“ህልውናችንን አስጠብቀን ሀገራችንን እናድናለን” አርበኛና ጠበቃ አስረስ ማረ

June 28, 2024

2 Comments

 1. ኮተቱን በክተት፟፤
  ለፋኖ የቀረበ ጥሪ
  ኦነጋዊው ብልጽግና እና ሕወሃት በአማራ ላይ ያልታወጀ የክተት ጥሪ አድርገው የጦርና የካድሬ ኮተታቸውን እያዘመቱበትና አዝምተውበት ይገኛሉ። ይህም ወረራና ጥቃት ሁለንተናዊ ሲሆን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፕሮፓጋንዳዊ ዘመቻዎች የተካተቱበት ነው። ሕወሃት ራያን በዳግም ወረራ ከመያዙ በተጨማሪ ለወልቃይት ቀነ ቀጠሮም ሰጥቶ ሙሉ ዝግጅት ከማድረግ አልፎ ወረራውንም በግልጽ ጭፍጨፋ ጀምሮታል። ለዚህ የሚውለው መዋእለ ንዋይም ሆነ የጦር መሣሪያ ከየትኛው “ወዳጅ” እንደተለገሠ ግልጽ ነው። ኦነግ ብልጽግናም በጅምላ አፈሳ ሳይቀር በቁጥጥሩ ሥር ያለውን ወጣት ወደ ጦር ግንባርና ወደ ማሠልጠኛ እያጋዘ ነው። ይህንን ሁለ ገብ የወረራ ኮተት ፋኖም እንደጠላቶቻችን ባልታወጀ ክተት ብቻ ሊመክተው ስለማይችል የፋኖ መሪዎች በአማራ ላይ የተቃጠውን ይህንን አደገኛ የሕልውና ጥቃት ሁሉን አቀፍ ክተት በማወጅ የአማራን ኅይል ከዳር እዳር በማንቀሳቀስ መመከት ይኖርባቸዋል።
  ይህ ዘመቻ ለአማራም ለኢትዮጵያም አልፎ ለኤርትራና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች የሕልውና ዘመቻ ነው። ወልቃይት የአማራን ሕልውና፣ የኢትዮጵያን ሕልውና የኤርትራንም ሕልውና የሚወስን ለሕወሃትም የመገንጠል ያለመገንጠልን አቅም የሚወስን እጅግ ቁልፍ በር ነው።
  ሕወሃት በትግራይና በሌላው ኢትዮጵያዊ መካከል (በተለይ በአፋርና አማራ) ያሉትን ትስስሮች ባላፈው ጦርነት በጣጥሶ የመለያየት ሥነ ልቡናዊ ዝግጅቱ የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ ደርሷል ብሎ የተማመነና የተፈጠረለትን (የተመሠረተበትን) ኢትዮጵያን ኤርትራንም አፍርሶ፣ የአማራን ምድር ቆርሶ፣ የኤርትራን ምእራባዊ ቆላ የማያጠቃልል የታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክ (ትግራይ ትግሪኝን) ለመመሥረት እየተንደረደረ መሆኑ ግልጽ ነው። ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ሆነች የጡት አባቱ ሲአይኤ ይሄንን ምሥራቅ አፍሪቃን አፈራርሶ ለብዝበዛ እና ቅኝ አዙር አገዛዝ ይበልጥ በሚያመች አዲስ አወቃቀር ለመቅረጽ የሚደረግ መንደፋደፍ ሙሉ ድጋፍ እየለገሱት እንደሆነ እየታየ ነው። ብልጽግናዊው ኦነግም ተስፋፍቶ የመገንጠል ቅዥቱ የሚሟላው የሕወሃትም ቅዥት ሲሳካ መሆኑን በማመን ከሙታን መንደር ትንሣኤ ስጥቶ ለሕወሃት ሁለንተናዊ ድጋፍ በመለገስ ላይ ይገኛል። ኦነግ ተስፋፍቶ የመገንጠል ቅዠቱን ለማሳካት አዲስ አበባን መሰልቀጥ እንደ ሞት ሽረት ክሥተት እንደሚያየው ሁሉ፣ ወያኔም ወልቃይትን መንጠቅን ለግንጠላ ፕሮጄክቷ እንደ ሞት ሽረት ነጥብ ነው የምታየው።
  እነዚህ አማራን አውድመው ኢትዮጵያን (ኤርትራ፣ ኬንያና ሶማሌንም አፈራርሰው) አዳዲስ አገሮች ለማዋለድ የሚቃዡ ሁለት የባእዳን ተላላኪ ቡድኖች የአዲስ አበባና የወልቃይት ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገው ሲታገሉ፣ አማራውም ሆነ የተቀረው ኢትዮጵያዊ እነዚህን ሁለት ማእከላት የሞት ሽረት አድርጎ አጥፊዎቹን መታገል፣ መመከትና መደምሰስ ይኖርበታል። የጥቃት እቅዱ እነዚህን ሁለት ነጥቦች በመሰልቀጥ የሚቆም ሳይሆን ወደ መላው የአማራ ሕዝብ ርስት ወረራና የሕዝቡ አጠቃላይ ውድመት፣ ስደት፣ ነቀላና ፍልሰት የሚሸጋገሩበት በር ስለሆነ በአማራ ሕልውና ላይ የተቃጡ የፍጻሜ ጦርነቶች አድርጎ በመረዳት በሕዝቡ ላይ የተቃጣው ሁለንተናዊ ጄኖሳይድ የማይቀለበስበት ቅርቃር ውስጥ ከመግባቱ በፊት የጉዳዩን ግዝፈት ያገናዘበ ውሳኔና የክተት ጥሪ ከፋኖ ይጠበቃል። በአስቸኳይ።
  ለዚህ ደግሞ በግድ አንድ ማእከላዊ የፋኖ የእዝ ማእከል መኖር የለበትም። ከሁሉም ፋኖ የተውጣጡ የወልቃይትን ክተት የሚመሩ የውጊያው አስተባባሪዎች ሰሜን ጎንደር በሚገኝ ሁነኛ የፋኖ እዝ ሥር ወረራውን ለመመከትና ለመቀልበስ ዘመቻ ለማድረግ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ነው። ሌሎችም የዘመቻ አመራር አማራጮች ይኖራሉ። ባለሙያዎች ይወቁበት። የግድ ግን ቀጠሮ የተያዘለት የወረራና የጦርነት እቅድ የደቀነውን ግዙፍ የሕልውና አደጋ የሚመጥን ክተት በአፋጣኝ ሊጠራና መላ አማራን ያሳተፈ ዘመቻ ሊካሄድ ይገባል። ጉዳዩ የሁሉም አማራ እንደመሆኑ ጋባዥ የሚፈልግ ጉዳይ አይደለም። አይመስለንም።
  በተመሳሳይ የኦነግና የሕወሃት ቅዠት ከኢትዮጵያ ያልተናነሰ የመበተን እድል ይዞላት ለሚመጣው ለኤርትራም የጋራ አደጋውን የሚቀለብስ እንቅስቃሴ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች አስፈላጊው ጥሪ ሊደረግ ይገባል። በዚህ ጉዳይ ኤርትራን ለማጃጃል ምእራባውያን ሰፊ ዘመቻ የከፈቱ መሆኑን ከሰሞነኛው እንቅስቃሲያቸው መረዳት አያዳግትም። አማራን በሐሳዊ እርቅና ድርድር ኤርትራን በኢንቨስትመንት ሕልም ደባብሰው ለማረድ ጥሪት መድበው እየተንቀሳቀሱ ነው። “በሬ ሆይ ሣሩን አይተህ..” የሚለውን ሥልጠና ለአቢይ አህመድ የሰጡት እነማን እንደሆኑ ልብ ይሏል።
  የተቀረውም ኢትዮጵያዊ ይህ ያሁኑ ታሪካዊ ምእራፍ ተላላኪና ባንዳ የሆኑት ሀገር አፍራሾች ወደ ዘመናት ቅዠታቸው በድል የሚሸጋገሩበት ወይም ቅዠታቸው የሚመክንበት፤ ለሀገርና ለወገን ሕልውና ወሳኝ ሰዐት መሆኑን ተገንዝቦ ተግባራዊ አቋም መውሰድ ይገባዋል።
  ዓለሙ

 2. ማስረሻሰጤ በእውቀት በልምድ በትግል ከዘመነ ካሴ የምታንስ አይደለህም በእድሜም አትተናነሱም አንተም አንቱታውን ተወው እሱም እኔ እኔ የሚለውን ያቁም ለናንተም አስፈላጊውን ክብር ይስጥ። መግለጫ ሲሰጥ እኛ ይበል በርቱልን በጸሎትና በምንችለው ድጋፋችን ከናንተ ዘንድ ነው። አምላክ ከለላውን ይስጣችሁ አይዞህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

191586
Previous Story

‹‹ብድር በምድር›› የሱዳን ጦር አፈገፈገ! | በሃይል የሄደው አልፋሽጋ በሚኒሻዎች ተመለሰ?

449094947 3807795739542251 3274854934486005595 n
Next Story

እናትነት !

Go toTop