የጠ/ሚ አብይን የ2017 ዓ.ም. እንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አነበብኩት፡፡ዘመኑ ላይ ተፈላሰፉበት ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ዘመን እድል ነው አሉን፡፡ እድል ማለት እንደ አማርኛው መዝገበ ቃላት ትርጉም ከሆነ እጣ ክፍል፣ ግንባር ወይም ድርሻ ማለት ነው፡፡
ለመሳሌ በአንድ አካባቢ ያለ አንድ ጋሻ የገበሬ መሬት ተሸንሽኖ ለአስር ገበሬዎች በእጣ ይታደላል እንበል፤ ለወንዙ የቀረበ መሬት አለ፡፡ ሜዳማ መሬት አለ፡፡ እንዲሁ ተዳፋት የሆነና ገደልስር ያለም ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ውሃ ገቡን ወይንም ሜዳማውን እድለኞች የሆኑ ያገኙታል፣ ይታደሉታል፡፡ እድለ ቢሱ ደግሞ ገደላማው ሸጥ ስር ይደርሰዋል፡፡
እንግዲህ አንዱ ምርቱን በቀላሉ ሲሰበስብ መጥፎ መሬት የደረሳቸው ደግሞ በብዙ ትጋትና ትግል እህላቸውን ያመርታሉ፤ ሰብላቸውን ይሰበስባሉ ማለት ነው፡፡ ቀጠል አድርገው፣ ዘመንን(እድል የሆነውን ማለት ነው) እግዚአብሔር ለሁሉም በእኩልነት ይሰጣል ይላሉ ጠ/ሚሩ፡፡ ይህን ብለውም አያበቁም፤በአግባቡ ላልሰራበት ዘመን መዓት ነው፤ በአግባቡ ለሰራበት ደግሞ ዘመን ምህረት ነው ይላሉ፡፡
በአውሎና በወጀብ ውስጥ ሆነን አስገራሚ ስራዎችን እንድንሰራ የፈቀደ እግዚአብሄር ዛሬም፣ ነገም ከእኛ ጋር ነው ይሉና መስራት የእኛ ማከናወን ደግሞ የእሱ ነው ሲሉ ነገራቸውን ይቋጫሉ፡፡ እዚህ ላይ ውስጠዘው የእሳቸው ተቀዋሚዎች ሁሉ ወጀብ ፈጣሪ፣አውሎ ንፋሶች የእግዚአብሔርን አላማና እቅድ የሚገዳደሩ የሴይጣን ልጆች ናቸው ማለት ነው፡፡
ሐይማኖት ላለው ሁሉ እንዲህ ያሉ ቃላት ተደጋግመው ሲነገሩት ቀስ ብሎ የሚሰርጽበት (Subliminal message) ተቀዋሚዎቼ አጋንንት ናቸው የሚል መልእክት ነው፡፡ ዘመን የሰራባቸው የሚሏቸው በሰነፍ ገበሬ የተመሰሉት መዓት የመጣባቸው ብለው የሚጠቅሷቸው ለስድሰት አመታት ያህል እየዞሩ የገደሏቸው አማራዎች፣ትግሬዎች፣ጉራጌዎች፣ጌድሆዎች፣ጋሞዎች፣ ኦሮሞዎች…ናቸው፡፡ ፈጣሪ (የሳቸው?) ካለላቸው ደግሞ ኤርትራንም ሄደው ይጨምራሉ፡፡
እስኪ አብይ ከወያኔ ምን አይነት ዘመንና ግዜ ነበር የተረከቡት? አፈናና አስራት የነበረበት ቢሆንም የወያኔ ግዜ ዘረፋ በመንግስት በግልጥ እንዲህ የታወጀበት ግዜ አልነበረም፡፡ ዜጎችም ከሞላ ጎደል ወጥተው ገብተው መስራት ይችሉ ነበር፡፡ ግድያውም እንዲህ የትየለሌ አልደረሰም፡፡ እሳቸው ወደ ስልጣን ሲመጡም ህዝቡ፤ ትግሬው፣ ኤርትራውና ሃገር ውስጥ ያለው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ነበር የተቀበላቸው፡፡
ውለው አድረው እነ ጀነራል ከማል ገልቹ እንደነገሩን አነ አብይ የመንግስት መዋቅርን ተጠቅመው ሸኔን አስታጠቁ፡፡ ህዝቡንም እንደ መንግስትና አማጺ ሆነው አሸበሩት፤ ገደሉት፡፡ ይህ በመላው ኦሮሚያና አዲስ አበባ ተፈጻሚ ሆኗል፤ እየሆነም ነው፡፡ አማራው ደግሞ የእዚህ ጥቃት አይነተኛ ሰለባ ነው፡፡ ሸኔ የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ሲያግትና ሲሰውር፣ ጠ/ሚ ወጥተው፣ ተማሪዎቹ ለመታገታቸው ማስረጃ እንደሌላቸው ነው የነገሩን፡፡
ፈተው የለቀቋቸውን አራዊቶች እነ አብይ አሁን መቆጣጠር አቅቷቸዋል፡፡ አሁን አሁን ብልጽግና ለራሱ ደንታ ሲል አስር ግዜ ሲቋጥር ሲፈታ የነበረው የፖለቲካው ቋጠሮ ውል ለእራሱ ጠፍቶበታል፡፡ ከእዚህ በኋላ ከብልጽግና ምንም የሰላም ነገር አይጠበቅም፡፡ ለዚህ ማሳያው ጠ/ሚሩ ሱማሌ ውስጥ የፈጠሩትን የፖለቲካ ውጥንቅጥ መመልከት በቂ ነው፡፡ ገና ብዙ-ብዙ ግንባር ይፈጥሩልናል፡፡
ዶ/ር ብረሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስደው በ2017 ዓ.ም. ወደ ዩነቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጥ፣ እንዲህ አለ፡፡ ለፈተና ከተቀመጡት 845000 ተማሪዎቸውስጥ 422500 ያክሉ 26 ከ 100 በታች ነው ያገኙት፡፡ ይህ ደግሞ አብዛኛው ተማሪ እንደው ዝም ብሎ ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ብሎ ፈተናውን ቢሞላ ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው፡፡
ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ላይ ሲወጡ 6ኛ ክፍል የነበሩት ተማሪዎች እኮ ናቸው አሁን የ12ኛ ክፍል ውጤታቸው እንዲህ የሆነው፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ የት/ሚ ሚኒሰተር ሆኖ ይኸው አራት አመት እየሞላው ነው፡፡ ይህን ያህል የትምህርቱ ጥራት ሲወድቅ ምን ይሰራ ነበር?
እንግዲህ ይህች ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ያላት ቃል ወክላ የገባችበት የአማርኛ ቃል “ነሲብ” የሚለውን ነው፡፡ ነሲብ ማለትን የአማርኛው መዝገበ ቃላት ሲተረጉመው እንዲህ ይላል፤ ያልተለካ፣ያለተመዘነ የግምት አስተያት፡፡ ከራሴ ተሞክሮ አንዳንድ ተማሪዎች የጥያቄዎቹ መልስ ምርጫዎች A,B,C,D አራት በመሆናቸው፣ ቅንድባቸውን እየነጩ ይመልሱ ነበር፡፡ አንድ ፀጉር ከተገኘ=A፣ ሁለት ፀጉር ከተገኘ=B፣ ሶስት=C፣ አራት=D ይህ ነው እንግዲህ የነሲብ መልስ የሚባለው፡፡
እንዲህ አይነቱ ምርጫን በነሲብ መመለስ በሳቸው ግዜ ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ተብሎ ይጠራ እንደነበር አላውቅም፡፡ የቃሉ መነሻ ግን ኦሮምኛ ይመስለኛል፡፡ ይኸውም “አነ ናማ ናማ አኒሞ” ትርጉሙም እኔ የሰው ልጅ ነኝ፣ እሱ ግን አየውቅም ነበር እንደማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ከዶ/ር ብርሃኑ አፍ ድንገት አምልጦ የወጣ ቃል ነው ወይስ ሁን ብሎ በለሆሳስ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት አለ? ቢያብራራው?
መቼም ያ የኢሕአፓ ፓርቲ ዘመን ትውልድ እኮ የማይሰራው ነገር አልነበረም፡፡ በኢሕአፓ ግዜ የኢለመንተሪ ተማሪ ሳለን የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነን ኢሕአፓዎቹ መምህራኖቻችን መዙሙር ያዘምሩን ነበር፡፡
ግባ ጫካ ተው ግባ ዱር
ነጻነትን ሃርነትን ለማሰከበር፡፡
የኢሕአፓ አንበሳ አቅራራ አገሳ
በዱር በገደል ብረት አነሳ…
ብሬ ጫማ ሊያስር ነው ጎምበስ ያለው? አይ ትምህርት
ብሬ ምን ብትለው ተዋርዶ አጎምብሶ በፎቶው እንዳየኸው ክብሩን ሽጦ አሜሪካኖች አይዞህ ጠሚኒስቴር ትሆናለህ ያሉትን እየጠበቀ ነው። በፎቶው ከታዩት መሀል ሽማግሌው እሱ ነው ኮሜዲያኑም እሱ ነው ቸገረው እንዳይባል ሀብታም ነው ይሉታል። ባደረሰው ጥፋት ሁሉ ጸጸት አይታይበትም ግርማ ሰይፉ ጋር ኢዜማ ነው አዚማም የተባለ ድርጅት ይዘው ይንገታገታሉ።ልብ ይስጣቸው እንደ ሆዳቸው ሁሉ።
Opposition parties will never flourish in Ethiopia. The past and current opposition parties’ leaders have always been stooges of the country’s rulers, with a thirst for power. The current misery of Ethiopians is partly a result of these enslaved politicians.
The New Year message of the Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed, for 2017 E.C. is jargoned with psychological symbolism. As it is read in this well-articulated article, PM Abiy deliberately associates every endeavor and success of his project with the presence of almighty God by his side. Rest assured, the intension behind it is to leave a subliminal message for his fans and the public at large that his opponents are hellrider demonic entities.
The PM tries to portray himself as the one and only, the know all and the one who carries Ethiopia over the lurking malevolent political sprites of the past, present and future. In depicting his religious magnanimity, picturing his aura encompassing the Abrahamic faiths; the Ethiopian Orthodox Church, the Ethiopian Protestant Church and the Ethiopian Sunni Islam is something all his medias are busy with.
In his trial to take the upper echelon in the spiritual realm, he uses the holy book’s stories parallel to his political synergy. Jesus, Moses, Ibrahim…are spiritual characters that he manifests himself and his ambitions. I personally feel sorry for all religious and public holidays, because the PM defiles their meaning with his derogatory associations.
In practical terms, he is taking the country to the abyss, although his walks are said as if he is dragging the country up to the tip of the hill against a storm and disaster. In his endeavor, people like Dr. Birhanu have no role more than wagging their tails or echoing him out. And they do this out of Machiavellian’s fear. So, coining words like “ani-mini-manimo” is the duty of these Intellectual Dwarfs to satisfy the ego of their master.
So, there is no stooging, but there is something which is even more divine.
“Mane, Tekel, Fares”