በኦሮሙማ ኃይሎች እየተዋጠች ያለችው ሲዳማ -ግርማ ካሳ

ሲዳማ ክልል ያለው ነገር በጣም እየተወሳሰበ ነው፡፡ የሲዳማ ወገኖች መስሏቸው ክልል ይሰጠን ብለው፣ የሲዳማ ክልል ተሰጣቸው፡፡ እነ ጃዋር መሐድ ኢጂቶዎችን እያበረታቱ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲለዩ አደረጓቸው፡፡ ከሌላው ከለዩዋቸው በኋላ፣ የኦሮሙማ ኃይሎች እንደ ስፖንጅ እየጨመቋቸው ነው፡፡

ሲዳማ፣ ያለ አዋሳ ፣ ትግራይ ያለ ወልቃይት እንደማለት ነው፡፡ የአዋሳ ከተማ ራሱን የቻለ እንደ አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል መስተዳደር ቢሆን ኖሮ፣ ሲዳማዎች የራሳችን የሲዳማ ክልል ይኑረን አይሉም ነበር፡፡ አዋሳን ስለሚወስዱ ነበር ፣ ክልል ይሰጠን ያሉት፡፡ በነገራችን አዋሳ በራስ መንገዛ ስዩም ተቆርቁራ በዋናነት ወልያታዎች ከጫካ አንስተው የገነቧት ከተማ ናት፡፡ ሲዳማዎች የገነቧት አይደለችም፡፡

አዋሳ የደቡብ ክልል፣ የሲዳማ ዞንም ዋና ከተማ ነበረች፡፡ የክልሉና የዞን መስሪያ ቤቶች በብዛት ነበሩባት፡፡ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ለመዝናናት፣ ለኮንፍራንሶች ሰዎች ወደ አዋሳ ነበር የሚመጡት፡፡ የቱሪዝም ከተማ ነበረች፡፡ ደቡብ ክልል ለአራት ሲከፋፈል፣ ለደቡብ ክልል ይሰጥ የነበረው ባጀት አዋሳ ላይ ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎች ከተሞች መሄድ ጀመረ፡፡ የደቡብ ክልል መስሪያ ቤቶች ተዘጉ፡፡ በነዚህ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ አዋሳን ለቀው ወጡ፡፡

የሲዳማ ፖለቲከኞች የክልሉን የስራ ቋንቋ ሲዳምኛ አድርገው፣ ሌላው ማህበረሰባት የሚገፋ አሰራር ስለዘረጉ፣ ሌላው ማህበረሰብ አንድ በአንድ አዋሳን ጥሎ መሄድ ጀመረ፡፡ ኢንቨስትመቶች ከአዋሳ ወደነ አርባ ምንጭ መጉረፍ ጀመሩ፡፡ ሆቴሎች ባዶ እየሆኑ መጡ፡፡ የሚደረጉ ኮንቪሽኖችና ስብሰባዎች በጣም ቀነሱ፡፡ የአዋሳ ኢኮኒሚ በቱሪዝም ላይ የተመሰረተ ነበርና ቱሪዝም አሽቆለቆለ፡፡ በአዋሳ አንድ ወዳጄ ሲነግረኝ፣ ከ400 በላይ ነጋዴዎች ማትረፍ ስላልቻሉ፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ለክልሉ መስተዳደር አስረክበዋል፡፡ ይሁእንን የኢኮኖሚ ውድቀት ተከትሎ፣ የሲዳማ ፖለቲከኞች እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት እንደሰሩ እየገባቸው መጣ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሻይ ቡና መላ፤ አለ ብልፅግና (መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ)

ይህ ብቻ አይደለም፣ ኢኮኖሚው ቢበላሽም ድሃ ሆኖ መኖር ይቻላል፤ አሁን ግን ህልውናቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ እያወቁ ነው፡፡ የኦሮሙማ ሃይሎች ሲዳሞዎችን አባብለው፣ አታለው፣ ለብቻቸው እንዲሆኑ ካደረጉና ፣ በተለይም ለዘመናት አብረዋቸው ከኖሩ የወላይታዎችና ሌሎች የደቡብ ወገኖች ጋር ካጋጯቸው በኋላ፣

አሁን እየዋጧቸው ነው፡፡ ከ19 በላይ የሲዳማ ቀበሌዎች የኦሮሙማ ኃይሎች የኦሮሞ ነው በሚል ወስደውባቸዋል፡፡ ቢሻን ጉራቻ የሚባለውን ቦታ በመጠቅለል፣ የሻሸመኔ ከተማ እስከ አዋሳ ድንበር በማስፋት፣ አዋሳ የኦሮሞ ነው ማለት ተጀምሯል፡፡ ቢሻን ጉራቻ ያለ እስታዲየምና የአዋሳ ኤርፖርት የሚራራቁት በግማሽ ኪሎሚተር ብቻ ነው፡፡ እንደ ወንዶ ገነት ያሉትን የኦሮሙም ኃይልች የኦሮሞ ነው እያሉ ነው፡፡ ምን አለፋችሁ ዘንዶ ያደነውን እንደሚውጥ፣ ሲዳማ በኦሮሙማ እየተዋጠች ነው፡፡

ከዚህም የተነሳ በሲዳማ ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ በጣም ትልቅ ስጋትና ድንጋጤ የተፈጠረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ለሲዳማ ወገኖች ያለኝ አንድ ምክር ቢኖር፣ በተለይም ከአጎራባችን ከጌዴኦ፣ ጋሞና ወላይታ ማህበረሰባት ጋር ምክክር እንዲያደርጉ ነው፡፡ በተለይም ከወላይታዎች ጋር፣ በአዋሳ ለተፈጠረው ጥፋት ካሳ ከፍለው፣ እጅና ጓንት መሆን መጀመር አለባቸው፡፡ ያለፈው አልፏል፣ ከዚህ በኋላ በጋራ የሚበጀውን ማድረግ ነው፡፡ “ምን እንባላለን ?” ብለው መሸማቀቅ የለባቸውም፡፡ በትላንቱ መታሰር የለባቸውም፡፡ አሁን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ሆነው ጨፍላቂ የሆነውን የኦሮሙማ ኃይል ከመመከት ውጭ ሌላ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ ከምንም ነገር በላይ ደግሞ ሲዳማዎች “እኛ ፋኖ ነን” ብለው ይነሱ፡፡

2 Comments

  1. ጆሮ ያለው ይስማ መፍትሄው ይሄው ነው አለበለዚያ ስምህ ተለውጦ አምላከህ ዋቄ ፈና እና ጁዋር መሀመድ አህመዲን ጀበለ ይሆናሉ፡፡ ምልጃህም አህመዲን ጀበለ ነብሴን ማራት ሽመልስ አብዲሳ ከክፉ ጠብቀኝ እያልክ የማንም መላገጫ ትሆናለህ፡፡ ቀድመን ነግረን ነበር ማን ይስማ? ነግሩ ጅብ ካለፈ ሁኗል፡፡ ለታየ ደንዳ ያልሳሳ ስርአት አልፎ ተርፎ ለወላይታ ይሳሳል ብዬ አልገምትም፡፡

  2. Great article. One serious error though.
    “ሲዳማ፣ ያለ አዋሳ ፣ ትግራይ ያለ ወልቃይት እንደማለት ነው፡፡” This is an absolutely wrong comparison. It is like saying, Sidama without Awasa is like Germany without Poland. While Awasa is an integral part of Sidama, Welkait was a territory of Begemdir Amhara forcefully annexed by TPLF for three decades. Awasa has always been part of Sidama while Welkait, over the pre-TPLF millenia, has never ever been part of Tigray.
    The grandiose dream-nations of Greater Tigray, Greater Oromiya and Greater Somalia all have regions of other countries/or people that they claim. It is Western Somalia for the Somali irredentists, Western Tigray for the TPLFites and Northern Oromia for the OLFites. It is ingrained into these elites by the Colonial masters who aspire for neocolonial domination by weakening and breaking up existing nations.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share