June 10, 2024
31 mins read

ፍኖተ እንጦሮጦስ -የብልጽግናው ፖለቲካ ድርድር፣

Abiy Ahmeds self dialogue committee 1

Abiy Ahmeds self dialogue committeeለኢኒን (Matrix)

ዲ/ን(?) ዳንኤል ክብረት በቅርብ ግዜ፣ በመፈናቀል በጦርነትም ሆነ በርሃብ ስለሚያልቀው ኢትዮጵያዊ አንድ ሰታትስቲክስ ነገር ሊያቀርብ ሞከረና ገረመኝ፡፡ እንደ ቀመራዊ ጥናቱ፣ እሱ እነደሚለው በጦርነት፣ መፈናቀልና ረሃብ  የሚያለቀው ኢትዮጵያዊ አስር ሚሊዮን ሆኗል ብንል እንኴን ሌላውን አንድ መቶ አስር ሚሊዮኑን እኛ አያኖረነው ነው አይነት ነገር ተናገረ፡፡

ይህ የሚያለቀው ህዝብ ብልጽግና በሚከተለው ፖለቲካ ዘይቤ፣ ግጭት ጥንሰሳና ጦረነት መሆኑን ልብ ይበሉ፣ እሱ ግን ሁን ብሎ ምክነያቱን ዘሎ አልፎታል፡፡ እንግዲህ ሂትለር፣ ጆሴፍ ስታሊንና ማኦ ዜዱንግ ሁሉም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደሉ ታሪክ በእኩየነታቸው መዝግቦ የያዛቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ስታሊን በግዜው ከነበረው 170 ሚሊዮን የሚቆጠር የተባበሩት የሶቬየት ህብረት ህዝቦች ከስድስት አስከ ዘጠኝ ሚሊዮን ህዝብ ነው የፈጀው፡፡ ሂትለርም በአማካኝ ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ገድሏል ይባላል፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ስድስት ሚሊዮኑ አይሁዶች ናቸው፡፡  በግዜ የነበረውን የአውሮፓ ህዝብ ቁጥር ወደ አምስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን የሚቆጠር ነበር፡፡

እንግዲህ በህዝብ ቁጥር ሬሾ ሲለካ ዲ/ን(?) ዳንኤል ክብረት በቀመሩ ከህዝባችን 8.33% ሲፈጅ፣ ሂትለር 3.58% አውሮፓውያንን ገድሏል፡፡ እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር የተበተኑትን በመላ አውሮፓ የነበሩትን አይሁዶችን  ተንከሲስ ህዝቦች ናቸው ብሎ ሰይሞ በትንሹ ቁጥራቸው ላይ ሙሉ ጥፋት ለማድረግ ነው የሞከረው፡፡

ሰታሊን ደግሞ ከሶቪየት ህብረት ህዝብ 4.41% ገድሏል ማለት ነው፡፡ ይኸውላችሁ እንግዲህ የዳንኤል ክብረት ስሌት ከሂተለርም ከሰታሊንም ያላቀ ሆኗል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ የኢትዮጵያን ህዝብ ስምንት በመቶ ያክሉን በጦርነትና ረሃብ ፈጅቶ የሚረጋገጥ ብልጽግና ይታያችሁ? ደግሞ ከግፉአኑ አብዛኛው መከረኛው አማራ ነው፡፡ ትግሬውንም፣ ኦሮሞውንም…ሌሎቹንም አልማረም ብልጽግና፣ መልከ ጥፉ በስም ይደግፌ አይደል የሚለው ተረቱ፡፡ይህ ቡድን ምን እያደረገ ነው ብለን ከጠየቅን መልሱ፣ ለጢልማቆሱ ጌታው የደም ግብር እያቀረበ ነው፡፡

ሂትለር እኛ ትልቅ ዘሮች ነን ብሎ በደም ጥራት ላይ በተመረኮዘ ዘረኝነት አይሁዶችና አውሮፓውያንን ፈጀ፡፡ ጆሴፍ ሰታሊን ደግሞ የአባት ሃገር ጠላትና ሰላዮች ያላቸውን የሶቬየት ህብረት ህዝቦችን ጨረሰ፡፡ ማኦ ዜድግ ደግሞ በባህል አብዮት ስም በግሬት ሊፕ ፎርዋርድ መርሆ የገዛ ህዝቡን ገደለ፡፡

ብልጽግናም ኦሮሙማ በተባለ ሁሉንም ጠቅልዬ የራሴ ቅጂ አድረጋለሁ በሚል ርዕዮተ አለም “በልዋጥህ ተደበልበል” መርሆ አፍሪካዊ ናዚዝምን ለመገንባት በሚያደረገው ሂደት ብዙዎች ተፈናቅለዋል፣ የዘር ፍጅት ተፈጽሟባቸዋል፡፡ እንደ ስታሊን ደግሞ ብልጽግና ሃገር አዳኝ ሌላውን የታሪካዊ ጠላቶቻችን ሰላይና ተላላኪ አድርጎ በመፈረጅ ህዝብን ያሳድዳል፣ ይገድላል…ምኑቅጡ፡፡ በሃገሬ ላይ መኖር አልቻልኩም ያለውን ሰው ሁሉ የወደፊቱን ምንጡቅ እድገት አደናቃፊ  እያለ እንደ ማኦ ዜዱንግ ቤት አልባ ያደርጋል፣ ዜጎችንም ህጋዊ ደሃ ያደርጋል ( የሸገር ከንቲባ ንግግርን ያስታውሱ)፡፡

እንግዲህ ብልጽግና ማለት ከሚሞቱ ዜጎች ይልቅ ስለ ለአስከሬን ዛፍ ጥላ መትከል የሚጨነቅ፣ የሃገሪቱን ሰሜናዊ ህዝቦች ለይቶ የሚመታ፣ እነሱን አጥፍቶ በመቃብራቸው ላይ  የአክሱም ሃውልት አፍርሶ  ከሌቻ መትከል የሚፈልገ፣ ብዝሃነትን እቀበላለሁ ቢልም አሃዳዊ የሆነና ቀይ ባህር ላይ እንኴን ኢሬቻን ካለከበርኩ የሚል ጨፍላቂ ሃይል ነው፡፡

እንደ ናዚው ፕሮፓጋንዳ ኃላፊ ጆሴፍ ጎበል የብልጸግናና የጠ/ሚ አብይ አህመድ ቱልቱላ ነፊ የሆነው ዳንኤል ክብረት አስር ሚሊዮን ህዝብን አጥፍቶ መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብን ማስተዳደር የሚል ጽሑፍ የትኛው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፎ እንዳነበባ አናውቅም፡፡ መቼም ይህን የተናገረው አለቃው ጠ/ሚ  አብይን ለማስደሰት ይመስላል፡፡ ያለበለዚያማ እነ ለማን ያልማረች የአብይ ጨንገር ትዘገያለች እንጂ እሱ ጋር መድረሷ አይቀርምና፡፡ በትግሬዎቹ ዘመን ከእናንተ ጋር ነኝ እያለ  “ፍርሃት አዶ ከበሬ” ሲጨፍር የነበረው ዳንኤል ዛሬም ከብልጽጋና ጋር ይወዛወዛል፡፡

ለብልጽግና አሽከርነት ለገቡና የልገባቸውንና የማያውቁትን አላማ ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ሰዎችን ሳስብ  አንድ ቀልድ ትዝ ይለኛል፡፡ አንድ ግዜ አንድ ደግ ሰው በጎጥ በተነሳ ግጭት በግርግር መሃል ተገኝቶ ይሞታል፡፡ ሰውዬው ደግና ቅን ሰለነበር እግዚአብሔር ገነትንም ሲኦልንም ጎብኝተህ ናና ከዚያ በገነት ታርፋለህ ይለዋል፡፡ ሰውዬውም እንደተነገረው ሲኦልን ሊጎበኝ ይሄዳል፡፡

በዚያም እምድር ላይ ሳለ ሰዎችን በየጎጡ እያደራጀ ሲያጋድል የነበረ ሰው ሲኦል መሃል ላይ በለው በርገንዴማው የውሃ ኩሬ ውስጥ ሦስት እርቃናቸውን የሆኑ ሴቶች ታቅፎና በእጁ ውስኪ ይዞ ያየዋል፡፡ ይሄኔ ደጉ ሰው ወደ እሚያሰጎበኘው መልአክ ዞሮ ይህ ሰው እምድር ላይም እያለ ሰው ከማጋደል ውጭ ይኸው ነበር ሱሱ፣ ሴትና መጠጥ የሙሉ ግዜው ስራው ነበሩ ፡፡ አሁንም እዚህ መጥቶ እንደልቡ ይሆናል አለው፡፡ መልአኩ ይህን ግዜ ለደጉ ሰው መልሶ እንዲህ አለው፡፡እዚያ በእጁ ይዞት የምታየው ጠርሙስ ከታች ቀዳዳ አለው፣ ሴቶቹ ግን ድፍን ናቸው፤ ዘላለሙን እንዲሁ እንደ ቃተተ ይኖራል፡፡

ዛሬ ፍትህና እኩልነት ለዜጋ የሚል ሁሉ፣ አህዳውያን በሚል የልጣፎ ስም  ለጥቃት ተላልፎ ይሰጣል፣ ይገደላልም፡፡ ግራም ነፈሰም ቀኝም ነፈሰ ስለምትናገረው ቋንቋ ትገደላለህ፡፡ እንደራጅ ስትል ደግሞ ጽንፈኛ ብለው ለግድያ ያዘጋጁሀል፡፡ እነሱ ግን (እንደ ዲ/ን(?) ዳንኤል ክብረት ያሉት ጠ/ሚ አብይ በመጽሐፋቸው እንዳሉት (እርካብና መንበር) በገንዘብ የማይሸነፍ የለምና፣ የሚያዩትን ግን የማይበሉትን እንደቃተቱ የሚያኖራቸውን ንዋይ መርጠዋል፡፡ በዚያም ውድቀታቸው በስጋም በነፍሰም ይሆናል፡፡

ወደ አጠቃላዩ የፖለቲካው ኩነት ስንገባና የብልጽግናን አምስት አመታት የፖለቲካ ጉዞን ስንመለከት ሶስት ገጽታዎች እናያለን፡፡ አንደኛው እስከ የኢህአዲግ መከሰምና ብልጽግና መከሰት ብሎም የተግራይ ጦርነት ጅማሮ ግዜ ያለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከትግራዩ ጦርነት እስከ ፕሪቶርያ ስምምነት ግዜ ድረስ የለው ነው፡፡ ሶስተኛውን ከፐሪቶርያ ስምምነት እስከ አሁን ያለውና ባአጠቃላይ የኢትዮጵያን በተለይም የአማራ ህዝብ መከራ ጥግ የደረሰበት ዘመን ነው፡፡

በመጀመሪያው ገጽታ ላይ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ማለት ይቻላል አመላቸውን በጉያ ይዘው ከዚህ ገበታ ምን መቋደስ ይቻላል ብለው ራሰቸውን ይጠይቁ የነበረበት ግዜ ነው፡፡ ወያኔም ቢሆን በግዜው ተስፋ ያልቆረጠበትና ለአብይም መመረጥ ድምጥ የሰጠበት ግዜ ነበር፡፡

ዶ/ር ደብረጺዮን እንኴን እኛ ያቃተንን አብይ ኢሱ እያለ ሲሉ የሰማንበት ግዜ ነበር፡፡…ከፕ/ት ኢሳያስ ጋር አብይ በነአንዳርጋቸው ጽጌ በኩል የጀመረውን ግንኙነት በማድነቅ ያወሩለት ነበር፡፡ አብይ ወደ ጠ/ሚነት ሲመጣም የወያኔ ድጋፍም ነበረው፡፡ ትግራይም ሄዶ በትግርኛ የተደነቀበትን ንግግር አድርጎ ነበር፡፡  ይኽ ወያኔዎቹ እራሳቸው መንገዳቸው ትክክል እንዳለነበር ይሰማቸው እንደነበርና ለውጥ ፈላጊዎች በመካከላቸው እንደነበሩ ያሳያል፡፡

ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብም  የሃገር ፍቅር ስሜትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው መሪ ተገኘ ተባለ፡፡ በሙሉ እምነት የገቡበትም ሆነ እስኪ ግዜ ይሰጠው ያሉ ኢትዮጵያኖች ሁሉ ሊደግፉት ሞከሩ፡፡ አለም አቀፉ ማህበረሰብም የኖቤል ሽልማት በማበርከት ፖለቲካውን አሟሟቀው፡፡

ትልቅ ተስፋ ነበር፡፡ ያ ተስፋ፣ አድሮ ቃሪያ የሚሆንብንን እጣ ፋንታችንን ይቀይራል የተባለ ቢጫ ፍኖት ይዞ ብቅ አለ፡፡ ከዚያ በኃላ ግን በአብይ ላይ ትንንሽ ምልክቶች ይታዩ ጀሞር፡፡ በወቅቱ አንድ ጋዜጠኛ እዚህ የምኖርበት ሃገር ካናዳ ውስጥ የአብይን የመደመር ፍኖት እንዴት ታየዋለህ ብሎ በራዲዮ ሾዉ ላይ እንደጠየቀኝ ትዝ ይለኛል፡፡ በግዜው የታየኝ ማይክል ጃክሰን ነበር፡፡ ሰውየው ፊት ለፊት ከአንተ ጋር ገጥመው እየተያዩ እንደ ማይክል ጃክሰን ወደኋላ እየተንሸራተቱ ነው የሚደንሱት አለኩት፡፡ አረ ምን ይህ ብቻ፣ ወደ ሶስት አራት ሴቶች ፊታቸውን አዙረው ከአንቺ ጋር ነኝ ከአንቺ ጋር ነኝ በማለት “ዳሪኝ ኴይኝ እቴ ሸንኮሬ…”  እስክስታ ወረዱብን እነጂ፡፡ አሁን ግን እንኴን ትከሻቸው እግራቸው ዝሏል፡፡ የፈረነጆቹን ቃል ልዋስና “So you think you could dance, where are your legs?” (መደነስ እችላለሁ ብለህ ነበር እግሮችህ የት አሉ?)

ሁለተኛውን ገጽታ ስንመለከት ደግሞ መጀመሪያ ለወያኔ ጁንታ የሚል ስም ሰጡና ይህ እንግዲህ ታግ ኔም መሆኑ ነው ከዚያም አውዳሚው ጦርነት ተካሄደ፡፡ ቢፀ ሃሳዊያኑ ማርኪስስት የጺዮን ወያኔዎች ከአማራ ህዝብ ይልቅ ሱዳኖች ይሻሉናል፣ ለትግራይ ህዝብ ጦርነት ባህላዊ ዳንኪራው ነው፣ ከአማራ ሊሂቃን ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለን፣ የትግሬና ዩአማራ ህዝብ በታሪክ አንድ ሆኖ አያውቅም፣ መብረቃዊ ጥቃት ከፈትን፣ አህያ ነበሩ ሰው አደረግናቸው፣ አድጊ ነይሩ ሰብ ኮይኑ …ወዘተርፈ ቱልቱላቸውን ነፍተው የእንድ እናት መንትያ ልጆችን አጋድለው ደም አቃቡ፡፡

የዛሬ ስልሳ አመት ገደማ አማራው( አምሃሪና)፣ የጎጃሙ ሊቅ አስረስ የኔሰው .፣ እናት አክሱም ጽዮን አንተ ማን ነህ ትልሃለች(መኑ ትብል እምነ አክሱም ጽዮን) ብለው የኦርቶዶክሲያኑ አማሮች ሰነ ልቦናዊ ውቅር  አቅጣጫው ወዴት እንደሆነ አሳይተውን ነበር፡፡ ምን ቢፈጠር ምን ዛሬም አቅጣጫው ወደዚያ ነው፡፡

እኔ በበኩሌ ጦር ለጦር ቢዋጋ አይ አፍሪካ እያልኩ እጣ ፋንታዬን እየረገምኩ እደበታለሁ፡፡ ትግራይ ውስጥ አክሱም ጺዮን ስትነካ፣ ነጃሺ መስጊድ ሲፈርስ ግን በእመነቱ ውስጥ ኖርኩም አልኖረኩም አልስማማም፡፡ በተለይ የትግራይን ህዝብ ጠ/ሚ አብይ እንደ ህዝብ ነው የወጉን ብለው ከበው ሲያስርቡ ወግድ ይሁዳ ነው ያለኩት፣ አሁንም እላለሁ፡፡ ለምንስ ኤርትራና ህዝቧስ ይነካል፣ ሱማሌስ ብትሆን…

ጠ/ሚ አብይ የመሳሪያ ደላሎች ሰለባ ናቸው እንዳልል ሰውዬው በፒ.ኤች.ድ. ደረጃ ተምሬለሁ ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ህጉ ከሆነ የተማርክ ከሆንክ ማገናዘብ ነበረብህ ተብሎ ወንጀሉ ይጠብቅብሃል፡፡ ጠ/ሚ አብይ የሁኔታዎች ሰለባ (Victim of circumstances)  ናቸው ብዬ አላምንም፡፡

መቼም የጻፉትን መጽፍ ላየ (እርካብና መንበር) በተለይ የበሬ ሆይ ነገርን ላነበበው ሰው፣ ሰውይው አድብተው የሚያከናውኑና  ወዳጅ አልባ እንደሆኑነው ነው የሚያጋልጣቸው፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ ያኔ በትግራዩ ጦርነት ግዜ ወታደሩ ያገኘውን የወያኔ ገንዘብ ውሰድ ለራስህ አድርግ ተብሎ መነገሩ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአብይ አህመድ አዋጅ ነበር፡፡ እንግዲህ ይህ ማለት ዝረፍ ማለት ነው፣ ሌላ ምን ትርጉም ይሰጠዋል? መቀሌን በሻሻ አድርገን ከፖለቲካ የስበት መአከልነት አውጥተናታል ሲሉ ጠ/ሚ ምን ማለታቸው ነው? አማራውንም ኤርትራውንም በዚሁ የፖለቲካ መደለዣ ላጲሳችን ደልዘን ሰሜናዊውን ህዝብ ተገዢና ተከታይ ማድረግ ነው አላማችን ነው ትርጉሙ፡፡

አሁንም በአማራ ክልል የቀጠለው ይሄው ነው፡፡ ፋኖን ኢላማ አድርጎ በአስቸኴይ ግዜ አዋጅ ስም ህዝብን መዝረፍ፣ ማሰር፣ መግደልና ማሰቃየት ነው የቀጠለው፡፡ ይህንንም ኢሰመጉ በማስረጃ አጠናክሮ ሰንዶታል፡፡ አሁንም ቢሆን አብይ ማስፈራራቱን አልተወም አንዴ አማራ ካላረፈ ይጎዳል ይላል፣ ሌላ ግዜ ደግሞ ትግሬዎቹን ያስፈራራል፡፡

የፋኖን ትግል መነሻ ዛሬ ሁሉም አውቆታለል የአሜሪካው ግዜው አምባሳደር እንደተናገሩት ሁሉ፡፡ በአጭሩ በሃገሬ እንደ ዜጋ ልኑር ነው፡፡ አትኖርም የሚለው ካለ ደግሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊትም ሆነ ጠ/ሚሩን መታገል ግድ ይለዋል፣ የህልውና ጉዳይ ነውና፡፡ በመሰባሰብ ላይ ያለው ፋኖ በተበታተነ ሁኔታ ትግል በሚያደርግበት ግዜ እንኴን ህዝባዊነትን ተላብሶ ስርአት ለማሰከበር ሞክሯል ያውም ባንክን ያህል ነገር እየጠበቀ አገልግሎት ማስቀጠልን ጨምሮ፡፡

ሃያና ሰላሳ ባነኮች በሸኔ ተዘረፉ በተባለበት ግዜ ስለ ሸኔ ታጣቂዎች ጃል ማሮ ከጃል ሰኚ ጋር አደረገ በተባለው የስልክ ምልልስን ጠለፍኩ ብሎ መንግስት ያወጣውን መረጃ ስንመለከት፣ ስለታጣቂዎቹ ጃል ማሮ ሰጠው የተባለው ትንታኔ ይገርማል፡፡ በእውነት ያ የስልክ ምልልስ የጃል ማሮ ከሆነ ጃል ማሮ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው መሆኑን ነው የሚያረጋግጠው፡፡

ጠ/ሚሩ የደምቢዶሎ ዩነቨርሰቲ ተማሪዎች የተጠለፉ ግዜ ምን ነበር ያሉት? ጭራሽኑ ይህ ነገር ማረጋገጫ የሌለውና እና የአማራ ፖለቲካ ኃይሎች ሴራ  እንደሆነ ነው የነገሩን፡፡ ያኔ ማረም ሲችሉ ምንም ያላደረጉት ስልጣናቸውን እስካልነካ ድረስ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ጠ/ሚ እንደሆኑ ነው ያረጋገጡልን፡፡

ዛሬ የአየር ኃይሉ አዛዠ ቤተሰብ ተጠለፉ፣ ወንድሞቻቸውም ሞቱ የሚል ወር እንሰማለን፡፡ የአብይ መንግስት እሳቸውንና ፖለቲከኞቻቸውን የሚጠብቅ ሪፓብሊካን ጋርድ ስልጣን በያዙ በወራት ግዜ ውስጥ ሲያቋቁም  እንዴት ቀላል መሳሪያ ይዘው ለሚገድሉ፣ ለሚያፍኑና ለሚዘርፉ ማስጠሎ ጨካኞችን የሚታገል ኃይል (Counter Insurgency) ማደራጀት አቃታቸው? ይሄ የኔ ጥያቄ  ብቻ አይደለም፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ አብይን ጥለው ከሃገር እንዲወጡ ያደረገ ጭምር ነው፡፡

ምንድን ነው እነ ሽመልስ አብዲሳ በጠ/ሚ አብይ መንፈስ ተሞልተው  ስለ ኦሮሙማ የነገሩን? ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ሰዎች እነ አብይ የኦሮሚያ ሪፓብሊክን ሊያወልዱ እየፈለጉ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ሰማኒያ ከመቶው ሞስሊም  ነው በሚል ቀመር ይዞ ተግቶ የሚሰራ አክራሪ ቡድን እንደአለ የሚተነትኑ አሉ፡፡

ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በጂማ የተዘረጋውን የአልቃይዳ እስትራክቸር በኦሮሞ ትግል ስም ለማዋለድ ሲ ሞከር ይታያል፣ ይህን ትግል ሱማሌ ካለው አልሸባብ ጋር ለማቀናጀት የአብይ ቡድን በደካማው ዲፐሎማሲ ሲታትር ይስተዋላል፡፡ ፊት ለፊት ያለውን ትተህ ድብቁን ተመለከት፡ (The overt and the covert)፡፡ ከዚያማ የኦሮሞ ትግል መጨረሻ አይ.ሲ.ሲን በኢትዮጵያ ማንሰራፋት ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሱፊያዎቹን ከመጅሊሱ በመጥረግ ጉዞው ተጀምሯል፡፡

እስኪ አሁን ወደ ፖለቲካው ድርድረ ሊኢነን (Matrix) እንሂድ፡፡ የመንግስት ዋናው ስራው የዜጎችን ደህንነት ወጥቶ መግባት ማረጋገጥ፣ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ሃብት ንብረት እንዲያፈሩ ሜዳውን ማመቻቸት ይህ እንዲሆን የህግ ጠለላ መስጠት፤ ሃገርን ከውጭ ወራሪ መጠበቅ…ናቸው፡፡

የአብይ መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ግን ሁከት፣ቀውስ፣ጦርነት፣ ሰው ሰራሽ ረሃብ፣ መፈናቀል፣ ግድያ፣ ጠለፋ፣ የሐይማኖት ትርምስ…ለኢትዮጵያ እጣ ፈንተዋ፣ እድል ተርታዋ ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ በኩል የሚዘወር ነው፡፡ ከሻሸመኔው ሐብትና ንብረት ውድመትና የዜጎች ግድያ ጀምረን በተጨባጭ ማስረጃ የመንግስትን እጅ በሁሉም ቀውስ ውስጥ እንዳለ ማሳየት እንችላለን፡፡ ይህ ደግሞ የፖለቲካውን ለኢኒን ድርድር ውጤትን ዜሮ ድርድር ያደርገዋል፡፡

በዚህ ሁሉ ቀውስ ውስጥ ሱፊያ ሞስሊሞች ከመጅሊሱ እንዲወገዱ ተደረገዋል፣ የፐሮቴሰታነቱ እምነት በመንደር ነብዬች የመድረክ ላይ ድራማ ተተክቷል፣ የኦርቶዶክስ እምነት ገና አልተዘረረችም እንጂ በተደጋጋሚ በብልጽግና ጡጫ መንጋጭለዋ ወልቋል፡፡

ጠ/ሚ አብይ በኦርቶዶክስ እምነት ባሉ ድርሳናት ላይ የነበብኩትን ታሪክ ያስታውሱኛል፡፡ ይኸውም በድርሳነ ገብርኤል ሃምሌ ወር ላይ የተጻፈውን ታሪክ ነው፡፡ አውር የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ትሁት አገልጋይ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሊያንጽ ስራ ጀመረ፡፡ ሴይጣን ይህን ግዜ በመቶ አመት አረጋዊ አምሳል ለአውር ተገለጸለት፡፡

ወደ አውር ተጠግቶም ከአንተ ጋር አስጠጋኝ ለዚህ ቤተ ክርስቲያን ስራም የአቅሜል እያገዝኩ ልኑር ብሎ ወተወተ፡፡ አውርም ጥያቄውን ተቀብሎ ውሃ በእንስራ እየቀዳ ለአናጺዎች እንዲያቀብል ነገረው፡፡ የውሃው ጉድጓድ ከቤ/ክ ሩቅ ስለነበር ውሃውን ከጉድጓዱ ይቀዳል፣ አህዮቹንም ያሸክማል እቤተ ክርስቲያኑ ጋር ሲደርስ ማድጋውን ( እንስራውን) ይሰብራል፡፡

እንዲህም ብሎ ያስባል አህዮቹን በሸክም ብዛት ጉለበታቸውን አደክማለሁ፣ ምነጩንም ውሃ አልባ በማድረግ አደርቃለሁ ከዚያም የቤ/ክኑን ስራ አስተጓጉላለሁ…እንዲህ እያደረገ ቢያስቸግራቸው ድንጋይ አቀብል አሉት፡፡ ዳግመኛም ሁለት ሶስት ሰው ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ እያነሳ ሰራተኞች ላይ  አንከባሎ በመጫን መግደል ጀመር፡፡ ለአካባቢው ሹመኞችም በዚህ ቦታ ሰው መግደል፣ ነፍስ መቃመት አለ እያለ ክስ አቀረበ፡፡ እንዲህ ከሚሆንስ የቤ/ክኑ ስራ ቢቆም ይሻላል ብሎ ጠየቀ፡፡

ታሪኩ ሲያበቃ ቅዱስ ገብርኤል ለአውር ተገልጾለት ሴይጣኑን በስንሰለት እንዲታሰረ ተደረገ፡ ፡የቤተ ክ/ትያኑም ስራ ተጠናቀቀ፡፡ እንግዲህ  ጠ/ሚ ሁለት የነበረውን ሲኖዶስ አንዱን በእሳቸው አውሮፕላን ከአሜሪካ ጭነው በማምጣት አንድ አደረጉ ተባለ፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሲኖዶስ ሶስት ደርሏል፡፡ ሰብስቦ መበተን ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ይዞታ የነበረውን መስቀል አደባበይ አደስኩ ብለው ለሶስት እምነቶች ሻሞ በማለት ኦርቶዶክሱ፣ ሙስሊሙና ፕሮቴስታነቱ እንዲጋጩና እንዲነታረኩ አድርገዋል…ይህን ሁሉ ትምህርት ከየት አገኙት? ድርሳነ ገብርኤልን ቢያነቡ ነው እንጂ፡፡

በጭለማ ሲጓዝ የነበረ የሃገሬ ገበሬ መብረቅ በላዩ ላይ ቢወርድበት በስመ አብ ብሎ ሳይጨርስ በመብረቁ ብልጭታ ብርሃን ከፊት ለፊቱ ሊወድቅበት የነበረውን ገደል ቢያይ “አንተስ በመአትህ ምረትህም እንዲ ይገለጻል” አለ ይባላል፡፡

በለፉት ስድስት አመታት ባለፍንባቸው የፖለተቲካ ውጥንቅጦች ኢትዮጵያን ሁሉ  ተነጣጥለን መኖር የሚያስችን አካባቢያዊ ዳረ እንደሌለን ሳንገነዘብ አልቀረንም፡፡ የተናጥሉ ጉሆ መጥፊችን ብቻ እንደሆነ ተረድተናል፡፡  መንግስት እንደሚለው በየጽንፉ ጎራ ካሉ፣ ከለዘብተኞቹም ፖለቲከኞች ኢትዮጵያን በጋራ ሊያሸግሯት የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ አይተናል፡፡ ስለዚህም ምክክር የሚል ወለፈንዴ አንድ ጋት የማያራምድ ተደማሪ ማደናበርን ትተን፣ ሽግግር የሚለውን የጋራ አካፋያችንን አስልቶ የሚሄድ መፍትሄ መያዝ ብቻ ነው የኢትዮጵያን ችግር ሊፈታ የሚችለው፡፡ እንግዲህ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አይደል የሚለው አባባሉ፡፡ ጉዱን ሽግግር ያድርግልን! አሜን!

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር፣ ካናዳ

 

 

 

 

 

1 Comment

  1. ዲ/ን ዲያቆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የቤትክርስቲያን ማእረግ መሰለኝ ሰውዬው ቤተክርስቲያን ላይ ሽንቶ ከሄደ በኋዋላ በዚህ ስም እሱን ማስቸገር ምን ይባላል? ጎበዝ በዚህም እኮ ሊከሰን ይችላል። ሰውየው እንደ ፒታች ከአብይ ጋር አብራችሁ ግደሉኝ ብሎ በአደባባይ ሃሳቡን የሰጠ አብይን ለማስደሰት ሃይማኖቱን የለወጠ ማህተሙን የበጠሰ ተውት እንጅ እንደ ሞተም ቁጠሩት በሌለ ነገር እንድናስብ አታድርጉን። አይዞህ ዳኒ ለስጋ ምቾትህ ያለእረፍት ድከምለት እውንተህን ነው ሙቶ የተመለሰ አላየነም። ክቡር ታየ ደንዳም አብይን ተሳድበው እንደወጡ ቀሩ እሳቸውስ የልባቸውን ተናግረው ነው አቶ ዳንኤል ወልፈጥ ቢል የሚደርስበትን ሳስበው ዘግነነኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

191070
Previous Story

“ይህ መንግስት ፀረ አማራ ብቻ ሳይሆን ፀረ ኢትዮጵያም ነው ” ዶ/ር አክሎግ ቢራራ.- ክፍል – 1

448095691 857731069735329 4606614059049850902 n
Next Story

ከተሰወሩ 3 ወራት ተቆጥሯል!! (እየሩሳሌም ዓለሙ -አሻም)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop