቃት ፈጻሚዎቹ “የእገታ ሙከራ” ሲያደርጉ ተጎጂዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ራሳቸውን በመከላከላቸው ምክንያት በአጋቾቹ በተወሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

©ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ቀበሌ 03 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሕፃን ኖላዊት ዘገየ የተባለች የ2 ዓመት ታዳጊ በወላጆቿ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በመጫወት ላይ እያለች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገተች መሆኑን፤ የሕፃኗ ወላጅ አባትም ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ስልክ ተደውሎ ለሕፃኗ ማስለቀቂያ 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ይሁን እንጂ የሕፃኗ ወላጅ አባት በሹፍርና ሙያ ተቀጥረው የሚሠሩ በመሆኑ የተጠየቀውን ገንዝብ ለመክፈል እንደማይችሉ በመግለጽ ከአጋቾች ጋር በስልክ በመደራደር 300,000 ብር ለመክፈል ይስማማሉ። ሆኖም የሕፃኗ ቤተሰቦች ከተለያዩ ሰዎችና ዘመዶቻቸው በመለመን የተጠየቀውን ገንዘብ አሰባስበው ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሸዋ ዳቦ ከተባለ አካባቢ በመሄድ በባጃጅ ገንዘቡን ለአጋቾች በመላክ ልጃቸውን እንዲሰጧቸው ሲጠይቁ “መኖሪያ ቤታችሁ ታገኟታላችሁ” የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ሕፃኗ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተጥላ ተገኝታለች። ይህንን ተከትሎ የከተማው ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ማእከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ድርጊቱን በማውገዝ በጎንደር ከተማ እየተፈፀመ ያለው እገታ እንዲቆም ድምጻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አሰምተዋል። የመንግሥት ጸጥታ አካላት ሰልፈኞቹን ለመበተን በተኮሱት ጥይት ቢያንስ 3 ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከ11 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕፃን ኖላዊት ዘገየ እንዲሁም ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ደግሞ ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም እና ልጃቸው በአምላክ አብርሃም ላይ የግድያ ወንጀል በአጋቾች የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጧል። መንግሥት በእገታ፣ በግድያና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን የሕፃን ኖላዊት ዘገየን ሞት ተከትሎ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በማጣራት እና እርምጃ በመውሰድ ውጤቱን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ምክር ቤቱ ገልጿል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የሥነ-ምግባር ብልሽት ያለባቸው፣ ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ የእገታው አባሪና ተባባሪ በመሆን የተጠረጠሩ 14 የጸጥታ አካላት ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ገልጿል።\

©ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ አዘዞ ጸዳ ክፍለ ከተማ፣ ጸዳ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 የመንግሥት የጸጥታ አባል ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጸዳ ካምፓስ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለገበያ ወደ ተሰበሰቡ ሰዎች ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን እንዲሁም አስፓልት መንገድ ላይ ያገኟቸውን 8 ወጣቶች በአጠቃላይ ቢያንስ 11 ሲቪል ሰዎችን የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጣቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ከተካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች ቢያንስ 20 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች እና የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው እየተወሰዱ በመንግሥት የጸጥታ አካላት እንደተገደሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከገጠር ወደ ደባርቅ ከተማ መጥተው አልጋ ይዘው የነበሩ 5 መምህራን ይገኙበታል። በተጨማሪ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች 36 ሲቪል ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተው የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1 የ3 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 2 ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ተችሏል።

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. እና የቀወት ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በመኖሪያ ቤታቸው ተገድለዋል።

©በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በቋራ ወረዳ ከግንቦት ወር መጀመሪያ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ እና የአገው ብሔረሰብ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ማለትም ይካዎ፣ አብተጋሆ፣ አጋም ውሃ፣ ገለሎ፣ ባምባ ውሃ እና ሌሎች ቀበሌዎች ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የመንግሥት የሚሊሻ አባላት ትጥቃቸውን እንዲያስረክቧቸው ጥያቄ በማቅረባቸው እና የሚሊሻ አባላቱ የመንግሥትን ትጥቅ እንደማያስረክቡ በመናገራቸው ግጭቶች መነሳት መጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የግጭቱ መነሻ እና መባባስን በተመለከተ የአካባቢው ሰዎች እንደሚያስረዱት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም.

የሚሊሻ አባላት ትጥቅ ለማስፈታት የመጡ ከ12 በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን በቁጥጥር ሥር አውለው ለመንግሥት ያስረክባሉ። በዚህ የተበሳጩ የታጠቀ ቡድኑ አባላት በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ፣ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በሚሊሻ አባላት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን አባላት መካከል ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ማኅበረሰብ ግጭት ተሸጋግሮ ባይካዎ እና አጋም ውሃ ቀበሌዎች ከሁለቱም ብሔር ተወላጆች ብዛታቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከሟቾች መካከልም ግጭቱን ማምለጥ ያልቻሉ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት የሚገኙበት መሆኑን እና በዚሁ ግጭት ቤቶች እና የሰብል ማሳ መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸል

ድል ለፋኖ..!!!
ድል ለአማራ ፋኖ

ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ሀሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
Twitter: twitter.comNISIRInternati1
https://buff.ly/3R2omte
Telegram: http://buff.ly/3Tcx06A
TikTok:- http://buff.ly/4csTyKP…
Website: http://buff.ly/3DETCqV
WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084

Leave a Reply

Your email address will not be published.

birhanu m000
Previous Story

 የአብይ አስተዳደርና የዶ/ር ብርሃኑ አኒ-ሚኒ-ማኒሞ

193751
Next Story

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፡ አያ ውበትም ጨቋኝ ተባለ?

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop