July 22, 2024
2 mins read

«ኮማንደር አሰግድ እጁን ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ ይቀለዋል» መሳይ መኮንን

451628420 491773623409845 242423440167739044 nኮማንደር አሰግድ መኮንን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ የሚለው የብልጽግናው ዲጂታል ሰራዊትን ወሬ ለማጣራት የተወሰኑ ሙከራዎች አድርጌአለሁ። ማረጋገጫ ማገኘት አልቻልኩም። ሆኖም አንድ የሰሜን ሸዋ እዝ ከፍተኛ አመራር ሊሆን የማይችል የካድሬዎች ጫጫታ ነው የሚል መልስ ሰጠኝ።

ማታ በስልክ እንደተገናኙና በዚህ አጭር ሰዓታት ውስጥ ሊለወጥ የሚችል ተአምር እንደሌለም ነገሩኝ። ለጊዜው የኮማንደሩና አጠገቡ ያሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ዝግ በመሆኑ አሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ነገር ግን ”ኮማንደር አሰግድ እጅ ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ እንደሚመርጥ” በመግለጽ አመራሩ እርግጠኝነቱን አሳየኝ።
”ብዙ ጊዜ ኔትወርክ ስለማይኖር እንዲህ ዓይነት በስልክ አለመገናኘት የተለመደ እንደሆነና ዛሬ ምን ተፈጥሮ ወሬው እንደተዛመተ አላውቅም” በማለትም አብራራልኝ። ወደኋላ ላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ነግሮኝ ተለያየን።

451139093 491773543409853 1756337320394443878 nእንግዲህ ስለጉዳዩ የማሳመን ሸክሙ የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት ላይ ወድቋል። ያዝን፡ እጁን ሰጠን ካሉ ያቅርቡና ያሳዩን። በተረፈ ቢሆንም ባይሆንም ትግል ነውና ትግሉ ይቀጥላል። ግለሰቦች በትግሉ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖራቸውና ያለመኖራቸው ተጽዕኖ ለህልወና ሲባል በተጀመረ ትግል ላይ የሚፈጥረው ኪሳራ ኢምንት ነው። የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ግለሰቦች አላስጀመሩትም።

ግለሰቦችም አያስቆሙትም። የጥቂት ቀናት ወሬ ሆኖ ይጠፋል። ትግል ይቀጥላል። ብልጽግናዎች ከበሮ መደለቁን በልኩ አድርጉት። ደረት መድቃትም ይኖራልና።

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

4 1
Previous Story

4 ኪሎን ያስጨነቀው የጄ/ል ተፈራ ጦር | “ፋኖ እኛን ሳይጨ-ርስ 4 ኪሎ አይገባም” ሽመልስ

LTV Show with Eskinder Nega
Next Story

እስክንድር ነጋ ይብቃው፣ ገለል ይበል

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop