August 17, 2024
35 mins read

አብይ አህመድ በገዛ ወሬው የስከረ መሪ – አንዳርጋቸው ጽጌ

ነሃሴ 2016
birhanu m000

የሚገርም ዘመን፣ ከዋናው የሃገር መሪ እስከ ተራው ካድሬ ምንም አይነት የሞራል ኮምፓስ የሌላቸው፤ የሞራል ልጓማቸው የተበጠሰባቸው ሆነዋል። የኢትዮጵያ ጉዶች ። እንዳንዴ ለእነዚህ ሰዎች አጓጉል ንግግር መልስ መስጠት እንደነሱ መሆን ነው በሚል ስጋት ዝምታ መምረጣችን የራሳቸውን ቅጥፈት እንደእውነት በመውሰድ በእብደት ህዲድ እንዲነጉዱ ከማድረጉ በላይ የእነሱን መበጥረቅ (ከኮሜዲያን እሸቱ መለስ የተማርኩት ዘመኑን የዋጀ ቃል) ጥቂቶችንም ቢሆን ማወናበዱ ስለማይቀር፣ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ የተመዘነና በቅጡ የታሰበበት ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ለዚህ ነው እየታከተኝም ቢሆን አልፎ አልፎ ብእሬን የማነሳው።

1. ሀተታ ላለማብዛት አጠቃላይ ከሆነው የሃገር ሁኔታ ልጀመር፤
“ኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነቷን እና ጥቅሟን የሚያስጠብቅላት መንግስት የላትም። መንግስቷ በአንድ በራሱ ምስል በስከረና ባበደ አደገኛ ግለሰብ እጅ ወድቋል። ይህ በራስ ምስል አምልኮት የአእምሮ በሽታ የተጠቃ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ካልተነሳ ኢትዮጵያና ህዝቧ ብሄራዊ ደህንነታቸው፣ ጥቅማቸው፣ ሰላማቸው ብልጽግናቸው አይረጋገጥም ስንል ዝም ብለን እንደ አብይ አህመድ፣ እየተበጠረቅን አይደለም። ኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ መሰረት አድርገን ነው።
አብይ አህመድና ደንገጡሮቹ ግን ይህ ማየት ከማይችሉበት የተዘጋ የአእምሮ ውቅር ወይም ህሊና ገንብተው ተቀምጠዋል። መስማት ብቻ የሚፈልጉትን እየሰሙ፣ ማየት ብቻ የሚፈልጉትን እያዩ፣ ማመን ብቻ የሚፈልጉትን እያጠለሉ እያመኑ እንዲኖሩ ያደረገ፣ እውነታን በካደ የቅዥተ አዙሪት ውስጥ ወድቀዋል።

እንደማይሰሙን ብናውቅም እስኪ ጥቂት እንበላቸው። ዝምታችን ለእብደታቸው የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ መፍቀዱ እኛንም ተባባሪ ያደርገናልና።

የአንድ ሃገር ብሄራዊ ደህንነት ጥቅም የሚከበረው በመከላከያ ሰራዊቱ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሰራው ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑ ቀርቶ የአንድ ግለሰብ ስልጣን ለማስጠበቅ ሲል ከመላው የሃገሪቱ ህዝብ ጋር ተራ በተራ ወይም በአንድ ጊዜ ሲዋጋ መኖር፤ የገዛ የሃገሩን ልጆች መግደልና በነሱም መገደል እጣው ከሆነ ሰነበተ። ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ዳር ድንበሯ ተደፍሮ፣ መሬቷ በውጭ ሃሎች እጅ ተይዞ ይህን ማስቆም የሚገባው የመከላከያ ተቋም መሳሪያውን፣ የሰው ሃይሉንና መሉ ጉልበቱን በኢትዮጵያውያን ፍጅት የአንድን ግለሰብ የስልጣን ሱስ ለማርካት በስራ ላይ እንዲያውል ተደርጓል። የሰራዊቱ ጄነራሎች ለዚህ ታማኝነታቸው ቢሸጡት እስከ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሬት ታደሏቸዋል፣ የሃገር ወርቅ ከየክልሉ መሪዎች ጋር በመሻረክ እያስቆፈሩ ከሃገር ውጭ ያወጣሉ፣ መሳሪያና መረጃ ለአልሸባብ ሳይቀር ይሸጣሉ፣ የግንባታ የንገድ ድርጅቶች፣ ከህንዶችና ከቻይኖች ጋር አቁመው ከሪል እስቴት አለፈው መለስተኛ ግድቦች ይገነባሉ። ለመከላከያ ከተመደበው ግዙፍ ባጀት የሚዘርፉትን እዚህ ላይ ማከል ነው።

ሌላው የአንድ ሃገር የብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም አስከባሪ ተቋም፣ የመረጃ የደህንነት ተቋሙ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ተቋም እንደተቋም መስራት ካቆመ ሰንብቷል። በሃሰት የትወልድ፣ የትምህርትና የማነንት መታወቂያ ማስረጃ፣ በዘመድ አዝማድ፣ በምልጃና በጉቦ የሚቀጥራቸውን ሰዎች እውነተኛ ማንነት መስሪያ ቤቱ ከማያውቅበት ደረጃ ላያ ደርሷል። ግለሰቦች በጠላት ሃገራት መንግስታትና ድርጅቶች ተመልምለው፣ በተቋሙ ውስጥ መተከላቸውን ወይም ከሰራተኞቹ መሃል ለጠላት ተመልምለው የሚሰሩ ከሃዲዎች እንዳይኖሩ የሚከታተል፣ በደህንነቱ መስሪያ ቤት ላይ የስለላ ስራ የሚሰራ ጸረ መረጃ የተባለው ክፍል ከደህነነት ተቋሙ ከጠፋ ስንብቷል። በዚህም የተነሳ አልሸባብ ወኪሎቹን በኢትዮጵያ የመረጃ መስሪያ ቤት አስቀጥሮ መረጃ መዝረፍ የቻለበት ሁኔታ ተከስቷል። ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች መሃል ምን ያህሉ አሁንም ለኢትዮጵያ ጠላቶችና መረጃ ለሚፈለጉ ሌሎች ተቋማት እንደሚሰሩ፣ መረጃ እንደሚሸጡ አይታወቅም። የመረጃ መስሪያ ቤቱ ከሱማሌው አልሸባብ እስከ ናይጀሪያው ቦኮ ሃራም አባላት የኢትዮጵያን ፓስፖርት በማደል በሃሰተኛ ስምና መረጃ በኢትዮጵያ ፓስፖርት በአለም ላይ መንቀሳሰ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥሯል።

የአንድ ሃገር ብሄራዊ ደህንነት ጥቅም የሚከበረው በመከላከያ ሰራዊቱ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሰራው ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑ ቀርቶ የአንድ ግለሰብ ስልጣን ለማስጠበቅ ሲል ከመላው የሃገሪቱ ህዝብ ጋር ተራ በተራ ወይም በአንድ ጊዜ ሲዋጋ መኖር፤ የገዛ የሃገሩን ልጆች መግደልና በነሱም መገደል እጣው ከሆነ ሰነበተ። ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ዳር ድንበሯ ተደፍሮ፣ መሬቷ በውጭ ሃሎች እጅ ተይዞ ይህን ማስቆም የሚገባው የመከላከያ ተቋም መሳሪያውን፣ የሰው ሃይሉንና መሉ ጉልበቱን በኢትዮጵያውያን ፍጅት የአንድን ግለሰብ የስልጣን ሱስ ለማርካት በስራ ላይ እንዲያውል ተደርጓል። የሰራዊቱ ጄነራሎች ለዚህ ታማኝነታቸው ቢሸጡት እስከ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሬት ታደሏቸዋል፣ የሃገር ወርቅ ከየክልሉ መሪዎች ጋር በመሻረክ እያስቆፈሩ ከሃገር ውጭ ያወጣሉ፣ መሳሪያና መረጃ ለአልሸባብ ሳይቀር ይሸጣሉ፣ የግንባታ የንገድ ድርጅቶች፣ ከህንዶችና ከቻይኖች ጋር አቁመው ከሪል እስቴት አለፈው መለስተኛ ግድቦች ይገነባሉ። ለመከላከያ ከተመደበው ግዙፍ ባጀት የሚዘርፉትን እዚህ ላይ ማከል ነው።

ሌላው የአንድ ሃገር የብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም አስከባሪ ተቋም፣ የመረጃ የደህንነት ተቋሙ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ተቋም እንደተቋም መስራት ካቆመ ሰንብቷል። በሃሰት የትወልድ፣ የትምህርትና የማነንት መታወቂያ ማስረጃ፣ በዘመድ አዝማድ፣ በምልጃና በጉቦ የሚቀጥራቸውን ሰዎች እውነተኛ ማንነት መስሪያ ቤቱ ከማያውቅበት ደረጃ ላያ ደርሷል። ግለሰቦች በጠላት ሃገራት መንግስታትና ድርጅቶች ተመልምለው፣ በተቋሙ ውስጥ መተከላቸውን ወይም ከሰራተኞቹ መሃል ለጠላት ተመልምለው የሚሰሩ ከሃዲዎች እንዳይኖሩ የሚከታተል፣ በደህንነቱ መስሪያ ቤት ላይ የስለላ ስራ የሚሰራ ጸረ መረጃ የተባለው ክፍል ከደህነነት ተቋሙ ከጠፋ ስንብቷል። በዚህም የተነሳ አልሸባብ ወኪሎቹን በኢትዮጵያ የመረጃ መስሪያ ቤት አስቀጥሮ መረጃ መዝረፍ የቻለበት ሁኔታ ተከስቷል። ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች መሃል ምን ያህሉ አሁንም ለኢትዮጵያ ጠላቶችና መረጃ ለሚፈለጉ ሌሎች ተቋማት እንደሚሰሩ፣ መረጃ እንደሚሸጡ አይታወቅም። የመረጃ መስሪያ ቤቱ ከሱማሌው አልሸባብ እስከ ናይጀሪያው ቦኮ ሃራም አባላት የኢትዮጵያን ፓስፖርት በማደል በሃሰተኛ ስምና መረጃ በኢትዮጵያ ፓስፖርት በአለም ላይ መንቀሳሰ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥሯል።

ስራው ነው። ይህን መስሪያ ቤት በአብይ ተላላኪዎች ከመሞላት አልፎ የአብይ አህመድ የግል ፍላጎት ማስፈጸሚያ ከሆነ ቆይቷል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከታዬ አጽቀስላሴ በላይ ተሰሚነት ያላት ምክትሉ ብርቱካን አያና ናት። አምባሳደሮች የሚያደገድጉት፣ የተሻለ ምደባ እንዲያገኙ ጉቦና ስጦታ የሚሰጡት ለዚች የአብይ አህመድ የቅርብ ሴት ነው።

የአብይ አህመድ እብደት በሚገባ የተገለጸበት፣ የሃገርና የህዝብ ደህንነትና ጥቅም ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት የመንግስት እንቅስቃሴ ቢኖር የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ ነው። በተሳሳተ የአብይ አህመድ የውጭ ጉዳይ እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ተጣልታለች። ማንም በበጎ አይን የሚያያት የለም። ምንም ደሃ ብትሆን በቀጠናውና በአለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎምሲ መስኩ ትታይበት የነበረው የላቀ ስፍራዋ ላይ ዛሬ የለችም።

ኢትዮጵያ ለደረሰባት ጉዳት ብዙ ምሳሌ ማቅረብ ቢቻልም ከሱማሌላንድ ጋር አብይ ገባሁ ያለው በቅጥፈት የተሞላ፣ ገና ከመጀመሪያ የትም እንደማይደርስ የተነበይነው የመግባቢያ ሰንድ ፊርማ ትልቁ ምሳሌ ነው። ሰነዱ በተፈረመበት ወቅት “ለሃገር ደህንነት አደገኛ ውሳኔ ነው” ብለን የተቃወምነው ግለሰቦች፣ አብይና አሽቃባጮቹ እንዳሉት ሃገር ሲያልፍላት አይናችን የሚቀላ ባናዳዎች ስለሆን አልነበረም። ይህን የሚሉት የባንዳነት ታሪክ በዘር ማንዘራችን እንደሌለ አጥተውት አይደለም። የሱማሌን ሉአዋላዊ ሃገርነት የሚጻረር ድርጊት በኢትዮጵያ ላይ ብዙ መዘዞች ያስከትላል ከሚል ተጨባጭ ስጋት በመነሳት ነበር ስምምነቱን ያወገዝነው።

ለአንድ ሰሞን ህዝብን የማወናበድና የማፋዘዝ ፕሮጀክት ሲባል የተፈጸመ ድርጊት ኢትዮጵያ ሰራዊቷን ከሱማሌያ የምታስወጣበትን፣ አልሸባብ ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ካምፕ የመሰረተበትን፣ ግብጽ በኢትዮጵያ ድንበር ሱማሌ ውስጥ ወታደሮቿን ማስፈር፣ የሱማሌን ሰራዊት ማሰልጠን የምትችልበትን፣ ቱርክ የሱማሌን የባህር ዳርቻዎች ደህንነት የምትጠብቅበትን ውሎች ከሶማሊያ ጋር መዋዋል የቻሉበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል። ህዝብ ለህዝብ መቀራረብ ጀመሮ በነበረው የኢትዮጵያና የሱማሌ ህዝብ ግንኙነት ላይ ያደረሰው ጉዳት ቀላል አይደለም። የመከላከያ የደህንነት ተቋማቷን አፍርሳ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ መስኩ የሃገሪቱን ጥቅም ተጻረው ለሚቆሙ ሃገራትና መንግስታት፣ እድሜ ለአብይ አህመድ፣ የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥራ አርፋዋለች።

ሌላው የአንድ ሃገር ሉአላዊነት፣ደህነነትና ጥቅም ማስከበር የሚችለው ሃይል ከህዝብ አንድነትና በህዝብና በመንግስት መቀራረብ የሚገኘው ጉልበት ነው። የአብይ አህመድ አገዛዝ ሆን ብሎ የሃገሪቱ ህዝቦች እርስ በርስ በጎሪጥ እንዲተያዩ፣ ከዛም አልፈው እንዲጨፋጨፉ የሚሰራ መንግስት ሆኗል። በአብዛኛው የሃገሪቱ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ተጋጭቷል። አሁንም እየተጋጨ ነው። ከጦርነት በተረፈው ህዝብ ላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚል ስም የኢኮኖሚ ጦርነት ከፍቶ፣ ከጥቂት ባላሃብቶችና የመንግስት ባላስልጣናት በቀር የእያንዳንዱን ዜጋ ህይወት የምድር ሲኦል አድርጎት አርፏል። አብይ በፈጸማቸው ዘርፈ ብዙ ጸረ ህዝብ ድርጊቶቹ ከህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል። ከሃገሪቱ የቆዳ ስፋት የሚቆጣጠረው እየጠበበ ሄዶ አገዛዙ እንደለቡ ያሻወን መፈጸም የሚችልበት ቦታ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሆኗል። አብይ አህመድ ህዝብንም ከሃገር ደህንነትና ጥቅም ማስጠበቅ ስራ አግሎታል። ኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ናት የምንለው ይህን ሁሉ ጉድ አይተን ነው።

2. ወደ ውቅታዊ ጉዳይ ስመለስ
አብይ አህመድ የጫካ ቤተመንግስት፣ የኮሪደር ልማት፣ አዲስ ቱሞሮ (ጥራዝ ነጠቅ ስትሆን የሚመጣ የእንግሊዝኛ አጠቃቀም) እያለ የአልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ፕሮፓጋንዳውን እራሱ እየሰራ፣ እራሱ እየተጋተ ሰከሮና ደንዝዞ መኖርን መርጧል። ይህን ድርጊቱን አያዋጣም የምንለውን በወሬ የምንኖር እራሱን በስራ የሚኖር አድርጎ መግለጽ ደግሞ የሰሞኑ የፐሮፕጋንዳ አቅጣጫው ሆኗል። ከዚህ ቀጥሎ የምላቸው ጥቂት ቃላቶች የአብይ አህመድ የሰሞኑ ጭኸቶች የቁራ ጭኸቶች እንደሆኑ የሚያሳዩ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልገባው እሱ የያዘው ስልጣን በአንዳንዶቻችን እጅ ቢገባ ለጫካ ቤተመንግስቱ አዲስ አበባ ላይ የሚያጠፋውን ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን የሚደርስ ዶላር ከሱ በተሻለ ሃገርና ህዝብን ወደከፈተኛ ብልጽግና መውሰድ የሚያስችል ስራ ማዋል የሚችሉ ልጆች ኢትዮጵያ እንዳሏት ነው። አብይና አሽቃባጮቹን በምክን ያት ተከራክሮ ማሳመን እንደማይቻል በገባንም በህዝብ ፊት ማሳፈር ስለሚቻል 10 ቢሊዮን ዶላሩን እንዴት እንደምናጠፋው ቀጥሎ እናቀርባለን።

10 ቢልዮን ዶላሩን ምን እናደርገው እንደነበር ስንነግራችሁ የጫካው ቤተመንግስት፣ በግንባታ ወቅት የሚቀጥረውንና ከተገነባ በኋላ ስራ የሚፈጥርለትን የሰው ብዛት፣ ግንባታው ሲያልቅ የሚያስገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅምና ሃገራዊ ፋይዳ በሚገባ ተመልክተን ነው።ዝርዝሩን ማቀረብ ያለበት አብይና ኩባንያው ነው። እኛ ማድረግ የምንችለው እንዲህ አይነቱ የጫካ ቤተመንግስት ኢንቨስትመንት ቱሩፋቶቹ ምን ይሆናሉ ብለን በመገመት ብቻ ነው። በተለይ ይህን ያህል ዶላር የፈሰሰበት ቤተመንግስት ሰላምና መረጋጋት በሌለበት ሃገር ቀርቶ ሰላም ቢኖርም ክወጭ የሚስበው ጎብኝ ይሁን በዚህ ቤተመንግስት ዙሪያ የሚገነቡ ህንጻዎች የሚስቡት የውጭ ኢንቨስትመንት እዚህ ግባ የሚባል የኢኮኖሚ ፋይዳ እንደማይኖር የታወቀ ነው። በግንባታ ስራውም ሆነ ካለቀ በኋላ የሚፈጥረው የስራ እድል ውሱን ነው። እንግዲህ ይህን አይነቱን በሃገራችን ከሚሰሩ ስራዎች ቅደም ተከተሉ እጅግ የተዛናፈን የዛሬ መቶ አመት እንኳን ሊሰራ የማይገባውን ስራውን እያመላከተ ነው አብይ አህመድ የስራ ሰው መሆኑን ሊነግረን የሚዳዳድው።

እኛ ደግሞ ይህን በጫካ ቤተመንግስት ላይ አብይ አህመድ የሚያወጣውን ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር፣ በ10 ቢሊዮን ዶላር ገድበን ይህን ገንዘብ በሀሃገራችን ውስጥ ቅድሚያ ማግኘት አለባቸው ከምንላቸው ስራዎች አንዱ በሆነው የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ምስረታ ላይ እንዴት እንደሚውልና ምን ሃገራዊ የኢኮኖሚ እርባና እንደሚኖረው በማሳየት አብይ የወሬ እንጂ የስራ ሰው አለመሆኑን ማሳየት እንችላለን።

የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ራሳችንን በምግብ ለመቻል፣ ከዛም አልፎ ግብርናውን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ አብዮት ለማስጀመር፣ በግብርና ምርታቸን ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ችግራችንን መቅረፍ የምንችልበት እድል ለመፍጠር፣ በግንባታው ወቅትና ከተገነባ በኋላ የሚቀጥረውን የቋሚ ሰራተኛ ብዛት፣ ኢንዱስትሪው ራሱ የሚያመርተው ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ተርፎ ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ በአንድ ላይ ግምት ወስጥ አስገብተን የአብይን 10 ቢሊዮን ዶላር በማዳበሪያ እንዱስትሪ ምስረታ ላይ ብናውለው ምን ውጤት እናገኝ ነበር የሚለውን ጉዳይ ለአብይ አህመድና በዙሪያው ላሉ አሽቃባጮቹና በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን እናስውባለን በሚልፕሮፓጋንዳቸው ሊያደነዝዙት የፈለጉትን ህዝብ የሚከተሉትን ሃቆች እንንገራቸው።

አብይ አህመድ ጫካ ቤተመንግስት የሚገነባባትን ገንዘብ ወደ ማዳበሪያ ኢንደስትሪ አዙሮት ቢሆን።
1. ለማዳበሪያ መስሪያ አስፈላጊ የሆነወን አሞኒያ የተባለ ኬሚካል በአመት በብዙ ሚሊዮኖች ሜትሪክ ቶን ማምረት ይቻል ነበር።
2. ለማዳበሪያ መስሪያ አስፈላጊ የሆኑትን ፎስፌትና ፖታሸ 1 እስከ 2 ሚሊየን ሚትሪክ ቶን በአመት ማምረት ይቻል ነበር።
3. ይህ የማዳብሪያ ኢንደስትሪ ኢትዮጵያ በአመት ለማዳበሪያ የምታወጣውን ከ800 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያሰቀር ነበር።
4. በውጭ የማዳበሪያ ኩባንያዎችና መጓጓዣዎች እንዲሁም በየጊዜው ከሚዋዥቅ የማዳባሪያ ዋጋ ራሷን ነጻ ማድረግ ትችል ነበር።
5. ዘመኑ የሚፈቅደውን የተራቀቀ ቴክኖሎጂ በማደበሪያ ማምርቻ ስራ ላይ ማዋል ትችል ነበር።
6. ይህ ዶላር በጥናትና ምርምር ላይ የተመስረተ ከማዳበሪያ ጋር የተያያዘ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የጥናትና የምርምር ተቋም እንዲኖረን ያስችል ነበር።
7. ለተፈጥሮ እና ለአካባቢ ጥበቃ እንብካቤ የሚያደርግ ኢንደስትሪ መገንባት የሚያስችል አቅም ይሰጠን ነበር።
8. በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች፣ ኤንጂኔሮች፣ ኬሚስቶችም የፋብሪካ ማሽነሪ አንቀሳቃሾች፣ የማእድን ሰራተኞች፣ የድጋፍ ስራ የሚሰሩ ሌሎችንም በመቶ ሸዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስራ ያስገኝ ነበር።
9. የማዳበሪያው ኢንደስትሪ ትልቅነት የአለምን የማዳበሪያ ገበያ ከ5 እስከ 15 በመቶ የመቆጣጠር ትልቅ አቅም ሰለሚኖረው ኢንቨስትመንቱ ከኢትዮጵያ ውጭ በሌሎች ሃገሮች ሳይቀር መስሪያ ቤቶች የሚኖሩትና ሰራተኞችም የሚቀጥር ይሆን ነበር።
10. ኢትዮጵያ ለማደባሪያ መስሪያ የሚሆን ትልቅ የፖታሽ ክምችት ቢኖራትም፣ ለፖታሽና ለሌሎችም ለማዳበሪያ መስሪያ የሚሆኑ ወሳኝ ግብአቶችን ሩቅ ሳትሄድ ከጎረቤቶቿ ማግኘት የምትችልበትን የኢኮኖሚ ትብብር እድል የሚከፈት ይሆን ነበር። ከኤርትራና ከጅቡቲ ጋር ፎስፌትና ፖታሽ በማውጣት፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከሱዳን ናይትሮጂን ለሚያስፈለገው የአሞኒያ ማዳበሪያ ለመስሪያ የሚሆነው የተፈጠሮ ጋዝ በመግዛት የሚፈጠረው የኢኮኖሚ መደጋገፍ ለቀጠናው ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር።
11. ጥናቶች የሚያሳዩት በ10 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የሚጀመር የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምርት ሲጀመር ከ 5 ቢሊዮን እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ አመታዊ ገቢ ሊኖረው የሚችል ይሆናል፣ ከዚህ ውስጥ ትርፉ በየትኛውም ኢንደስትሪ ከሚገኝ ትርፍ የላቀ እንደሚሆን ይገመታል።

12. ይህ ስራ ለማስጀመር
• የአሰሳና የአዋጭነት ጥናት ለማጥናት ከ50 እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር፤
• የመስረተ ልማት ስራ ትልቁ ነው። የማእድን ማውጫ መሳሪያዎች፣ የማጓጓዣ ስራ፣ የኤነርጂ አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት ስራ ከ500 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚኖረው ይገመታል።
• ማእድን ማውጣትና ማጣራት ማምረት ፋብሪካዎችን ማቆም ከ 1 ቢሊዮን እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ይገመታል።
• ለሎጂስትክ ለሃገር ውስጥና ወደ ውጭ ማጓጓዣ ከ300 ሚሊዮን እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር፤
• አመታዊ የሰራተኛ ደሞዝ፣ የጥገና የመለዋወጫና ሌሎችም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ መንቀስቃሰ እሰክሚችል ድረስ የሚያፈልገው ወጪ ከ 200 እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር ይሆናል።
አጠቃላይ የአንድ ትልቅ የማዳበሪያ ፋብሪካ የኢንቭስትመንት ወጪ ከ2 ቢሊዮን ዶላር እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል።

ስራው አድካሚ ነው። በትንሹ አምስት አመታት ጊዜ ይወስዳል። እንደ ኮሪደር ልማት፣ እንደ ጫካ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ቤተመንግስቱ አካባቢ ለአብይ አይን ማረፊያነት የሚሰራ አይሆንም። አብይ ጠዋትና ማታ የሚጎበኘው፣ ውጤቱም በሚብለጨጩ ህንጻዎች በቀላሉ የማይታይ ስራ ነው።

እንግዲህ ይህ ቁልፍና መሰረታዊ የሆነ የሃገርና የህዝብ ትልቅ ችግር ለመቅረፍ የሚያስፈለግ፣ ከዛም አልፎ በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘትና ከፍተኛ ቁጠር ያለውን ቋሚ ሰራተኛ ለመቅጠር የሚያስችል አንድ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከ 2 እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ ከሆነ፣ የጫካው ቤተመንግስት በሚሰራበት በ 10 ቢሊዮን ዶላር በአማካይ 3 ትልልቅ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች መገንባት ይቻል ነበር ማለት ነው።

ይህን ኢንደስትሪ ለጫካው ከሚወጣው ወጪና የጫካው ፕሮጀክት ለሃገርና ለህዝብ ከሚሰጠው ፋይዳ ጋር ማነጻጸሩና የፋይዳወን ልዩነት የመገመቱ ስራ ለብልሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንተወዋለን። የአብይ አህመድ አገዛዝ የሀገር ጠንቅ ነው። ብልጭልጭ ፕሮጀክቶቹም የግለሰቡን ብኩን ስብእና የሚያሳዩ ናቸው የምንለው፣ በበልጽግና ዙሪያ አብይ እንደሰበሰባቸው የፓርቲው ደናቁርትና እነሱን እንዲያጅቡ አብይ ስልጣን ያጋራቸው እንደብርሃኑ ነጋ እንደ ግርማ ሰይፉ እንደነ በለጠ ሞላ ከአብይ እግር ስር እየወደቀን ጭራችንን የማንቆላው፣ በዘራችሁ አይድረስ ከሚል የመዋረድ እርግማንም ራሳችንን የምናድነው ጌታቸውና ፈጣሪያቸው አብይ እንደሚለው በወሬ ስለምኖር ሳይሆን፣ ለግል ስማችን፣ ክብራችንና ሆዳችን ሳይሆን ሃገርን የሚጠቅምና የሚጎዳ ተግባር ምን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው። ይች በድህነት የተጨማደደች ሃገራችን እና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ደሃ ህዝባችን ወደ ብልጽግና የሚያመራው ጥቂት ከተሜዎችና ዳያስፖራዎች፣ አብይ እንዳለው ፎቶ መነሳት የሚችሉባቸውን ቦታዎች አዲስ አበባ ላይ ለመፍጠር ሲባል ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን በከንቱ በማባከን እንዳልሆነ ስለምናውቅ ነው። የከተማወን ህዝብ ረሃብ ለማስታገስ ማዳበሪያ ያለውን ትርጉም ስለምናውቅ ነው። ልኡላዊነትን አሳልፎ የሸጠ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስራ ላይ እንዳናውል የሚያደርገንን፣ ከፍተኛ የሆነ የወጭ ምንዛሪ ፍላጎታችንን የሚቀንስ፣ ኢንደስትሪው ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝልን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው። ግብርናን መሰረት ያደረገ የኢንደስትሪ አብዮት በማካሄድ አስተማማኝ ልማት ለህዝባችን ማጎናጸፍ እንደሚችል ስለሚገባን ነው። የአብይ አገዛዝ ያለበት ችግር በእውነት፣ በሃቅ፣ በእውቀት ላይ ተመስርተው ስካርና እብደቱን ከሚያመላክቱት ሰዎች ይልቅ እሱ የሚለውን እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ፣ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር እንደተዋወቀች አይና አፋር ለጃገረድ የሚሽኮረሞሙ ወራዶችን ማቅረቡ ነው።

ከእነዚህ ሰዎች መሃል እኔ በግሌ የማውቃቸው በአንድ ወቅት ትልቅ ክብርና ግምት የሰጠኋቸው ሰዎች መገኘታቸው ነው፤ “እንዲህ አይነት ውርደት በዘራችሁ አይድረስ” እንድል ያሰኘኝ።

በገዛ ወሬው የስከረ መሪ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop

Don't Miss

አንዳርጋቸው ጽጌ ሣይቀር የሚሣለቅበት አማራ ይህችን የጨለማ ዘመን ካለፈ ምንም አይል – ሥርጉት ካሣሁን (አዲስ አበባ)

ይሄ “እንደሠራ አይገድል” የሚባል አማርኛ አንዳርጋቸው ጽጌን የመሳሰሉ የታሪክ ዝቃጮችንና