June 25, 2024
16 mins read

የፀረ ግፍ አገዛዝ ታጋድሎ እና መልካምና ፈታኝ ሁኔታዎች

June 23, 2024
ጠገናው ጎሹ

Abiy 3በአጭር አገላለፅ መልካም ሁኔታ (opportunity)  አንድን  ጉዳይ በአወንታዊነት ወደ ፊት ለማስኬድና ለማሳካት የሚያስችሉ አመች እድሎችን (አጋጣሚዎችን) የሚገልፅ ፅንሰ  ሃሳብ ሲሆን ፈታኝ ሁኔታ (challenge)  ደግሞ በመልካም ሁኔታዎች (አጋጣሚዎች) ላይ  አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ወይም ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን የሚገልፅ ፅንሰ ሃሳብ ነው።

ስለ መልካም ሁኔታዎች ስንነጋር ከፈታኝ ሁኔታዎች ነፃ ስለ መሆን ሳይሆ ተገቢውንና ወቅታዊውን ተሞክሮ በመውሰድ ፣ አስተሰባችንና አካሄዳችን ይበልጥ ምክንያታዊ በማድረግ እና ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰን ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ መልካም ሁኔታነት በመለወጥ የስኬታማነት መንገዶቻችንን ወደ ፈለግነው ግብ እንዲያደርሱን ስለማድረግ ነው የምንነጋገረው ።

ከገዛ ራሳችን የአረዳድና የአያያዝ ድክመት ካልሆነ በስተቀር   ፈታኝ ሁኔታ (challenge) የህይወት ምንነት፣ ለምንነትና እንዴትነት ትርጉም እንዲኖረው የሚያደርግ እንጅ የህይወትን መሽመድመድና መሸነፍ የሚያሳይ አይደለም። ህይወት የሚሽመደመደውና የሚሸነፈው ፈታኝ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተረድቶና ተጠቅሞ ወደ መልካም ሁኔታነት ለመለወጥ የሚያስችል አቋምና ቁመና የሚገድ (የሚጎድል) ከሆነ ነው።

እጅግ አስከፊና  ዘመን ጠገብ የሆነው ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ሰለባዎች በመሆን የዓለም ከንፈር መምጠጫና መሳለቂያ ሆነን የመቀጠላችን ዋነኛው ምክንያት ከዚሁ እጅግ ግዙፍና መሪር ውድቀታችን የሚመነጭ ነው።

አዎ! በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን እኩያን ገዥ ቡድኖች በሥልጣነ መንበር ላይ እየተፈራረቁ የሚዘረጉብንን የመከራና የውርደት መረብ ፅዕኑና ዘላቂ በሆነ የጋራ ጥረት በመበጣጠስ የጉልቹች ሳይሆን የሥርዓት  ለውጥ እውን ለማድረግ ያለመቻላችን ውድቀት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ መልካም አጋጣሚነት ለመለወጥ ያለመቻላችን ብቻ ሳይሆን የተፈጠሩልንን መልካም ሁኔታዎችንም እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የማበላሸታችን እንቆቅልሽ ነው።

ለዚህ አይነት ውድቀታችን እውነትነት መሬት ላይ ከሆነውና እየሆነ ካለው ግዙፍና መሪር የመከራና የውርደት ዶፍ በላይ ማስረጃ የሚያስጠይቅ ጉዳይ አይደለም።  ከስድስት ዓመታት ወዲህ ከሆነውና እየሆነ ካለው ለማመን ቀርቶ ለማሰብም በእጅጉ ከሚከብደው አጠቃላይ ማለትም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሞራላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ እና መንፈሳዊ ውድቀታችን ገና በቅጡ ባለመማራችን አሁንም ግልፅና አበረታች የሆኑ ሁኔታዎችን አበላሽተን (እንዳልነበሩ አድርገን) ማለቂያ የሌለው የመከራና የውርደት ታሪክን ለትውልደ ትውልድ እንዳናወርስ ያሰጋናል።

በዚያን ዘመን በነበረው የአገር ውስጥ ፍፁም ፀረ ተሃድሶ (ፀረ ለውጥ)  የዘውድ አገዛዝ ሥርዓት እና  በሁለት ተፃራሪ  የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ካምፖች ተከፍሎ ሲሻኮት በነበረው የዓለም ፖለቲካ መነሻነት እኢአ 1960ዎቹ አጋማሽ የተከሰተውን የሶሻሊስት አብዮት ምክንያትን፣ ሂደትንና ውጤትን ገንቢነት ባለው ወይም  ከስህተት ለመማር በሚያስችል ይዘት፣ አቀራረብ፣ አቋም እና ቁመና ሳይሆን እጅግ ደምሳሳ በሆነ የዚያ ትውልድ ረጋሚነት/ኮናኝነት/አውጋዥነት ላይ በመጠመዳችን ከ17 ዓመታት የፋሽስታዊው ወታደራዊ አገዛዝ በኋላ በእጅጉ አደገኛ የሆነ  የጎሳ አጥንት ስሌት የፖለቲካ ፕሮግራሙን ህገ መንግሥት አድርጎ ዛሬ ለምንገኝበት 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አስከፊና አሳፋሪ ሁኔታ ለዳረገን የፖለቲካ ቁማር በር ከፈትንለት። እናም ወደ መልካም የለውጥ አቅጣጫና ሂደት ልንለውጠው ይገባን የነበረውን እጅግ ፈታኝ ሁኔታ በጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች (ህወሃትና አሽከሮቹ) ተጠልፎና ተጠርንፎ እጅግ ወደ ባሰ የውድቀት አዙሪት እንዲወርድ አደረግነው።

በጎሳ/በዘር አጥንት ስሌት ፖለቲካ መርዝ የተመረዙ ህወሃቶች-ኢህአዴጎች በ1983 “የድል” አዋጃቸውን ሲያውጁና ከአራት ዓመት በኋላም የሴራ፣ የሸፍጥ ፣ የመለያየት፣ የጥላቻ እና የመጠፋፋት ፖለቲካ ፕሮግራማቸውን በህገ መንግሥትነት ሲያውጁ ሲሆን ከምር አይሆንም የሚል ቢያንስ ግን በፍፁም ጠቅላይነት (ጠርናፊነት) አገርን ምድረ ሲኦል የሚያደርጉበትን አቅም የሚገዳደር የፖለቲካ ሃይል ለመፍጠር አልተቻለንም። ለምን? ቢባል የመልካም እና የፈታኝ ሁኔታዎችን ምንነትና እንዴትነት በአግባቡ ተረድተንና በተግባር ውሎ ላይ ተገኝተን በትክክለኛው ፍኖተ ለውጥ ላይ ተያይዘን በመገስገስ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ለማድረግ የፖለቲካና የሞራል ስንቅ አልነበረንምና ነው።  

መልካም አጋጣሚዎችን እና ፈታኝ ሁኔታዎችን የእኩያን ሥርዓትን እንደ ሥርዓት አስወግዶ በህዝብ፣ ለህዝብና ከህዝብ በሚሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ከመጠቀም ይልቅ የዚያው ሥርዓት ጉልቾች የሚለዋወጡበትን (የሚተካኩበትን)  አውደ ፖለቲካ እንደ ለውጥ እየቆጠርን በግልብ ስሜት የመጋለባችን አስቀያሚና አስፈሪ እኛነት በነፃነትና ፍትህ ትግሉ ላይ ያሳደረው ጎጅ ውጤት ከቶ ቀላል አይደለም።

በሟቹ መለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ ተሸካሚነት ( as a hardware) የመለስን ሌጋሲ ሲያስፈፅም ከቆየ በኋላ የሙት መንፈሱ ሶፍት ዌር (software ) እያረጀ/እያለቀለት መሄዱን ሲያውቅ መንበሩን ለአብይ አህመድ አስረክቦ የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ታሪክ ተሠራ በሚል የእኩያን ገዥዎች አደንቆሮ የመግዛት ሰለባ በሆነው ህዝብ ላይ የተሳለቀውን ሃይለማርያም ደሳለኝን ማስታወስ ይጠቅማል። እርግጥ ነው የእኩያን ገዥ ቡድን ካድሬና ባለሥልጣን ከነበረ ግለሰብ  ከዚህ የተሻለ የፖለቲካና የሞራል ማንነት መጠበቅ አይቻልም።

በእጅጉ የሚያሳዝነው ግን አስከፊ የሆኑ ሁኔታዎች ፈፅሞ ባልተለወጡበት መሪር እውነታ ውስጥ የሃይለማርያም ደሳለኝን በአብይ አሀመድ መተካት እንደ እውነተኛ የመልካም አጋጣሚ (እድል) በመቁጠር እጅግ አሳፋሪ በሆነ የተስፈኝነት አረንቋ ውስጥ የመዘፈቃችን መሪር እውነት ነው።

ህወሃት-ኢህአዴግን እንደ ሥርዓት ሳይሆን ህወሃትን ብቻ  ማስወገድን እንደ የሥርዓት ለውጥ በሚቆጥር ግልብ የህዝብ ስሜት ድጋፍ  የጠቅላይነቱን መንበረ ሥልጣን የወረሰውን አብይ አህመድን ከሰብአዊ ፍጡር በላይ በሚያስመስል ሁኔታ የተቀበልን እለት ነበር የመልካም አጋጣሚዎችን እና የፈታኝ ሁኔታዎችን ትክክለኛ ምንነት፣ ለምንነት እና እንዴትነት ተረድተን ለምንፈልገው ዓላማና ግብ ለማዋል የመቻላችን አቅምና ዝግጁነት  ፈተና ላይ የወደቀው። 

በሩብ ምእተ ዓመቱ የህወሃት- ኢህአዴግ አገዛዝ ወቅት የተፈጠሩ የፖለቲካ ስንጥቆችን (የለውጥ አጋጣሚዎችን) ተጠቅመን ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቀነስ ፣ መልካም ሁኔታዎችን በማብዛትና በማጎልበት እና የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞችን ቀንበር በመስበር የዜጎቿ ሁሉ መብትና ነፃነት የሚከበርባትን ዴሞክራሲያዊት አገር እውን ለማድረግ ያስችሉን የነበሩትን መልካም አጋጣሚዎች ሁሉ ለእኩያን ገዥ ቡድኖች ርካሽ የፖለቲካ ተውኔት አሳልፈን እየሰጠን ነፃነትና ፍትህ ናፋቂዎች የመሆናችን ጉዳይ አስቀያሚ እንቆቅልሽ  ነው።

የብዙ ዓመታት የመከራና የውርደት (አገራዊ ህመም) ዋነኛ ምክንያት የሆነውን የእኩያን ገዥ ቡድኖች ሥርዓተ ፖለቲካ የትኛውንም መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ብቻ ሳይሆን ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ መልካም አጋጣሚነት በመለወጥ መጋፈጥ ሲገባን  መንግሥትን (ገዥ ፓርቲ ተብየውን) “እባክህ መጥፎ ሁኔታዎችን ወደ በጎ ሁኔታዎች ለውጠህ ከመከራና ከውርደት ገላግለን” የሚል ተማፅኖ (ወራዳ ደጅ ጠኝነት) ውስጥ እየተርመጠመጥን ስለ የትኛው የሰብአዊ መብት፣ የነፃነት፣ የፍትህና የሞራል እሴት እንደምናወራ ለመረዳት በእጅጉ ይከብዳል።

ዛሬም እጅግ ኋላ ቀር እና የሴረኛ ገዥ ቡድኖች ሰለባ የሆነው የፖለቲካ ባህላችን ለዘመናት ለመጣንበትና አሁንም በባሰ አኳኋን ተዘፍቀን ለምንገኝበት መሪር ሁኔታ ያለው አስተዋፅኦ እንዳለ ሆኖ አንፃራዊ በሆነ አረዳድና  እይታ የተሻለ የህልውና፣ የነፃነትና  የፍትህ ፋኖነት/አርበኝነት/ጀግንነት/ ተጋድሎ በማካሄድ ላይ ያሉት ወገኖች የመኖራቸውን እውነታ እንኳንስ ለማስተባበል አሳንሶ ለማሳየት መሞከር ፈፅሞ ትክክል አይሆንም።

ከምር የነፃነትና የፍትህ ሥርዓትን እውን መሆን የምንፈልግ ከሆነ ዘመን ጠገብና እጅግ አስከፊ የሆነው ፖለቲካ ወለድ መከራና ወርደት የወለዳቸው ፋኖዎች/አርበኞች/ጀግኖች  ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ መልካም እድልነት በመለወጥ የሁሉም ልጆቿ (ዜጎቿ) መብትና ነፃነት የሚከበርባትን ዴሞክራሲያዊት አገር እውን ለማድረግ የሚያካሂዱትን ተጋድሎና የሚከፍሉትን በቁሳዊ ዋጋ የማይተመን መስዋእትነት ገንቢ በሆነ ሂሳዊ ሃሳብ እና በማነኛውም የትግል አስተዋፅኦ መደገፍና ለግብ ማብቃት የግድ ነው።

አዎ! ከዘመናት ፖለቲካ ወለድ አስከፊ የሆነ የመከራና የውርደት ማንነትና ምንነት ሰብሮ ለመውጣት ያስችሉን የነበሩ መልካም የለውጥ እድሎችን (ሁኔታዎችን) በእኩያን ገዥ ቡድኖች እያስነጠቅን እና እነርሱ (እኩያን ገዥዎች) በሚያዘጋጁልንና በሚያሸክሙን ፈታኝ ሁኔታዎች ሥር አይወድቁ ውድቀት እየወደቅን ወይም የግፍ አሟሟትና የቁም ሞት ሰለባዎች እየሆን የመጣንበትና አሁንም ያለንበት እጅግ አሰቃቂ (painfully tragic)  ሁኔታ ማብቃት ካለበት የአማራ ፋኖዎች/አርበኞች/ጀግኖች እና ሌሎች የነፃነት፣ የእኩልነት፣ የፍትህና የጋራ እድገት አገር ባለቤት መሆንን አጥብቀው የሚሹ ወገኖች ተጋድሎ የዘመናት የክሽፈት ታሪክ አካል እንዳይሆን ብርቱ የጋራ ርብርብ ለነገ የሚባል መሆን የለበትም!!!

አዎ! አሁን ያለንበት ሁኔታ ሸክስፒር እንደሚለው የመሆን ወይም ያለመሆን (to be or not to be) ጥያቄ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop