June 25, 2024
34 mins read

ደርና ጎጃም እልፍ  ጥይት ከሚጮህ፣አዲስ አበባ የሚባርቅ አንድ ጥይት የብልፅግና መንግሥትን ያንቀጠቅጠዋል!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

ይድረስ ለአማራ ፋኖ እዝ፤ጥናታዊ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ዳሰሳ  

የፖለቲካ ዳሰሳ

Koree Nageenyaa

ፋኖ ‹‹እሣት ሲያንቀላፋ፣ ገለባ ጎበኘው!!! እሣት ሲያንቀላፋ፣ ገለባ ጎበኘው!!! ፋኖ ሲያንቀላፋ፣ ገለባ ጎበኘው!!!››   ጎንደርና ጎጃም እልፍ  ጥይት ከሚጮህ፣ አዲስ አበባ የሚባርቅ አንድ ጥይት የብልፅግና መንግሥትን ይነቀንቀዋል! ኮሬ ነጌኛን ያንቀጠቅጠዋል! ያስነጥሰዋል!!! የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የአዲስ አበባን ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት (Human Shields) ይዘዋልና!!! የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ለፋኖ ሜዳውን በአማራ ክልል ውስጥ ብቻ እንዲጫወት ፈቅዶልና!!! ትህነግ ከትግራይ ገስግሶ የአማራ ግዛት አቆርጦ፣ መቐለ፣ ፣ራያ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋ ሮቢት፣ደብረሲና፣ ደብረድርሃን ብሎም አዲስአበባ ለመያዝ በትረ-ስልጣኑን ለመጨበጥ የህወሓት ዋና የፖለቲካ ኢላማ ነበር፡፡ ፋኖም የአራት ኪሎ ጭራቆች መንግሥት የአዋጅ መፈልፈያ ፋብሪካ ፓርላማን በመቆለፍ ስልጣኑን መቆጣጠር አለበት፡፡ ፋኖ በተካነው የጦርነት ስትራቴጂና ታክቲክ የኦህዴድ ብልጽግና የአራት ኪሎ መንግሥትን አከርካሬ መስበር ታሪካዊ ግዴታው ነው፡፡

የማህበራዊ ጉዳይ ዳሰሳ

በመላ-ኢትዮጵያ የሚገኙ ነባር የብዙኃን ድርጅቶች (Mass Organaizations) የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር፣ የመምህራን ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች ማህበር፣ የገበሬዎች፣የሴቶች ማህበራት በሙሉ በደርግ ዘመን ጀምሮ፣ በመለስና ኮነሬል አብይ አንባገነኖች የግፍ አገዛዝ ስር ፈርሰዋል፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሰባ ሽህ የኢትዮጵያ መምህራን አባላት ይገኛሉ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር አርባ አራት ሽህ ደርሶል፣ የባንክ ሠራተኞች ቁጥር ስልሳ ሽህ ደርሶል፣ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ዞን ስልሳ ሽህ ሠራተኞች  አሉት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁለት መቶ ኃምሳ ሽህ ወታደሮች አሉት፣ ኢትዮቴሌ አርባ ሽህ ሠራተኞች አሉት፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ስልሳ ሁለት ሽህ ሠራተኞች አሎቸው (Apr 21, 2021 — The Ethiopian garment sector employs some 62,000 workers*, of whom over 60 per cent are women.) የታክሲ ማህበራት አስራአምስት ሽህ ሹፌሮች አባላት ቢኖሩም በማህበር ተደራጁተው መብቶቻቸውን እንዳያስከብሩ ተደርገዋል፡፡ በማህበር ተደራጅቶ መታገል የመሰብሰብ፣ የሠላማዊ ሠልፍ፣ የሥራ ማቆም አድማ ወዘተ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት አንባገነናዊ አገዛዝ ዘበት ሆኖል፣ ታዲያ እንዴት የአዲስአበባ ህዝብ  ተደራጅቶ ሊታገል ይችላል? ሃምሳ አራት ጋዜጠኞች በተሰደዱበትና ቀሪዎቹም በታሰሩበት አገር፣ አስር ሽህ የአማራ ምሁራኖች በእስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 107260 (መቶ ሰባት ሽህ ሁለት መቶ ስልሳ) እስረኞች በአዲስ አበባ ወህኒ ቤቶች፣ ሸዋ ሮቢት፣ድሬዳዋ፣ ዝዋይ፣ አዋሽ አርባ፣ ጦላይ   ወዘተ እንደሚገኙ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ገልፆል፡፡

 

የአዲስ አበባ ህዝብ መዓት ወርዶበታል፣ በመርካቶ አሜሪካ ጊቢ፣ ሱማሌ ተራ መንደሮች ፈርሰዋል፣ በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት፣ እሪ በከንቱ ሰፈሮች ቤቶች ወድመዋል፣ በፒያሳ ውቤ በርሃ፣ሠራተኛ ሠፈር፣ ድሮ (ዶሮ) ማነቂያ ሠፈሮችና ቤቶች ፈራርሰዋል፣ አረ ስንቱ! ስድስ ኪሎ፣ ካዛንችስ፣ አቦሬ፣ ሾላ፣ ልደታ፣ ቄራ፣ ለጋሃር፣ ሳር ቤት፣ ወዘተ መንደሮችና ቤቶች ፈርሰዋል፡፡ የመዲናዋ ንዋሪዎች ማህበራዊ ግንኙነቶች ድርና ማግ የነበሩት እድሮች፣ እቁብ፣ የጽዋ ማህበራቶች፣ ሁሉ ፈራርሰዋል፡፡ ታዲያ እንዴት የአዲስ አበባ ህዝብ ተደራጅቶ በማመፅ ቤተ-መንግሥቱን ሊቆጣጠር ይችላል? ኮረኔል አብይ ብልጽግና መንግሥት አዲስ አበባን እያፈራረሰው ነው፣ የልማት ጉዳይ ሳይሆን የስነ-ህዝብ (ዴሞግራፊ) ለውጥ ለማምጣት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ልማት ህዝብን ያላሳተፈ ልማት ነው፡፡ የወንዝ ልማት ፕሮጀክት፣ የፓርኮች ፕሮጀክቶች፣ የከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፣ የጫካ ፕሮጀክት (የኮነሬል አብይ ቤተ-መንግሥት)፣ የኦህዴድ ፕሮጀክት (የሽመልስ አብዲሳ ቤተ-መንግሥት) ልማት ሁሉ ሰው ሰው ያልሸተተ፣ ሚሊዮኖቹን ንዋሪዎች ያፈናቀለ ጉዑዝ ልማት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ልማት  የኮንክሪት ጫካ ወይም የህንፃ  ጫካ ጥፋት ነው፡፡ በአዲስ አበባ በቅርስ የተመዘገበ ታሪካዊ ስፍራ የማፍረስ ፕሮጀክት  አካል ነው፡፡  ለቀጣዩ ምርጫ ኦህዴድ ብልጽግና እንዲያሸንፍ የአማራ ህዝብን የማፈናቀልና የማሳደድ  ፕሮጀክቶች አካል ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ፃረ-ሞት ካንጃበበበት ድፍን ስድስት አመታት ተቆጠረ፣ አሳሩ አላልቅ አለ፣ ታዲያ እንዴት አድርጎ በየቦታው የተፈናቀለው ህዝብ ተደራጅቶ ይታገል ይባላል፡፡ የአማራ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ መግባትም መውጣትም በእነሱ ፍቃድ ሆኖልና!!! ህዝብ በአዲስ አበባ መንገዶች ደብረብርሃን መንገድ፣ ባህር ዳር መንገድ፣ አዳማ መንገድ ጅማ መንገድ፣ አምቦ መንገድ ተዘወሪ መኪና እንዳሻው የመዘዋወር መብቱን ተነጠቀ፡፡ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት የእነዐቢይን የኦሮሙማ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ለመጣል ለአዲስአበቤው የክተት ጥሪ በማቅረብ አዲስአበቤው የእራሱን አሻራ እንዲያኖር ተፈርዶበታል፡፡ አዲስ አበቤ የኦህዴድ ብልጽግና አንባገነኖች ‹‹እየመጡ ነው!!! እየመጡ ነው!!!›› እያለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሥርዓቱን ታግሎል፡፡ ለአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ደማቸው ለፈሰሰው ለሠማዕታቱ ናሁ ሠናይና ጎደኞቹ መታሰቢያ ትሁን፣ ከድል በኃላም ታሪካችሁ በኮነሬል አብይ መቃብር ላይ ህያው ኃውልታችሁ ይታነፃል፡፡

ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር የግንባታ ወጪና  በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ የሸገር ከተማ ለመመሥረት የሚወጣ  ሌላ ትሪሊዮን ብር በአስቸኳይ እንዲቆም በማስደረግ ለሚሊዮን ተፈናቃዬች ህይወትን መታደግ፣ በትግራይ በአማራና አፋር ክልሎች የወደሙ መሠረተ-ልማቶች በተለይ የጤና፣ የትምህርት፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ አገልግሎቶች ቅድሚያ እንዲሠጣቸው ማድረግና በህዝቡ ላይ የደረሰውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥታዊ ድጎማዎች ማድረግ፣ ግብርና ታክስ መቀነስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ማፍረስ ማስቆም አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎች የአማራ ፋኖ ማስቆም ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት፡፡

 

የኢኮኖሚ ዳሰሳ፡-

ኮረኔል አብይ ብልጽግና መንግሥት አዲስ አበባን እያፈራረሰው ነው፣ የልማት ጉዳይ ሳይሆን የስነ-ህዝብ (ዴሞግራፊ) ለውጥ ለማምጣትና አማራን በኢኮኖሚ ዘርፎች ማደህየትና ከአዲስ አበባ ከተማ መንቀል የመሬት ዘረፋ (Land Grabbing) የኦሮሙማ ዘረኛ አገዛዝ  የመሬት ኬኛ ፕሮጀክት ነው፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን ፓርኮች፣ የጫካው ፕሮጀክት፣ አድዋ ዚሮዚሮ፣ የአቧሬ ፕሮጀክት፣ የወንጪ ዳንዲ፣ ሃላላ ኬላ፣ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ጮርጮራ ወዘተ ፕሮጀክቶችን  ያለ አንዳች ጫረታ የሚያሠራው ለኦህዴድ ብልጽግና በኃይሞኖት እሚያውቃቸው ጎደኞቹ መሆኑና ግልፅነት የሌለው፣ የዘር ጎደኝነት ላይ የተመሠረተ ስራ ሲሆን በአጠቃላይ መልካም አስተዳደር የሌለውና አድሎና ሙስና የኦህዴድ ብልፅግና መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ የተንሠራፋ የሥርዓቱ መገለጫ ሆኖል፡፡ ይህን በመሳረጃ ለማሳየት በቴሌቨዝን በሬዲዩ፣ በጋዜጦች ላይ የፕሮጀክቶቹ ሥራ አንድ ቀንም ጨረታ ወጥቶ እንደማያውቅ ይታወቃል፡፡

 

{1} ሸገር ከተማ ፕሮጀክት፡- የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ህዝብን ሳያማክር በኦክቶበር 2022 እኤአ የሸገር ከተማ መሠረተ አዲስ የከተማ ማዕከል ስትሆን የአዲስ አበባን ዙሪያ ገባ ተከትላ የተዋቀረች ከተማ ናት፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር  ስፍት አላት፡፡ Covering  an area of over 1,600 square kilometers, Sheger City encompasses six Oromia towns.የሸገር ከተማ በስድስት ክፍለ ከተሞች የተመሠረተች ስትሆን እነሱም ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ያካትታሉ፡፡ የሸገር ከተማ አዲስ አበባን ዙሪያዎን ከበዋታል፡፡

የሸገር ከተማ ምሥረታ የተረጋገጠው ከኦግስት 2022 አኤአ በኃላ የአዲስ አበባ ከተማና በፍንፍኔ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን በተካለለ ጊዜ ነበር፡፡   ወሰኑ ግልጽ ባለመሆኑ ምክንያት ግጭትና አለመረጋጋት አስከትሎ ነበር፡፡ የኮነሬል አብይ የኦሮሙማ የእጅ አዙር አገዛዝ፣  የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ተቆርሷ የተሠጠ የሸገር ከተማ 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ወይም 1600 000 000 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን) ካሬ ሜትር ቦታ  ህገ-መንግሥቱን በጣሰ መንገድ ተዘርፎል፣ ህዝብ ያላማከረና 600000 (ስድስት መቶ ሽህ) ሰዎችን በግፍ ያፈናቀለ የኦሮሙማ አገዛዝ ያለአንዳች ማስተር ፕላን ጥናት በኦህዴድ ብልጽግና ዘረኛና ተረኛ የኦሮሙማ ሥርዓት የከተማ ህዝብ ንቅለ ተከላ የተከናወነበት ዘመን ነው፡፡ ማንነት ተኮር በአማራነታቸው ምክንያት የተፈላቀሉ ነበሩ፣ ከኦሮሞ ገበሬዎች በማፈናቀሉ የተነሳ ኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ ተቃውሞ ገጥሞቸው ነበር፡፡ ኦሮሞ ያልሆኑ ንዋሪዎችም  በተለይ አማራዎች የኦሮሞ አስተዳደር ድብቅ አጀንዳ የአዲስ አበባን ከተማ ወደ ኦሮሚያ ለማካተትና ለመሰልቀጥ የተወጠነ መሆኑን በሸገር ከተማ ምስረታ ማግስት ህገወጥ ተብለው የፈረሱት የአማራ ቤቶች በመሆናቸው ተቃውሟቸውን  አሰምተው ነበር፡፡

ሸገር ከተማ ፕሮጀክት፡- የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማን ከአዲስ አበባ መንገዶች ጋር ለማስተሳሰርና ለማሳለጥ 150 ኪሎ ሜትር  የመንገዶች ግንባታ  4.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦ ተጀምሮል፡፡ የክልሉ ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የመንገድና ሎጂስቲክ ኃላፊ ሄለን ታምሩ እንዲሁም የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሸመ አዱኛ ሥራውን አስጀምረዋል፡፡ “Oromia Regional State has luunched 150 km mega road project, the first in its kind in Ethiopia, in kura Jida sub city of Sheger city.The road project to be completed within 5 years is said to connect all sub cities in Sheger city. The first phase of the road project which starts from Kura Jida will be constructed with 4.5 billion birr> and this project create a highway network between Taffo,Koye Feche and Gelan sub cities of sheger city, oromia regional state.”………………………………..……….(1)

 

{2} የ2016/17 ዓ/ም የአማራ በጀት ፡-የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የ2016 ዓ/ም በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት የአማራ ክልል በበጀቱ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ኮነሬል አብይ የሸገር ከተማን፣ ፓርኮች፣ የጫካው ፕሮጀክት (ቤተመንግሥቱን)፣አድዋ ዚሮዚሮ፣ የአቧሬ ፕሮጀክት፣ የወንጪ ዳንዲ፣ ሃላላ ኬላ፣ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ ጮርጮራ ወዘተ ፕሮጀክቶችን በአማራ ህዝብ ኪሳራ ግንብቶበታል፡፡ የአማራ ፋኖ በፍጥነት ይሄን የበጀት ማእቀብ በጦርነት አሸንፎ የሥርዓት ለውጥ ካላደረገ የሚቀጥለው የ2017 ዓ/ም በጀትም ከአማራ ህዝብ ተነጥቆ ለኦሮሙማ ፕሮጀክቶች መዋሉ እሙን ስለሆነ የኦሮሙማን ፕሮጀክቶቸ እየተከታተሉ ማውደም አማራጭ የሌለው የመደራደሪያ መንገድ ነው፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ የሚያራምደው የኦሮሙማ ፕሮጀክቶች አሻራ ሆነው እንዲቀጥሉ በማድረግ የአማራውን ታሪካዊ ቅርስና አሻራ በማውደም ላይ እንደሆነ አለመረዳት የኢኮኖሚ እድገት መዛባት፣ ያልተስተካከለ የምጣኔ ኃብት ክፍፍል ሰፍኖ እንደ ህወሓት የልመና አቆማዳ በመዘርጋት የኩሩውን ትግራይን ህዝብ ስብእና አዋርደዋል ከወያኔ እንማር፡፡ ኮነሬል አብይ መቐለን በሻሻ አድርገናታል   እንዳለ ሁሉ ባህርዳርን በሻሻ አድርገናታል እንዳይለን፣ የፋኖ አማራ እዝ መስርቶ   አራት ኪሎን ተቆጣጥሮ የሽግግር መንግሥት መስርቶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመጨረሻ ግባችን ሊሆን ይገባል እንላለን፡፡ የፋኖ አማራ እዝ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ጸንቶ፣ ለዴሞክራሲያዊ መብቶችና ስብዓዊ መብቶች መከበር ዋስትና አፅንቶ፣ በምርጫ ህዝባዊ መንግሥት የሚመረጥበትን ሃቀኛ ፌዴራላዊ ሥርዓት  ማዋቀርይጠበቅበታል፡፡

{3} የአዲስ አበባ ከተማ መንደሮችና ቤቶች ፈረሳ ፕሮጀክት፡- መላው የአዲስ አበባ ህዝብ፣ በዘመናት ሂደት ከገነባው መኖሪያ እና የንግድ ቤት በግፍ በኮነሬል አብየ ትእዛዝ ተፈናቅሎል፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከፈረሰው መንደሮችና ቤቶች መሬት ሽያጭ 99 (ዘጠና ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የመሬት ሽያጩ ሰባ ሽህ ብር በካሬ ሜትር ተሰልቶ ነው፡፡ለኦህዴድ ብልፅግና ጡት አባት ቱጃር ቢሊየነሮች ህንጻ ለመገንባት የባንክ ብድር ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ደሃው ህብረተሰብ የገዛ መሬቱን ተነጥቆ በየቀበሌው መጋዝኖች ውስጥ ከነቤተሰቡ ተጠልሎ የክረምቱን ዝናብና ብርድ ማሳለፍ ግዴታው ሆኖል፡፡

‹‹ ሁሉም ባንኮች ካበደሩት 1.9 ትሪሊዮን ብር 23.5 በመቶው ለአሥር ተበዳሪዎች ለእየአንዳዳቸው 446 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር  መሰጠቱ ታውቋል፡፡ ጥቂት ተበዳሪዎች ከበርካታ ባንኮች ተደጋጋሚ ብድሮችን የሚወስዱ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊዎች ሲገልጹ ነበር፡፡ ከባንኩ የሚወጡ ሪፖርቶችም ይህን የሚያሳዩ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ አሁን እየከለሳቸው ባሉት ሕጎች አማካይነት ይህን ድርጊት ለማስቆም እያሰበ እንደሆነ ሪፖርተር ከባንኩ ከፍተኛ ኃላፊ አረጋግጧል።  የባንኩ ተበዳሪዎች ከ18 ባንኮች ጋር በአንድ ጊዜ እየሠሩ የሚያንቀሳቅሱት የንግድ ሥራ ቢበላሽ ብድር የሰጧቸውን ሁሉንም ባንኮች በአንድ ጊዜ ችግር ውስጥ ሲከቱ በተደጋጋሚ ታይቷል። አስር ቢሊየነሮች ከፍተኛ ተበዳሪዎች ሲሆኑ በባንክ የፋይናንስ ዘርፍ የባንኮችን ኃብት እየተጠቀሙበት ያሉት በጣት የሚቆጠሩ አስር ባለኃብቶች መሆናቸው ታውቆል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) ላይ እንደተጠቀሰው፣ የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው ይገኛሉ።›› ………………………(2)

{4} የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ፡- የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መንግሥት የዜጎችን ንብረት የመውረስ አዋጅ ረቂቅ ህግ በቀርብ ጊዜ ያፀድቃል፡፡ በዚህም የአማራ ባለኃብቶችንና የዲያስፖራ ወገኖችን ንብረትና ኃብት በመውረስ ሊያካሂደው የአማራ ክልል ጦርነት መሳሪያና ጥይት መግዣ ብዙ ቢሊዮን ብሮችና ዶላሮች ማግኘት ይቻላዋል፡፡ የዚህ ሰለባ የሚሆኑት ውስጥ የሼክ አላሙዲን ሜድሮክ ኢትዮጵያ ንብረት ኮነሬል አብይ ዶላር ተጠይቀው   ባለመስጠታቸው፣ እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ሥራ አስኪያጅ ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ጉቦ ተጠይቀው ባለመስጠታቸው የባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ከአገር እንዲኮበልሉ አድርገዋል፡፡ ኮነሬል አብይ ከዓለም የገንዘብ ድርጅትና ዓለም ባንክ የጠየቀውን የሰባት ቢሊዮን ዶላር ብድር ማግኘት ስላልቻለ የጦርነት ኢኮኖሚውን ማስቀጠል አልቻለም፡፡ ለዚህ ነው የመሬት ነቀላና ተከላ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ደሃውን ወገን መሬት እየነጠቁ፣ ለኃብታም መሬቱን በ99 ቢሊዮን ብር የመሸጥ እቅድ የነደፉት፡፡ በንብረት ማሰመለሰና መውረስ ፕሮጀክት ንብረታቸውን የሚያጡ ብዙ ሽህ የአዲስ አበባ  ዜጎች ብዙ ቢሊዮን ብር እንደሚዘርፉበት ይገመታል፡፡ ይህንን ማስቆም የሚችል ብቸኛ ኃይል የአማራ ፋኖ መሆኑን ሁሉም ዜጋ ያምናል፡፡ ኮነሬል አብይ እድሜ ከሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ የዘረፋ ፕሮጀክት ሲያጠናቅቅ ወደ መቀሌ፣ ሃዋሳ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ወዘተ ከተሞች ይቀጥላል፡፡

የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መስፋፋት አባዜ፡- የኦህዴድ ብልፅግና በሁሉም ክልሎች ድንበር በኩል የድንበር ግጪት ከሱማሌ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ህዝቦች፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዎ ወዘተ ህዝብ ጋር ጦርነት በመጫር ላይ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ምሁራን ይሄንን የግዛት የመስፋፋት ጥያቄ የአስራስድስተኛውና የአስራሰበተኛው ክፍለ ዘመን ጥያቄ መሆኑን በማጤን ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት አታብዙበት እንላለን፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በሠላምና በህብረት እንዲኖር ማድረግ የስልጣኔ መንገድ በመሆኑ መምከር ይጠበቅባችሆል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ አንደበት ‹‹ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት አዲስ አበባ ይገባል፡፡ ኦነሠ አዲስ አበባን ከመቶ ኪሎ ሜትር ራድየስ ርቀት ላይ ኮነሬል አብይ ህልውናውን ማስጠበቅ አልቻለም፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍንፊኔ ሠላሳና አርባ ኪሎሜትር  ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአራት ኪሎው የአብይ ቤተ-መንግሥት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የመድፍ ላንቃዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በቅርብም አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ›› ብለዋል፡፡……………………………(3)

የአዲስ አበባ ህዝብ በስባዓዊ ጋሻነት (Human Shields) ተይዞል፡- በአንድ በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ አስተዳደር የሸገር ከተማ  ህዝብን ሳያማክር መሠረተ፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር  ስፍት ሲኖራት በውስጦም ስድስት ክፍለ ከተሞች ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ይካተታሉ፡፡ ከእላይ በስዕሉ እንደሚታየው የሸገር ከተማ አዲስ አበባን እንደ ስብዓዊ ጋሻነት ዙሪያዎን ከበዋታል፡፡ ኦህዴድ ብልጽግና አንዴ ውኃ እቆርጣለሁ፣ አንዴ ከርስና ፈርስ፣ አንዴ በሰበሩብን ቦታ ሠበርናቸው ወዘተ እያሉ የአዲስ አባባን ህዝብ ያስፈራራሉ፡፡  በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ህዝብ  ኦሮሞ መጣልህ እያሉ አንዴ ኮነሬል አብይ ከሱሉልታ፣ከለገዳዲ የኦሮሞ ፈረሰኞች መንግሥታችን ተነካ ብለው ሊያስነኩት ሲሉ ይለናል፣ አንዴ አዳነች አቤቤ ቤቶች ስታፈርስና ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ስታፈናቅል፣ አንዴ ሽመልስ አብዲሳ የሸገር ከተማ ኬኛ፣ የጫካ ፕሮጀክት ቤተ-መንግሥት ኬኛ እያለ ህዝቡን በስባዓዊ ጋሻነት አግተውታል፡፡  የአዲስ አበባ ህዝብ በስባዓዊ ጋሻነት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ከተያዘ እጣ ፈንታው ምን ይሆናል፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ አዲስ አበባ በፋኖ የአማራ ሠራዊት ከምትያዝ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብትያዝ የኦሮሞ መንግሥት ይቀጥላል የሚል ጽኑ እምነት እንዳለው ይታወቃል፡፡ የፋኖ የአማራ ሠራዊት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገው ግሰጋሴና  የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወደ ፊንፌኔ ከተማ ግስጋሴ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥትን ለመጣል ከሆነ በጋራ ፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ መወያየት ከወዲሁ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ በሁለቱ ቡድን ጦርነቱን ማስቀረት የሚቻለውና በኮነሬል አብይ መንግሥት ላይ የጋራ ግንባር ፈጥሮ መዋጋት የአብይን መንግሥት ይቀጨዋል፡፡  ፋኖ የአማራ ሠራዊት የትግል የድጋፍ ጥሪ ማስተላለፍ ለሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ደብብ ክልል፣ ሲዳማ፣ ቤኒሻንጉል፣ ትግራይ፣ ሃረሪ፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንኑነቱን ማጥበቅ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

{5} የባንክ አገልግሎት ማቆረጥ፡- በአማራ ክልል የሚገኙ ባንኮች በመዝጋት የህብረተሰቡን የባንክ አገልግሎቶች የንግድ፣ የስራ፣ የደሞዝ፣ የገንዘብ ዝውውር በማገድ ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን  ማድረግ እቅድ ተተግብሮል፡፡ የኦህዴድ/ብልፅግናው መንግሥት በአማራ ክልላዊ አስተዳደር የሚገኙ የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንተርኔት አገልግሎት በመዝጋት፣ የመብራት የውኃ አገልግሎት በማቆረጥ፣ የትምህርት ቤቶችን፣ ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት በመዝጋትና ለፈተና እንዳይቀርቡ በማድረግ፣ የጤና አገልግሎቶችን እንዳይሰሩ በማድረግ የአማራን ህዝብ አደህይቶና አስርቦ ለመግዛት የቶርነት ፕሮጀክት ነድፎል፡፡

የኦሮሙማ ‹‹ኮሬ ነጌኛ›› በኦሮሞ ህዝብ ላይ በፀጥታና ደህንነት ኮሚቴ ሽፋን የተቌቌመው የገዳዬች ቡድን ዶክተር አብይ አህመድ ሥልጣን እንደያዘ የተደራጀ ስውር ቡድን ሲሆን ከዋና መሥራቾቹ  ውስጥ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት፤ ፍቃዱ ተሰማ፣የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዜዳንት፤ አወሉ አብዲ፣የኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ አራርሳ መርዳሳ፣ የኦሮሚያ ሠላምና ደህንነት ኃላፊ ስውር ቡድን የተዋቀረ ቡድን ነው፡፡ የሮይተርስ የምርመራ ቡድን ጥናት መሠረት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመፅ እንዳይነሳ በህቡዕ የሚንቀሳቀሰው ገዳይ ቡድን ህገወጥ ግድያና እስራት  በመፈፀም የኢትዮጵያ ህዝብ በፍርሃትና በስጋት ውስጥ እንዲኖርና ማድረግ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን የስብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ግድያና አስገድዶ መሰወር ወንጀሎች በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal court) ኮነሬል አብይ ከነገዳዬቻቸው መቅረብ የአማራ ፋኖ የትግል ውጤት ነው እንላለን፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop