ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ውጥረትና መካረር የበዛበት የህወሃት ፖለቲካዊ ተቃርኖ ልዩነቶች አሁንም ጎልተው መታየታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የህወሃትን 14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በውዝግብ ውስጥ ሆኖ እያከናወነ ያለው የነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ቡድን አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰምቷል፡፡
የህወሃት ሊቀመንበር ቡድን ዛሬ ባወጣው መግለጫም በ14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ያልተሳተፉ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከዛሬ ነሃሴ 11 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም መድረክ በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀሱ ማገዱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህም የታገደው ቡድን ማለት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራና 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን የያዘ ሲሆን በህወሃት ስም የሚደረግ የዚህ ቡድን እንቅስቃሴ እንደማይታወቅ በሊቀመንበሩ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በኩል የወጣው መግለጫ ያመላክታል፡፡
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስም በአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን በኩል ምላሽ አልተሰጠም፡፡
አዲስ ማለዳ