August 22, 2024
2 mins read

‹‹ህወሃት የራሱን ሰዎች በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ ለመመደብ የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም›› ዶ/ር ደብረጺዮን

456311355 1044574107287976 7469489562618089452 n
ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ህወሃት የራሱን ሰዎች በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ ለመመደብ የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም ሲሉ የህወሃት ሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል፡፡
በመቀለ ሳምንታትን ያስቆጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
ለሁለት ተከፍሎ ውዝግብ ውስጥ የገባው ህወሃት አባላቱ ጉባኤ ማካሄድ አለብን ወይስ የለብንም የሚለው ፖለቲካዊ ክርክራቸው ከፍ ብሎ ቀጥተኛ ወደሆነ የስልጣን ሽሚያ ውስጥ እንደገቡ ብዙዎች እየገለጹ ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚኖራችሁ ሚና በቀጣይ ምን አይነት ነው የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የህወሃት ሊቀመንበር ደ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ህወሃት በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ አባላቱን ለመመደብ ከማንም ፍቃድ አይጠይቅም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር መወያየት ያስፈልጋል ያሉት ሊቀመንበሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አሁን ላይ በህወሃት ውስጥ ውክልና ስለሌለው ጊዚያዊ አስተዳደሩን የመምራት አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡
ቀስ በቀስ ልዩነታቸው እየሰፋና ፖለቲካዊ መካረራቸው እየበረታ የመጣው ሁለቱ ቡድኖች እርስ በእርሳቸው እየተወቃቀሱና ሹም ሽር እያከናወኑ ቀጥለዋል፡፡

አዲስ ማለዳ

5 Comments

  1. እባቡ ደብረጽዪን የትግራይ ህዝብ በሽታ ነው። ያን ያህል ወጣት ከፊትና ከህዋላ በራሳቸው አመራሮች እየተተኮሰበት አልቆ አሁን ወያኔን ለማዳን በሚል ሰበብ ሌላ የፓለቲካ አተካራ ይዞ ብቅ ማለቱ ምን ያህል ወያኔ የሻገተ የፓለቲካ ስብስብ እንደሆነ ያሳያል። ወያኔ ያለ ጦርነትና ረሃብ መኖር አይችልም። መኖርን የሚለኩት በራሳቸው የዘረፋ ልክ በመሆኑ ለአንተ ነው እየተባለ የሚነገድበት የትግራይ ህዝብ ምክንያትና ለክፉ ጊዜ መጠለያ እንጂ አንድም ቀን ለህዝቡ አስበው አያውቁም። ግን እስከ መቼ ነው የትግራይ ህዝብ በእነዚህ የፓለቲካ ስንኩላን ሃበሳ እንደቆጠረ የሚኖረው? በእውነት በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆችና ህዝቡ ወያኔ ድኖ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለሌላው እፎይታ ይሆናል ብለው ያምናሉ? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር እንደሚሉት ነው። ወያኔ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው።
    አሁን ከጌታቸው ጋር ያለው ግብግብ የተከሰተው በዚያው ሰበብ ከብልጽግና ጋር ለመላተም እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። የትግራይ ታጣቂ ሃይሎች ገለልተኛ እንደሆኑ ተጠየቁ ገለ መሌ መባሉም ውሸት ነው። ለምድሪቱ የሚያስብ ታጣቂ ሃይል እነዚህን የእድሜ ልክ የወያኔ መሪዎች ሰብስቦ አንድ ቤት መዝጋትና እድሜ ልካቸውን በዚያው እንዲያሳልፉ ማድረግ ነበር። ግን ትግራይ ሃገር ትሆናለች፤ የትግራይ የበላይነት ተመልሶ ይመጣል፤ እኛ የምንፋለመው ለትግራይ ህዝብ ነው እየተባለ ግማሽ ምዕተ ዓመት ውሸትን የተጋተ ህዝብ በቀላሉ አይነቃም። ሆኖም ግን አሁን ላይ በውጭም ይሁን በሃገር ውስጥ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ቢዘገዪም ጉዳዪ የገባቸው ይመስላል። ወያኔንና የፓለቲካ ሽኩቻውን በመድረክ በግልጽ እየተፋለሙት እንደሆነ የሚያመላክቱ አበራታች ጉዳዪች መታየት ጀምረዋል። ነገርዬው ቢዘገይም ጭራሽ ከሚቀር አሁን ላይ መነቃቃት መታየቱ እሰየው የሚያሰኝ ነው።
    አንድ ሚሊዪን የትግራይ ወጣት ቢያልቅም 6 ሚሊዪን አድነናል የሚሉት እነዚህ የደምና የአጥንት ባለስልጣኖች የፓለቲካ ጥፋታቸውን በሌላው ላይ እያላከኩ ራስን ለማትረፍ የሚያቀርቧቸው ነጥብ ሁሉ የሚያስገርሙ ናቸው። እንዴት በልጆቻቸው ሞትና መጥፋት የትግራይ እናትና አባቶች እያለቀሱ የፓርቲ ጉባኤ አድርጎ ሰው ከበሮና ክራር እየመታ ሰው ዘፈን ይዘፍናል? ድሮ ሰው ሰው እያለ እናቴ ተው ራዲዪ እንዳትከፍቱ ጎረቤት ሃዘን ተቀምጧል እንባል ነበር። ዛሬ ላይ ሰው አውሬ ሆኖ እንሆ ያን ያህል ህዝብ አልቆ ጭፈራ የሚያስገርም ነው። ለነገሩ ለአመታት የጠበቃቸውን የመከላከያ ሰራዊት ገድለውና ልብሳቸውን አውልቀው በበድናቸው ዙሪያ የጨፈሩ እብዶች አይደሉንም። የበደነና የደነዘዘ ትውልድ እንዲያ ያደርጋል። በወንድምና በእህቱ ሬሳ ላይ ይፎክራል፤ ይጨፍራል። አይ ጊዜ! የብሄር ታጋዪች ሲጀመር የጭንቅላት በሽተኞች ናቸው። ለዚህ ነው በትንሹ የጀመራቸው ቆይቶ የአናት ግማት ያመጣባቸው።
    ደብረጽዪንና ተከታዪቹ ህዝቡ ለሌላ እልቂት እያዘጋጅት እንደሆነ ቃልና ተግባራቸው በግልጽ ያሳያል። በዚህ ላይ የብልጽግናው መንግስትም ዝምታ ያደናግራል። ወያኔን ያኔውኑ አድኑኝ እያለ አሜሪካን የሙጥኝ ሳይል የአሜሪካ ማስፈራራት ወደኋላ እርግጦ ወያኔን ቦታ አስይዞት ቢሆን ኑሮ ዛሬ ላይ የትግራይ ህዝብ የዋይታ መንደር ባለሆነም ነበር። ግን ፓለቲካ የጥልልፎሽ መንገድ በመሆኑ አንድ ሲባላ ሌላ እያየ በተራው ደግሞ ሌላው ይበላዋል። ተያይዞ ገደል የሚባለው ይሄ ነው። ግን እናንተ ደንባራ የወያኔ አቀንቃኞች መቼ ነው የትግራይ መሬት ያለ ጦርነትና ሁከት በሰላም የሚኖረው። መቼ ነው ሰው የመናገር፤ የመጻፍና የመሰብሰብ መብት ኑሮት እንደልቡ ገብቶ የሚወጣው? የ50 ዓመት የብሄር ፓለቲካ ፉርሽ መሆኑን አትረድም? ግን ወያኔ እያለ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ብልጽግናን አያገኝም። ወያኔ የሙታኖች ስብስብ ነው። ባጠቃላይ የኢትዮጵያ የብሄር ታጋዪች ሁሉ ገልቱዎች ናቸው፡ ዓለም ጥሎን ሂዷል። እኛ ግን በቤታችን በራፍ ላይ ቆመን አለም ሁሉ ይሄው ነው በማለት ራሳችን አሳምነን አይመስሉንም የምንላቸውን ገድለን፤ ዘርፈን ተራፊዎችን አፈናቅለናል። ይህ ነው የብሄር ፓለቲካ ቱሩፋቱ! የወያኔ አሁን ለሁለት መከፈልም ለትግራይ ህዝብ ተጨማሪ ስጋት እንጂ ሰላምን አያስገኝም። ወያኔ መጥፋት መክሰም ያለበት ድርጅት ነው። በቃ አለቀ… ከዚያ ውጭ ሰላም በትግራይም ሆነ በሃገሪቱ ሊኖር አይችልም።

    • ተስፋ ግርም(ር ን ጠበቅ አድርገው) ትላለህ የነገር እይታህ የተዛባ ነው። አገር ምድሩን የሞላው የትግሬ ምሁር ከፈረንጅ ሀገር ገብቶ በስብሰባው ላይ ጌታቸው ረዳን አውግዞ ደብረ ጽዮንን ተክሎ ሲሄድ ዛሬ ላይ ደጽዮንን ማውገዝ ምን ይሉታል። በውጭም በውስጥም ያለ ትግሬ ህወአትን ሲያወግዝ ሰምተሀል?ትግሬ ከሆንክ በውነቱ አላውቅም በሀገር ውስጥና ውጭ ያለ ትግሬ የህወአትን ዘመን በእጅጉ ይናፍቃል። በበረባሶ ጫማ ገብቶ አቃጥለህ የማትጨርሰው የተዘረፈ ሀብት አካብቷል። መጻፍ ማንበብ የማይችል ትግሬ ፒያሳ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅ ሁኗል ይህን የብልጽግና ዘመን ትግሬን አትናፍቅ ማለት አግባብነት የለውም።

      እኔ ይልቅ ትንሽ ያዘንኩበት ታየ ደንዳን ጥጋቡ እስኪበርድ ብሎ ይሄን ያህል ማሰር ፣አቡነ ቀሲስ በላይ ስድስት ሚሊዮን ሀያ ሽህ ብር የሰው ገንዘብ አጭበርብረው ሊወስዲ ሲሉ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው መታሰራቸው። ጠሚኒስቴር ጁዋር መሀመድ በደራርቱ ግብዣ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ሀብት ፓሪስ ተምበሽብሾ መሄዱ ሲሆን ለሚቀጥለው ኦሎምፒክ እስከዛው ካልሞተ በቀለ ገርባንም ጋብዙት ነው የምንለው።

      • ስማ ወስላታው – የእኔ ችግር የትግራይ ተወላጆች ለምን በስልጣን ላይ ሆኑ አይደለም። ለ 27 ዓመትም የመሰላቸውን ሰርተዋል። ይህን ደግሞ ከታሪክ መዛግብት መፋቅ የሚችል የለም። የእኔው ችግር ሰው ለሰው የሆነ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ አሰራር መዘርጋቱ ቀርቱ የብሄር አብላኝ ላብላህ መሆኑ ነው ችግር የፈጠረው። ሲጀመር ብሄርተኞች ማንም ይሁን ማን ጤና የጎደላቸው ናቸው። ይህም ችግር የሚታየው በትግራይ ተወላጆች ብቻ አይደለም። ሁሉም ተለክፏል። ለዚህ ነው ለጠባብ ብሄርተኞች በዓለም ላይ ፈውስ የለም የምንለው።
        ማንበብ መጻፍ የማይችል ስልጣንና ስራ ይዟል ትላለህ። የአንተ መጻፍና ማንበብ ያተረፈው ምንድን ነው? መልሱ ነገር ማማታት ነው። ጃዋር እንዲህ አርጎ እንዲያ ሰርቶ ትላለህ። እንኳን ፓሪስ ህዋ ደርሶ ቢመለስ ለእኔ ችግር የለብኝም። የሰው ስም በዚህም በዚያም ያላግባብ እየጠሩ ከመቀባጠር ዝም ማለት ይመረጣል። የሰውን ሞት የሚመኝ ራሱ በቁም የሞተ ነው። እኔንም ለቀቅ አርገኝና ከመሰሎችህ ጋር ተሰለፍ።

        • አቶ ተስፋ ስድቡን አለዝበው ቀረርቶ ሞላበት ሆነ እኮ ጽሁፍህ። የጁዋር ስም መጠራቱ የሰው ስም ተብሎ ይታለፋል? ጁዋርን አታውቀውም መሰል ወይም ስራው አስደስቶህ አልፈኸዋል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ጠላት በኢትዮጵያ ሃብት ፓሪስ ተምነሸነሸበት እኮ ነው የምልህ የነገር አረዳድህ ደካማ ከሆነ ሰዎች ይተርጉሙልህ። ብሄረተኝነት መሰረቱን የያዘው በትግሬዎች ነው ሌላው ፍላጻው ያረፈበት ነው አካሄድህ ሁሉ ወንጀለኞችን ለማዳን ይመስላል። እስቲ ሰላሙን ይስጥህ ምን ይባላል? እኔ ሰው ይሙት ብያለሁ?

  2. ደብረ ጽዮን ልክ ነህ ማንም አያገባውም ወጣት ግን እንዳታስገባ ገዝግዘው ይጥሉሃል ይሮብንም ከሻቢያ አታስለቅቅ የስዩም መስፍን እጣ ይደርስሃል። በተረፈ የማእከላዊ መንግስት በጀት ሊከለክልህ ስለሚችል ልብስ ቆጥብ በኋላ ጉድ ትሆናለህ። ብትችል አዜብ መስፍንን ምክትልህ አድርጋት። ይሄን የህወአት ቀፋፊ ኮፊያና ስካርፍ አታድርግ ያስጠላብሃል ሌሎቹ ይልበሱ ገገማዎች ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

456328113 524741236693555 5379586887323993242 n
Previous Story

“ዘርይሁን – 13″ የሚል ስያሜ የተሰጠው የጦር መሳሪያ ማምረቻ የምርምር ማዕከል አቋቁመናል!” -ፋኖ አስረስ ማረ

Fano qomen
Next Story

የአማራ ፋኖ ተጋድሎዎች ከሰሞኑ | የአማራ ፋኖ ተጋድሎዎች ከሰሞኑባህርዳር ከባድ ፍንዳታ ስብሰባው በድንገት ተበተነ |, ፋኖ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እየገሰገሰ ነው‼️

Latest from Blog

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን

 የአብይ አስተዳደርና የዶ/ር ብርሃኑ አኒ-ሚኒ-ማኒሞ

የጠ/ሚ አብይን የ2017 ዓ.ም. እንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አነበብኩት፡፡ዘመኑ ላይ ተፈላሰፉበት ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ዘመን እድል ነው አሉን፡፡ እድል ማለት እንደ አማርኛው መዝገበ ቃላት ትርጉም ከሆነ እጣ ክፍል፣ ግንባር
Go toTop