September 8, 2024
7 mins read

አማራ መታገል ያለበት ለመኖር ብቻ ሳይሆን ታሪኩ እየተገሸለጠ እንዳይጣል፣ መቀበሪያ እንዳያጣና የተቀበረውም በግኒደር እየታፈሰ መወርወሩ እንዲቆም ነው!

የለም እስቲባል ድረስ አማራ ራሱን እረስቶ ስለኖረ ዛሬ የህልውና አደጋ ብቻ ሳይሆን መቀበርያ እያጣና የተቀበረውም በግንዲር እየተዛቀ ሲጣል ይውላል፡፡ በቋንቋና በዘራቸው ተደራጅተው ቋንጃህን ስልንስብር መጣን ሲሉትም  ምሁር ተብዬው “ለኢትዮጵያ ስንል፣ እንደነሱ አናንስም፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ድስኩሮችና ሰበቦች እየደረደረ አማራ ተደራጅቶ ራሱን ስላልተከላከለ ዛሬ ላለበት የመከራ ዘመን እንደ ደረሰ ይታወቃል፡፡ ከዚህ የመከራ ዘመን አማራ ትልቅ ዘላለማዊ ትምህርት መቅሰም ሲኖርበት አንዳንዱ ከንቱ አንሁም እርስ በርሱ መናከሱንና መንዘላዘሉን ቀጥሏል፡፡

ከግማሽ ክፍለ ዘመን የከፋ የመከራ ዘመናት በኋላ እንኳ አማራ በዘሩ ምክንያት የግፍ ሰለባ መሆኑን  ተቀብሎ ታሪክ የሚጠይቀውን ኃላፊነት ተወጥቶ እንዳያልፍ ሰበብ የሚደርድር  የደነዘዘ ሆዳም አማራ ዛሬም ሞልቷል፡፡ ለምሳሌ ጭራቆች የሚሰሩትን ታሪክ የማይረሳው ወንጀል ለመሸፋፈን አንዳንድ ተአማራው አይደለንም የሚሉ “ግፍ የተሰራባቸው” ሰዎች በሕዝብ መገናኛ ብቅ ብቅ እያደረጉ ሲያስቀባጥሩ ሆዳሙ አማራ “የተፈናቀለው፣ ቤቱ ወይም መቃብሩ የፈረሰው እኮ የአማራው ብቻ አይደለም” የሚል ጅል ሰበብ ይደረድራል፡፡

ጅልና ሆዳም አማራ ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በአማራ ዘንድ የተሰራውን ግፍ አሰላስሎ፣ አሁንም የሚሰራውን ግፍ በጥሞና አጢኖ ወደ ፊት የታቀደውንም ቁማር ለመተንበይ የሰፋው ከርሱ ይጋርደዋል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር አስራት ያለ ልባም አማራ ግን እንኳን በፊት የተሰራውን ግፍ መርሳት ወደ ፊት የሚፈጠመውን ተንኮልም ጭራቆች ተማቀዳቸው በፊት አስቀድሞ ያውቃል፡፡

፩. የዘር ማጥፋት ወንጀል፡- ከወልቃይትና ራያ የጀመረው የአማራ ዘር ማጥፋት ዛሬ በመላው አገሪቱ በከፋ ሁኔታ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የዘር ማጥፋት ዘመቻው በባሩድ ብቻ ሳይሆን ወላዶችን በማምከን፣ በጅምላ እያፈሱ በእስር በማንገላታት፣ በማሰደድ፣ ለበሽታ በማጋለጥና ለድህነት በመዳረግ ተካሂዷል፤ በመፈጠም ላይም ይገኛል፡፡

፪. ታሪክን የማጥፋት ዘመቻ፡- የአማራን ታሪክ የማጥፋት ዘመቻው ፊደሉና ቋንቋው ተአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መጠቀሚያ እንዳይሆን ተመከልከል ጀምሮ ዛሬ ቅድመ አያቶቹ በቆረቆሯቸው ከተሞች ያሉ ቅርሶች በተለያዩ ስበቦች እየተፋቁ እንዲጠፉ እየተደረገ ነው፡፡ ቤተክርስትያኖቹና ሌሎችም ታሪካዊ ቅርሶቹ በቦንብና በመድፍ እየጋዩ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲፈጠም ሞኝ ሰው የሚታየው የቤት መፍረስና መፈናቀል ብቻ ነው፡፡ እየተሰራ ያለው ግን የአማራን ታሪክ ማጥፋት ነው፡፡ ታሪክ የሌለው ወይም ታሪኩ የጠፋ ሕዝብ ደሞ ስሩ የተቦደሰ ዛፍ ማለት ነው፡፡

፫. መቀበርያ ማሳጣትና የተቀበረውንም በግንዲደር እየዛቁ የመወርወር አረመኔአዊ ድርጊት፡- በልጅነታችን “የሞተን ሰው የሚያከብሩና የማይነኩ የዱር አውሬዎች አሉ” ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ ዛሬ የሞተን ሰው መቀበርያ የሚከለክሉና ሲሻቸውም ስልጣናቸውን ተጠቅመው የራሳቸውን ሰዎች በሚፈልጉት ቦታ በሰፋፊ መቃብሮች ውስጥ እየቀበሩ ሌላውን በተለይም በመሰረታት አገሩ መጤ የሚባለውን አማራ ለመቀበርያ ከአስር እስከ አስራ እምስት ሚሊዮን ብር እሚጠይቁ፤ የተቀበረውንም በልማት ስም በግኒደር እየዛቁ የሚወረውሩ ከዱር አውሬም ያነሱ ፍጡሮች እያየን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰው ዘመዱ ሲሞት ከአገሩ ይልቅ ዉጭ አገር መቅበርን እየመረጠ ነው፡፡

አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀልን፣ ታሪክን የማጥፋት ዘመቻን፣ መቀበርያ የማጣትንና እሬሳውን በግኒደር የመዛቅ ግፍ መታገል ያለበት በነቂስ ተደራጅቶና አንድ ሆኖ ነው፡፡ በእነዚህ ግፎች ዙርያ አንድ የማይሆን አማራ ከሰውነት የወጣ ከአውሬም ያነሰ ከንቱ ፍጡር ነው፡፡ አውሬ እንኳ ዘሩን የሚያጠፋ ኃይል ሲመጣ ሰበቡን እየደረደረ ሆዱን ሞልቶ ይተኛል ወይም እርስ በእርሱ ይናከሳል ማለት ዘበት ነው፡፡ አይኑ እያዬ ዘሩን አስጠፍቶ፣ ታሪኩን አስፍቆ፣ የመቃብር ቦታ የሚነፈገውና ሬሳው ተፈንቅሎ የሚወረወር አማራ ከእንሰሳም በታች መቆጠሩን ልብ ይበለው፡፡  አማራ በነቂስ ወጥቶ አንድ ሆኖ መታገል ያለበት ለመኖር ብቻ ሳይሆን ታሪኩ እየተገሸለጠ እንዳይጣል፣ መቀበሪያ እንዳያጣና የተቀበረውም በግኒደር እየታፈሰ መወርወሩ እንዲቆም ነው! አመሰግናለሁ፡፡

 

ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop